Addis ketema woreda 9 communication

Call Website

Addis ketema woreda 9 communication this is adis ketema woreda 9 communnication office

የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የአንድነትና የመቻቻል እሴቱን  በጠበቀ ሁኔታ እንዲከበር፣ ፎሌዎች ሚናቸውን እንዲወጡ ተገለፀ።**************************መስከረም 20- 2019 ዓ.ምየአ...
30/09/2026

የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የአንድነትና የመቻቻል እሴቱን በጠበቀ ሁኔታ እንዲከበር፣ ፎሌዎች ሚናቸውን እንዲወጡ ተገለፀ።
**************************
መስከረም 20- 2019 ዓ.ም

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የኢሬቻ ክብረ በዓል በሰላም፣ በሥርዓትና በመተባበር እንዲከበር ፎሌዎችና ቀሬዎች ከፀጥታ አካላትና ከሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት የተሰጣቸውን ኃላፊነትና ተግባር በብቃት እንዲወጡ የሥራ ስምሪት ተሰጥቷል።

መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፋኪያ ሸሪፍ የኢሬቻ በዓል ሰላማዊና ስኬታማ ሆኖ እንዲከበር የሁሉም አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፣ የፎሌና ቀሬ አባላት በበዓሉ ወቅት የህዝብን ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ለታዳሚዎች ትክክለኛ አቅጣጫና መረጃ መስጠት፣ ህጻናትን፣ አረጋውያንንና እርዳታ የሚፈልጉ ታዳሚዎችን ማገዝ፣ የበዓሉን ሥነ-ሥርዓት ማስከበርና የተረጋጋ የበዓል ድባብ እንዲኖር በትጋት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅሩ ሐጂ በበኩላቸው የኢሬቻን ባህላዊና ማህበራዊ እሴቶች በማክበር፣ የሰላም፣ የመቻቻል፣ የአንድነትና የመከባበር መልዕክቶችን በማጠናከር ለበዓሉ ታዳሚዎች አርአያ እንዲሆኑ በመጥቀስ፣ የፎሌ አባላት በበዓሉ ወቅት የሚኖረውን የህዝብ ብዛትና የተለያዩ የበዓል እንቅስቃሴዎች ታሳቢ በማድረግ፣ በትዕግስት፣ በትህትናና በኃላፊነት መስራት እንዳለባቸው ገልፀዋል።

የክፍለ ከተማው የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በበኩላቸው የፎሌ አባላት ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅትና በመረጃ ላይ በተመሠረተ መንገድ መስራት እንዳለባቸው ገልፀው፤ በተለይ አጠራጣሪ ወይም አሳሳቢ እንቅስቃሴ ሲያዩ በራሳቸው ጉዳዩን ከመያዝ ይልቅ በፍጥነት ለሚመለከተው የፀጥታ አካል ማሳወቅ፣ የህዝብ ፍሰትን በሥርዓት ማስተካከል፣ የጠፉ ሰዎችን በተለይም ህጻናትንና አረጋውያንን ለማገዝ መተባበር እንዲሁም በአደጋ ወይም በአስቸኳይ ሁኔታ ተገቢውን አካል በአፋጣኝ ማሳወቅ ከፎሌ አባላት የሚጠበቁ ዋና ተግባራት መሆናቸውን አመልክተዋል።

የውይይት ተሳታፊ ፎሌዎችና ቀሬዎች በበዓሉ ወቅት ከሚመጡ ማንኛውም ሁኔታዎች በፊት በመከላከል፣ ከህብረተሰቡና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና የመከባበር በዓል ሆኖ እንዲከበር በንቃት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

#ኢሬቻ #ፎሌ

አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት አደረጃጀትየአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው የመንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤ፣ የከተማዋን አስተዳደር መዋቅር የሚቀይርና አዳዲ...
30/09/2026

አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተቋማት አደረጃጀት

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው የመንግስት ምስረታና 4ኛ ዙር የመክፈቻ ጉባኤ፣ የከተማዋን አስተዳደር መዋቅር የሚቀይርና አዳዲስ ቢሮዎችን የሚያቋቁም ረቂቅ አዋጅ አጽድቋል።

በዚህም መሠረት የተደረጉ መዋቅራዊ ለውጦች፦

• የሥራና ክህሎት ቢሮ፦ ለሁለት በመክፈል የሠራተኛና ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ እና የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ቢሮ ተብሎ እንዲደራጅ ተደርጓል።

• ባህልና ቱሪዝም፦ የባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ እና የቱሪዝም ኮሚሽን በመዋሃድ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሆኗል።

• ትራንስፖርት፦ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ታጥፎ ተግባሩ ለትራንስፖርት ቢሮ፣ ለመንገዶች ባለሥልጣን እና ለአዲሱ ትራንስፖርት ማኔጅመንት ማዕከል ተከፋፍሏል።

• ኢንቨስትመንት፦ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አደረጃጀት ባለሥልጣን በኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ተተክቷል።

• የተሰረዙ ተቋማት፦ የመሥሪያ ቦታዎች ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ፣ የምግብ ኤጀንሲ፣ የአዲስ አበባ ሥራዎች አካዳሚ እና የህዳሴ ግድብ አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት ታጥፈው ተግባራቸው ለሌሎች አካላት ተላልፏል።

•
አዲሱ አዋጅ 7 ክፍሎች እና 98 አንቀጾች ያሉት ሲሆን፣ ቀልጣፋ አሠራር በመዘርጋት የከተማዋን ዕድገት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

ለዚህች ታሪካዊ ቀንና ሰዓት ላደረሰን፣ ለረዳንና ላበረታን ፈጣሪ አምላክ በቅድሚያ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ውቢቷን መዲናችን አዲስ አበባን በድጋሚ እንድመራ ለተሰጠኝ ዕድል፣ ለተጣለብኝ አደራና...
30/09/2026

ለዚህች ታሪካዊ ቀንና ሰዓት ላደረሰን፣ ለረዳንና ላበረታን ፈጣሪ አምላክ በቅድሚያ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።

ውቢቷን መዲናችን አዲስ አበባን በድጋሚ እንድመራ ለተሰጠኝ ዕድል፣ ለተጣለብኝ አደራና እምነት፣ በቅድሚያ ፈጣሪ አምላክን፣ በመቀጠልም የመረጡንን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ የተከበረውን ምክር ቤት እና ፓርቲዬ ብልፅግናን ከልብ ማመስገን እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓትን ለመካፈል ዛሬ ጠዋት ኬንያ ገብተዋል።Prime Minister Abiy Ahmed arrive...
30/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ጣቢያ የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ሥርዓትን ለመካፈል ዛሬ ጠዋት ኬንያ ገብተዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed arrives in Kenya this morning ahead of the groundbreaking ceremony for the Lamu Refinery.

ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ ከተማ የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ቃለ-መሀላ ፈፀሙ
30/09/2026

ምክትል ከንቲባና የአዲስ አበባ ከተማ የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ ቃለ-መሀላ ፈፀሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የከተማውን የካቢኔ አባላት ሹመት አፅደቀበዚህም መሰረት፦• ዶ/ር አህመዲን መሃመድ - የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ...
30/09/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት የከተማውን የካቢኔ አባላት ሹመት አፅደቀ
በዚህም መሰረት፦

• ዶ/ር አህመዲን መሃመድ - የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ

• ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ - የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ

• ኢንጂነር አያልነሽ ኃብተማሪያም - የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ኃላፊ

• ወ/ሪት ጽዮን ደረጀ (የአብን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል)- የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ

• ኢንጂነር ህይወት ፀጋዬ - የግንባታ ቁጥጥርና ፈቃድ ቢሮ ኃላፊ

• ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ - የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ኃላፊ

• ወ/ሮ ዚያዳ ካሚል - የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ

• አቶ ግርማ ሰይፉ -የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ

• አቶ ቢኒያም ምክሩ -ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

• አቶ ሙሉቀን ታሪኩ - የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ

• ወይዘሮ ሃቢባ ሲራጅ - የንግድ ቢሮ ኃላፊ

• ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ - የጤና ቢሮ ኃላፊ

• ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

• አቶ አወሌ መሃመድ ኡመር - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ

• ዶ/ር ተፈራ ሞላ - የትራንስፖርት ቢሮ

• ኢንጂነር አይሻ መሃመድ - የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር

• ኢንጂነር ሔለን ገመዳ - የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ ሃላፊ

• ወ/ሮ ልዕልቲ ግደይ - የህፃናት ማህበራዊ ጉዳይና ሴቶች ቢሮ

• አቶ ተስፋዬ ደጀኔ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ

• አቶ አሰግደው ወልደጊዮርጊስ - የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ

• አቶ መላኩ ታምሩ - የመሬት ልማት ቢሮ ኃላፊ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ   የተሾሙ አመራሮች ቃለ መሀላ ፈፀሙ።አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአ...
30/09/2026

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በከንቲባ አዳነች አቤቤ አቅራቢነት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተሾሙ አመራሮች ቃለ መሀላ ፈፀሙ።

አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።

አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል

አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሄር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆነው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል

አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ሆነው ቃለ መሀላ ፈፅመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አራት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመቶችን አጸደቀየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ሹመቶችን ለከተማ አስተ...
30/09/2026

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አራት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ ሹመቶችን አጸደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የተለያዩ ሹመቶችን ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አቅርበዋል።

በዚሁም፡-
አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ

አቶ ጥላሁን ከበደ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ በአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ

አቶ ሀፍታይ ገብረእግዚአብሄር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ

አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ በመሆን በከንቲባዋ የቀረቡ ናቸው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የቀረቡትን ሹመቶች አጽድቋል።

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሾሙአቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የአዲስ ...
30/09/2026

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሾሙ

አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል።

"ያለፉትን አምስት አመት  የከተማችንን መልክ እንቀይራለን ፣ የህዝባችንን ክብር እናስጠብቃለን፣ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አዲስ እናደርጋለን ብለን ቃል ገብተን ነበር ይህም ከጠበቅነውና ...
30/09/2026

"ያለፉትን አምስት አመት የከተማችንን መልክ እንቀይራለን ፣ የህዝባችንን ክብር እናስጠብቃለን፣ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አዲስ እናደርጋለን ብለን ቃል ገብተን ነበር ይህም ከጠበቅነውና ካቀድንው በላይ ተሳክቶልናል፡፡

ሆኖም የትላንቱ ስኬት የነገ ኃላፊነትን አይተካም፡፡ ትላንት የከተማችንን ገፅታ ለመቀየር ሰርተናል በርካታ ስራዎችንን አከናውነናል ያቀድንውም ተሳክቶልናል በቀጣይ የነዋሪዎቻችንን ኑሮ በተጨባጭ ማሻሻል የሚችሉ ስራዎችን ማከናወን ይጠበቅብናል፡፡

ሪፖርታችን ብዛት ወይም ቁጥር አይሆንም በዜጋው ህይወት ላይ በመጣው ተጨባጭ ለውጥ ብቻ መሆን ይገባዋል"፡፡

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis ketema woreda 9 communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share