23/02/2026
የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ በአዲስ አበባ ሴት ማህበር ልደታ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ የሴቶች መጠለያ በመገኘት በጎ ፍቃደኛ የሴቶች ክንፍ ደጋፊዎችን በማስተባበር ለሴቶች እና ህፃናት ማእድ አጋራ።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሰሚራ አያሌው እንደገለፁት ብልፅግና ፓርቲ ከሚተገብራቸው መርሆች አንዱ የሆነው ሰው ተኮርነት እና ሰብአዊነት መሆኑን ገልፀው የክንፉ አመራሮች እና አባላትም ይህንን ተግባር እንደየሁልጊዜው ለማስቀጠል በርካታ ተግባራትን እየሰሩ መሆኑን ገልፀው በተለይ በሴቶች ዙሪያ በሚደረጉ ማንኛውም በጎ ፍቃድ ተግባራት ሁሌም ግንባር ቀደም ሆነው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ እና አመራሮች ተገኝተዋል።
15/02/2026
በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሴቶች ክንፍ አዘጋጅነት በቂርቆስ፣ በየካ፣ በቦሌ፣ በለሚኩራ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ እና በልደታ ክ/ከተሞች ከወረዳ ጀምሮ በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ የሰነበተው የክንፉ አባላት ማጠቃለያ ከተማ አቀፍ የውይይት መድረክ ተካሂዷል!!
በክብር እንግድነት የተገኙት በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መሠረት መስቀሌ ባደረጉት ንግግር ለተመዘገበው ስኬት የሴቶች ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል።
የዘመናት የዴሞክራሲ ጥያቄ የመመለስ ተግባር አንግቦ የተነሳው ፓርቲያችን አካታችና አቃፊ በመሆን የሁሉ ወገኖች ድምፅና ፍላጎት እየመለሰ የሚገኝ ነው ብለዋል።
የፓርቲያችን የልማት ፣ የዘላቂ ሰላም እንዲሁም የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ እሳቤዎች በተግባር እንዲተረጉሙ በማድረግ በተመዘገቡ ውጤቶች ሁሉ የሴቶች ሚና ላቅ ያለ በመሆኑ አጠናክረው እንዲያስቀጥሉ አሳስበዋል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ዶክተር ሜኢሳ ኢሌማ፣ በበኩላቸው ለሀገር ግንባታ የሴቶች ሚና ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸው የዲሞክራሲ ስርዓት እንዲሰርፅ እሳቢያችን እንዲሰፋ ለሀገር እድገት አውንታዊ ተፅኖ ፈጣሪ እንዲሆኑ በተለይም የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባትና በሀገረ መንግስት ግንባታ ላይ ድርሻቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ሴቶች ላይ የተጀመረውን ስራ ማጠናከር ተገቢ ነው ብለዋል።
አዲሰ አበባ ከተማችን ለመኖር አስቸጋሪ የነበሩበት እንደስሟ አዲስ ሆና አበባ እንድትሆን በቆራጥ አመራሮችና አባላት ስኬታማ የልማት ስራ መስራት መቻሉን ዶክተር ሜኢሳ ገልጸዋል።
ይህን ስኬት አልቆ ለማስቀጠል የሴቶች ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
በብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ሴቶች ክንፍ ፅ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ የሺ ወልዴ የውይይት መነሻ ሰነዱን ያቀረቡ ሲሆን የሴቶች ክንፍ ተቋሙን ከመገንባት በተጨማሪ በተለያዩ በሰው ተኮር ስራዎች እና በልማት ሰራዎች ላይ በስፋት ሲንቀሳቀስ መቆየቱንና እየተገበረ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በሁሉም መስክ የሴቶችን ተሳታፊነት በማረጋገጥ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ማሻሻል እንደተቻለና ተሳትፎ ውጤት ብቻ ሳይሆን ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ መሆኑን በተግባር እየገለጥን መጥተናል ብለዋል።
በ7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫም ያቀድናቸውን መንትያ ግቦች በላቀ የሴቶች ተሳትፎ በማሳካት እውነትና ሀቅ ላይ ሆነን ለፓርቲያችን መስራትና ሴቶች ሰላምን በመስበክ ቀዳሚነታቸውን ማረጋገጥ ህብረብሔራዊ ኢትዮጵያን መገንባት የፀናች ተፅኖ ፈጣሪ የሆነች ሀገር መፍጠር በምንሰራው ስራ ግንባር ቀደም መሆን ፅንፈኝነት መታገል ባንዳና ባዳን መለየት እና ለኢትዮጵያ የሚጠቀመውን መንገድ መከተል ከሴቶች ይጠበቃል ብለዋል።
በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሴቶች የጀመሩትን ንቁ ተሳትፎ እንዲያስቀጥሉ ወ/ሮ የሺ አሳስበዋል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቅ/ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ አደፍርስ ኮራ በበኩላቸው እንኳን ወደ አዲስ ፈርጥ ወደሆነች ቂርቆስ በሰላም መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው በከተማችን ሁለንተናዊ ዕድገት የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በከተማው የተሰሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ማከናወን መቻሉን የጠቀሱት አቶ አደፍርስ ሁለተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ የተጀመረው የሴቶች ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ሴቶች በተሰማሩበት መስክ ሁሉ ቀን ከሌት መትጋትና ግንባር ቀደም ናቸው።
13/02/2026
የቦሌ ክፍለከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ “ለ7ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲን የምርጫ ምልክት የማስተዋወቅ መድረክ አካሄደ”
የቦሌ ክፍለከተማ የብልጽግና ሴቶች ክንፍ ሃላፊ ወ/ሮ ሳምራ አያለው ፓርቲው በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መንታ ግቦችን ይዞ ወደተግባር መግባቱን በማስገንዘብ ምርጫው ነፃ፣ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ተአማኒነት ያለው እንዲሆን ግብ አስቀምጦ እየሠራ እንደሚገኝ በመግለጽ ሴቶች በምርጫው ለምርጫው በሁሉም መስክ በመዘጋጀት፣ በመመዝገብ፣ በመምረጥና በመመረጥ እንዲሁም የምርጫውን ውጤት በአግባቡ በመጠበቅ የዜግነት ኃላፊነታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው በማብራራት በቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 12 የብልጽግና የምርጫ ምልክት ለሴቶች ክንፍ አባሎች የማስገንዘብ መድረክ አካሂዷል።
የቦሌ ወረዳ 12 ዋና ስራ አስፈፃሚ ገዛኸኝ በየነ ለምርጫ የሴቶች መዋቅር ሚና የላቀ ነው ይህንን ለማሳካት ምልክታችንን ማወቅ እና ሰላማዊ ምርጫን በውጤት የታጀበ ማካሄድ አለብን የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት “የስንዴ ነዶ” ነው። የስንዴ ነዶ የመደመር፣ የአንድነት፣ ትብብርና የሉአላዊነት መገለጫ ነው ነው በማለት አብራርቷል
በመድረኩም የወረዳው ኮር አመራሮች እና የሴቶች ክንፍ መዋቅር ተገኝተዋል።
12/02/2026
ያሳካልን ፈጣሪ አምላክ ይመስገን!!
ከኡራል በቦሌ መድሃኔለም ወደ ቦሌ ድልድይ! አዲስ አበባን በሁሉም አቅጣጫ እንደ ስሟ ዉብ አበባ አድርገን ሰርተናታል ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
11/02/2026
"በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የሴቶች የውይይት መድረክ ተካሄደ።
በቦሌ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት በሴቶች ክንፍ "በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የሴቶች የውይይት መድረክ ተካሄዷል ።
በመድረኩ የተገኙት ቦሌ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ክፍሌ ለማ እንደገለፁት ሴቶች በከተማችን ብሎም በክፍለ ከተማችን ለሚሰሩ ተግባራት ግንባር ቀደም መሆናቸውን ገልፀው የሴቶች ተሳትፎ በከተማችን እየተመዘገቡ ላሉ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችና ለሀገር ግንባታ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ እንደሚኝ ገልፀው የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ የሴቶችን ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የሴቶች ክንፍ ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሰሚራ አያሌው እንደተናገሩት ሴትምች የህብረተሰባችን ግማሽ እና ከዛ በላይ አካል መሆናቸውን ገልፀው ለሁለንተናዊ ተጠቃሚነታቸውም ክንፉ እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል
10/02/2026
የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት “የስንዴ ነዶ” ነው። የስንዴ ነዶ የመደመር፣ የአንድነት፣ ትብብርና የሉአላዊነት መገለጫ ነው።
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
የስንዴ ነዶ (Wheat Sheaf)
ለፓርቲያችን መወዳደሪያ ምልክትነት ሲመረጥ፣ በጣም ጥልቅ እና አዎንታዊ መልዕክቶችን ማስተላለፍ የሚችል ምልክት ነው።
ይህንን ምልክት በተለያዩ እይታዎች እንደሚከተለው መተርጎም ይቻላል፡
1. ኢኮኖሚያዊ እና የልማት እይታ (Economic and Developmental View)
* ብልጽግና እና የተትረፈረፈ ምርት፡ የስንዴ ነዶ የተሰበሰበ ምርትን ይወክላል። ፓርቲው ሀገሪቱን ከምግብ ዋስትና አልፎ ወደ ውጭ መላክ የሚያስችል የኢኮኖሚ ብልጽግና እንደሚያመጣ ያሳያል።
* የግብርናው ዘርፍ ፡ ከኢኮኖሚ ፓሊሲያችን አንዱ በግብርና ምርት መላቅ እንደመሆኑ መጠን፣ ይህ ምልክት የገበሬውን አቅም ማሳደግ እና ዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂን ማስፋፋት ዋና አጀንዳው መሆኑን ያመለክታል።
2. ማህበራዊ እና አንድነት እይታ (Social and Unity View)
* አንድነት እና ጥንካሬ፡ አንድ የስንዴ አገዳ በቀላሉ ሊሰበር ይችላል፣ ነገር ግን አንድ ላይ የታሰረ ነዶ ለመስበር አስቸጋሪ ነው። ይህም "አንድነት ኃይል ነው" የሚለውን መርህ በመያዝ፣ ፓርቲው የህዝብን አንድነት እንደሚያጠናክር ያሳያል።
* የጋራ ጥረት (Communal Effort)፦ ነዶው ብዙ አገዳዎች በአንድ ላይ ተያይዘው የተሰሩ ናቸው። ይህም የህዝቡን አብሮ መሥራት፣ መደጋገፍ እና የጋራ ራዕይ ይወክላል።
3. ታሪካዊ እና ባህላዊ እይታ (Historical and Cultural View)
* ታታሪነት እና ጥረት፦ ስንዴ ለማምረት ከፍተኛ ልፋት፣ ትዕግስት እና ጥረት ይጠይቃል። ይህ ምልክት ፓርቲው ለሀገር ግንባታ ታታሪ እና ደከመኝ ሰለቸኝ የማይሉ መሪዎች አሉት የሚል መልዕክት ያስተላልፋል።
* ቀጣይነት እና ተስፋ፦ የስንዴ ዘር መዝራት፣ ማሳደግ እና ማጨድ የሕይወት ዑደት ነው። ይህም የፓርቲው የረዥም ጊዜ ራዕይ እና ለወደፊት ትውልድ የተሻለ አገር የማስረከብ ተስፋን ያሳያል።
4. የፖለቲካ ፍልስፍና እይታ (Political Philosophy View)
* የህዝብ ወገንተኝነት፦ ስንዴ የዕለት ተዕለት የምግብ ምንጭ ነው። ስለዚህ ምልክቱ ፓርቲው ከመሬት ጋር የተያያዘ፣ የህዝቡን መሰረታዊ ፍላጎት (የምግብ ዋስትና፣ ሰላም፣ መረጋጋት, ሰው ተኮርነትን) የሚያሟላ የህዝብ ፓርቲ መሆኑን ያሳያል።
በአጠቃላይ፣ ይህ ምልክት "ከተጋድሎ በኋላ የሚገኝ ውጤት፣ በአንድነት መቆም፣ እና የሀገር ብልጽግና" የሚሉትን ሀሳቦች አጣምሮ የያዘ ነው።
06/02/2026
በሴቶች ተሣትፎ የፀናች እና የበለፀገች አዲስ አበባ!
አዲስ አበባ የሁሉም ዜጎች ከተማ ናት፤ የሴቶች ንቁ ተሳትፎ ሲጠናከር ከተማችን የበለፀገች፣ የፀናች እና ዘላቂ ልማት ያላት ትሆናለች።በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ ልማት፣ በአመራር እና በማህበረሰብ ግንባታ ዘርፎች የሴቶች ሚና ከፍ ሲል፣ አዲስ አበባ ወደ ተሻለ ነገ ትጓዛለች።
ዛሬ ሴቶች በንግድ፣ በቴክኖሎጂ፣ በትምህርት፣ በጤና እና በማህበራዊ አገልግሎት ዘርፎች ያሳዩት ንቁ ተሳትፎ የከተማችንን ገጽታ እየቀየረ ይገኛል። ይህም የፀናች እና የበለፀገች አዲስ አበባን ለመገንባት መሠረት ነው ሴቶችን ማብቃት ማለት ከተማችንን ማብቃት ማለት ነው በአንድነት እንስራ፤ በሴቶች ተሳትፎ የፀናች እና የበለፀገች አዲስ አበባን እንገንባ ብለዋል።
በዛሬ ዕለትም የቦሌ ክ/ከተማ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የብልፅግና ፓርቲ የሴት ክንፍ በሴቶች ተሣትፎ የፀናች እና የበለፀገች አዲስ አበባ በሚል መሪ ቃል የሴቶች መድረክ አካሂደዋል ።
23/01/2026
"በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጲያ"
የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ በሴቶች ተሳትፎ የፀናች እና የበለፀገች ኢትዮጲያ በሚል ንቅናቄ በአዲስ አበባ ሴት ማህበር ልደታ ክፍለ ከተማ ቅርንጫፍ የሴቶች መጠለያ በመገኘት ለሴቶች እና ህፃናት የሚሆን የንፅህና መጠበቂያ እቃዎች እና የልጆችና የሴቶች አልባሳት ድጋፍ አደረገ።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሀላፊ ወ/ሮ ሰሚራ አያሌው እንደገለፁት ብልፅግና ፓርቲ ከሚመካባቸው መርሆች አንዱ የሆነው ሰው ተኮርነት እና ሰብአዊነት መሆኑን ገልፀው የክንፉ አመራሮች እና አባላትም ይህንን ተግባር ለማስቀጠል በርካታ ተግባራትን እየሰሩ መሆኑን ገልፀው በተለይ በሴቶች ዙሪያ በሚደረጉ ማንኛውም በጎ ፍቃድ ተግባራት ሁሌም ግንባር ቀደም ሆነው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የክፍለ ከተማ ሴት ማህበር ሰብሳቢ ወ/ሮ መሰረት ሶሬሳ እንዲሁም የሁሉም ወረዳ የሴት ክንፍ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ።
22/01/2026
"በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጲያ"
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጲያ በሚል ርእስ ለአቅመ ደካማ ሴቶች ከሀይማኖት ተቋም ጋር ትስስር በመፍጠር የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም የማእድ ማጋራት አደረገ ።
22/01/2026
በወቅታዊ አገራዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ፣ በተለይም “ገዢ ትርክት” በሚል በተዘጋጀ ሀሳብ ላይ ውይይት ተካሄደ
በብልፅግና ፓርቲ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ አማካኝነት በተዘጋጀው እና የብልፅግና ቤተሰብ አመራሮች በተሳተፉበት "ገዢ ትርክት" ምንድን ነው፣ የገዢ ትርክት አቅም፣ አውንታዊ እና አሉታዊ ጎኖች እና አካታችነቱስ ምን ያህል ነው በሚል ነጥቦች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
ገዢ ትርክት በተለይ አንድነትን እና የጋራ የሆነ ማንነት ለመገንባት ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳ እንዳለው በውይይቱ በተደጋጋሚ ተንፀባርቋል። ውይይቱን የመሩት በብልፅግና ፓርቲ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፋጡማ የሱፍ በመድረኩ ጤናማ ማህበረሰብ ለመገንባት ያሉትን ሂደቶች ገዢ ትርክቶች በሂስ መመልከትና ለጋራ መግባባት የሚጠቅሙ አዳዲስ ትርክቶችን እነደ ሀገር መገንባት እና መቅረጽ እንደሚገባ አጽንኦት ሰተው ። ሴቶች ለገዢ ትርክት መስረፅ ጉልህ ሚና እንዳላችፕውና ይህንንም ተግባር በተደጋጋሚ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለፁት የወረዳው የሴት ክንፍ ሀላፊ ወ/ሮ ፍሪኬኒ ኢብሳ ናቸው።በመጨረሻም መድረኩ በጋራ መግባባት ተጠናቋል።
ጥር 14/2018
03/01/2026
የዜጎችን ሁለንተናዊ የሰው ተኮር ብልፅግና ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል
ዜጎችን በመርዳት፣ አቅማቸውንም ታሳቢ በማድረግ ፓርቲው ሰውተኮርነትን ተግባር ያከናውናል።
በዚህም መሰረት የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ለአቅመ ደካማ ነዋሪዎች የቤት እድሳት አስጀመረ።
31/12/2025
/ቤት
የቦሌ ል/ከተማ ወረዳ 06 ብልፅግና ሴት ክንፍ
''በጎነት በትምህርት ቤት በሚል በትምህርት ቤት በጎ ተግባር አከናውኗል
የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የብልጽግና ሴቶች ክንፍ ከህብረት አመራሮች ጋር በመሆን በት/ቤት ተገኝተው ተማሪዎችን የመመገብ እና መጋቢ እናቶችን በማገዝ ድጋፍ አድርገዋል።
የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሀላፊ ወ/ሮ ፍሪኬኒ ኢብሳ እንደገለፁት በበጋ በጎ ፈቃድ ስራ ላይ በት/ቤት ለተማሪዎች በምገባ ለተሰማሩት እና
ቶችን ማሳረፍ እና ማገዝ በዛውም የነገ የሀገር ተረካቢ የሆኑትን ህፃናቶች መንከባከብ እንዳለብን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።