Grand Ethiopian Renaissance Dam,Addis Ababa
ራዕይ
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በመላ የከተማችን ነዋሪ ህዝቦች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ተጠናቆ የሰላም ፣ የኢኮኖሚና የብልፅግናችን ምንጭ ሆኖ ማየት፡፡
ይህ የፌስቡክ ገጽ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ነው፡፡
በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ መላ የሀገራችን ህዝቦች እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የፋይናንስ፤የአካባቢ ጥበቃና ተፋሰስ ልማት ድጋፍ በማጎልበትና የቁጠባ ባህል እንዲያድግ በማድረግ ታሪካዊ አሻራቸውን እንዲያሳርፉ በማስቻል፤የሀገራችንን ገጽታ ግንባታና ብሄራዊ መግባባት ማጠናከር ነው፡፡
03/04/2026
02/04/2026
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ ሀሉም ኢትዮጵያዊ ያለምንም ልዩነት በጋራ በመነሳት ገንብቶ በማጠናቀቅ የፍሬው ተቋዳሽ ሆኗነል። በቀጣይም ሌሎች መሰል ፕሮጀክቶችን በተጠናከረ አንድነት መገንባት እንደምንቺል ትልቅ ማሳያ ነው።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ትናንትና ዛሬ
26/02/2026
ዜና ሹመት
የካቲት 19/2018ዓ.ም
ወ/ሮ መቅደስ አዱኛ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ።
በእለቱም ከቀድሞዋ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሪት አንቺነሽ ተስፋዬ ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል ። ወ/ሮ መቅደስን በጸ/ቤታችን ስም እንኳን ደህና መጡ ለማለት እንወዳለን።
26/02/2026
የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አመራርና ባለሙያዎች ከክ/ከተማ የህዳሴ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በመሆን የቀድሞ የጽ/ቤቱን ምክትል ስራ አስኪያጅ የሽኝት መርሃ ግብር አዘጋጁ።
የሽኝት መርሃግብሩን በንግግር የከፈቱት የጽ/ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ንዒመተላህ ከበደ የቀድሞ የጽ/ቤታችን ም/ስራ አስኪያጅ የነበሩትና አሁን የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ስራአስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ሪት አንቺነሽ ተስፋዬ በስራ ሂደት ስለነበራቸው የአብሮነት ቆይታ አመስግነው አሁን የተሰጣቸውን ኃላፊነትም በብቃት እንደሚወጡና ብቃት ያላቸው አመራር እንደሆኑ ገልፀዋል። ከክ/ከተማና ከማዕከል የባለሙያ ተወካዮችም በስራ በቆዩበት ወቅት ስለነበራቸው መልካም ግንኙነት አመስግነው መልካም የስራ ዘመን እንዲገጥማቸው ምኞታቸውን በመግለፅ የሽኝትና የምስጋና መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።
06/02/2026
የከተማችንን ጐስቋላ ገፅታ በመቀየር ውብ፣ ፅዱ እና አረንጓዴ ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለጐብኝዎች ሳቢና አለማቀፍ ተወዳዳሪ እንድትሆን በ24/7 የስራ መርሀ ግብር ሰርተን ውጤት ያስመዘገብንበት ነው ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
05/02/2026
“በአፍሪካ ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲሁም የውሃ ታሪፍ በማቅረብ ረገድ ኢትዮጵያ በየጊዜው በአንደኝነት ትጠቀሳለች!” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
03/02/2026
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ያለአንድብር የውጭ እርዳታ በኢትዮጵያዊያን ሃብት ብቻ የተገነባ ታላቅ ፕሮጀክት፤
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
1000
