Hadiya zone Government Communication

Call

Hadiya zone Government Communication የሀድያ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ የሆነ የመንግሥት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ሥርዓት በመገንባት መንግስትና ሕዝብን ማገናኘት

This is the offical facebook home page of Hadiya Zone Communication

‹ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ተደራሽ የሆነ የመንግሥት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ሥርዓት በመገንባት መንግሥትንና ሕዝብን ተጠቃሚ በማድረግ አንድ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማኀበረሰብን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረግ ነው።

የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ዛሬ ይካሄዳል ሆሣዕና ፤ መስከረም 25/2019 (ሀድያ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን )የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ  ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይከናወናል። በግንቦት ወር 2018 ዓ....
05/10/2026

የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ዛሬ ይካሄዳል

ሆሣዕና ፤ መስከረም 25/2019 (ሀድያ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን )

የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይከናወናል።

በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ መጠናቀቁ የሚታወስ ነው።

በዚሁ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10,438 እጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተሳትፈዋል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌደራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን ተጠሪነቱም ለሀገሪቱ ሕዝብ መሆኑ ተደንግጓል።

በተጨማሪም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀመር በተደነገገው መሠረት፣ የመንግሥት ምስረታ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ይከናወናል።

በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መንበር ያገኘው የፖለቲካ ፓርቲ የፌደራሉን ሕግ አስፈጻሚ አካል የሚያደራጅ ሲሆን፣ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ ሕግ አስፈጻሚ አካል በዕለቱ በይፋ ኃላፊነት ይረከባል።

ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።

ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች አስቀድመው የመንግስት ምስረታ አካሂደዋል።(ኢዜአ)

"የተሰጠን አደራ አለ። የተሰጠንን አደራ ይዘን የጀመርነውን በስኬት እናጠናቅቃለን።"ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
04/10/2026

"የተሰጠን አደራ አለ። የተሰጠንን አደራ ይዘን የጀመርነውን በስኬት እናጠናቅቃለን።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከህዝብ ድምፅ ወደ መንግሥት ምሥረታ ውስጥ የማይቀለበሰው የዴሞክራሲ ጉዞ፣ የታሪክ አሻራዎች እና የታላቋ ኢትዮጵያ የቀጣይ ከፍታ ራዕይ***********************ኢትዮጵያ በሺህዎች የ...
04/10/2026

ከህዝብ ድምፅ ወደ መንግሥት ምሥረታ ውስጥ የማይቀለበሰው የዴሞክራሲ ጉዞ፣ የታሪክ አሻራዎች እና የታላቋ ኢትዮጵያ የቀጣይ ከፍታ ራዕይ
***********************

ኢትዮጵያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዓመታት የሀገረ-መንግሥት ታሪክ ባለቤት የሆነች፣ በፈተናዎች እሳት ውስጥ አልፋ ጽናቷን ያረጋገጠች ግዙፍ አፍሪካዊት ሀገር ናት።

ህዝቧ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ድምፁን ሰጥቶ ያሻውን መሪ ከመረጠበት የታሪክ ምዕራፍ ተነስቶ ወደ አዲስ መንግሥት ምሥረታ የሚደረገው ሽግግር ኢትዮጵያ ያላትን ጥልቅ የፖለቲካ ብስለት፣ የሰከነ ህዝባዊ ወገንተኝነትና የጸና የህግ የበላይነት ባህል በዓለም አቀፍ መድረክ ዳግም ያስመሰከረ ነው።

ይህ ሰላማዊና ሥርዓት ያለው የዴሞክራሲ ሂደት ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የሚገጥሟትን የውስጥና የውጭ ውጣ ውረዶች በራሷ ልጆች ብርታት አልፋ፣ ወደ ላቀ የከፍታ ማማ መሸጋገር የምትችል ብርቱ ሀገር መሆኗን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ያለፈው መንግሥት በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ መስኮች ላይ ያስቀመጣቸው ቁልፍ አሻራዎች ዛሬ ለደረስንበት ተስፋ ትልቅ መሰረት ሆነዋል።

የውጭ ጫናዎችንና የዲፕሎማሲ ሴራዎችን በጽናት በመመከት፣ በገዛ አቅም ታላቁን የሕዳሴ ግድብ ወደ ፍፃሜ ማድረስ መቻሉ የትውልዱ ትልቁ የድል አርማ ነው።

ከዚህም ባሻገር ሀገራዊ ምክክርን በማካሄድ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ የመፍታት ባህልን ማዳበር፣ እንደ ማዳበሪያና ነዳጅ ያሉ ግዙፍ የኢኮኖሚ አቅሞችን በራስ አቅም ለመገንባት መጀመር፣ በአዲስ ዕይታ የከተማና የትራንስፖርት መሠረተ-ልማቶችን መገንባት እንዲሁም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተከናወኑ አመርቂ ተግባራት የስልጣኔ ጀንበር ብቅ ማለቷን ያበሰሩ ናቸው።

እነዚህ የተመዘገቡ ስኬቶች ኢትዮጵያ አቅሟን አስተባብራ በህብረት ከተነሳች የማትሻገረው ተራራ እንደሌለ ለዓለም ያስመሰከሩ ህያው ማሳያዎች ናቸው።

አሁን በህዝብ ሙሉ ውክልና የሚመሰረተው አዲሱ መንግሥት ደግሞ የተጀመሩትን እነዚህን ታላላቅ ሜጋ ፕሮጀክቶችና የልማት ምዕራፎች በማስቀጠል፣ የጎደለውን ሞልቶና ክፍተቶችን አርሞ ሀገርን ወደ ሙሉ ብልጽግና የማሻገር ታላቅ ታሪካዊ ኃላፊነት ተጥሎበታል።

አዲሱ የዜጎችን እኩልነት፣ ሰላምና ፍትሕ ይበልጥ በማስፈን፣ የኑሮ ውድነትንና የኢኮኖሚ ጫናዎችን በማቃለል እንዲሁም የህግ የበላይነትን በማጽናት የህዝቡን የልብ ትርታ በተግባር ለመመለስ ጽኑ ቃል ኪዳን ሰንቋል።

ይህ የለውጥና የስራ ምዕራፍ ያለፈውን ጥንካሬ አጠናክሮ ጉድለቶችን የሚሞላ፣ ተቋማዊ አቅምን የሚገነባና የህዝብን የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ በተግባር የሚያረጋግጥ ነው።

ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነት፣ እውቀትና መስዋዕትነት ታፍራ፣ ተከብራና ሉዓላዊ ክብሯ ተጠብቆ እንድትኖር የማድረግ ራዕይ የቀጣዩ ጉዞ ዋነኛ ማዕከል ነው።

ሰንቀን እንደመነሳታችን መጠን፣ የባሕር በር ተፈጥሯዊ መብትን ከማስከበር ጀምሮ የቀጠናው የሰላምና የልማት ማዕከል የመሆን ጉዟችን በማንኛውም የጠላቶች ሴራና ጊዜያዊ ፈተና አይገታም።

የኢትዮጵያ ህዝብ በዴሞክራሲያዊ መንገዱ የመረጠውን መንግሥት በማጽናት፣ ከዳር እስከ ዳር በአንድነት ቆሞ የሀገሩን ክብርና ብልጽግና እንደሚያረጋግጥ ጥርጥር የለውም።


#ኢቢሲ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ምስረታና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመክፈቻ ጉባዔ ነገ ይካሂዳል
04/10/2026

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የመንግስት ምስረታና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመክፈቻ ጉባዔ ነገ ይካሂዳል

ከሆረ ፊንፊኔ እስከ ሆረ ሀርሰዴ፤ የኢትዮጵያ ኅብረ-ቀለም የሚታይበት የኢሬቻ በዓል*******************ኢሬቻ የምስጋና፣ የሰላም፣ የፍቅር እንዲሁም የእርቅ በዓል ነው። በኦሮሞ ሕዝብ...
04/10/2026

ከሆረ ፊንፊኔ እስከ ሆረ ሀርሰዴ፤ የኢትዮጵያ ኅብረ-ቀለም የሚታይበት የኢሬቻ በዓል
*******************

ኢሬቻ የምስጋና፣ የሰላም፣ የፍቅር እንዲሁም የእርቅ በዓል ነው። በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየው ይህ ታላቅ ባህላዊ ትውፊት፣ ክረምቱ አልፎ መስከረም ሲጠባ "መልካም ጊዜ ስላሳየኸን፣ ከዝናቡና ከጎርፉ ጠብቀህ ለብርሃን ስላበቃኸን" ተብሎ ፈጣሪ የሚመሰገንበት መድረክ ነው።

የኢሬቻ በዓል ከምስጋና በዓልነቱ ባሻገር የበርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላዊ አልባሳትና ውበቶች የሚንጸባረቁበት ትልቅ አህጉራዊ አደባባይ ሆኗል። በዓሉ በሚከበርባቸው በሆረ ፊንፊኔ እና በሆረ አርሰዲ መድረኮች ላይ የኦሮሞ፣ አማራ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ጋሞ እና የሌሎችም በርካታ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ተወካዮች በየራሳቸው ባህላዊ አልባሳት አጊጠው ይገኛሉ።

በበዓሉ ዕለት በአረንጓዴ ሳርና በነጫጭ ባህላዊ ልብሶች የደመቀው አደባባዩ፣ የኢትዮጵያን የባህል ብዝሃነትና ውበት በአንድ ላይ አጣጥሞ የሚያሳይ እውነተኛ የኅብረ-ቀለም መድረክ እየሆነ መጥቷል።

በኢሬቻ አከባበር ወቅት ቂም ይረሳል፤ ሰላምና ወንድማማችነት ይበሰራል። ሕዝቡ ወደ ወንዞችና ሐይቆች በመሄድ እርጥብ ሳር፣ አለንጌ እና ቦኩ ይዞ አምላክን በማመስገን በተፈጥሮና በሰው ልጅ መካከል ያለውን ጠንካራ ቁርኝት ያሳያል። በአባ ገዳዎች እና በሀደ ሲንቄዎች በሚመራው በዚህ ሥርዓት ላይ ባህላዊ ዘፈኖችና ጭፈራዎች የበዓሉን ድምቀት የበለጠ ያጎሉታል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የኢሬቻ በዓል ከሀገር ውስጥ አልፎ በርካታ የውጭ ሀገር ቱሪስቶች እና የዲያስፖራ አባላት የሚታደሙበት ዓለም አቀፋዊ የቱሪዝም ሀብት እየሆነ መጥቷል።

ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ እንግዶች ሀገር በቀል እውቀቶችን፣ የባህል አልባሳትንና የጥበብ ስራዎችን እንዲተዋወቁ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል፤ ይህም ለሀገር ውስጥ ኢኮኖሚና ለቱሪዝም እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው።

በአጠቃላይ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ እሴት ከመሆኑም በላይ፣ የኢትዮጵያውያንን አንድነትና ኅብረ-ቀለም በግልጽ የሚያሳይ የጋራ መድረክ ሆኗል። ታዳሚዎች የተፈጥሮን መታደስ እያሰቡ አምላክን ማመስገን፣ ሰላምን መስበክና ባህላዊ ውበቶችን ማጎልበት የዚህ ታላቅ በዓል ዋና መገለጫዎች ናቸው።



የካይሮ የጥላቻ ዲፕሎማሲ እና የኢትዮጵያ የፀና ሉዓላዊነት*******************ኢትዮጵያ በቅርቡ በብሔራዊ ደኅንነቷ እና በሉዓላዊነቷ ላይ የተደቀነን አደጋ በማክሸፍ፣ የዲፕሎማሲያዊ ከ...
04/10/2026

የካይሮ የጥላቻ ዲፕሎማሲ እና የኢትዮጵያ የፀና ሉዓላዊነት
*******************

ኢትዮጵያ በቅርቡ በብሔራዊ ደኅንነቷ እና በሉዓላዊነቷ ላይ የተደቀነን አደጋ በማክሸፍ፣ የዲፕሎማሲያዊ ከለላን ለስለላ እና ተቀባይነት ለሌለው ተግባር ያዋለ የግብፅ ዲፕሎማትን ከሀገር እንዲወጣ ማድረጓ የተጣለባትን ታሪካዊና ሕጋዊ ኃላፊነት የተወጣችበት ውሳኔ ነው፡፡

ይህ እርምጃ በ1961 በተደነገገው የቪየና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ኮንቬንሽን አንቀጽ 9 ለማንኛውም ተቀባይ ሀገር የሚሰጠውን የመብት ጥበቃ መሠረት ያደረገ ሲሆን፣ የሀገርን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ አካላትን "ፐርሶና ኖን ግራታ" ብሎ የማባረር ሙሉ ሕጋዊ መብትን ያረጋገጠ ነው፡፡

ይህንን ተከትሎ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ እና ያንጸባረቀው አቋም፣ መጥፎ ድርጊቷን ለመሸፈን የምታደርገውን የተለመደ የፖለቲካ አሻጥር የሚያሳይ ነው፡፡

የካይሮ ባለሥልጣናት "በሌሎች ሀገራት የውስጥ ጉዳይ አንገባም" የሚል የዲፕሎማሲ ሽፋን በመጠቀም የተለመደውን ማስተባበያ ቢያቀርቡም፣ እውነታው ግን በተቃራኒው እንደሆነ ታሪክ እና ወቅታዊ ሁነቶች ይመሰክራሉ፡፡

ግብፅ የኢትዮጵያን ዕድገት፣ ሰላም እና ልማት ለማስተጓጎል አቅዳ ስትሠራ መቆየቷ በታሪክ ሰነዶች ላይ የሰፈረ እውነት ነው፡፡

በዓባይ ውኃ ፍሰት ላይ ያለፉትን የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶች ተንተርሳ የበላይነትን ለማስጠበቅ ካላት ፍላጎት በመነሳት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚነሱ ልዩ ልዩ አማጺያንን እና ታጣቂ ቡድኖችን በገንዘብ፣ በወታደራዊ ቁሳቁስ እና በሥልጠና ስታደራጅ እና ስትረዳ ቆይታለች፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ግዙፍ የፕሮፓጋንዳ ማሽኖቿን በመጠቀም በሕዝቦች መካከል መጠራጠር እንዲነግሥ፣ የሕዝብ አንድነት እንዲላላ እና የኢትዮጵያን ገጽታ በዓለም አቀፍ መድረክ ለማጠልሸት የተለያዩ ስልቶችን ስትጠቀም ኖራለች፡፡

የካይሮ እኩይ ሴራ በፖለቲካዊ መስክ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ይልቁንም መንፈሳዊ እና ሰማያዊ የሆነውን ሃይማኖት እንኳን ሳይቀር ለፖለቲካዊ ጥቅም መገልገያ ስታደርገው ቆይታለች፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ከእስክንድርያ ይሾሙ የነበረበትን እና እስከ እ.አ.አ 1959 ድረስ የዘለቀውን የ1 ሺህ 600 ዓመታት የታሪክ አጋጣሚ ግብፅ ጥቂቶቹን እንደ ለስላሳ ኃይል መሣሪያ በመጠቀም፣ የኢትዮጵያ ነገሥታት በዓባይ ወንዝ ላይ የልማት ሥራ እንዳይሠሩ ጫና ስታደርግ ነበር፡፡

በዲፕሎማሲያዊ መብት እና ከለላ ስም የተላኩ የግብፅ ዲፕሎማቶች ከተሰጣቸው ተልዕኮ ወጥተው በደኅንነት መዋቅር ላይ አደጋ የሚያደርሱ ተግባራት ላይ መገኘታቸው፣ ካይሮ ዲፕሎማሲን ለስለላ እና ላልተገባ ዓላማ መጠቀሟን ያረጋገጠ ነው፡፡

ይህ ሁሉ ሴራ እና ትንኮሳ ሲፈጸምባት የኖረችው ኢትዮጵያ ግን አፍሪካዊ ወንድማማችነትን እና ቀጣናዊ ትስስርን መርሕ በማድረግ አጸፋዊ አጥፊ እርምጃዎችን ከመውሰድ ተቆጥባ በትዕግሥት እና በሰላማዊ መንገድ አልፋዋለች፡፡

የኢትዮጵያ ትዕግሥት እና ምክንያታዊነት የረጅም ዘመን ታሪካዊ ልዕልና እና የዲፕሎማሲ ብስለት መገለጫ እንጂ የድክመት ምልክት አለመሆኑን የካይሮ ፖሊሲ አውጪዎች ሊረዱት ይገባል፡፡

የዲፕሎማቱን ከሀገር መባረር ተከትሎ ግብፅ እውነታውን ለማዞር እና ራሷን እንደ ተበዳይ ለማቅረብ የምታደርገው ጥረት፣ በዓለም አቀፍ ሕግ እና በዲፕሎማሲያዊ ልማዶች ፊት ተቀባይነት የለውም፡፡

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነቷን እና ሉዓላዊነቷን አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም አካል በጽናት የመመከት ሕጋዊ እና ሞራላዊ መብቷ የተጠበቀ ነው፡፡

ካይሮ ታሪካዊ ስህተቶቿን በዲፕሎማሲያዊ መግለጫዎች ለመሸፈን ከመሞከር ይልቅ፣ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ መከባበርና እኩልነት ላይ የተመሠረተ እውነተኛ አጋርነት መገንባት ብቸኛው የቀጣናው ሰላም ማረጋገጫ መንገድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባታል፡፡




04/10/2026



ብቃት እንጂ ኮታ አይደለም - ለአዲሱ የመንግሥት ምስረታ የቀረበ ጥሪ፣ መስከረም 24፣ 2019  በነገው ዕለት የሚካሄደው የመንግሥት ምስረታ ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ከተደቀኑባት ዘ...
04/10/2026

ብቃት እንጂ ኮታ አይደለም - ለአዲሱ የመንግሥት ምስረታ የቀረበ ጥሪ

፣ መስከረም 24፣ 2019 በነገው ዕለት የሚካሄደው የመንግሥት ምስረታ ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ከተደቀኑባት ዘመን ተሻጋሪ ፈተናዎችና እድሎች አንፃር ሲታይ እጅግ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

የሚመሰረተው አዲስ መንግሥት ሀገርን የሚያሻግር፣ ፍትህን የሚያረጋግጥ፣ ሀገር የሁሉም መሆኗን በተግባር የሚያሳይና በጋራ ጠንካራ ሀገር የመመስረት ሂደቱን ይበልጥ የሚያፋጥን እንዲሆን የሕዝብ ተስፋ ከፍተኛ ነው።

ሆኖም ይህ ተስፋ እውን ሊሆን የሚችለው የመንግሥት ስልጣን ክፍፍል በብቃት፣ በአርቆ አሳቢነትና በሀገር አራማጅነት ላይ ሲመሰረት፤ በብሄር ወይም በቡድን "ኮታ" ስብስብ ላይ ሳይወድቅ ሲቀር ብቻ ነው።

የስልጣን ክፍፍልን በኮታ ማደላደል ለጊዜያዊ የፖለቲካ ማረጋጊያ ይጠቅም ከሆነ እንጂ፤ በረጅም ጊዜ ውጤቱ የተቋማት መዳከምን፣ የሙስና መስፋፋትንና የአመራር ውድቀትን እንደሚያስከትል የታሪክ ተሞክሯችን ያሳያል።

ሀገርን ወደተሻለ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚቻለው ይዘውት የሚመጡት የብሄር ወይም የቡድን ማንነት ብቻ ሳይሆን፤ ያላቸው እውቀት፣ ክህሎት፣ ስነምግባር እንዲሁም አርቆ አሳቢነት በሚመዝናቸው አዳዲስ መሪዎችና ባለሙያዎች ስብስብ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት በተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ እንደገለጹት፤ የአንዲት ሀገር ጥንካሬ በምትገነባቸው ጠንካራ ተቋማትና በተቋማቱ ውስጥ በሚመደቡ ብቁ ስብዕናዎች ይወሰናል፡፡

ስልጣን ኮታ ሲሆን ተቋማት የቡድን ጥቅም ማስጠበቂያ ይሆናሉ፤ ብቃት ሲሆን ግን ተቋማት ለሕዝብ እኩል አገልግሎት የሚሰጡ የአገልግሎት ማዕከል እንደሚሆኑም ይኸው መጽሐፋቸው ያትታል፡፡

ቀጣይ ሀገር ለመምራት በሚመሰረተው መንግሥት ውስጥ የሚካተቱ አመራሮች የዕለት ተዕለት የፖለቲካ ትኩሳትን ብቻ የሚመለከቱ ሳይሆን፤ የሀገሪቱን የቀጣይ ዓመታት ህልም የሚቀርፁ አርቆ አሳቢዎችና ለውጡን ከመሬት የሚያገናኙ ሀገር አራማጆች ሊሆኑ ይገባል።

«የመደመር መንገድ» መፅሐፍ ውስጥ እንደተወሳው፤ ሀገራዊ ትረካችንን ከግጭትና ከከፋፋይነት ወደ ልማትና ህብረት ለመቀየር የላቀ የሀሳብ ልህቀት ያላቸው መሪዎች ያስፈልጉናል።

ብቃት ያለው አመራር የህግ የበላይነትንና ፍትሃዊነትን ያረጋግጣል፤ የሁሉም ዜጋ መብት እኩል የሚከበረውና ሀገር የሁሉም መሆኗ የሚረጋገጠው የመንግሥት አመራሮች ለሁሉም ዜጋ እኩል የሚቆሙ የሙያ ብቃት ሲኖራቸው ብቻ ነው።

አሁን ያለንበት ሀገራዊና ዓለምአቀፋዊ ሁኔታ በስሜት ሳይሆን በዕውቀትና በስትራቴጂ የሚመራ አመራርን ይፈልጋሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ጊዜያት ደጋግመው እንደገለጹት፤ ሀገር የምትገነባው በጋራ ስራና በችሎታ እንጂ በዘርና በፖለቲካ ቅርጫ አይደለም፡፡

ሀገር የሁሉም የምትሆነው ሁሉም ዜጋ በችሎታውና በስራው የሚመዘንበት ስርዓት ሲዘረጋ ነው፤ ይህ እውነት በነገው ዕለት ለሚመሰረተው መንግሥትም ዋና መርህ ሊሆን ይገባል።

FBC

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች በተገኙበት በተካሄደ መርሃ ግብር፤ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከብሔራዊ ምክክሩ የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦችንና ምክረ...
03/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዲሁም ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል አመራሮች በተገኙበት በተካሄደ መርሃ ግብር፤ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከብሔራዊ ምክክሩ የተገኙ የአጀንዳ ነጥቦችንና ምክረ ሐሳቦችን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሁም ለፌደራል እና ለክልል መንግሥታት ዛሬ በይፋ አስረክቧል።
‎
‎ይህ የሰነድ ርክክብ፤ በምክክርና በሰላማዊ መንገድ የኢትዮጵያን የቆዩ ሀገራዊ ፈተናዎች መፍታት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ፤ በመደመር መንግሥት ሕጋዊና ተቋማዊ ማዕቀፍ የተበጀለትን የሀገራዊ ምክክር ሂደት አንድ ትልቅ ምዕራፍ ያበስራል። ሂደቱ ለውይይት፣ ለጋራ መግባባት እና ስምምነትን ለመፍጠር የሚያስችል አካታች መድረክ መሥርቷል።
‎
‎ባለፉት አራት ዓመታትም ይህ ሂደት በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ማሳተፍ ችሏል። ተሳታፊዎች ባደረጓቸው ሰፊ ምክክሮች እና በተጠናቀቀው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ አማካኝነት እይታዎቻቸውን ለማንጸባረቅ፣ ልዩ ልዩ አመለካከቶችን ለመስማት እና የጋራ መግባባት የተደረሰባቸውን መስኮች ለመለየት ዕድል አግኝተዋል። የእነዚህ ውጤቶች በይፋ መቅረብ በምክክሩ የተሰበሰቡ እይታዎችንና የውሳኔ ሐሳቦችን ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ለማሸጋገር የተቀየሰ ትልቅ እርምጃ ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል መንግሥት እንዲሁም ለክልል...
03/10/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የተገኙና የአጀንዳ ነጥቦች እና ምክረ ሐሳቦች ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለፌደራል መንግሥት እንዲሁም ለክልል መንግሥታት በይፋ ርክክብ የተደረገበትን መርሃ ግብር ዛሬ ተከታትያለሁ።
‎
‎ይህ የሰነድ ርክክብ ሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ውስጥ ጉልህ ምዕራፍ የሚያስመዘግብ ሲሆን የኢትዮጵያን ዘላቂ ሀገራዊ ፈተናዎች አካታች በሆነ ውይይት፣ በሰላማዊ ምክክር እና በራሳችን ሀገር በቀል የመፍትሔ አምጭ እሴቶች ለመፍታት ያለንን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።

Address

Centeral Ethiopia Region
Hossana

Telephone

+251465551908

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hadiya zone Government Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share