29/05/2026
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን ከኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት ያለመ ውይይት ተካሄደ
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና ከኢትዮ–ጅቡቲ ብሔራዊ የባቡር መስመር ጋር ለማገናኘት በታቀደ የባቡር ፕሮጀክት ዙሪያ የባለድርሻ አካላት ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውደይይቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን መሬት እና መሰረተ ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጸጋየ ዘካሪያስ የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና እስከ 4,000 ሄክታር የመስፋት አቅም እንዳለው ጠቁመው ቀድሞ ከአማራጭ የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ጋር ማስተሳሰር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠናን ከባቡር ለማገናኘት የለጋሾች ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ጸጋዬ ለጋሾች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የነጻ የንግድ ቀጠናውን ከባቡር መስመሩ ጋር ለማገናኘት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ ገለጻ ያቀረቡት በኮርፖሬሽኑ የዲዛይን መምሪያ ሃላፊ አማኑኤል ለሚ በአሁኑ ጊዜ ወደ ነፃ ንግድ ቀጠናው የሚገቡና የሚወጡ ጭነቶች በአብዛኛው በመኪና የሚጓጓዙ ሲሆን፣ ይህም ከባቡር ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ የሎጂስቲክስ ወጪ እንደሚያስወጣ ገልጸዋል።
የባቡር መስመሩን ከነጻ ንግድ ቀጠናው ጋር የሚያገናኘው ፕሮጀክቱ እውን ሲሆን 30 በመቶ ያህል የጭነት ማጓጓዣን ከመንገድ ወደ ባቡር ለማሸጋገር ያለመ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በገለጻው ላይ ፕሮጀክቱ በፋይናንስ አዋጭነት ከፍተኛ እንደሆነ፣ የጥናት ሥራዎች መጠናቀቃቸው እና ለኢንቨስትመንት ዝግጁ ደረጃ መድረሱ ተመላክቷል።
ፕሮጀክቱን የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፣ የኢንዱስትሪ ልማት ፖሊሲ እና የብሔራዊ ሎጂስቲክስ ስትራቴጂ ጋር የተጣጣመ መሆኑም ተገልጿል።
በዩናይትድ ኪንግደም ሴንተር ኦፍ ኤክስፐርታይዝ የተዘጋጀው የውይይት መድረክ የድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጠናን ከኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መስመር ጋር ከማገናኘት ባለፈ በከተማዋ ሊተገበሩ በታሰቡ ሌሎች ፕሮጀክቶች ዙሪያ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አሳትፏል፡፡
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30
24/05/2026
በአዲሱ የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ሥልጠና ተሰጠ
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሚገኙ የግዥ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈጻጸም መመሪያን በተመለከተ ሥልጠና ተሰጥቷል።
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የኮርፖሬሽኑ የግዥ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት የማነ ሥልጠናው በአዲሱ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የግዥ መመሪያ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር የሚፈጸሙ ግዥዎችን በተቀላጠፈ መልኩ ማከናወን እንዲቻል ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ለሁለት ተከታታይ ቀናት በተዘጋጀው በዚህ ሥልጠና ላይ የኮርፖሬሽኑ የሥራ መሪዎች፣ የቅርንጫፍ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ሥልጠናው በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አማካኝነት የተዘጋጀ መሆኑም ታውቋል።
በተሻሻለው የመንግስት ልማት ድርጅቶች የግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ መሠረት የተዘጋጀው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ከሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ መዋሉ ይታወሳል።
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB3
19/05/2026
የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶች በአዲስ አበባ የሚገኙ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን ጎብኙ
በአዲስ አበባ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎችን፣ የኩባንያዎችን የሥራ ሂደት ተመልክተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ የጉብኝት መርሃ ግብር ላይ ቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን፣ የቂሊንጦ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን፣ እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ፓርክን ጎብኝተዋል።
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኦፐሬሽንና ፓርክ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ፍጹም ከተማ ለዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡና አምባሳደሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ ለዝግጅቱ መሳካት ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ ፍጹም በንግግራቸው ኮርፖሬሽኑ በአሁኑ ወቅት በመላው ኢትዮጵያ 14 ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችን እና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እያለማና እያስተዳደረ መሆኑን ጠቅሰው እነዚህ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ማዕከላት ኢንቨስትመንትን፣ ኢንዱስትሪያላይዜሽንን፣ የኤክስፖርት እድገትን፣ተኪ ምርት ማምረትን፤ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እና የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማበረታታት ታስበው የተገነቡ ናቸው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት የአይሲቲ ፓርክን ጨምሮ በእነዚህ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ከ300 በላይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙና ከ100,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል።
የዛሬው የቦሌ ለሚ፣ የቂሊንጦ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች እና የአይሲቲ ፓርክ ጉብኝት ለዲፕሎማቶቹ በኢንቨስትመንት ሥነ ምህዳሩ ውስጥ ስላሉት ዕድሎችና ቀጣይ ዕድገቶች አጭር ግንዛቤ ያስጨበጠ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ ይህ ዓይነቱ ትብብር አዳዲስ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ለሚገኙ ባለሀብቶች የሚደረገውን ድጋፍና አጋርነት ለማጠናከር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አስገንዝበዋል።
በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚው ዘርፍ እያደረገች ያለው እንቅስቃሴ ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ መሆኑንና በተለይም ልዩ የኢንኮኖሚ ዞኖች የተለያዩ ሀገራት ባለሀብቶችና አልሚዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚያነሳሱ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ዲፕሎማቶቹ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አልምቶ ከሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች በተጨማሪ በግል ባለሃብቶች የለሙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝተዋል፡፡
Diplomats Visit Special Economic Zones in Addis Ababa to Explore Investment Opportunities
Ambassadors and members of the diplomatic community based in Addis Ababa visited several special economic zones in the capital to observe ongoing development activities and the operational performance of companies working within the zones.
The visit was organized collaboratively by the Ministry of Foreign Affairs, the Ethiopian Investment Commission, and the Industrial Parks Development Corporation (IPDC). During the tour, the diplomats visited the Bole Lemi Special Economic Zone, the Kilinto Special Economic Zone, and the Information Communication Technology (ICT) Park.
Speaking during the event, IPDC Deputy Chief Executive Officer for Operations and Park Administration, Fitsum Ketema, welcomed the ambassadors and diplomats and thanked the Ministry of Foreign Affairs and the Ethiopian Investment Commission for their cooperation in organizing the visit.
Fitsum stated that the corporation is currently developing and managing 14 special economic zones and industrial parks across Ethiopia. According to him, the worldclass facilities were established to promote investment, industrialization, export growth, import substitution, technology transfer, and employment creation.
He further explained that more than 300 investment projects operating in various sectors — including those in the ICT Park — are currently active within the special economic zones, generating permanent employment opportunities for over 100,000 Ethiopians.
The deputy CEO noted that the tour provided diplomats with insight into the opportunities and prospects within Ethiopia’s investment environment. He added that such engagements are essential not only for attracting new foreign investment but also for strengthening support and partnerships with investors already operating in the country.
The participating ambassadors and diplomats praised Ethiopia’s ongoing economic transformation, describing it as a positive example for other countries. They emphasized that the special economic zones are playing a significant role in attracting international investors and developers to Ethiopia.
In addition to the government-developed and managed special economic zones under the Industrial Parks Development Corporation, the diplomats also visited industrial parks and SEZs established by private investors.
በዌብሳይት - https://ipdc.gov.et/
በፌስቡክ - https://www.facebook.com/IPDCEthiopiaofficial
በትዊተር (ኤክስ) - https://x.com/EthiopiaIpdc
በቴሌግራም - https://t.me/ipdcofficial
በሊንክድ ኢን - https://www.linkedin.com/company/ipdcethiopiaofficial
በኢንስታግራም - https://www.instagram.com/ipdc_et
በዩቲዩብ - https://www.youtube.com/
በቲክቶክ - https://www.tiktok.com/
በቴሌግራም ቦት፡- https://t.me/ipdctchatbot
በዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCUHKJP21D0s3OEB30 See less