ስንኖር/Sinenor /ማህበራዊ ክላስተር

ስንኖር/Sinenor /ማህበራዊ ክላስተር

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ስንኖር/Sinenor /ማህበራዊ ክላስተር, Government Organization, Bole Road, Addis Ababa.

21/09/2025

እሁድን በስራ

28/05/2022

የህግ የበላይነት መከበር የሁላችንም ዋስትና ነው።

Photos from የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia's post 18/03/2022

የሚበረታታና ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ተግባር ነውና በርቱልን!

Photos from የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia's post 11/03/2022
Photos from ስንኖር/Sinenor /ማህበራዊ ክላስተር's post 27/02/2022

በቅንነት ማገልገል ያስመሰግናል ያሸልማል!

በቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የገነት ሆቴልን እስከ 45 አመት በማገልገል ጡረታ ለወጡ ሰራተኞች፣ ሆቴሉን በሥራ አስኪያጅነት እንዲያገለግሉ ተመድበው ሲሰሩ የቆዩት አቶ አበበ ኡርጌሳ እንዲሁም በሥራ አመራር ቦርድ አባልነት ያገለገሉትን ግለሰቦች የምስጋናና እውቅና መርሃ ግብር አከናውነናል። በቦርድ አባልነት የምስክር ወረቀት፣ በጡረታ ለተሰናበቱት የሸማ ውጤቶችና ቦርዱን በሥራ አስኪያጅነት ሲያገለግሉ በመልካም ስነምግባር፣ የሰራተኞችን ችግር በመፍታትና በማበረታታት፣ ከቦርዱ የሚሰጡ ተግባራትን በመቀበል የከርሰምድር ውሃ እንዲወጣ፣ አዳራሽና የሆቴሉን ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲታደስ፣ የመዋቅር ጥናት በማስደረግ አገልግሎቱ እንዲሻሻልና የውጭ ገፅታውን በማሻሻል ላደረጉት ትጋትና ውጤት የወርቅ ሀብል ተበርክቶላቸዋል። ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱ በርካታ ችግሮች ያሉበት ቢሆንም ከችግሮቹ በላይ እልፍ ምቹ ሁኔታዎች ያሉት በመሆኑ በአዲሱ የመንግስት አደረጃጀት የስልጠና አቅሙ እንዲያድግ፣ በበጀትና በለጋሽ ድርጅቶች ድጋፍ ታግዞ ሰፋፊ የሥራ እድል የሚፈጥሩ የሥልጠና እድሎችን የሚያዘጋጅ በመሆኑ የገነት ሆቴል ከዚህ ቁጥቁጥ እድገት ተላቆ ሞዴል ሆቴል፣ ኢንስቲትዩቱም የልህቀት ማእከል እንዲሆን በሥራና ክህሎት ሚንስትሮቾ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተለያዩ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ ነው። ለዚህም የተቋሙ አመራሮችና ማህበረሰብ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በአንድነት በመቆም የተጣለብንን ሃላፊነት እንድንወጣ ጥሪ ለማስተላለፍ እወዳለሁ።

Photos from Office of the President, Ethiopia's post 28/11/2021
20/11/2021

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ ህጻናት ቀን የተፈናቀሉና በችግር ውስጥ የሚገኙ ህጻናትን በመደገፍ ይከበራል፦ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ
*******************

የዘንድሮው ዓለም አቀፍ ህጻናት ቀን የተፈናቀሉና በችግር ውስጥ የሚገኙ ህጻናትን በመደገፍ እንደሚከበር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አስታወቁ።

ሚኒስትሯ ይህን ያሉት ህዳር 11 የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የህጻናት ቀንን አስመልክተው በጽ/ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።

አገሪቱ ሳትወድ በገባችው ጦርነት ሳቢያ ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ወገኖችን በማጽናናትና በመደገፍ እንዲሁም ህጻናትን በሚያሳትፉ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች እንደሚከበር ተገልጿል፡፡

ዓለም አቀፍ የህጻናት ቀን ዘንድሮ “ሀገር የሚገነባው ለዛሬዎቹ ህጻናት በምንሰጠው ትኩረት ነው!” በሚል አገራዊ መሪ ቃል በአለም ለ32ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ16ኛ ጊዜ “ ይከበራል፡፡

በሰሜኑ አካባቢ እየተካሄደ ያለውን ህግ የማስከበርና የህልውና ዘመቻ ተከትሎ አሸባሪው ህወሓት ታዳጊ ህጻናትን በአውደ ውጊያ እንዲሳተፉ በማስገደድ ለከፋ ስቃይና እንግልት አልፎ ተርፎም ለሞት እንዲዳረጉ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ በሀይል ወረራ በፈጸመባቸው አማራና አፋር ክልሎች ህጻናትን ጨምሮ በንጹሃን ዜጎች ላይ ኢ-ሰብዓዊና አረመኔያዊ ድርጊት በመፈጸም በርካቶችን ለህልፈትና አካል መጉደል ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል::

ጥቂት በማይባሉ ልጃገረዶችና ታዳጊ ሴት ህጻናት የአስገድዶ መደፈር ወንጀል መፈጸሙን በሰብዓዊ ተቋማት መረጋገጡን የጠቀሱት ሚኒስትሯ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ያለወላጅና ያለአሳዳጊ ቀርተዋል ብለዋል፡፡

ለችግር ተጋላጭ የሆኑ እነዚህ ህጻናት የገጠማቸውን ተደራራቢና ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታትና ህይወታቸውን በዘላቂነት ለመታደግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ኤርጎጌ “ሀገር ትቀጥላለች፤ትዉልድም ይቀጥላል ለዚህም ሁላችንም ለዛሬዉ ህጻናት አስፈላጊዉን ትኩረት ልንሰጥ ይገባናል” ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/EBCworld/
የመዝናኛ ቻናላችን የቪዲዮ መረጃዎችን ለማግኘት የዩቲዩብ የመዝናኛ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCp9pS23Vw1n8WpcpZBDJNmA
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
https://www.instagram.com/ebcnews1/
አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ
https://twitter.com/ebczena
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/EBCNEWSNOW

Photos from የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር   Ministry of Women and Social Affairs's post 23/10/2021
Photos from Wondim Teklu's post 21/06/2021
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

Bole Road
Addis Ababa
1444