Akaki Kality Woreda 9 communication-አቃቂ ቃሊቲ
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ኮሙኒከሽን ጉዳዮች ቢሮ በወረዳችን የተሰሩ ስራዎች እና መሰራት ያለባቸውን የህዝብ ጥያቄዎች ተደራሽ ያደርጋል።
02/06/2026
የረዳን ፈጣሪ አምላክ የተመሰገነ ይሁን!!
ዛሬ በምርጫ ማግስት የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአገልግሎት መስጫዎች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ተመርቀው ለህዝብ ክፍት አድርገናል።
በከተማችን ለሚገኙ ለብዙዎቹ ወንዞች መነሻና የከተማችን ሳምባ የሆነው ደን የሚገኝበት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ ያለው አካባቢ ወደ ተፈጥሯዊ ይዘቱ ተመልሶ የአካባቢውን ማህበረሰብ አኩሪ የስራ ባህል የሚዘክሩ ሃውልቶችና ቅርሶች ተገንብተውለት አካባቢው ፍፁም ማራኪ እና የሚያስደንቅ ገፅታን ተላብስሶ ተጠናቋል።
የቀጨኔ አካባቢ ከዚህ ቀደም ለሰው ኑሮ ምቹ ያልሆነ፣ ለአደጋ የተጋለጠ እና የተጎሳቆለ አካባቢን መልሶ በማልማት ውስን የሆነውን የከተማዋን የመሬት ሀብት ለብዙሃን አገልግሎት እንዲሰጥ በሚያስችል መልኩ ለምቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።
597 ሄክታር ቦታ እና 9.6 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ለመዝናኛ፣ ለንግድና ለተለያዩ ማህበራዊ ኩነቶች ተስማሚ በሆነ መልኩ የተገነባ ሰፊ የከተማ መናፈሻ ሆኗል።
በከተማ ግብርና ስራዎች 15 ሄክታር ቦታ በአረንጓዴ የተሸፈነ ሲሆን፣ ቀሪው ደግሞ በ210 ቀፎ ዘመናዊ ንብ እርባታ፣ በአበባ ጋርደን እና በእፀዋት ጋርደን ለምቷል።
እንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ያካተታቸው ሌሎች መሰረተ ልማቶች፦
6.4 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ፣ 8 ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ፣ 22 ክሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣ 4 ኪሎ ሜትር ሃይኪንግ መንገድ፣ 39 ቼክ ዳም ተገንብተዋል።
2 አዲስ የተሽከርካሪ ድልድዮች ሲገነቡ፣ 3 ነባር የተሽከርካሪ ድልድዮች እድሳት ተደርጎላቸዋል። እንዲሁም ሌሎች የእረንጓዴ ልማት ጥንቅቅ ብለው ለምተዋል።
የከተማችን ነዋሪዎችን እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ፣ ይህንን ልዩ ሆኖ የተጠናቀቀ የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት አዕምሮችሁን ዘና አካላችሁን ፈታ እያደረጋችሁ እንድትገለገሉበት እና ረጅም አገልግሎት እንዲሰጥ እንድትንከባከቡት አደራ እላለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያና እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
02/06/2026
ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት፣ ዛሬ ጠዋት ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለውን የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በይፋ ስራ አስጀምረናል።
ይህ ትልቅ ተነሳሽነት፤ የተራቆቱ አካባቢዎችን በዘመናዊ የአፈር ጥበቃ እና በወንዝ ማጣራት ወደ አረንጓዴ ስፍራዎች በመቀየር፣ የፍራፍሬ ፓርኮችን ከእግር ጉዞ እና ከብስክሌት መንገዶች ጋር በማቀናጀት መዲናችንን አድሷል።
በአጠቃላይ 22.25 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማትን የሚሸፍነው ይህ ፕሮጀክት፤ የማይቆራረጥ የልማት ስራችን ህያው ምስክር ከመሆኑም በላይ የሃገራዊ ዕድገታችን፣ የአካባቢ ጥበቃ እና የከተማ እድሳት በተግባር የታየበት ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አሕመድ
02/06/2026
የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የድምፅ መስጫ ሂደቱ እስከ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ሲከናወን ቆይቷል። በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
በትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ግንቦት 24 ቀንም ሆነ ሌሊት ምንም አይነት ወንጀል አለመፈጸሙ ተገልጿል።
ድምጽ የመስጠት ስርዓቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ መራጩ ህዝብ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዕጩዎች እና ታዛቢዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለተወጡ መላው የጸጥታ አካላት ኮማንድ ፖስቱ ምስጋናውን አቅርቧል።
ድምጽ ቆጠራው ቀጥሏል።
ድህረ ምርጫ ያለው ሂደት በተመሳሳይ በስኬት እንዲከናወን ባለ ድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የተደራጀው የምርጫ ኮማንድ ፖስት ጥሪውን አቅርቧል።
02/06/2026
ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!
ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ኹሉ በፈለገችው ጊዜና ኹኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች፡፡ ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል፡፡ ዛሬ የተደገመዉም ይኸው ነው፡፡
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር፡፡
በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈዉ ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው፡፡
ምርጫዉ እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተዉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡
የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃዉ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫዉን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፡፡
የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ግንቦት 25 2018፣አዲስአበባ፣ኢትዮጵያ
01/06/2026
እስከ ሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ድረስ በሰልፍ የቆዩት የአዲስ አበባ ጽኑ ሕዝብ
01/06/2026
01/06/2026
አዲስ አላጠናቀቀችም አሁንም እየመረጠች ነዉ።
ፅኑ ህዝብ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
01/06/2026
01/06/2026
"ድምፃችንን ሳንሰጥ ወደ ቤት አንገባም"፦ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የወረዳ 9 ነዋሪዎች ድምፅ ለመስጠት የወጡ ነዋሪዎች
Click here to claim your Sponsored Listing.
