Federal Urban Job Creation and Food Security Agency - Ethiopia

Federal Urban Job Creation and Food Security Agency - Ethiopia

Share

Federal Urban Job Creation and Food Security Agency

15/04/2022

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚያዝያ 9 ቀን ጀምሮ አውደ ርዕይ እና ባዛር ያካሂዳል
***********************************************
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚያዝያ 9 ቀን እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ አውደ ርዕይ እና ባዛር እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡
በአውደ ርዕዩ 181 አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች 10 መካከለኛ ማኑፈከቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም 8 ተቋማት በድምሩ 199 ኢንተርፕራይዞች ተሳታፊ ይሆናሉ፡፡
በሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን መሪ ወይዘሮ አቦዘነች ነጋሽ እንደገለፁት÷ 50 በመቶ ኢንተርፕራይዞቹ የሴቶች ሲሆኑ አምስት ኢንተርፕራይዞች ደግሞ የአካል ጉዳተኞች ናቸው፡፡
አውደ ርዕዩ እና ባዛሩ 22 ሺህ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሯ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዋናነትም የገበያ ትስስርን ለማጠናከር እና ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በምርትና በጥራት መሻሻሎችን ማሳየታቸውን ለማረጋገጥ ታስቦ መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡
አውደ ርዕዩ ጀሞ ቁጥር 1 አደባባይ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
በፈትያ አብደላ
ምንጭ ፋና ድረ ገጽ

15/04/2022
Photos from Federal Urban Job Creation and Food Security Agency - Ethiopia's post 13/04/2022

ዘመናዊ የሀብት ምዝገባ ስርዓት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ
---------
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር አመራርና ሰራተኞች ሀብት በዘመናዊ የሀብት ምዝግባ መረጃ ስርዓት (web based) ማከናወን የሚያስችል ስልጠና ሚያዚያ 4/2014 ዓ.ም ከፌደራል ጸረ-ሙስና ኮሚሽን በተገኙ ባለሙያዎች ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናዉን የሰጡት የፌዴራል ጸረ- ሙስና ኮሚሽን የሀብት ምዝገባ ባለሙያ አቶ ግርማ አበበ፤ በተቋማት ላይ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ለማስፈን ሀብትና ንብረትን ማስመዝገብ የጎላ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡
አቶ ግርማ አክለዉም ከዚህ በፊት በሰነድ የሀብት ምዝገባ ሥርዓት በርካታ ሥራዎች የተሰራ ቢሆንም በዲጅታል ሀብት ማስመዝገብ ማከናወን የተለያዩ ጉድለቶችን የሚዘጋ እና ዘመናዊ በሆነ መልኩ ለመከታተል ያስችላል ብለዋል፡፡

ዲጂታል የሀብት ምዝገባው ጊዜና ወጭ ቆጣቢ፣ የመረጃ ጥራትን፣ ትክክለኛነትንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያስችላል ተብሏል፡፡

በሀብት ማስመዝገብ ስርዓት ዉስጥ የሚካተቱት ተሿሚዎች፣ተመራጮች እና ሰራተኞች ሲሆኑ የሚንቀሳቀስ ሀብት፣ የማይንቀሳቀስ ሀብት፣ልዩ ልዩ ገቢዎችንና ህጋዊ የሆኑ እዳዎች በሀብት ማስመዝገብ ስርዓቱ የሚያልፉ መሆኑንም ተገልጿል፡፡

Photos from Federal Urban Job Creation and Food Security Agency - Ethiopia's post 24/02/2022

ስራ አጥ የነበሩ ወጣቶች ወደ ሥራ ማስገባት የሚስችል ተግባር ተኮር ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
************************************************
የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከጂ አይ ዜድ ጋር በመተባበር ለ 110 (አንድ መቶ አሥር) ወጣቶች በሳሙና፣ በዘይት፣ በሻማ እና በካልሲ አመራረት ዙሪያ የተዘጋጀ 34 ቀን የሚፈጅ በተግባር የተደገፈ ስልጠና በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ስልጠና ማዕከል እየተሰጠ ይገኛል፡፡

ወጣቶቹ በ22 ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ሲሆን የተግባር ስልጠናዉ ካጠናቀቁ በኋላ የማምረቻ ማሽን ቀርቦላቸዉ በቂርቆስ ክ/ከተማ በተዘጋጀላቸዉ የማምረቻ ቦታ ወደ ስራ እንዲሚገቡ ተገልጿል፡፡ በተመሳሳይ የብድር አገልግሎትም እንዲያገኙ ሁኔታዎች መመቻቸዉን ተጠቁሟል፡፡

ወጣቶቹ ከዚህ መፊት ምንም አይነት ስራ ያልነበራቸዉ የዩንቨርስቲ እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ምሩቃን ሲሆኑ ከተግባር ስልጠናዉ በተጨማሪ የኢንተርፕረነርሺፕ ስልጠና እና የንግድ እቅድ ስልጠና እንዲወስዱም ተደርጓል፡፡

Photos from የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ / Ministry of Labor and Skills- Ethiopia's post 07/02/2022
Photos from Federal Urban Job Creation and Food Security Agency - Ethiopia's post 01/02/2022

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራር እና ሠራተኞች በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ጎብኝተዋል።

በተለያዩ ዘርፎች የተደረገው ጉብኝት የቴክኒክና ሙያ ስልጠና፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና የኢንዱስትሪ ፓርኮችን ያካተተ ነው።
በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ በሀዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በተደረገው ጉብኝት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሌሎች ኮሌጅና ኢንስቲትዩቶች ጋር በማስተሳሰር ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
በቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚደረጉ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች የምርትና አገልግሎት አሰጣጥ ዘዴን የሚያሻሽሉ፣ ገቢን የሚየሳድጉ እና የህብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ የሚቀይሩ መሆን አለባቸው ተብሏል።
በሥራ ፣ ስራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ የተመራው ጉብኝት በሀዋሳ ከተማ በስምንቱ ክፍለ ከተሞች ካሉት 11 የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች የመናኸሪያ ፣ የመሀል ከተማ እና የምስራቅ ክፍለ ከተሞች ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮዎች የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች ተጎብኝተዋል።
በማክሮ ኢኮኖሚው ውስጥ ሚናቸውን የሚጫወቱ ኢንተርፕራይዞችን ለማፍራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ግብ እንደመሆኑ በሲዳማ ብሔራዊ ክልል ደረጃቸውን የጠበቁ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎችን ለማደራጀት እየተደረገ ያለው ጥረት ተመስግኗል።
በሠራተኛ ዘርፍ የተጎበኘው የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሲሆን ፓርኩ ለሠራተኞች ምቹ በመሆን እና ቴክኖሎጂን ለሀብት አጠቃቀም በማዋል በኩል ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆን ስራ መሰራቱ ተገልጿል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa