05/06/2026
ኮርፖሬሽኑ (EEC) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 85 ፕሮጀክቶችን በብቃት ማጠናቁቁን ገለጸ
ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ፤
ኮርፖሬሽኑ፣ በሥራ ላይ ከነበሩት 385 ፕሮጀክቶች መካከል በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት 85 ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ ከዕቅድ አኳያም ቀሪ የአንድ ወር ጊዜ ኖሮም በጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆኑ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
ይህ የተገለጸው አዲሱንና ኮርፖሬሽኑ ተግባራዊ ያደረገውን የመዋቅር አደረጃጀትና የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም በተመለከተ ከሠራተኞች ጋር ባደረገው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡
ውይይቱ በኮርፖሬሽኑ ሁሉም ቢዝነስ ዩኒቶች እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በትናንትናዉ ዕለት የዲዛይንና ማማከር ቢዝነስ ዩኒት በቁጥር 800 ገደማ ከሚሆኑ የቢዝነስ ዩኒቱ አጠቃላይ ሠራተኞችና በየደረጃው ካሉ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የዲዛይንና ማማከር ቢዝነስ ዩኒት ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቢይ ፀጋዬ (ኢንጅነር) በፓወር ፖይንት የተደገፈ ገለጻ አቅርበዋል፡፡
የቀረበውን ገለጻ ተመስርቶም ተሳታፊ ሠራተኞች ይህን መሰሉ ውይይት ኮርፖሬሽኑ ሊያሳካ ላቀዳቸው የላቁ ግቦች ውጤታማነት ጅምር በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
ሠራተኞቹ አያይዘውም፤ በመዋቅሩ አሰራርና በሠራተኞች ምደባ ዙሪያ፣ በውሎ አበል፣ በስልጠና፣ በሕክምናና በቢሮ ውስጥ የህጻናት ማቆያ ስፍራን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎችን አንስተዋል፡፡
ለተነሱት ጥያቄዎችም የሚመለከታቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በምላሹም ከስትራክቸሩ ጎን ለጎን የተለያዩ የአሰራር ማኑዋሎች ተግባራዊ በመሆን ላይ ሲሆኑ በአሁን ሰዓት እየተዘጋጁ ያሉት የአሰራር ሥርዓቶች ተከትሎ ከቤቱ የቀረቡት ልዩ ልዩ ጥያቄዎች በየደረጃው ምላሽ የሚያገኙበት መሆኑ ተመልክቷል፡፡
በመጨረሻም የኮርፖሬሽኑ (EEC) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሽመልስ እሸቱ (ኢንጅነር) በሰጡት ማጠቃለያ፣ ኢንዱስትሪው አሁን ባለበት ሁኔታ ተቋሙ በውጤታማነት ቀጥሎ መዋቅር መስራቱና ተግባራዊ ማድረጉ፤ ሊበረታታ የሚገባው ተግባር መሆኑን አስምረውበታል፡፡
አክለውም፤ ኮርፖሬሽኑ እያከናወናቸው ያሉትን ትላልቅ አገራዊ ሜጋ ፕሮጀክቶች በመጥቀስ፤ ከነዚህ መካከል የጂኦ ፖለቲካውና የነዳጅ ችግሮች ያስከተሉትን መስተጓጎል ተቋቁሞ፤ 85 ያህሉን በላቀ ብቃት ማጠናቀቅ የተቻለው፣ አመራሩና አጠቃላዩ ሠራተኛ ባደረገው ያላሰለሰ ትጋት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ ይኸው ተጠናክሮም ተቋሙን ወደፊት ማሻገር ይገባል ብለዋል፡፡
“የኮርፖሬሽኑ ትልቁ ሀብቱ ሰው ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በቀጣዩ አንድ ወር ቀሪ ተግባራትን ያለማንጠባጠብ መተግበር እንደሚገባና የሠራተኛውም አፈጻጸም በአግባቡ ሊመዘን እንደሚገባው፤ በተያያዘም በተመሳሳይ ከሠራተኞች የሚነሱ ጥያቄዎች እታች ባለው መዋቅር መፈታት የሚችሉትን አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
27/05/2026
Negele borena "Geda Airport" construction project inaugurated by PM Abiy Ahmed (Dr.)
We are very proud to participate on this valuable project.
27/05/2026
EEC wishes you a peaceful and blessed Eid al-Adha!
26/05/2026
ኮርፖሬሽኑ በአማካሪነት እየሠራበት የሚገኘው የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የአስፓልት ማንጠፍ ስራው ተጠናቋል
(ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ.ም)፣ አዲስ አበባ፤
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) የዲዛይን ማማከር እና የቁጥጥር ሥራ የሚያከናውንበት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው የአምቦ - ወሊሶ የመንገድ ግንባታ የአስፋልት ማንጠፍ ሥራ ተጠናቋል ፡፡
መንገዱ 63 ኪሎሜትር ርዝመት ሲኖረው፤ በግንባታው ሒደት የአፈር ቆረጣና ሙሌት ፣ የሰብ ቤዝ እና የቤዝ ኮርስ፣ የ 5 ድልድዮች ግንባታ በተጨማሪም 63 ኪሎሜትር የአስፋልት ንጣፍ ሥራ የተከናወነለት ሲሆን በቀበሌ 7 ሜትር፣ በዞን እና በወረዳ 14 ሜትር እንዲሁም በከተማ ደግሞ ወደጎን 21 ሜትር ስፋት ኖሮት ተገንብቷል፡፡
ይህ በ’ንዲህ እያለ የመንገዱን ቀሪ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ይኸውም ፡- የስላብ ከልቨርትና የድሬኔጅ ሥራዎች ፣ የመንገድ ምልክቶች እንዲሁም በአምቦ እና በወሊሶ ከተሞች የእግረኛ መሄጃ የመንገድ ሥራዎችን እየተገባደደ ባለው በጀት አመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል ።
ከአዲስ አበባ በ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከምትገኘዉ አምቦ ከተማ ተነስቶ ወሊሶ ከተማ ላይ የሚያበቃው ፕሮጀክቱ፣ የምዕራብ ሸዋ (አምቦ) እና የደቡብ ምዕራብ ሸዋ (ወሊሶ) ከተሞችን እንዲሁም የጭቱ ወረዳን፣ የዳርያን እና አልቱፋ ቀበሌዎችን በቅርበት ከማስተሳሰሩ ባለፈ፤ ቀድሞ ይወስድ የነበረውን የጉዞ ጊዜም ያሳጥራል፡፡
ይህን ተከትሎም፤ የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ችግር ከመቅረፍ ባሻገር፤ በአካባቢዉ የሚመረተውን የግብርና ምርት በቀላሉ ወደ ገበያ እንዲገባ በማድረግ፤ አምራቹንም ሆነ ሸማቹን ህብረተሰብ ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
ከዚህ በተጓዳኝም የገበታ ለሐገር ማዕቀፍ የሆነው ‘’የወንጪ ኢኮ ሎጅ’’፣ መንገዱ በሚያልፍበት አቅራቢያ ይገኛል።
21/05/2026
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ለዓለም ከተሞች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑ ተገለጸ
(ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም) አዲስ አበባ፤
በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወነው አስደናቂ የኮሪደር ልማት ሥራ፣ ከተሞችን እንዴት ለዜጎች ምቹ፣ ውብና ተስማሚ አድርጎ መገንባት እንደሚቻል ለመላው ዓለም ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን እንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ዳንኤል ካርል ገለጸ።
በኮሪደር ልማቶቹ ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ ያለው ኮርፖሬሽናችን (EEC) በከተማ ፕላን የረጅም ጊዜ ልምድ ያለው ሲሆን፣ መዲናችን አዲስ አበባን ጨምሮ በክልል ከተሞች ይኸውም፡- በጂማ፣ በሐዋሳ፣ በአዳማና በቢሾፍቱ ከተሞች ባሉ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶች ላይ በአማካሪነት በመሳተፍ የዚህ አንፀባራቂና ዘመን ተሻጋሪ ልማት፣ የታሪክ ተቋዳሽ መሆኑን በማስመስከር ላይ ነው፡፡
መቀመጫቸውን በእንግሊዝ አገር ያደረጉ ስምንት ዓለም አቀፍ ምሁራንና ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ ፈጣን የለውጥ ጉዞ ላይ ጥናት ማካሄዳቸውን ጋዜጠኛው የገለጸ ሲሆን፣ ይህ ጥናታዊ ግኝታቸውም በቅርቡ መጽሐፍ ሆኖ ታትሟል።
በጥናቱ ላይ በንቃት የተሳተፈው ጋዜጠኛ ዳንኤል ካርል፤ ከዓመታት በፊት የምናውቃት አዲስ አበባ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ባከናወነችው ዘመናዊ የከተማ ልማት ግንባታ በአሁኑ ወቅት ዓለም ሁሉ ሊያያቸውና ሊጎበኛቸው ከሚጓጓላቸው ከተሞች ተርታ መሰለፏን ገልጿል።
ከተማዋ በአሁኑ ወቅት በአረንጓዴ ሽፋኗ፣ በበለጸገ ውበቷ እንዲሁም በእግርና በሳይክል ለመጓዝ ባላት ምቹነት ተወዳጅ አድርጓታል ሲል ጋዜጠኛው ጠቁሟል።
የተከናወነው የከተማ ልማት ሥራ በተለይም የአፍሪካ መሪዎች ከተሞቻቸውን ለዜጎቻቸው በሚመጥን መልኩ እንዴት ማልማት እንዳለባቸው የሚያሳይ ተመራጭ ተግባራዊ ሞዴል መሆኑ ተብራርቷል ሲል ከአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ (AMN) የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
18/05/2026
Strategic Alignment Session at EEC
A strategic session was held at a core EEC Business Unit.
bringing teams together to reflect on EEC’s journey, purpose, and pillars while strengthening alignment toward our shared goals.
The discussion also reviewed the Corporation’s 9-month performance, ex*****on priorities, and key focus areas for the next 75 days, reinforcing our commitment to collaboration, accountability, and impactful delivery.
15/05/2026
🎉🎉 We are delighted to announce that we have signed a contract with the Environmental Protection Authority(EPA)
Client: Environmental Protection Authority
Consultant: Addis Ababa Science and Technology University
Scope: Design and Build for the Construction of 3B+SB+G+18+T Structural work of the Environmental Protection Authority Headquarters
Duration: 24 months
Location: Addis Ababa, Ethiopia
We thank our team for their dedicated work on securing this project.
We wish good luck and success to the entire team to be involved.
06/05/2026
የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ እየተፋጠነ ነው
(ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም)፣ አዲስ አበባ፤
የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (EEC) የማማከርና የቁጥጥር ሥራ እያከናወነበት የሚገኘው የጣፎ አደባባይ - ለገዳዲ - ኩራ ጅዳ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት እየተፋጠነ ይገኛል፡፡
15 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ያለው የመንገዱ ግንባታ፣ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እና በሸገር ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙትን ኤካ ጣፎ እና ኩራ ጅዳ ወረዳዎችን አቋርጦ የሚያልፍ ነው።
መንገዱ ቀደም ሲል ከነበረበት 7 ሜትር የጎን ስፋት፣ በግራና በቀኝ 4 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ በሚችል ሁናቴ፣ ወደ28 ሜትር ስፋት እንዲያድግ ተደርጓል።
ይህን ተከትሎም የፕሮጀክቱ ግንባታ የትራፊክ ፍሰቱን ከማሳለጡ ጎን ለጎን 4 ሜትር የአረንጓዴ ስፍራ እንዲሁም 14 ሜትር የእግረኛና የሳይክል መንገዶችን አካትቷል፡፡
የመንገዱ ግንባታ ሲጠናቀቅ በመስመሩ ላይ የሚታየውን ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ በመቅረፍ፤ ከአዲስ አበባ ወደ ሰሜኑ የአገራችን ክፍል ይኸውም፡- ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ሲና፣ ኮምቦልቻ እና ደሴ ከተሞች የሚደረጉ ጉዞዎችን በማቀላጠፉ ’ረገድ ከፍ ያለ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡