Affini Media

Affini Media ሁለም ከእውት ጎን እንቆማለን

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ቀደም ሲል ለተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያቀረቧቸው ማመልከቻዎች ሦስት ጊዜ ውድቅ እንደተደረገባቸው ተሰማ።ለእነዚህ ውድቅ መደረጎች...
23/09/2026

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ቀደም ሲል ለተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያቀረቧቸው ማመልከቻዎች ሦስት ጊዜ ውድቅ እንደተደረገባቸው ተሰማ።

ለእነዚህ ውድቅ መደረጎች እንደ ዋና ምክንያት ተጠቃሽ የነበረው የድህረ-ምረቃ ተማሪዎችን የምርምር ሥራ በበላይነት የመከታተልና የመደገፍ (Supervision) ግዴታቸውን አለመወጣታቸው ነበር።

ምንም እንኳን ጎደሎ የተባሉትን መስፈርቶች ማሟላታቸውን በመጥቀስ ፋይላቸው ለቦርድ እንዲመራላቸው የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንቱን ቢወተውቱም፣ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ግን ያለ በቂ ማስረጃ ክፍተቶችን ዝም ብሎ መሙላት ለተጠያቂነት ስለሚያጋልጥ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። በመሆኑም ዶ/ር ችሮታው ቢያንስ የተማሪዎችን የምርምር ሥራ መምራታቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎች እንዲያመጡ አጥብቀው አሳስበው ነበር።

በዚህም ምክንያት ዶ/ር ችሮታው አምስት ተማሪዎችን በምርምር ሥራ እንደረዱ የሚገልጽ ማስረጃ እንዲሰጧቸው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኃላፊዎችን በዝምድና በጥቅማጥቅም ማሳመን ችለዋል። ይህንን ሰነድ በእጃቸው ካስገቡ በኋላ ቀሪዎቹ መስፈርቶች የተሻሩላቸው ሲሆን፣ ለአካዳሚክ ማዕረጉ በድጋሚ በማመልከት በሚያስገርም ሁኔታ የደረጃ ዕድገት አግኝተዋል።

ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው የዶ/ር ችሮታው የቅርብ ዘመድና የቀድሞ የሥራ ባልደረባ በሆኑት በዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት አማካኝነት እንደሆነ ተገልጿል። እሳቸውም ዶ/ር ችሮታው የተጠቀሱትን አምስት የምርምር ፕሮጀክቶች መምራታቸውን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ሰጥተዋል። ይሁን እንጂ ይህ ማስረጃ ትክክለኛነቱና የተጠቀሱት የምርምር ፕሮጀክቶች በእርግጥ በዶ/ር ችሮታው ክትትል ሥር የተከናወኑ መሆናቸው በነፃና ገለልተኛ ምርመራ ሊረጋገጥ ይገባል።

መስፈርቶቹን ማሟላት ቢችሉ ኖሮ፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ እያሉ የደረጃ ዕድገቱን ያገኙ ነበር የሚለውም ጥያቄ ተገቢ የሆነ ምርመራ ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚመለከተው አካል በአካዳሚክ ማዕረግ አሰጣጥ ሂደት፣ በቀረቡት ማስረጃዎች እና በተጠቀሱት አምስት የድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የምርምር ሥራ ክትትል ዙሪያ ግልጽና ከአድልዎ ነፃ የሆነ ምርመራ እንዲያደርግ እንጠይቃለን።

ማንኛውም ዓይነት ማጭበርበር ወይም የሐሰት ማስረጃ ማቅረብ ከተረጋገጠ፣ በሕጉ እና በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ማዕረግ አሰጣጥ ደንብ መሠረት ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ በጥብቅ እናሳስባለን።

Borkena ሚዲያ በሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ህዝብ ዙሪያ የሚፃፋቸው ፅሑፎች የሀሰት እና የጥላቻ መልዕክት ያላቸው ናቸው።ሀዋሳ በሲዳማ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የነዋሪዎቿ ሁሉ ናት። ታሪኳ እና ማ...
21/09/2026

Borkena ሚዲያ በሀዋሳ ከተማ እና ሲዳማ ህዝብ ዙሪያ የሚፃፋቸው ፅሑፎች የሀሰት እና የጥላቻ መልዕክት ያላቸው ናቸው።

ሀዋሳ በሲዳማ ክልል ውስጥ የሚኖሩ የነዋሪዎቿ ሁሉ ናት። ታሪኳ እና ማንነቷም ሊከበር ይገባል።

«ሀዋሳ የነዋሪዎቿ ናት» በሚል ርዕስ በBorkena ሚዲያ የቀረበው ጽሑፍ ስለ ሕዝብ ንብረት፣ ስለ ከተማ ልማት፣ ስለ ማፈናቀል፣ ስለ ግልጸኝነት እና ተጠያቂነት ጥያቄዎችን ያነሳል። እነዚህ በማስረጃ ላይ ተመስርተው ልቀርቡ የማይችሉ ጉዳዮችን አጀንዳ ማድረግ ለምን አስፈለገ ?
ጽሑፉ ስለ ንብረት አስተዳደር ከሚነሱ ሕጋዊ ጥያቄዎች ባሻገር ሰፊ ብሔርን እና ፖለቲካን ወደ ማጠልሸት የተሸጋገረ ይመስላል።

ሀዋሳ የአንድ ብሔር ንብረት ብቻ ናት ያለም የለም። ነገር ግን ታሪክ፣ ማንነት ወይም ሀገር በቀል ሕዝብ የሌላት ከተማም አይደለችም። ሀዋሳን ከሲዳማ ባህልና ማንነት ጋር አያይዞ ማየት ኢትዮጵያዊነት እኮ ነው።

ሀዋሳ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የክልሉ ዋና ከተማ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። ለወደፊትም ያገለግላል።

ይህ ታሪካዊ እና የማንነት እውነታ በሀዋሳ ውስጥ የኖሩ፣ የሠሩ፣ ኢንቨስት ያደረጉ እና ሕይወታቸውን የገነቡ ሌሎች ኢትዮጵያውያን መገለል አለባቸው ማለት አይደለም። ሀዋሳ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን እና ጎብኚዎች አቃፊ፣ ሰላማዊ እና አበልፃጊ ከተማ ሆና እንድትቀጥል ነው።

ማስረጃ ጠይቁ እንጅ በሀሰተኛ መረጃ ብሔርን አትውቀሱ:
* የሕዝብ ንብረቶች በሕገ-ወጥ መንገድ ከተላለፉ፣ ሰነድ
ካለ አቅር ቡ።
* ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ ከተፈናቀሉ የሀሰት ወሬ
ከሚታሰራጩ ጉዳዮን መርምሩ።
* ሙስና ከተፈጸመ፣ ተጠያቂ የሆኑ ግለሰቦች ተጠያቂ
ይሆናሉ።

እነዚህ ጥያቄዎች በመሬት መዝገቦች፣ በውሎች፣ በግምገማ ሰነዶች፣ በጨረታ መዝገቦች፣ በፍርድ ቤት ውሳኔዎች፣ በካሳ መዝገቦች እና በሌሎች ሊረጋገጡ በሚችሉ ማስረጃዎች ሊመለሱ ይገባል እንጂ ስለ አንድ ሙሉ ብሔር በሚገመቱ ግምቶች መሆን የለበትም።

አንድ የተወሰነ ብሔር በጋራ የሕዝብ ንብረትን «ወሰደ» ወይም "የሕዝብ ሀብት ስልታዊ በሆነ መንገድ ለአንድ ብሔር ተከፋፈለ" የሚለው ሀሳብ ማስረጃ የለለው ነው።

በልማት ምክኒያት ማፈናቀል የተባለውን ደግሞ ማን፣ የት፣ እና እንዴት የሚለውን ጥያቄ ለራሱ ለBorkena ልተውለት።

የከተማ ልማት ከተሞችን መለወጡ አይቀሬ ነው። መንገድ፣ ኮሪደሮች፣ የሕዝብ ቦታዎች፣ መኖሪያ ቤቶች እና መሰረተ ልማቶች የሰዎችን ሕይወት የሚያሻሽሉ ናቸው።
ተጠያቂነትም ከሆነ ተቋማዊ፣ እውነተኛ እና ተገቢ በሆነበት ቦታ ግለሰባዊ መሆን አለበት እንጂ የብሔር ስብስብ ውቀሳ መሆን የለበትም።

የሲዳማ ማንነት ለሌሎች ኢትዮጵያውያን ስጋት አይደለም

የሲዳማን ታሪክ፣ ባህል እና ማንነት መከላከል ለሌሎች ማህበረሰቦች እንደ ጠላትነት ሊወከል አይገባም። አይችልምም።

የሲዳማ ሕዝብ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ቋንቋውን፣ ባህሉን፣ ቅርሱን፣ ታሪካዊ ቦታዎችን እና ስሞቹን የመጠበቅ ሕጋዊ መብት አለው።

በተመሳሳይ መልኩ በሀዋሳ የሚኖሩ ሁሉም ማህበረሰቦች በሰላም የመኖር፣ የመሥራት፣ ኢንቨስት የማድረግ እና በከተማዋ ልማት የመሳተፍ መብት አላቸው።
እኩልነት ታሪካዊ ማንነቶች እንዲጠፉ አያደርግም። አድርጎም አያውቀውም ።

በህዝቡ ላይ የግል የፖለትካ ጥላቻ ያለውም ቢኖር ወደ ብሔር ጠላትነት መለወጥ አያስፈልገውም።

የሀዋሳ ከተማ ይፋዊ ራዕይ ከተማዋን ለመኖሪያ፣ ለቱሪዝም እና ለኢንቨስትመንት መድረሻ አድርጎ መስራት ነው። በተመሳሳይ ጊዜ የሕዝብ ተጠቃሚነትን፣ ግልጸኝነትን፣ ተጠያቂነትን፣ ፍትሃዊነትን እና ትብብርን ማጎልበት ነው። እኛም ልንደግፈው የሚገባን አቅጣጫ ያ ነው።

ባለቤትነቱ የሲዳማን ሕዝብ ታሪክ እና ማንነት የሚወክል ነው። ሀዋሳን መኖሪያቸው ያደረጉ ሌሎችን ኢትዮጵያውያንን እንደ ሲዳማ አድርጎ ማየት እንጅ ማግለል ማለት አይደለም።

ከወሬ ይልቅ መዝገቦችን፣ ከብሔር አጀንዳ ይልቅ ማስረጃዎችን፣ ከጋራ ውቀሳ ይልቅ ተጠያቂነትን፣ ከማፈናቀል ይልቅ ልማትን እንጠይቅ።

ሀዋሳ የሲዳማ ማንነት የሚከበርበት፣ የሁሉም ነዋሪዎች መብት የሚጠበቅበት፣ የሕዝብ ንብረት በግልጽነት የሚስተዳደርበት እና ሁሉም ማህበረሰቦች በክብር እና በጋራ መከባበር በጋራ የሚኖሩበት ከተማ መሆኗን ማንም ያውቃል።

18/09/2026

የሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታድዬም ጉዳይ ያሳስበኛል

ጋዜጠኛ ሰለሞን አባቡ የሀዋሳ አለም አቀፍ ስታድየም ጉዳይ የአንድ ሰሞን አጀንዳ ብቻ መሆን የለበትም በማለት ስለ ጉዳዩ አጠንክረው እየፃፈ ይገኛልስሙ አለምአቀፍ ሆኖ  ዛሬ ላይ ግን እንዲህ ...
18/09/2026

ጋዜጠኛ ሰለሞን አባቡ የሀዋሳ አለም አቀፍ ስታድየም ጉዳይ የአንድ ሰሞን አጀንዳ ብቻ መሆን የለበትም በማለት ስለ ጉዳዩ አጠንክረው እየፃፈ ይገኛል

ስሙ አለምአቀፍ ሆኖ ዛሬ ላይ ግን እንዲህ የአረም መከማቻ እና የፍልፈል መጫወቻ ስለሆነው ይህ ሜዳ ሁሉም ሀሳቡን ማዋጣት ይኖርበታል ሲል ጋዜጠኛው ተናግራል።

ከሲዳማ ቡና እና ሀዋሳ ከነማ ባሻገር ለውቢቷ ከተማ ሀዋሳ ተጨማሪ የስፖርት ቱሪዝም መስዕብን የሚፈጥሩ ትላልቅ ሀገራዊ ሁነቶችን ለማስተናገድ የዚህ ስታድየም በፍጥነት መጠናቀቅ ከምንም በላይ አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ምላሽ ተቀባይነት ማጣቱ ተገለጸበሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን እና የፕሬዝዳ...
30/08/2026

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ምላሽ ተቀባይነት ማጣቱ ተገለጸ

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ችሮታው አየለ አስተዳደራዊ ውሳኔዎች ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን እና የፕሬዝዳንቱን ምላሾች ተከትሎ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ ጠንካራ ትችቶችና አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ።

ፕሬዝዳንቱ በአካባቢው ብሔር ምሁራን፣ ሠራተኞች እና አመራሮች ላይ በደል እያደረሱ ነው በሚል የሚቀርቡ አቤቱታዎች እና ትችቶች በይፋ እየተንጸባረቁ ይገኛሉ። ተጠባባቂ ፕሬዝዳንቱ የብሔሩን ባህላዊ ልብስ ለብሰው የብሔሩ ወዳጅ መስለው ለመታየት በሚሞክሩበት ወቅት፣ ከአስር በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ ምሁራን አለአግባብ ከስራ መባረራቸውን፣ መከሰሳቸውን እና ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን ምንጮች ይጠቁማሉ።

ይህን ድርጊት ተከትሎ ከተለያዩ ወገኖች በተሰጠው አስተያየት፣ የባህላዊ መገለጫዎችን መጠቀም ብቻውን መዋቅራዊ እና አስተዳደራዊ ጥያቄዎችን እንደማይመልስና የቀረበው ምላሽ ተቀባይነት እንደሌለው ተጠቅሷል።

አስተያየት ሰጪዎች ማህበረሰቡን በውጫዊ የባህል አልባሳት ከማንጸባረቅ ይልቅ፣ የአካባቢውን ህዝብ እና ሰራተኞች በእውነተኛ ተግባር፣ በፍቅር እና በመልካም አስተዳደር መደገፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ከምሽት 1፡00 ጀመሮ ማየት እንደሚቻል ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።የሀገረ አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች...
25/08/2026

የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት ከምሽት 1፡00 ጀመሮ ማየት እንደሚቻል ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የሀገረ አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት የሚታይባቸውን አድራሻዎች ይፋ አድርጓል።

አገልግሎቱ የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ/ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ማየት እንደሚችሉም አሳውቋል።

ተፈታኝ ተማሪዎችም ውጤታቸውን የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን (Link) በመጠቀም ማየት የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ገልጿል።

አያይዞም ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን ምአገልግሎቱ ያሳውቃል።

ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

ምክክሩን ከባድ ያደረገው አለመተሳሰባችን ነው ብዬ አምናለሁ። እያንዳንዳችን የጋራ ጥቅማችንንና የጋራ እሴታችንን ከማየት ይልቅ፣ የቡድን ጥቅማችንን ብቻ እያሰብን ከተንቀሳቀስን፣ እውነተኛ መግ...
24/08/2026

ምክክሩን ከባድ ያደረገው አለመተሳሰባችን ነው ብዬ አምናለሁ። እያንዳንዳችን የጋራ ጥቅማችንንና የጋራ እሴታችንን ከማየት ይልቅ፣ የቡድን ጥቅማችንን ብቻ እያሰብን ከተንቀሳቀስን፣ እውነተኛ መግባባት ላይ መድረስ እንቸገራለን። በምክክሩ የታየው ይህ ነው። ምክክር ማለት የራስን አቋም ብቻ ማስጠበቅ ሳይሆን፣ የሌላውንም ስሜት፣ ታሪክ፣ ማንነትና ጥቅም በመረዳት የጋራ መፍትሔ መፈለግ ነው።

በምክክሩ ወቅት አንዳንዶች አጀንዳውን ራሳቸው ሲያነሱትና አቋማቸውን ሲያራግቡት ታይተዋል። ነገር ግን ተመሳሳይ ጉዳይ በሌላው ወገን ሲነሳ በተለየ መልኩ መመልከት አይገባም። ያንተ ቋንቋ የፌዴራል ቋንቋ ይሁን ሲባል የማይከፋህ ከሆነ፣ የእኔም አካባቢያዊ ቋንቋ የፌዴራል ቋንቋ ይሁን ሲባል ለምን ይከፋሃል? እኩልነት ማለት ለራሳችን የምንፈልገውን መብት ለሌላውም መፍቀድ ነው።

“ሲዳማ ቡና” የሚለውን ስም በደስታ ተጋርተን የምንጠቀም ከሆነ፣ “ሲዳሙ አፎ” የሚለው ጉዳይ ሲነሳ ብቻ ሊከፋን አይገባም። ሌላውን ለራሳችን ጥቅም ስንፈልገው እንደምናከብረው ሁሉ፣ የሌላውንም ማንነትና መብት በእኩልነት ማክበር ይኖርብናል።

መተሳሰብ ከሌለ፣ በማመሳሰል የምናመጣው አንድነት ዘላቂ አይሆንም። እውነተኛ አንድነት የሚመጣው ልዩነታችንን በመቀበል፣ የሌላውን ስሜት በመረዳትና ለሁሉም በእኩል የሚሠራ መፍትሔ በመፈለግ ነው።

“ሲዳሙ አፎ” በፌዴራል ቋንቋዎች ውስጥ እንዳይካተት የተደረገበት አግባብ አሳማኝ ብቻ ሳይሆን አግላይም ነው ብዬ አምናለሁ። ብልፅግና ፓርቲም ቀድሞ የፌዴራል ቋንቋዎችን በማለት ወስኖ ለተሳታፊዎች ማቅረቡ፣ በምንም መመዘኛ ተቀባይነት ያለው አሠራር አይደለም። ይህም የምክክሩን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ ከቶታል። በተለይም የምክክሩ ዓላማ የተለያዩ ድምፆችን በእኩል ማዳመጥና የጋራ መፍትሔ ማፈላለግ ከሆነ፣ አንድ ጉዳይ ከውሳኔ በፊት በተወሰነ መልኩ ቀድሞ መቅረቡ ተገቢ አይደለም።

ይህ ጥያቄ የሌላውን መብት ለመንፈግ ወይም የአንዱን ቋንቋ ከፍ ለማድረግ ሳይሆን፣ ለሁሉም በእኩል የሚሠራ ፍትሃዊና ግልጽ መመዘኛ እንዲኖር የሚቀርብ ጥያቄ ነው። የቋንቋ ጉዳይ የአንድ ቡድን ጥቅም ብቻ ሳይሆን፣ የማንነት፣ የእኩልነትና የክብር ጉዳይም ነው።

ስለዚህ የሲዳማ ክልል መንግሥትም ይህንን ጉዳይ በአፅንኦት መከታተልና የሲዳሙ አፎ ጉዳይ በፍትሃዊና ግልጽ መመዘኛ እንደገና እንድታይ ተገቢ ጥያቄ ማቅረብ አለበት።

የምንፈልገው ልዩነታችንን በማክበር፣ መብታችንን በእኩልነት በማስጠበቅና በመተሳሰብ ላይ የተመሠረተ እውነተኛና ዘላቂ አንድነት ነው። የምንገነባውም ሁላችንም በእኩል የምንኮራበት ሀገር መሆን አለበት።

ማርቆስ ቡዱሳ

የኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን የሲዳማ ቡና አምራች አርሶ አደሮች የልማት ጥያቄሲዳማ ቡና የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ የቡና ምልክት፣ የሀገራችን ኩራት እና በዓለም ገበያ ኢትዮጵያን የሚ...
23/08/2026

የኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን የሲዳማ ቡና አምራች አርሶ አደሮች የልማት ጥያቄ

ሲዳማ ቡና የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ የቡና ምልክት፣ የሀገራችን ኩራት እና በዓለም ገበያ ኢትዮጵያን የሚወክል የገቢያችን የጀርባ አጥንት ነው። በጥራቱ የተመረጠ፣ በዓለም ገበያ ተፈላጊ የሆነ እና ለሀገራችን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ ምርት ነው።

ነገር ግን አንድ አሳዛኝ ጥያቄ አለ: ይህን የኢትዮጵያ ኩራት የሚያመርተው አርሶ አደር ምን አገኘ? የፈደራል መንግስት ለሲዳማ ቡና እንክብካቤ፣ ምርትና ምርታማነት ላይ ትኩረት ያልሰጠው ለምንድ ነው?

ቡናው የሚመረትባቸው ብዙ የገጠር አካባቢዎች እስካሁን በቂ የመንገድ፣ የመብራት፣ የመጠጥ ውሃ፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የመጋዘንና የማቀነባበሪያ መሠረተ ልማት ተደራሽነት የላቸውም። የቡና ምርት ወደ ውጭ ገበያ ስቀርብ የሚያመጣው የውጪ ምንዛሬ እየጨመረ ቢሄድም፣ ያንን ሀብት የሚፈጥረው የአርሶ አደር ሕይወት በተመጣጣኝ መጠን ሲለወጥ አይታይም።

ቡናችን ዓለምን እየደረሰ አርሶ አደሩ ለምን በመሠረተ ልማት እጦት ውስጥ ይቀራል?
ይህ ቅሬታ የፖለቲካ ጥያቄ ብቻ አይደለም፤ የፍትሃዊ ልማት፣ የአርሶ አደሩ ክብር እና የቡና ምርት ዘላቂነት ጥያቄ ነው።
የፌዴራል መንግስት ለእነዚህ የቡና አምራች አካባቢዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ፦
☑️ የገጠር መንገድና ትራንስፖርት
☑️ የመብራትና የቴሌኮሙኒኬሽን ተደራሽነት
☑️ የመጠጥ ውሃ፣ ጤናና ትምህርት
☑️ ዘመናዊ የቡና ማቀነባበሪያና ማከማቻ
☑️ የተሻለ የገበያ ትስስርና የዋጋ ጥበቃ
☑️ የአርሶ አደሮች የምርታማነትና የገቢ ማሻሻያ
☑️ የአፈርና የአካባቢ ጥበቃ
☑️ የቡና ተክል እድሳትና የአየር ንብረት መላመድ
ላይ የተጠናከረ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ሊኖረው ይገባል።
የቡና ልማት ማለት ቡናን ብቻ መግዛትና መላክ አይደለም። የቡና ልማት ማለት የቡናውን አምራች ሰው ማልማት ነው።
የሲዳማ ቡና የኢትዮጵያን ስም በዓለም ካስጠራ፣ የሲዳማ ቡና አምራች አርሶ አደርም በክብር፣ በተሻለ ኑሮ እና በልማት መኖር አለበት።
የሲዳማ ቡና ዋጋ በዓለም ገበያ ብቻ አይለካም፤ የሚለካው ቡናውን በሚያመርተው አርሶ አደር የኑሮ ለውጥም ጭምር ነው።
#ሲዳማቡና CoffeeFarmers

ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አዲስ አበባጉዳዩ፡ ቅሬታ ስለማቅረብ ይሆናል በጉዳዩ እንደተቀጠቀሰው እኛ ስማችን ቀጥሎ በፊርማችን ያረጋገጥን የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ተወካዩች የሲዳሙ አ...
21/08/2026

ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡ ቅሬታ ስለማቅረብ ይሆናል

በጉዳዩ እንደተቀጠቀሰው እኛ ስማችን ቀጥሎ በፊርማችን ያረጋገጥን የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ተወካዩች የሲዳሙ አፎ/ሲዳሚኛ ቋንቋ/ የፌደራል የስራ ቋንቋነት ዝርዝር ከተካተቱ 5 ዋና ዋና ቋንቋዎች ውጪ መደረግ አስመልክቶ ያለንን ቅሬታ ቀጥሎ አቅርበናል።

1ኛ. በቡድን አራት (4) የሀገር ግንባታ አጀንዳ ስር የሲዳሚኛ ቋንቋ በፌደራል የሥራ ቋንቋዎች ምድብ ውስጥ እንዲካተት በአሥር፣ በአምሳ፣ በሁለት መቶ አምሳ እና በአምስት መቶ ቡድኖች ላይ ምክረ-ሀሳብ ቀርቦ ስምምነት ላይ የተደረሰ ቢሆንም፤ አጀንዳዎች ተጣጥመው በአንድ ላይ ተዋቅረው ሲቀርቡ 5 ቋንቋዎች (አፋን ኦሮሞ፣ አማርኛ፣ ትግርኛ፣ አፍ ሶማሌ እና አፋርኛ) ቀጥታ የፌደራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ፤ ሲዳሚኛ ግን አስፈላጊነቱ በቀጣይ ታይቶ እንዲወሰን ተብሎ መቅረቡ ቅሬታ ፈጥሮብናል። ይህም፡-
* 1.1. የፌደራል መንግሥቱን የሥራ ቋንቋ ለመበየን ግልጽ የሆነ የአመራረጥ መስፈርት ባልተቀመጠበት ሁኔታ የሲዳሚኛ ቋንቋ ከቀዳሚዎቹ 5 ተመራጭ ቋንቋዎች ውጪ መደረጉ አግባብ አለመሆኑ፤
* 1.2. ከሁሉም ቡድኖች ተወጣጥተው የተመረጡ 120 አጠናቃሪዎች የውሳኔ ሀሳብ የማቅረብም ሆነ የቀረበውን ምክረ-ሀሳብ የመሻር ወይም የመለወጥ ሥልጣን በምክክር ኮሚሽኑ አሰራር የማይፈቀድ ሆኖ ሳለ፣ ተመካካሪዎች በቋንቋ ዙሪያ ያቀረቡትን ምክረ-ሀሳብ በመለወጥ ደረጃ መድበው ማቅረባቸውን የማንቀበለው መሆኑን፤

2ኛ. በሀገራችን በአሁኑ ወቅት ያሉት 12 ክልሎች እና 2 የከተማ አስተዳደሮች፤ በአጠቃላይ 6 የመንግሥት የሥራ ቋንቋዎችን (አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛ፣ ሶማሌኛ፣ አፋርኛ እና ሲዳሚኛ) በሕገ-መንግሥቶቻቸው ተቀብለው ተግባራዊ አድርገዋል። ይህም ማለት ከሲዳሚኛ ቋንቋ በስተቀር የሁሉም ክልሎች የመንግሥት የሥራ ቋንቋዎች የፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ምክረ-ሀሳብ የቀረበ መሆኑን ያመላክታል። ከዚህ አኳያ የሲዳሚኛ ቋንቋ ብቻ ተነጥሎ ከዝርዝሩ ውጪ መደረጉ ኢ-ፍትሐዊ ከመሆኑም በላይ አግላይ በመሆኑ በድጋሚ እንዲታይልን እንጠይቃለን።

3ኛ. የሲዳማ ክልል የፌደሬሽኑ አባል ክልል መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ የሲዳሚኛ ቋንቋ በክልሉ ሕገ-መንግሥት የሥራ ቋንቋ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል። በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብና ቤት ቆጠራ የሲዳማ ብሔር በቁጥር 2,966,474 የነበረ ሲሆን፣ በ2018 ዓ.ም የክልሉ ተወላጆች ቁጥር ከ5.5 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ግምት ያሳያል። በዚህም ከኦሮሞ፣ ከአማራ፣ ከሶማሌ እና ከትግራይ ቀጥሎ በሕዝብ ቁጥር በአምስተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጥ አንጋፋ ሕዝብ በመሆኑ፤

4ኛ. በተጨማሪም የመማሪያና የምርምር ቋንቋ በመሆን ከቅድመ-መደበኛ እስከ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ (MA) ደረጃ ድረስ ትምህርት የሚሰጥበት፣ ሙሉ የሥነ-ልሳን ጥናትና ምርምር የተካሄደበት፣ የሕግ፣ የአዋጆች እና የቴክኖሎጂ አገልግሎት ላይ የዋለ አንጋፋ ቋንቋ በመሆኑ ከሌሎች አቻ ቋንቋዎች ተለይቶ ከፌደራል መንግሥት የሥራ ቋንቋነት መገለሉ መሠረታዊ ስህተት በመሆኑ፤

5ኛ. የሲዳሚኛ ቋንቋ ከክልሉ በተጨማሪ ከአጎራባች ሕዝቦች (ከኦሮሞ፣ ከጌዲዮ እንዲሁም ከወላይታ) ጋር በአዋሳኝ ወሰኖች ላይ ዋነኛ የመግባቢያ ድልድይ ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን፤ በተጨማሪም በፍልሰት ምክንያት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተናጋሪ ከክልሉ ውጪ በዋናነት በአዲስ አበባ ከተማ እና በሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች ተሰራጭቶ ይገኛል። በዚህ ምክንያት የሲዳሚኛ ቋንቋ የፌደራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ ሆኖ ቢካተት የሕዝቦችን ትስስር የበለጠ ያጠናክራል የሚል እምነት ያለን በመሆኑ፤

6ኛ. የሲዳሚኛ ቋንቋ ከአፋን ኦሮሞ፣ ከአማርኛ፣ ከአፍ ሶማሌ፣ ከትግርኛ እና ከአፋርኛ ቀጥሎ የገዥው ፓርቲ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት፣ የምርጫ ቦርድ እና የምክክር ኮሚሽን ከሚጠቀሙባቸው የሥራ ቋንቋዎች ውስጥ አንዱ ነው። ነገር ግን ከእነዚህ ቋንቋዎች መካከል የሲዳሚኛ ቋንቋ ብቻ ተነጥሎ ከዝርዝር ውጪ መደረጉ ኢ-ፍትሐዊ እና አግላይ በመሆኑ በድጋሚ እንዲታይልን እንጠይቃለን።

በእነዚህ እና በሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ ኮሚሽኑ ቅሬታችንን ተቀብሎ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጠን በትሕትና እንጠይቃለን።

ሰበር ዜና !የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ተወካዮች በፌደራል የስራ ቋንቋነት ጉዳይ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያቀረቡትን ቅሬታ በፊርማ አረጋግጠው ለማስገባት ላይ መሆናቸው ተገለጸየሲዳማ ክልል የህ...
20/08/2026

ሰበር ዜና !

የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ተወካዮች በፌደራል የስራ ቋንቋነት ጉዳይ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያቀረቡትን ቅሬታ በፊርማ አረጋግጠው ለማስገባት ላይ መሆናቸው ተገለጸ

የሲዳማ ክልል የህብረተሰብ ተወካዮች የሲዳሚኛ ቋንቋ በፌደራል የስራ ቋንቋነት ከተካተቱት አምስት ዋና ዋና ቋንቋዎች ውጪ መደረጉን በመቃወም ያዘጋጁትን ይፋዊ የቅሬታ ደብዳቤ በፊርማቸው አረጋግጠው ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለማስገባት በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተገለጸ።

ተወካዮቹ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ባዘጋጁት በዚህ ደብዳቤ፣ በቡድን አራት የሀገር ግንባታ አጀንዳ ስር በነበሩ ውይይቶች ሲዳሚኛ በፌደራል የስራ ቋንቋነት እንዲካተት በምክረ-ሀሳብ ደረጃ ስምምነት ላይ ተደርሶ የነበረ ቢሆንም፣ አጀንዳዎች ተጣጥመው ሲቀርቡ ግን «በሂደት ታይቶ የሚወሰን» ተብሎ መገፋቱ አግላይና ፍትሃዊ ያልሆነ አሰራር መሆኑን በመግለጽ ተቃውሟቸውን አዘጋጅተዋል።

ተወካዮቹ በፊርማቸው አረጋግጠው ለኮሚሽኑ ለማስገባት የተዘጋጁበት የቅሬታ ሰነድ እንደሚጠቅሰው፣ የፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋዎችን ለመበየን ግልጽ የሆነ የአመራረጥ መስፈርት ባልተቀመጠበት ሁኔታ ሲዳሚኛን ከቀዳሚዎቹ አምስት ቋንቋዎች ውጪ ማድረግ አግባብ አይደለም። በተጨማሪም ከየቡድኑ የተመረጡ 120 አጠናቃሪዎች የተመካካሪዎችን ምክረ-ሀሳብ የመሻር ወይም የመለወጥ ስልጣን ሳይኖራቸው የውሳኔ ሀሳቡን ቀይረው ማቅረባቸው ተቀባይነት እንደሌለው አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ከሚገኙ 12 ክልሎችና 2 የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የሲዳሚኛን ጨምሮ 6 የስራ ቋንቋዎች በህገ-መንግስት ደረጃ ተቀባይነት አግኝተው ተግባራዊ እየተደረጉ ቢሆንም፣ ከሲዳሚኛ ውጪ ያሉት አምስቱ ቋንቋዎች ብቻ ለፌደራል የስራ ቋንቋነት መጠቆማቸው ኢ-ፍትሃዊ መሆኑን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል የሲዳማ ብሔር ከ5.5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያለውና በህዝብ ቁጥር አምስተኛው ትልቅ ብሔር መሆኑን የጠቀሱት ተወካዮቹ፣ ቋንቋውም ከቅድመ-መደበኛ እስከ ሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ትምህርት መስጫ፣ የስነ-ልሳን ጥናት የተካሄደበት፣ የህግና ቴክኖሎጂ ግልጋሎት ላይ የዋለ በመሆኑ ከሌሎች አቻ ቋንቋዎች ተለይቶ መገለሉ መሰረታዊ ስህተት መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሲዳሚኛ ከአጎራባች ብሔረሰቦች (ኦሮሞ፣ ጌዲዮ፣ ወላይታ) ጋር የጋራ መግባቢያ ከመሆኑም በላይ በአዲስ አበባና በተለያዩ ሀገሪቱ አካባቢዎች በስፋት የሚነገር በመሆኑ የህዝቦችን ትስስር ያጠናክራል ብለዋል።

በመጨረሻም የሲዳማ ክልል ህብረተሰብ ተወካዮች የቋንቋው ከዝርዝር ውጪ መሆን ኢ-ፍትሃዊና አግላይ አሰራር መሆኑን በማስገንዘብ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በፊርማ የተደገፈውን ቅሬታ ተቀብሎ ጉዳዩን በድጋሚ በመመርመር አፋጣኝና ፍትሃዊ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ ደብዳቤውን ለኮሚሽኑ ለማስገባት የመጨረሻ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።

Address

Addis Ababa
ET00000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Affini Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share