05/06/2026
ታክስ የሚከፈልባቸው የዓይነት ጥቅማጥቅምች ይህ ቻናል በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁ.2 ቅ/ጽ/ቤት የከፈተው ኦፊሴላዊ የዩቲዩብ ቻናል...
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁ.2 ቅርንጫፍ - MOR Medium Taxpayers No 2, Government Organization, Road From Mexico to Kera Street Kassa Grand Mall, Addis Ababa.
05/06/2026
ታክስ የሚከፈልባቸው የዓይነት ጥቅማጥቅምች ይህ ቻናል በገቢዎች ሚኒስቴር የመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁ.2 ቅ/ጽ/ቤት የከፈተው ኦፊሴላዊ የዩቲዩብ ቻናል...
03/06/2026
የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ጥቅም እና ኪሣራ
**********************
ማንኛውም ግብር ከፋይ በንግድ ሥራ ሂደት ውስጥ ከውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ተመን መዋዠቅ የሚያገኘው ጥቅም ወይም ትርፍ እንደ ማንኛውም መደበኛ የንግድ ሥራ ገቢ ተቆጥሮ በግብር ስሌቱ ውስጥ የሚካተት ይሆናል።
የምንዛሪ ኪሳራ ማካካሻ እና ማሸጋገርያ መንገዶች ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ የወጪ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ኪሳራ ካጋጠመው፣ ይህንን ኪሳራ በዚያው ዓመት ካገኘው የምንዛሪ ጥቅም ጋር ማካካስ ይችላል።
•በዓመቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያልተካካሰ የኪሳራ መጠን ካለ፣ ግብር ከፋዩ ያንን ያልተካካሰ ኪሳራ ወደ ሚቀጥሉት ዓመታት በማሸጋገር ወደፊት ከሚያገኘው የምንዛሪ ጥቅም ጋር ሙሉ በሙሉ እስኪካካስ ድረስ ኪሳራውን ላልተወሰነ ጊዜ የማሸጋገር ይችላል፡፡
•ሆኖም ይህ መብት ተፈጻሚ የሚሆነው ግብር ከፋዩ የደረሰበትን የኪሳራ መጠን ለገቢዎች ባለሥልጣን በሚያሳምን አኳኋን ማረጋገጥ ሲችል ብቻ ነው።
በሌላ በኩል፣ የምንዛሪ ኪሳራ የገጠመው አካል የፋይናንስ ተቋም (እንደ ባንክ እና ኢንሹራንስ) ከሆነ፣ ከላይ የተጠቀሰው የኪሳራ ማሸጋገርያ ሥርዓት በእነሱ ላይ ተፈጻሚ የማይደረግ ሲሆን የፋይናንስ ተቋሙ የደረሰበትን ኪሳራ መጠን ለባለሥልጣኑን በሚያሳምን አኳኋን ማረጋገጥ ከቻለ የኪሳራው መጠን እንደተቀናሽ ወጪ ይያዝለታል፡፡
ጥቅምና ኪሳራው እውን የሚሆንበት ሁኔታ
•ግብር ከፋይ በውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሬ ጥቅም አገኘ ወይም ኪሳራ ገጠመው የሚባለው ጥቅሙ ወይም ኪሳራው በተግባር እውን (Realized) ሲሆን ብቻ ነው።
•ግብር ከፋይ በውጭ ሀገር ገንዘብ ግብይት የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ጥቅም ማግኘቱ ወይም የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ኪሳራ ያጋጠመው መሆኑን ለመወሰን ከግብይቱ ጋር በተያያዘ
ግብር ከፋዩ ራሱ ወይም ከእሱ ጋር ግንኙነት ያለው ሰው በገባው ከኪሳራ ሥጋት የመዳን ውል (Hedging) ላይ ያለው አቋም አብሮ ከግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል።
መሠረታዊ የቃላት ትርጓሜዎች
የሕጉን አፈጻጸም ግልጽ ለማድረግ የተወሰኑ ቃላት ፍቺ ተሰጥቷቸዋል። በዚህም መሠረት
የውጭ ሀገር ገንዘብ ግብይት፡- ማለት የንግድ ሥራ ገቢ ለማግኘት ሲባል በውጭ ሀገር ገንዘብ የሚደረግ ግብይት፣ በውጭ ሀገር ገንዘብ የተገለጸን የዕዳ ግዴታ መስጠትን ወይም መቀበልን ወይም በውጭ ሀገር ገንዘብ የተገለፀ ሌላ ማንኛውም ግብይትን የሚያካትት ነው።
የዕዳ ግዴታ ፡- ማለት ገንዘብ ለሌላ ሰው ለመክፈል የተገባ ግዴታ ሆኖ፣ ተከፋይ ሂሳቦችን እንዲሁም ከቃልኪዳን ሰነዶች፣ ከሃዋላ ሰነዶች ወይም ከቦንዶች የሚመነጩ ግዴታዎችን ይጨምራል።
የውጭ ሀገር ገንዘብ ምንዛሪ ጥቅም እና ኪሳራ፡- የሚባሉት ከውጭ ሀገር ገንዘብ ግብይት ጋር በተገናኘ በምንዛሪ ተመን መዋዠቅ ምክንያት የሚገኙ ጥቅሞች ወይም የሚደርሱ ጉዳቶች ሲሆኑ፤
ከኪሳራ ሥጋት የመዳን ውል (Hedging Contract) የሚባለው ደግሞ አንድ ሰው በዚህ የምንዛሪ ተመን መዋዠቅ ምክንያት ሊደርስበት የሚችለውን የፋይናንስ ጉዳት ለማስቀረት ወይም ለመቀነስ ከሌላ ወገን ጋር የሚገባው ውል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
30/05/2026
በግምት የተወሰነ የታክስ ስሌት ስህተት እንዴት ይታረማል?
*********************
ባለሥልጣኑ በታክስ ሕግ መሠረት የታክስ ከፋዩ የሰጠው የታክስ ስሌት ማስታወቂያ ወይም ሌላ ሰነድ በታክስ ሕግ ወይም በጉዳዩ ኩነቶች ላይ ትርጉም ጥያቄ የማያስነሳ የጽሑፍ፣የሂሳብ ስሌት ወይም ሌላ ማንኛውንም ስህተት የያዘ በሚሆንበት ጊዜ ባለስልጣኑ ስህተቱን ለማረም ሲባል የታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ወይም ሌላውን ሰነድ የታክስ ስሌት ማስታወቂያው ወይም ሰነዱ ለታክስ ከፋዩ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ዓመታት ውስጥ ማሻሻል ይቻላል፡፡
በዚህ መሠረት የሚታረም የታክስ ስህተት የሚባለው፡-
•የመደመር፣የመቀነስ፣የማባዛትና የማካፈል ስህተት፤
•በስሌት ማጠቃለያ ላይ ከመንደርደሪያ ሀሳብ መለየት ወይም መቃረን፤
•ከአንድ የሂሳብ ቁጥር ከፊት ወይም ከኋላ የቁጥር መጨመር ወይም መቀነስ ወይም የሂሳብ ቁጥር ቦታ መቀያየር (transposition)፤
•የገቢ ወይም የወጪ ኮድ አመዘጋገብ ስህተት፤
•የቃል ወይም የሐረግ በአዎንታ ወይም አሉታ መቀያየር፤
•የሒሳብ ቁጥር ወይም ሀሳብ መተው ወይም መዘለል (omission)፤
•ከግብር ነጻ የሆነ ገቢን ግብር በሚከፈል ገቢ ውስጥ መጨመር፤
•በአንድ ታክስ ከፋይ ሒሳብ ውስጥ የሌላ ታክስ ከፋይ ሒሳብ መጨመር ወይም ማቀያየር፤
•የታክስ መጣኔን ወይም የትርፍ ህዳግን መሳሳት፤
•በታክስ ቅሬታ አጣሪ የሥራ ክፍል፣ በታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ወይም በመደበኛ ፍ/ቤት እንዲስተካከል የተወሰነን ጉዳይ አለማስተካከል፤
•በዚህ መሠረት ስህተት ሊታረም የሚችለው በታክስ ውሳኔ መጠን ላይ በመጨመር ወይም በመቀነስ ለውጥ የሚያመጣ ሲሆን ብቻ ሆኖ ለውጥ የማያመጣ በመሆኑ የማይታረም ስህተት ሲኖር ለታክስ ከፋዩ በጽሑፍ ይገለጻል፡፡
30/05/2026
29/05/2026
የክሬዲት እና የዴቢት ሰነዶች
**********************************
የተከፈለው የተጨማሪ እሴት ታክስ በመብዛቱ ወይም በማነሱ ምክንያት የሚደረግ ማስተካከያ ስለማድረግ የተመለከቱት ሁኔታዎች በሚሟሉበት ጊዜ የተመዘገበው ሰው ለሌላው የተመዘገበ ሰው እንደሁኔታው የክሬዲት ሰነድ ወይም የዴቢት ሰነድ መስጠት አለበት፡፡
የተመዘገበው ሰው ለአቅርቦቱ ገዢ የክሬዲት ወይም የዴቢት ሰነድ የሚሰጠው ሰነዱ እንዲሰጥ ምክንያት የሆነው የማስተካከያ ተግባር በተፈጸመበት የሒሣብ ጊዜ መጨረሻ ሊሆን ይገባል፡፡
የክሬዲት ሰነድ የሚከተሉትን መረጃዎች ሊይዝ ይገባል፦
ሀ) በሚታይ ቦታ ላይ “የክሬዲት ሰነድ” የሚል ጽሁፍ፤
ለ) የአቅራቢው ስም፤ አድራሻ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ቁጥር፤
ሐ) የአቅርቦቱ ተቀባይ ስም፤ አድራሻ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተመዘገበ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ቁጥር፤
መ) የክሬዲት ሰነዱ መለያ ቁጥር እና የተሰጠበት ቀን፤
ሠ) ክሬዲት ሰነዱ የተሰጠበትን ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ለይቶ ማወቅ የሚያስችል ግልጽ የሆነ መረጃን ጨምሮ፤ የክሬዲት ሰነድ ለመስጠት ምክንያት የሆነውን የሚያስረዳ አጭር መግለጫ፤ እና
ረ) በታክስ ደረሰኙ የተመለከተው የአቅርቦቱ ዋጋ፤ ትክክለኛው የአቅርቦቱ ዋጋ፤ በእነዚህ ሁለት ዋጋዎች መካከል ያለው ልዩነት፤ እና በልዩነቱ ላይ የሚታሰበው የተጨማሪ እሴት ታክስ መጠን::
የዴቢት ሰነድ የሚከተሉትን መረጃዎች ሊይዝ ይገባል፦
ሀ) በሚታይ ቦታ ላይ “የዴቢት ሰነድ” የሚል ጽሑፍ፤
ለ) የአቅራቢው ስም፤ አድራሻ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዘገባ ቁጥር፤
ሐ) የአቅርቦቱ ተቀባይ ስም፤ አድራሻ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የተመዘገበ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ቁጥር፤
መ) የዴቢት ሰነዱ መለያ ቁጥር እና የተሰጠበት ቀን፤
ሠ) ዴቢት ሰነዱ የተሰጠበትን ታክስ የሚከፈልበት አቅርቦት ለይቶ ማወቅ የሚያስችል ግልጽ የሆነ መረጃን ጨምሮ፤ የዴቢት ሰነድ ለመስጠት ምክንያት የሆነውን የሚያስረዳ አጭር መግለጫ፤ እና
ረ) በታክስ ደረሰኙ የተመለከተው የአቅርቦቱ ዋጋ፤ ትክክለኛው የአቅርቦቱ ዋጋ፤ በእነዚህ ሁለት ዋጋዎች መካከል ያለው ልዩነት፤ እና በልዩነቱ ላይ የሚታሰበው የተጨማሪ እሴት ታክስ መጠን::
28/05/2026
የአንድ ጊዜ ስልጠና ተሰጠ
*****************************
(ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም፡ መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
የፌደራል የገቢ ግብር አዋጅ 979/2008ን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ የሚሰጠው ስልጠና ተጠናክሮ በመቀጠል ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋዮች የአንድ ጊዜ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ሥልጠናዉ የተዘጋጀበት ዋነኛ ዓላማ አዳዲስ ህጎች ሲወጡ ለግብር ከፋዩ ግልጽ በማድረግ የሚጠበቅበትን ግብር በወቅቱ እና በትክክል እንዲከፍል ማድረግ ሲሆን በአቶ አወቀ ግዛው የታክስ ከፋዮች ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ ተሰጥቷል፡፡
ስልጠናው በአዋጁ የተካተቱ አዳዲስ ድንጋጌዎችን እንዲሁም የተደረጉ ለውጦችን በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡ የአዋጁ ማሻሻያ ዓላማዎች፣ ማሻሻያ የተደረገባቸው አንቀፆች፣ ምጣኔዎች፣ አዳዲስ የተካተቱ ድንጋጌዎች እንዲሁም ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠናዉ ያተኮረ ሲሆን ስልጠናዉን መሰረት አድርጎ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
ግብር÷ ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/?_r=1&_t=ZS-96Owjv8C6Ro
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/-MTO2
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
28/05/2026
ለተጫማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበ ሰው ግዴታዎች
*************************
1. ታክስ የሚከፈልበትን የስራ እንቅስቅሴ በማይንቀሳቀስ የሥራ ቦታ የሚያከናውን ማናቸውም የተመዘገበ ሰው፡-
•ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ በሚያካሂድበት ዋንኛ የስራ ቦታ በግልጽ በሚታይ ሥፍራ ዋናውን የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የመለጠፍ፣
•የተሰጠውን የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ቅጂ ታክስ የሚከፈልበት እንቅስቃሴ በሚያካሂድባቸው ሌሎች የስራ ቦታዎች ሁሉ በግልጽ በሚታይ ሥፍራ የመለጠፍ፣ ግዴታ አለበት፡፡
2. የተመዘገበ ሰው ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገበበትን ዝርዝር መረጃ ታክስ የሚከፈልበትን ስራ በሚያከናውንበት ዌብሳይት፤ የማህበራዊ ሚዲያ እና ሌላ የኤሌክትሮኒክ መድረክ ላይ ማስፈር አለበት፡፡
3. ከላይ ከተዘረዘሩት መረጃዎች በተጨማሪ በሚከተሉት መረጃዎች ላይ ለውጥ ሲያጋጥም የተመዘገበ ሰው ይህንኑ በ30 ቀን ጊዜ ውስጥ ለታክሱ ባለስልጣን ማስታወቅ አለበት፡፡
•የተመዘገበው ሰው የስልክ ቁጥር፣ የፋክስ ቁጥር፣ የኤሌክትሮኒክ እና ሌሎች የግንኙነት አድራሻዎች፡፡
•አዳዲስ ቅርንጫፎችን ወይም የሥራ ክፍሎችን መክፈትና መዝጋትን እንዲሁም የኢንተርኔት፤ የማህበራዊ ሚዲያ ወይም ለንግድ ስራ እንቅስቃሴ ጥቅም ላይ የሚውል ሌላ የኤሌክትሮኒክ መድረክ አድራሻ መለወጥን ጨምሮ የተመዘገበው ሰው ታክስ የሚከፈልበትን እንቅስቃሴ በሚያከናውንበት ቦታ ወይም በሚያከናውንባቸው ቦታዎች፡፡
•የተመዘገበው ሰው የንግድ ሥራ ባህሪ፣ እና ሌሎች የሚዘረዘሩ መረጃዎች፡፡
| Monday | 08:00 - 17:00 |
| Tuesday | 08:00 - 17:00 |
| Wednesday | 08:00 - 17:00 |
| Thursday | 08:00 - 17:00 |
| Friday | 08:00 - 17:00 |
| Saturday | 08:00 - 12:00 |