20/10/2021
የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል አመራሮችና ሠራተኞች በሰሜን የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ጦርነት ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኞች የምግብ ፍጆታና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ፡፡
በማዕከሉ የተቋቋሙ ኮሚቴዎች የተገዙትን የምግብ ፍጆታዎችና አልባሳት በአካል በመገኘት ወ/ሮ ስህን ፖሊ ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ ለሚገኙ ሴቶችና ህጻናት ስደተኞች ድጋፉን አድርጓል፡፡
27/09/2021
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ
……………………………………………………………………………..
የከፋተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል በዓሉ የሰላም የጤና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል
23/09/2021
የኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ማዕቀፍና የከፍተኛ ትምህርት እና ስልጠና የዕውቅና አሰጣጥ ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነዶች ላይ ግምገማ ተደረገ፡፡
------------------------------------------------------------------------------------------------------------
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ከቀረቡት ረቂቅ ሰነዶች አንዱ በማዕከላችን ከፍተኛ ተመራማሪ በሆኑት ወ/ሮ አማረች ከበደ የኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት ማዕቀፍ ረቂቅ ሰነድ የቀረበ ሲሆን የከፍተኛ ትምህርት እና ስልጠና የዕውቅና አሰጣጥ ስትራቴጂ ረቂቅ ደግሞ ደረጄ እንግዳ ዶ/ር ቀርቧል፡፡ በቀረቡ ሰነዶች ላይ ከታዳሚዎች ጠንካራ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተዋል፡፡ ውይይቱ በነገውም ዕለት የሚቀጥ ይሆናል
21/09/2021
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት የአካዳሚክ ነጻነት ዙሪያ የተደረገ ውይይት
https://www.youtube.com/watch?v=v0vDtjK9Spo&t=201s
09/09/2021
የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል አመራሮችና ሠራተኞች የደም ልገሳ መርሀ ግብር አከናወኑ፡፡
………………………………………………………………………………………………………………………………
ጳጉሜ 4 የጀግንነት ቀን በሚዘከርብት ቀን ለመከላከያ ሠራዊታችን የደም ልገሳ በማድረግ ከጀግናው ሰራዊታችን አብሮነታቸውን በመግለጽ አክብረው ውለዋል፡፡
04/09/2021
የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል 14 የሚደርሱ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ እና የማዕከሉ የውጪና የውስጥ የተገልጋይ እርካታ የዳሰሳ ጥናት ላይ ውይይት አደረገ፡፡
************************************************************************
የመርሃ ግብሩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ሃብታሙ ተካ ሲሆኑ በንግግራቸውም ማዕከሉ በበጀት ዓመቱ ያቀዳቸውን ስራዎች በወቅቱ በመጠናቀቃቸው ከዚህ በፊት እንደክፍተት ይታዩ የነበሩት የማዕከሉ ድክመቶችን መሻሻል እንደታየበት የሚያመለክቱ 14 የሚሆኑ የተጠናቀቁ የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦች ለውይይት መቅረባቸውን በመግለጽ መድረኩን በይፋ ከፍተዋል፡፡
ማዕከሉ ነሐሴ 28 እና 29/2013ዓ.ም በአዳማ ከተማ ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል በ2013 ዓ.ም አቅዶ ካጠናቀቃቸው ስራዎች መካከል 14 የሚሆኑ የፖሊሲ ምክረ ሃሳቦች የቀረቡ ሲሆን ጥናቶቹም፡-
1. በመውጫ ፈተና ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን የሚፈታ አማራጭ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ
2. የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ወደ ስራ ዓለም የሚሸጋገሩበትን ሁኔታ አማራጭ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ
3. በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ሙስና (Academic Dishonesty) ችግሮችን ለመፍታት አማራጭ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ
4. በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተከታታይ፣የርቀትና የመደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ በማጥናት አማራጭ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ
5. የከፍተኛ ትምህርት የአመራርና የአካዳሚክ ስታፍ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎትን ለማሳደግ የሚያስችል መመሪያ
6. የከ/ት/ተቋማት የበጎ ፍቃድ እና ብሔራዊ አገልግሎት ተግዳሮቶችን የሚቀርፍ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ
7. የምርምር ዩኒቨርስቲዎችን ለማልማት የሚያስችል ፍኖተ ካርታ
8. በTVET ተቋማት ሀገር በቀል ታለንት እና ክህሎት ችግሮችን የሚፈታ አማራጭ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ
9. በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገር በቀል እውቀት የሚለማበትና የመመራበትን ስርዓት ለመፍጠር አማራጭ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ
10. የምርምር ዩኒቨርስቲዎች አገር አቀፍ ስታንዳርድ
11. የ Applied & technical university አገር አቀፍ ስታንዳርድ
12. Comprehensive university አገር አቀፍ ስታንዳርድ
13. በከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና የአደጋ ጊዜ ክስተቶች ተጽዕኖን ለመቀነስና በዘላቂነት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል አማራጭ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ
14. የሳይንሳዊ ባህል ግንባታ እና ሀገር በቀል እውቀት ተግዳሮቶች እና እድሎች ላይ አማራጭ የፖሊሲ ምክረ ሃሳብ ሲሆኑ
በመጫረሻም የማዕከሉ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ሀብታሙ ተካ እና የማዕከሉ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ ሙህዬ በቀረቡት አስራ አራት ምክረ ሃሳቦች እና የማዕከሉ የውጪና የውስጥ ተገልጋይ እርካታ የዳሰሳ ጥናት ላይ ከተሳታፊዎች በተነሱ ሀሳቦች ላይም ጥልቅ ውይይት በማድረግና የተገኙ ጠቃሚ ግብኣቶች በማካተት ለቀጣይ ጥናቱ ውጤታማነት እንደሚሰራ እና የ2014 ዓ.ም ስራዎች አተገባበር ላይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡