"ዜጋው በምርጫው ዕለት የዴሞክራሲ መብቱን ተጠቅሞ በአግባቡ መርጧል"
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
South omo zone Prosperity Party - የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ
ይህ የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ይፋዊ የማህበራዊ ሚድያ አገልግሎት የፌስቡክ ገጽ ነው ።
04/06/2026
"ኢትዮጵያ አሸንፋለች" በማሌ ልዩ የምርጫ ክልል ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ አደረገ ።
ዲመካ ፣ ግንቦት 27/2018 ዓ/ም
በማሌ ልዩ ምርጫ ክልል በሰላማዊ ሁኔታ ሲካሄድ የቆየው የምርጫ ሂደት መጠናቀቁን ተከትሎ፣ የሕዝብ ድምፅ የተመዘገበበት ጊዜያዊ ውጤት ዛሬ በምርጫ ክልል ማዕከል ይፋ ተደርጓል ።
ቀደም ጊዜያዊ ውጤቱ በየምርጫ ጣቢያዎቹ ተለጥፎ መቆየቱ ይታወሳል።
በ53 የምርጫ ጣቢያ ተለጥፎ የቆየውን ውጤት መነሻ በማድረግ የአካባቢው ነዋሪዎችና መራጮች ይፋ የሆነው ውጤት የራሳቸው የሉዓላዊ ሥልጣናቸው መግለጫ መሆኑን በተለያየ መልኩ በመግለጽ ውጤቱን እየተመለከቱ ይገኛሉ።
በምርጫው የተሳተፉ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመራጩን ሕዝብ ድምፅ ሊያከብሩና ለሕዝብ ውሳኔ ሊገዙ እንደሚገባ ነዋሪዎቹ አሳስበዋል ።
04/06/2026
የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር የ120 ቀን ዕቅድ እየገመገመ ይገኛል ::
ግንቦት 27/2018 ዓ.ም ዲመካ
በመድረኩ የዞን አስተባባሪ ኮሚቴ የካቢኔ አባላትና ሌሎች አመራሮች የተሳተፉ ሲሆን የዞኑ አስተዳደር ልዩ አማካሪ አቶ ዮናታን ሰይድ የ120 ቀን ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል ::
የምርጫ ስራን በተመለከተ የተቀመጠውን ግብ ሙሉ በሙሉ ማሳካት መቻሉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ገልፀው በምርጫው ወቅት አመራሩ ላሳየው ቁርጠኝነት አመስግነዋል ::
ቀጣይ የህዝብ ጥያቄ በሚመልስ መልኩ መጠነ ሰፊ ስራ መሰራት እንዳለበት ዋና አስተዳዳሪው በግብርናው ዘርፍ ሪፎርም መደረግ እንዳለበትም አቶ ማዕከል ማሊኮ አሳስበዋል ::
ቀበሌ ድረስ ያለው የግብርና አመራሩና ባለሙያዎች ከወትሮው በበለጠ መነሳሳት በመፍጠር የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባም ተመላክቷል ::
በሌላ በኩል የኩቡር ጠቅላይ ሚንስተራችን ኢንሸቲቭ በተፈለገው ደረጃ አለመፈፀም በዕቅድ አፈፃፀሙ ወቅት በአንዳንድ መዋቅሮች የተስተዋሉ ችግሮች መሆናቸውን ልዩ አማካሪው ጠቁመዋል ::
በቀጣይ የገቢ አማራጮችን በመለየት ገቢ 100% አሟጦ መሰብሰብ እንዳለበት አቶ ማዕከል አሳስበው በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት መሰራት ይገባል ብለዋል ::
በተመሳሳይ የመንገድ ውሃ መብራትና ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ተደራሽ በማድረግ ህዝቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ መደረግ እንዳለበት ዋና አስተዳዳሪው አሳስበዋል ::
04/06/2026
"7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኢትዮጵያ እያደገ በመጣዉን የዴሞክራሲ ስርዓት ላይ የራሱን አሻራ ያኖረ ነው" የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት
ግንቦት 27/2018 ዓ.ም
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በክልሉ በ56ቱም የምርጫ ክልሎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በሰላም ስለ መጠናቀቁ ምክር ቤቱ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል ።
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ አቶ ጎበዜ አበራ በመግለጫቸዉ እንደጠቆሙት በክልሉ ሀገራዊና ክልላዊ የምርጫ ስራዎች በተዘጋጀው ዕቅድ መሰረት ወደ ተግባር የተገባ ስለመሆኑ ጠቁመዋል ።
ምርጫው በሰላምና በስኬት ስለመጠናቀቁ የገለፁት አቶ ጎበዜ ፣በክልሉ በ56ቱም የምርጫ ክልሎች የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በተያዘላቸው ጊዜ ተጠናቋል ብለዋል።
በክልሉ ለ7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለውድድር የቀረቡ 22 የፖለቲካ ፓርቲዎችና 2 የግል ዕጩዎች እንደነበሩም በመግለጫቸው አብራርተዋል ።
7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በኢትዮጵያ እያደገ በመጣዉን የዴሞክራሲ ስርዓት ላይ የራሱን አሻራ ያኖረ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ጎበዜ ፣ምርጫው ከዚህ ቀደም ከነበሩበት የተሻለና የዴሞክራሲ ምህዳር የተረጋገጠበት እንደሆነ አስረድተዋል ።
የዘንድሮው ምርጫ በሂደቱም ሆነ በድምፅ አሰጣጥ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንደነበረ ገልፀው ፦ሁሉም ፓርቲዎች የአማራጭ ሀሳባቸውን ያካሄዱበት ሂደት ተጠቃሽ ስለመሆኑ አመላክቷል ።
የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሳጌ ሻምባ በበኩላቸው በክልሉ ዴሞክራሲ እንዲዳብር ህዝቡ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቁመው ፥በዚህም ምርጫው ስኬታማ እንደነበረ አስረድተዋል ።
በቀጣይም ህዝብ በሁሉም ተግባራት የሚያደረገውን የነቃ ተሳትፎ እንዲያጠናክር ምክትል ሰብሳቢዉ ገልፀዋል ።
የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ፀሐፊ አቶ ወልዴ ዳና 7ተኛ ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁ ገልፀው ፣ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ውጤቱን በፀጋ እንዲቀበል ጠቁመዋል ።
በመጨረሻ 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱት አካላት የክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክርቤት ምስጋና አቅርቧል ።
03/06/2026
የደቡብ ኦሞ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የሚዲያና ህዝብ ግኑኝነት ዘርፍ ኃላፊ ወጣት ኤፍሬም ኤርሚያስ ለመራጩ ህዝብ በማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጹ መልዕክት አስተላልፈዋል
የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል
በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ድምጻችሁን በነጻነትና በሰላማዊ መንገድ በመስጠት፣ የሀገራችንን ብሎም የዞናችንን የዲሞክራሲ ጉዞ አንድ እርምጃ ወደፊት ላስቀጠላችሁ ለመላው የዞናችን ህዝብ የከበረ ሰላምታዬ ይድረስ ።
በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ ትልቁና ዋናው አሸናፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይሆኑ የኢትዮጵያ /የዞናችን ህዝብና እራሷ ኢትዮጵያ/ዞናችን ናት።
የህዝብ ድምጽ የሀገር አንድነት መሰረት ነው ። የአንድ ሀገር ጥንካሬና ሉዓላዊነት የሚለካው በህዝቦቿ አንድነትና በምርጫ ካርዳቸው በሚያሳዩት ብስለት ነው።
ስለሆነም በዚህ ምርጫ የታየው ከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ የሚያረጋግጠው አንድ እውነታ አለ፦የበሰለ የፖለቲካ ባህል፦ ልዩነቶችን በሃሳብና በምርጫ ካርድ የመፍታት ጥበብ በተግባር ታይቷል። ሁለተኛው የህዝብ የበላይነት፦ የስልጣን እውነተኛው ባለቤትና ምንጭ ህዝብ መሆኑ ዳግም ተመስክሯል። ሦስተኛው ለነገዋ ኢትዮጵያ የተጣለ መሰረት፦ ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ የሰላምና የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ተጀምሯል።
ሰለሆነም የዞናችን ህዝቦች ወደፊት መጓዝ ይኖርብናል ።
"በምርጫ ሂደት ውስጥ የተለያዩ ሃሳቦች ሊንጸባረቁ ይችላሉ፤ ምርጫው ሲያበቃ ግን ሁላችንም የምንቆመው ለአንዲት ጠንካራና የበለጸገች ኢትዮጵያ ነው።" አሁን ከተፎካካሪነት ወደ አብሮነት፣ ከምርጫ ቅስቀሳ ወደ ሀገር ግንባታ የምንሻገርበት ወቅት ነው።
የተሰጠው እያንዳንዱ ድምጽ ተከብሮ፣ አገራዊ ውጤቱን በመግለጽ ስልጣን የተሰጠው ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ስሆን ይፋዊ መግለጫ እስከሚሰጥ በመረጋጋት በመጠበቅ የህዝብ አደራን በታማኝነት በመወጣት የሀገራችንን ብሎም የዞናችንን ሰላም፣ ልማትና ፍትሃዊነት ማረጋገጥ የሁሉም ኃላፊነት ይሆናል።
የህዝብ ድምጽ ይከበር!
ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና ጥንካሬ ለዘላለም ትኑር!
03/06/2026
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ እንኳን ደስ አለን - የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ የተሰማውን ደስታ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ገልጿል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የፀጥታ ኃይል አካላት እንዲሁም ሕዝቡ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በሙሉ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ለተወጡት ሀገራዊ ኃላፊነት እና ላሳዩት ፅናትም ምክር ቤቱ ያለውን ምስጋና እና አድናቆት ገልጿል።
ምክር ቤቱ በመግለጫው፣ “ልዩነቶቻችንን እና ችግሮቻችንን በዴሞክራሲያዊ መንገድ በመፈታት በምርጫው የታየውን ሰላም በማስቀጠል የበኩላችንን ሚና እንወጣ፤ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም በጋራ እንቁም” ሲል ጥሪውን አቅርቧል።
03/06/2026
#7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ አፈፃፀም በዳሰነች ወረዳ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተገመገመ
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ/ም ኦሞራቴ፣ በዳሰነች ወረዳ በታሪካዊነቱና በከፍተኛ ህዝባዊ ተሳትፎው የሚታወሰው 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ አጠቃላይ አፈፃፀምን አስመልክቶ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰፊ የግምገማና የውይይት መድረክ አካሄደ።
በግምገማ መድረኩ ላይ እንደተገለጸው በወረዳው የተካሄደው ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የጋራ ምክር ቤቱና መላው የወረዳው ማህበረሰብ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
በወረዳው በአጠቃላይ 43,679 ዜጎች በነቂስ ወጥተው ድምጽ በመስጠት ሉዓላዊ መብታቸውን ተጠቅመዋል። ይህ ቁጥር በወረዳው የፖለቲካ ንቅናቄና በምርጫ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ የተመዘገበበት መሆኑ የዳሰነች ወረዳ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ እና የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሣዳም አሊ ተናግረዋል። በምርጫው ሂደት ላይ የሴቶች ተሳትፎ በከፍተኛ ደረጃ ጎልቶ የታየበትና በድምጽ አሰጣጡም ላይ ያሳዩት ተደራሽነት አመርቂ እንደነበር ተጠቁሟል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤቱ አማካኝነት የነበሩትን ልዩነቶች በውይይት እየፈቱ ለህዝብ ሰላምና ለምርጫው ስኬት በቅንጅት መስራታቸው ለሌሎች አካባቢዎች አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑ የጋራ ም/ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ እና የዳሰነች ወረዳ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ሪኮይ አሪከር ተናግረዋል።
"ይህ 7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በዳሰነች ወረዳ በሰላም መጠናቀቁ የህዝባችንን የዴሞክራሲ ባህል ማደግ የሚያሳይ ሲሆን ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤት ደረጃ ያሳዩት የመደማመጥና አብሮ የመስራት መንፈስ የወረዳችንን ልማትና አንድነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው" ሲሉ የጋራ ም/ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ ገልጸዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ታዲዮስ ለበን በበኩላቸው ከምርጫው ሂደት የተገኙ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና በአንዳንድ የምርጫ ጣቢያዎች የታዩ ውስንነቶችን በማረም በቀጣይም በወረዳው ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን የህዝብን አንድነት ለመገንባትና የአካባቢውን ልማት ለማፋጠን በጋራና በትብብር መንፈስ እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ታዲዮስ ለበን በቅርቡ የተካሄደውን የምርጫ ውጤት በሙሉ ልብ እና በፀጋ እንደሚቀበሉ የገለጹ ሲሆን የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን ትልቁ አሸናፊ የኢትዮጵያ ሕዝብና የጀመርነው የዲሞክራሲ ሥርዓት ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ምርጫው የሕዝብን ድምፅና ፍላጎት ያንጸባረቀ በመሆኑ ሂደቱን ማክበርና ውጤቱን በየዋህነትና በዲሞክራሲያዊ መንፈስ መቀበል የሁሉም ወገን ኃላፊነት መሆን አለበት ብለዋል።
የጋራ ምክር ቤቱ አመራሮች በሰጡት መግለጫ ምርጫው በስኬት መጠናቀቁ የወረዳው ህዝብ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት ነው ብለዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ምክር ቤቱ በኩል ያሳዩት የጎለበተ የፖለቲካ ባህል፣ መቻቻል እና ለህዝብ ሰላምና አንድነት ቅድሚያ የመስጠት መርህ ለሌሎች አካባቢዎች አርአያ መሆን የሚችል መሆኑም ተመላክቷል።
"ይህ ምርጫ የዳሰነች ወረዳ ህዝብ የዴሞክራሲ ብስለቱንና የሰላም ወዳድነቱን በተግባር ያረጋገጠበት ታሪካዊ መድረክ እንደሆነ ሀሳባቸውን ገልፀዋል።
ምክር ቤቱ የግምገማ መድረኩን ሲያጠቃልል ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የልማት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለበትና ህዝቡ በምርጫው ያሳየውን ከፍተኛ ተነሳሽነት ወደ ልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች በመቀየር የወረዳውን ሁለንተናዊ እድገት ማፋጠን እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በተጨማሪም አብሮነትን ማጠናከርና ከምርጫው ማጠናቀቅ በኋላም ቢሆን በፓርቲዎችና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን የጋራ ተጠቃሚነትና የሰላም እሴት ይበልጥ ማጎልበት እንደሚገባ ተገልጿል።
በመጨረሻም፣ ምክር ቤቱ ለምርጫው ስኬታማነት ሌሊትና ቀን ለደከሙ የፀጥታ አካላት፣ ለምርጫ አስፈፃሚዎች እና ሙሉ ሂደቱን በሰላማዊ መንገድ ላጠናቀቀው መላው የዳሰነች ወረዳ ህዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።
።
03/06/2026
✍️ የ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲጎለብት አድርጓል ሲሉ የሐመር ወረዳ እና የዲመካ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤቱ ገልፀዋል።
✅✅ ግንቦት፦ 26/2018 ዓ.ም
#ዲመካ
✍️ በሐመር ወረዳ እና በዲመካ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታውቀዋል።
✍️ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሠላማዊ፣ ዴሞክራስያዊ እና ታዓማኒ እንደሆና ምርጫው ያለምንም ችግር ሰላማዊ ሆኖ መጠናቀቁን የሐመር ወረዳ እና በዲመካ ከተማ አስተዳደር ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በለጠ በቀለ ተናግረዋል።
✍️ የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በለጠ አክለውም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የውይይት ባህል የጠነከረበት እንደነበር አስታውሰው፤ በቅድመ ምርጫ፣በምርጫና በድህረ ምርጫ ሂደቶች ወቅት ፓርቲዎች በጋራ እየመከሩና ለክፍተቶች መፍትሄ እየሰጡ መሄዳቸው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲጎለብት አድርጓል ብለዋል።
✍️ የሐመር ወረዳ እና የዲመካ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዋና ም/ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በሱፍቃድ ጎይቲ እንደጠቀሱት የ7ኛው ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና በህዝብ ዘንድ ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ማሳያው የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱና እንዲሳተፉ ማድረጉ ካለፉት ምርጫዎች የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።
✍️ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሚያስፈልገው በጋራ ጉዳዮች ከምርጫ በፊት ጀምሮ ተቀናጅተንና ተናበን እየሰራን ቆይተናል ያሉት የጋራ ምክርቤቱ አባል የሆኑት አቶ አስቻለው አባይነህ የ7ኛው ዙር ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ምንም ዓይነት ችግር ሳይፈጠር በሰላም መጠናቀቅ መቻሉን ገልጸዋል።
✍️ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ፀኃፊ የሆኑት አቶ ተሾመ ግርማ በበኩላቸው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛው ኃገራዊ ምርጫ ከሂደቱ እስከ ውጤት አሰጣጥ ድረስ ያሳዩትን ብርቱ ጥንካሬና ትብብር በሌሎች የልማት ስራዎች ላይ እንዲያሳዩ ጠይቀው የምርጫው ሂደት ከጅማሮ እስከ መጠናቀቅ ድረስ ፍፁም ሠላማዊና ታዕማኒ መሆኑን ተናግረዋል።
✍️ በመጨረሻም የሐመር ወረዳ እና የዲመካ ከተማ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ህብረተሰቡ ምርጫውን የመረጡበት መንገድም ፍፁም ሠላማዊ አምኖና ወዶ በመሆኑ የሰጡት ድምፅ ተሰብስቦ በየደረጃው መረጃ ተጣርቶ ከምርጫ ቦርድ ህጋዊ ሰውነት አግኝት ይፋ እስከሚደረግ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቅ የሀደራ መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል።
✍️ በመድረኩም የደቡብ ኦሞ ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ሰብሳብና የኢዜማ ተወካይ አቶ ሙልጌታ ሻሆ፣ የደቡብ ኦሞ ዞን ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ፀኃፊ የሆኑት አቶ የሺዋስ አባይ ተገኝተዋል።
03/06/2026
የሣላማጎ ወረዳ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋራ ምክር ቤት አባላት በሣላማጎ ወረዳ በ3ቱ ልዩ ምርጫ ክልል 36 ምርጫ ጣቢያ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ደሞክራሲያዊ ፣ ሰላማዊ ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ መሆኑን ገለፁ።።
ሃና ፤ ግንቦት፤ 26/2018 ዓ.ም የሣላማጎ ወረዳ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋራ ምክር ቤት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ደሞክራሲያዊ ፣ ሰላማዊ ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ መሆኑን በውይይት መድረካቸዉ አረጋግጠዋል።
መድረኩ በዋናነት ሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ማድረግና መተግበር ባለባቸው የምርጫ መርሆዎች አተገባበርና አፈፃፀም ፣ የታዛቢዎች የስርዓት አፈፃፀም ና አጠቃላይ የድምጽ ህዴቱ በተመለከተ እና እንዲሁም በቀጣይ የድህረ ምርጫ ስራዎች የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ዉይይት አድርጓል።
የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዮሀንስ ወ/ገብርኤል በመድረኩ እንደገለፁት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ደሞክራሲያዊ ፣ ሰላማዊ ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ሆኖ መጠናቀቅ እንዲችል የተፎካካሪ ፓርቲ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሷል።
ለዚህም ሁሉም ተፎካካሪ ፖርቲዎች የምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸውን ህጎችና ደምቦች አክብረው እንዲሁም መብትና ግዴታ ለይቶ በማወቅ በመንቀሳቀስ በወረዳዉ በ36 ምርጫ ጣብያ ያለምንም ችግር ድምጽ የመስጠት ሂደቱ በሠላም ተጠናቋል ።
በተለይም በተፎካካሪ ፓርቲዮች አማካኝነት የሚደረግ የይምረጡ ቅስቀሳ መርሀ ግብሮች የጥሞና ጊዜ ከመቆጠብና የምርጫ ቦርድ ህግ የጠበቁ ከመሆን አንጻር፤ የአንድ አከባቢ ህዝብ የነበሩ ችግሮች አባላቶች ከግንዛቤ ችግር የተፈጠሩ ችግሮች ብኖሩም ችግሩን በዉይይት መፍታት መቻሉ ገዥዉ ፓርቲና መንግስት ምን ያክል ለዴሞክራሲ ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንዳለ ማሳያ ነዉ ተብለዋል ።
የሣላማጎ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለትካና ህ/ግ/ዘ/ኃላፊና እና የፖለቲካ ፓርትዎች የጋራ ም/ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ ጌታያዉቃል ዮሀንስ በበኩላቸው በምርጫ ሕግጋት፣ደንቦችና የሥነ-ምግባር መመሪያዎች ፤በመራጮችና ዕጩዎች መብትና ግዴታ ፤
ብሔርን ፣ ሃይማኖትንና ጾታን መሠረት ያደረጉ የጥላቻ ንግግሮችን በመከላከል ዙሪያ ሁሉም ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ኃላፊነት በተገቢው የተወጡ መሆኑን ጠቅሰዉ።
አክለውም ምርጫ የሰላማዊ ትግል ብቸኛው መሣሪያ ነዉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅንጅታዊ አሰራርን በመዘርጋት ለህዝብና ለመንግስት የሚጠቅም አጀንዳዎች ላይ በመንተራስ ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል: ለዝህም ገዥዉ መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እና ዴሞክራሲን ለመትከል ሠፊ ስራ እየተሠራ ያለ ስሆን ለተፎካካሪ ፓርቲዎች፣የብሽሽቅ ፖለቲካ የትጥቅ ትግል አማራጭ ሊሆን እንደማይችልም አሳስበዋል።
የጋራ ም/ቤቱ አባል እና የኢዜማ ፓርቲ ተወካይ አቶ ታደለ በንግግራቸዉ አያይዘውም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፣ ፍትሐዊ ፣ ዲሞክራሲያዊና ተዓማኒነት የተረጋገጠ እንዲሆን የፓርቲ አባሎች የምርጫ ቦርድ ያስቀመጣቸው ህጎችና ደንቦች አክብረዉ መንቀሳቀሳቸው ለቀጣይ ተሞክሮ የሰጠ ነዉ ተብለዋል ።
03/06/2026
በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማጎልበት የተሠሩ ሥራዎች አበረታች ናቸው - የአፍሪካ ኅብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድን
የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ እና የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የቡድኑን የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያ ግምገማ ውጤትን በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ውቅት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ዴሞክራሲን ለማጎልበት የሠራውን ሥራ እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።
አጠቃላይ የምርጫው ሂደትም የኢትዮጵያን እና የዓለም አቀፍ ሕጎች ማዕቀፍን በተከተለ መልኩ መካሄዱን በግምገማው ማረጋገጣቸውን ጠቁመዋል።
ከቅድመ ምርጫው ጀምሮ የነበረው ሂደት አበረታች እንደነበር የገለጹት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የአፍሪካ ኅብረት ከምርጫው ዋዜማ አንሥቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይቶችን ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።
የመራጮች ትምህርት አሰጣጥ በተመለከተም ሕዝቡ እንዴት መምረጥ እንዳለበት ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲያገኝ መደረጉን እና በምርጫው ዕለት የነበረው የተቀናጀ መናበብ ለመራጮች ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን አስረድተዋል።
በምርጫው ሂደት ጥቅም ላይ የዋለው ቴክኖሎጂ በተለይም ለወጣቶች የፈጠረው ዕድል ከፍተኛ መሆኑን የታዛቢ ቡድኑ መሪ በመግለጫቸው አብራርተዋል።
የድምፅ መስጫ ሰዓት መራዘሙ ለመራጮች ተጨማሪ ዕድል መፍጠሩን፣ እንዲሁም ለአካል ጉዳተኞች እና ለአረጋውያን በድምፅ አሰጣጡ ሂደት ቅድሚያ መሰጠቱ የዜጎችን ተሳትፎ በእጅጉ ማነቃቃቱንም ጠቁመዋል።
በመላው ኢትዮጵያ የምርጫ አስፈፃሚዎች እና የፀጥታ አካላት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በጥሩ ሁኔታ መወጣታቸውን፣ የመገናኛ ብዙኃንም በተመሳሳይ በከፍተኛ ኃላፊነት ስሜት ሥራቸውን ማከናወናቸውን አድንቀዋል።
ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫው ያሳየው ተሳትፎ እና ትልቁን ኃላፊነቱን በጀግንነት መወጣቱ እጅግ የሚያስመሰግን መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ ኡሁሩ ኬንያታ አስታውቀዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa
