በዛሬው ዕለት እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጉለሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ከ10ሩ ወረዳ ለተወጣጡ ነባር በጎ ፈቃደኞች ስልጠና ሰጥተናል በዚህ አጋጣሚ ወቅቱን ያልጠበቀ የበጋ ዝናብ ስለገጠመን የጎርፍ አደጋ እንዳይገጥመን በቅድሚያ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንድያደርግ
1ኛ፡የመንገድ ከሪብ ስቶን እንድፀዳ
2ኛ፡የመንገድ አከፋይ ወሃ መሄጃ እንድፀዳ
3ኛ፡ወሃ መሄጃ ቱቦዎች በቆሻሻ እንዳይደፈን
4ኛ፡ክፍት ዲቺ ወሃ መሄጃ በቆሻሻ እንዳይደፈን
5ኛ፡ በወንዝ ዳርቻ ያለው ማህበረሰብ በከባድ ዝናብ ጊዜ ጥንቃቄ እንድያደርግ እንድያግዙ መግባባት ተፈጥሮዋል፡፡
Gulele Fire Disaster Risk mgt. Commission
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gulele Fire Disaster Risk mgt. Commission, Government Organization, addis Ababa . Winget, Addis Ababa.
19/03/2025
በመጪዉ የበልግ ዝናብ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የጎርፍ አደጋዎችን ቀድሞ መከላከል አንደሚገባ ተገለጸ።
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጉለሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 7 ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በቀጣይ የበልግ ወቅት የሚጥለዉን ዝናብ ተከትሎ ሊያጋጥም የሚችል የጎርፍ አደጋን ቀድሞ መከላከል በሚያስችል ጉዳይ ላይ ከወረዳዉ ነዋሪዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል፡፡
በኮሚሽኑ የጉለሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ኒቆዲሞስ ቡቼ በዉይይት መድረኩ ላይ እንደተናገሩት በቀጣይ የበልግ ጊዜ የሚጥለዉን ዝናብ ተከትሎ ለጎርፍ አደጋ መከሰት ምክንያት የሚሆኑትን የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችን ማጽዳትና በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ጠቅሰዉ ወንዞች በሚገኙባቸዉ አካባቢ የሚኖረን እንቅስቃሴ በማስቀረት አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግና ከኮሚሽን መ/ቤቱ የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን መተግበር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ወ/ሮ እጅጋየሁ ካሀሊው የወረዳ 7 ስራ አስኪያጅ ጽ /ቤት ኃላፊ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከኮሚሽን መ/ቤቱ ጉለሌ ቅርንጫፍ ጋር በተቀናጀ ሁኔታ በትብብር እንደሚሰሩ ጠቅሰዉ የወረዳዉ ነዋሪዎችና ባለድርሻ አካላትም ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመቀነስ በሚደረገዉ ጥረት ሁሉ አስፈላጊዉን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ኃላፊነታቸዉን እንደሚወጡ ተናግረዋል።
የዉይይቱ ተሳታፊዎች በኩላቸዉ እንደተናገሩት በወረዳቸዉ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ተረድተዉ በሰዉና በንብረት ሊደርስ የሚችልን አደጋ ቀድሞ በመከላከል ረገድ ከዉይይቱ ግንዛቤ እንዳገኙ አብራርተዉ ባገኙት መረጃና ግንዛቤ እራሳቸዉንና አካባቢያቸዉን ከአደጋ እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
ለእሳትና ለላሎች ድንገተኛ አደጋዎች አንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎት በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa
