Transitional Justice in Ethiopia/የሽግግር ፍትሕ - በኢትዮጵያ

Transitional Justice in Ethiopia/የሽግግር ፍትሕ - በኢትዮጵያ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Transitional Justice in Ethiopia/የሽግግር ፍትሕ - በኢትዮጵያ, Government Organization, Addis Ababa.

Photos from Transitional Justice in Ethiopia/የሽግግር ፍትሕ - በኢትዮጵያ's post 18/02/2025

በሽግግር ፍትህ ትግበራ ሂደት ባለፉት ሁለት ሳምንታት የተከናወኑ ተግባራት እንደሚከተለው ቀርበዋል

1. የሽግግር ፍትህ ረቂቅ የህግ ማዕቀፎችን በመድብል መልክ የማጠቃለል ስራው ተጠናቋል፡፡ በዚህም መሰረት የባለሙያዎች ቡድኑ የሽግግር ፍትህ ልዩ ችሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን እና የአለም አቀፍ ወንጀል ህግ አዋጅን እራሳቸውን ችለው እንዲቀጥሉ ያደረገ ሲሆን የሽግግር ፍትህ ተቋማትን ማለትም የልዩ ዐቃቤ ሕግ ጽ/ቤትን፣ የእውንት ኮሚሽንን እና የማጥራት ኮሚሽንን የሚያቋቁሙ ድንጋጌችን በመጽሃፍ በመከፋፈል በመድብል መልክ የማዘጋጀት ስራውን አጠናቋል፡፡ በቀጣይ ቀናትም የባለሙያዎች ቡድኑ በህግ ረቂቆች ላይ የሚያደርገውን የመጨረሻ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

2. በሽግግር ፍትህ ሂደት ባለቤት ከሆኑት የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል ሁለቱ ተጎጂዎች እና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡ በፍኖተ ካርታው ላይ በሰፈረው መሰረትም የእነኚህን ተሳትፎ በሂደቱ ለማረጋገጥ የሚያስችል ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ውይይቱን መሰረት አድርጎ የተነሱ ሃሳቦችን በማካተት በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጨረሻው የስትራቴጂ ሰነድ ለህዝብ የሚጋራ ይሆናል፡፡ በዚህ ሰነድ ሴቶች፣ ህጻናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ ተፈናቃዮች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን እና በሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች በሁሉም የሽግግር ፍትህ ማስተግበሪያ ስልቶች አተገባር ውስጥ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያበረቱቱ መርሆዎች እና አሰራሮችን የሚመለከቱ ሃሳቦች ተካትተዋል፡፡

3. የሽግግር ፍትህ ረቂቅ ህጎች የግብዓት ማሰባሰቢያ የምክክር መድረኮች የመመሪያ ማእቀፍ እና የድርጊት መርሃ ግብር ረቂቅ ተጠናቆ ለአስተያየት ለባለሙያዎች የተሰራጨ ሲሆን በግብዓቶቹ መሰረት ሰነዱን በማጠናቀቅ በቀጣይ ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ ጥቅም ላይ እንዲውል በጥንቃቄ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህ ሰነድ ውስጥ በምክክር መድረኩ የሚሳተፉ ሰዎች፣ ውይይቶቹ ስለሚካሄዱባቸው ቦታዎች፣ ተሳታፊዎች ስለሚለዩበት ሁኔታ እና በመለየት ሂደቱ ሊሳተፍ ስለሚገባ አካላት፣ የጊዜ እና የበጀት መግለጫዎች ተካተዋል፡፡

4. በሽግግር ፍትህ ሂደት ለትምህርት የሚሆን ልምድ ካላት ሀገር ኮሎምቢያ አምባሳደር የተከበሩ YEISON ARCADIO MENESES COPETE ጋር የሽግግር ፍትህን አተገባበር ውጤታማነት ለማስጠበቅ የኮሎምቢያ ኤምባሲ ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት ለመስራት ፍላጎቱን የገለጸበት የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡ በዚህ በፍትህ ሚኒስቴር በተካሄደ የውይይት መድረክ የኮሎምቢያ አምባሳደር ሀገራቸው ለኢትዮጵያም ሆነ ለሌሎች በተመሳሳይ ሂደት ውስጥ ለሚገኙ ሀገራት ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ እንደሆነች ገልጸው ሀገራቸው በኢትዮጵያ የተጀመረው የሽግግር ፍትህ እውን እንዲሆን እስከ መጨረሻው ድጋፏን እንደምትቀጥል ገልጸዋል፡፡

5. የሽግግር ፍትህን ሂደት አስመልክቶ ለፍትህ ሚኒስቴር እና ለክልል ፍትህ ቢሮዎች አመራሮች ገለጻ ቀረበ፡፡ የፍትህ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትህ ቢሮዎች፣ የፌዴራል እና የክልል ፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የፍትህ ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተካሄደው 7ኛው የጋራ ጉባዔ ላይ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ሂደትን የሚመለከት ገለጻ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡

Photos from Transitional Justice in Ethiopia/የሽግግር ፍትሕ - በኢትዮጵያ's post 15/01/2025

የኢትዮጵያ የሽግግር ፍትህ ለተፈጸሙ በደሎችና የሰብዓዊ ጥሰቶች ምላሽ ይሰጣል
********************

በሀገራችን በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ ግጭቶች ሳቢያ የተከሰቱ ችግሮችን እና የእርስበእርስ ቁርሾዎችን ለመቅረፍ የሽግግር ፍትህ አስፈላጊ እንደሆነ የሽግግር ፍትህ ህጎች ትግበራ አርቃቂ ቡደን አባል ገለፁ፡፡

በዛሬው የኢቲቪ አዲስ ቀን "የሀገር ጉዳይ" ላይ የቀረቡት የሽግግር ፍትህ ህጎች ትግበራ አርቃቂ ቡደን አባል የሽግግር ፍትህ ሰላምን ለማጽናት ትልቅ ሚናም እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የቡድኑ አባል እና በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ የሽግግር ፖሊሲ መምህር ማርእሸት ታደሰ (ዶ/ር) የሽግግር ፍትህ በተያዘው ዓመት ለማስጀመር ዕቅድ ተይዟል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ቀደም ባሉ ጊዜያት በግጭቶች ሳቢያ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ በደሎች እና ቁርሾዎች ለመሻገር የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ መቀረፁን ገልፀዋል፡፡

አሁን የሚደረገው የሽግግር ፍትህ ከዚህ ቀደም ከተደረጉ የሽግግር ፍትህ ሙከራዎች እጅጉን የተለየ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

እስከ አሁን የተሞከሩ የሽግግር ፍትህ ሙከራዎች አሳታፊነት፣ ሀገራዊ ግብአት የማሰባሰብ ላይ የተመሰረቱ አለመሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

አሁን የተጀመረው የሽግግር ፍትህ ሀገራዊ ግብአት ማሰባሰብ ላይ ተመስርቶ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ፍትህ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡

ከዓመት በላይ ሀገር አቀፍ ግብአትን በማሰባበብም እንደተቆየም አንስተዋል፡፡

የሽግግር ፍትሁ መነሻው ሁሉንም አሳታፊ በመሆኑ የእርስ በእርስ አለመግባባቶችን አንደሚቀርፍ ጠቅሰዋል፡፡

የሽግግር ፍትህ አንድ የሰላም ግንባታ ነው የሚሉት መምህሩ፤ ፍኖተ ካርታው በመዘጋጀቱ በዚሁ መሰረት እንደሚከናወን አንስተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በሀገራችን ሆነ በዓለም ላይ የሽግግር ፍትህ ከወረቀት ሳያልፉ ወደ ትግበራ ያልደረሱበት አጋጣሚ በመኖራቸው አሁን ላይ ይህ የሽግግር ፍትህ እንዲተገበር ከህብረተሰቡ እና ከብዙ ባለድርሻ አካላት ብዙ እንደሚጠበቅ ነው የጠቆሙት፡፡

የሽግግር ፍትህ ተቋማት ቅንጅታዊ አመራር ጊዜአዊ ሴክሬተሪያል አወል ሱልጣን በበኩላቸው፤ የሽግግር ፍትህ ብቻ በስፋት በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ወንጀል ላይ የተሳተፉ ሰዎችን በወንጀል ተጠያቂነትን የሚያደርግ ስለመሆኑ ነው ያመላከቱት፡፡

ለሽግግር ፍትህ ልዩ አቃቤ ህግ እንደሚቋቋምም አንስተዋል፡፡

በሽግግር ፍትህ ፖሊሲው የወንጀል ተጠያቂነት ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ ያሉ ጉዳዮች የሚታዩ ሲሆን እርቅ፣ ምህረት እና ማካካሻ ደግሞ ከ1987 ዓ.ም በፊት ያሉ ጉዳዮች ማስረጃ እና መረጃ እስከተገኘባቸው ድረስ ተፈጻሚ እንደሚሆኑም ተናግረዋል፡፡

ማህበረሰቡ ለመጨረሻ ጊዜ እርቅ እንዲያወርድ፣ ውስጡ ያለውን ቁርሾ እንዲፈታ እና እርቅ ወርዶ መጪው ዘመን የሰላም ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ የሽግግር ፍትህ ለተፈጸሙ በደሎች እና የሰብአዊ ጥሰቶች ምላሽ ይሰጣል ነው ያሉት፡፡

ለሽግግር ፖሊሲ ስኬታማነት የማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ እንደሆነ አንስተው፤ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትም ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ኢቢሲ

02/01/2025

የፍትሕ ሚኒስቴር እና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች በሽግግር ፍትሕ ትግበራ ሂደት ዙሪያ ምክክር አደረጉ

የኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሃና አርዓያስላሴ እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በጋራ በመሩት እና ትኩረቱን የሽግግር ፍትሕ ላይ ባደረገው በዚህ ውይይት ላይ ከፍትህ ሚኒስቴር እንዲሁም ከፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

የውይይቱ ዓላማ ተቋማቱ የሽግግር ፍትህ ትግበራ ምዕራፍ ውስጥ ተቋማዊ ነጻነታቸውን ጠብቀው ለሂደቱ መሳካት የበኩላቸውን ሚና ስለሚወጡበት ሁኔታ የጋራ ምክክር ማድረግ ነው ሲሉ ንግግራቸውን የጀመሩት የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ መድረኩ በተለይም በህግ ዝግጅት ሂደት የሁለቱ ተቋማት ተናቦ እና ተቀናጅቶ መስራት በትግበራ ሂደት ሊፈጠሩ የሚችሉ ተግዳሮቶች ከስር ከስር እየፈቱ ለመሄድ ሁነኛ አበርክቶ አለው ብለዋል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው በሽግግር ፍትህ ትግበራ ምዕራፍ ውስጥ የሽግግር ፍትሕ ጉዳዮችን የሚመለከተውን ልዩ ችሎት በማቋቋም ረገድ ትልቁን ሚና የሚጫወቱት የፌዴራል ፍርድ ቤቶቹ እንደመሆናቸው መጠን ግልጽነት የሰፈነበት እና ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር ለመፍጠር ወቅቱን የጠበቀ ምክክር ማድረጉ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የሽግግር ፍትህ እንዲተገበት ከተወሰነበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የተከናወኑ አበይት ተግባራት እና የረቂቅ ስራቸው በመጠናቀቅ ላይ በሚገኙት የሽግግር ፍትህ የሕግ ማዕቀፎች ላይ ገለጻዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የሁለቱም ተቋማት የስራ ኃላፊዎች በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክትም በቀጣይ በረቂቅ ሕጎች ላይ በሚካሄዱት የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ በከፍተኛ ትኩረት ጥልቅ አስተያየቶችን በመስጠት ለህጎቹ ጥራት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንደሚኖርባቸው አጽዕኖት ሰጥተው ገልጸዋል፡፡ ፈጣን የመረጃ ልውውጥ እና ቋሚ የግንኙነት መስመር ለመዘርጋት እንዲቻልም የተቋማዊ ቅንጅታዊ አመራር መድረክ በመመስረት ወደ ስራ እንዲገባ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

30/12/2024

ለሽግግር ፍትሕ ስኬታማነት ሁሉም አካል ድርሻ አለው'' የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ “የሽግግር ፍትሕ አሥተዳደር” በሚል መሪ ሃሳብ ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ነው።

የሽግግር ፍትሕ ዓላማዎችን እና መርኾዎችን በመገንዘብ በኢትዮጵያ ሊደረግ ለታሰበው የሽግግር ፍትሕ ግንዛቤ የመፍጠር አካል በኾነው ሥልጠና የዞን እና የክልል የፍትሕ አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻዎች ተካፍለዋል።

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም የሽግግር ፍትሕ ዓላማ ችግሮችን በመደበኛ ሕግ መፍታት በማይቻል ጊዜ የተበላሹትን በማቃናት፣ የተበደሉትን በማካካስ፣ እርቅ በመፍጠር እና በመፍታት ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ዓይነተኛ መፍትሄ መኾኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የተፈጠሩ ችግሮችን በሽግግር ፍትሕ እልባት እንዲያገኙ የሚያስችል አሠራር በማደራጀት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ሲደረግ ቆይቷል።

ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣመ፣ ሰብዓዊ መብት ተኮር የኾነ እና የሀገሪቱን ነባራዊ ኹኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ አሠራርን ለመተግበር የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ወጥቷል።

በዚህም መሠረት ዕውነትን በማፈላለግ እና ዘላቂ መፍትሄ በማበጀት በኩል ክልሎች የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ይጠበቃል ነው ያሉት።

ክልሎችም የተፈጠሩ ግጭቶች ቆመው፣ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ ዕውነትን የማፈላለግ፣ የተፈናቀሉትን በመመለስ፣ በአጥፊዎች ላይ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ብሎም የተበደሉ አካላት እንዲካሱ በማድረግ ዘላቂ ሰላም እና መተማመን እንዲኖር ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው አቶ ብርሃኑ የተናገሩት።

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ በክልሉ የሽግግር ፍትሕ እንዲጠናከር የሚያስችሉ ኹኔታዎችን በመፍጠር፣ ቅንጅታዊ አሠራርን በመከተል እና ስለ ሽግግር ፍትሕ ለሕዝቡ ግንዛቤ በመፍጠር የሽግግር ፍትሕ ውጤታማ እንዲኾን የመሥራት ኀላፊነት እንዳለበት አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል።

ኀላፊው ካለፈው በጀት ዓመት ጀምሮ ስለ ሽግግር ፍትሕ ምንነት፣ አስፈላጊነት እና ተያያዥ ጉዳዮች ለሕዝቡ እና ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ መጀመሩን ገልጸዋል።

ሥራውንም ከአጋር አካላት ጋር ለመሥራት በሽግግር ፍትሕ አስፈላጊነት እና ጠቀሜታ ላይ በመግባባት የግንዛቤ ፈጠራ እና የአቅም ግንባታ ሥራ መቀጠሉን ጠቅሰዋል።

"ለሽግግር ፍትሕ ስኬታማነት ሁሉም አካል ድርሻ አለው'' ያሉት አቶ ብርሃኑ የውይይቱ ተሳታፊዎችም ለተግባሩ ውጤታማነት ያለባቸውን ኀላፊነት ተረድተው ለሽግግር ፍትሕ ተግባራዊነት ዕውቀት እና አቅም በመገንባት የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ጠይቀዋል።

ምንጭ፤ የአሚኮ

Photos from Transitional Justice in Ethiopia/የሽግግር ፍትሕ - በኢትዮጵያ's post 29/12/2024

የፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በሽግግር ፍትሕ ትግበራ ሂደት ዙሪያ ተወያዩ

ከታህሳስ 18 ቀን 2017 ጀምሮ ለሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ በቆየው የፍትሕ ሚኒስቴር ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የስልጠና እና የውይይት መድረክ ላይ 'የሽግግር ፍትህ በኢትዮጵያ' በሚል ርዕስ በቀረበ ገለጻ ላይ ውይይት ተካሂዷል።

በገለጻው የሽግግር ፍትህ አስፈላጊነት፣ የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ዝግጅት ሂደት፣ በፖሊሲው የተዘረዘሩ የሽግግር ፍትህ ስልቶች እና የማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ ይዘት እና እስከ አሁን ድረስ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርበዋል። በሽግግር ፍትህ ቀጣይ ተግባራት ዙሪያም ለታዳሚው መረጃ ተሰጥቷል።

ገለጻውን ተከትሎ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች የፍትህ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች እና የሽግግር ፍትህ ትግበራ ሂደት አስተባባሪ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

29/12/2024
Digital Press Briefing: Ambassador Beth Van Schaack, Ambassador-at-Large for Global Criminal Justice, Office of Global Criminal Justice - United States Department of State 19/12/2024

የአሜሪካ የወንጀል ፍትህ አምባሳደር ቫን ዣክ (Van Schaack) በምስራቅ አፍሪካ ሲያካሂዱ የቆዩትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ ሙሉ ይዘት ከዚህ ስር የተጋራውን ሊንክ በመጠቀም ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

Digital Press Briefing: Ambassador Beth Van Schaack, Ambassador-at-Large for Global Criminal Justice, Office of Global Criminal Justice - United States Department of State MODERATOR: Good afternoon to everyone from the U.S. Department of State’s Africa Regional Media Hub. I welcome our participants logging in from across the continent and thank all of you for joining us. Today, we are very pleased to be joined by Ambassador-at-Large for Global Criminal Justice in th...

Photos from Transitional Justice in Ethiopia/የሽግግር ፍትሕ - በኢትዮጵያ's post 14/12/2024

የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሀና አርዓያስላሴ መቀመጫቸውን ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮች እና የዓለም ዐቀፍ ተቋማት ተወካዮች በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ትግበራ ምዕራፍ ዙሪያ ገለጻ አቀረቡ

የፍትህ ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሃና አርዓያስላሴ በገንዘብ ሚኒስቴር በተዘጋጀው እና መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና የዓለም ዐቀፍ ተቋማት ተወካዮች በታደሙበት የውይይት መድረክ ተገኝተው የሽግግር ፍትህ ትግበራ በኢትዮጵያ ያለበትን ደረጃ አስመልከቶ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

ሚኒስትሯ የሽግግር ፍትህ ተግባራዊ እንዲሆን በመንግስት ከተወሰነበት ጊዜ ጀምሮ በፖሊሲ ዝግጅት ሂደት የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ ባቀረቡት ማብራሪያ በፖሊሲ አማራጭ ሰነድ ዙሪያ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ከ80 በላይ የሚሆኑ የምክክር መድረኮች መካሄዳቸውን አስታውሰው በውይይት ሂደቱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች በሰነዱ ላይ ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሽግግር ፍትህ ፖሊሲውን ማጽደቁን ተከትሎ የትግበራ ምዕራፉን የማስተባበር ኃላፊነት የተጣለበት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴርም በሽግግር ፍትህ ሂደት የሚከናወኑ ተግባራትን፣ ተግባራቱ የሚፈጸሙበትን የጊዜ ርዝመትና ፈጻሚ ባለ ድርሻ አካላትን በግልጽ ያስቀመጠ ማስተግበሪያ ፍኖተ ካርታ አዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱን ተናግረዋል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሃና አክለው በፖሊሲው በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረትም የሽግግር ፍትህ ማስተግበሪያ ስልቶችን የሚተገብሩ ተቋማትን ለማቋቋም የሚያስችሉ የህግ ረቂቆች መዘጋጀታቸውን ገልጸው በሀገር ዓቀፍ ደረጃ ከሚካሄዱ የግብዓት ማሰባሰቢያ መድረኮች በኋላ ረቂቆቹ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልከው እንደሚጸድቁ ገልጸዋል፡፡

ፖሊሲው የወንጀል ተጠያቂነት፣ እውነትን ማውጣት፣ ቅድመ-ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ምህረት፣ ማካካሻ እና ተቋማዊ ማሻሻያ ስልቶችን በመተግበር ባለፉት አመታት በሀገሪቱ የተፈጸሙ ጉልህ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን እንዲሁም ጥሰቶቹ የፈጠሩትን በደሎች እና ቁርሾዎችን በማከም እና እልባት እንዲያገኙ በማድረግ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የወጠነ መሆኑን ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ይህን ዓላማ ለማሳካት የሚቋቋሙ ተቋማት በህግ የሚጣልባቸውን ኃላፊነት መወጣት በሚያስችላቸው ደረጃ ነጻ እና ገለልተኛ ሆነው በሚቋቋሙበት ሁኔታ ላይ በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ሀና በመድረኩ የታደሙ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ ተወካዮች ማብራሪያውን ተከትለው ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በስተመጨረሻም ሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የተለያዩ መፍትሄዎችን ቀርጻ ለመተግበር ጥረት በምታደርግበት በዚህ ወሳኝ ጊዜ ዓለም ዐቀፍ ተቋማት እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች የሽግግር ፍትህ ሂደቱ ውጤታማ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ማድረግ ያለባቸው መሆኑን አጽዕኖት ሰጥተው የገለጹት ሚኒስትር ወ/ሮ ሃና ለመድረኩ ታዳሚዎችም ባስተላፉት ጥሪም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና ዴሞክራሲ ይሰፍን ዘንድ በአዲስ አበባ መቀመጫቸውን ያደረጉ የልማት አጋሮች በሙሉ ከምን ጊዜውም በላይ ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ የአምሳደርነት ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

Addis Ababa
10000