08/01/2026
🇪🇹 ዋልያዎቹ አሰልጣኝ 513 ሺ ብር ደሞዝ ይከፈላቸዋል
| ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ፣ ሹመታቸውን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን የተመራው ይኸው መግለጫ፣ አሰልጣኙ የተመረጡበትን መመዘኛ እና የውል ዝርዝራቸውን ይፋ አድርጓል።
🔍 ምርጫው እንዴት ተካሄደ?
ከአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ስንብት በኋላ፣ ፌዴሬሽኑ ለቦታው ብቁ የሆኑ ሦስት እጩዎችን ይዞ እንደነበር ተገልጿል። እነሱም፦
* አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ
* አሰልጣኝ ውበቱ አባተ
* አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ ነበሩ።
✅ ዮሐንስ ሳህሌ ለምን ተመረጡ?
የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አሰልጣኝ ዮሐንስን ለመምረጥ የተጠቀመባቸው ቁልፍ መመዘኛዎች፦
* ከዚህ ቀደም በብሔራዊ ቡድን የነበራቸው ልምድ እና ያስመዘገቡት ውጤት።
* ቡድኑን ለቻን (CHAN) እና ለአፍሪካ ዋንጫ የማሳለፍ ብቃታቸው።
* በታዳጊዎች ልማት ላይ ያላቸው ስራ እና ከፌዴሬሽኑ ራዕይ ጋር አብሮ የመጓዝ ፍላጎታቸው።
* ያላቸው የታክቲክ ጥልቀት እና ወቅታዊ የስልጠና ብቃት በሰፊው ተገምግሟል።
💰 የውል ዝርዝር እና ደሞዝ
አሰልጣኙ ለሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ብሔራዊ ቡድኑን የሚመሩ ሲሆን፦
* የውል ዘመን፦ ከታህሳስ 27 ቀን 2018 እስከ ታህሳስ 26 ቀን 2020 ዓ.ም.
* የወር ደሞዝ፦ 513,000 (አምስት መቶ አስራ ሶስት ሺህ) ያልተጣራ ብር ከተጨማሪ ጥቅማ ጥቅሞች ጋር።
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ዋልያዎቹን ወደ ቀደመ ዝናቸው ለመመለስ እና በታዳጊዎች ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ቡድን ለመገንባት ትልቅ ኃላፊነት ይጠብቃቸዋል።
#ኢትዮጵያ #እግርኳስ #ዋልያዎቹ #ዮሐንስሳህሌ
02/01/2026
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) አሠልጣኝ ሆኖ ለተሾመው አሠልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ መልካም የስራ የስኬት የድል ዘመን እንዲሆንልህ እንመኛለን መልካም እድል ጆኒ !!!!!!!!!!!!
06/09/2025
ብሄራዊ ቡድናችን ጥሩ የመከላቀል ቅርፅ ይዞ የራሱን ሜዳ compact በማድረግ የግብፆችን ነፃ የኳስ እንቅስቃሴ የመግታት መሻሻል አሳይቷል። ነገር ግን የሚከተሉት ድክመቶቹን ማረም ይኖርበታል።
- አሁንም እንደ ቀድሞው ብሄራዊ ቡድናችን ከተቃራኒ ቡድን ጫና ሲደረግበት በቀላሉ በየትኛውም ሜዳ ላይ ሆኖ ኳስ ለተቃራኒ ያስረክባል። ይህ ድክመት ከድሮ ጀምሮ ብሄራዊ ቡድኑ ላይ የሚታይ ችግር እና በአፍሪካ አህጉር ጫወታ ብልጫ የሚወስድበት ድክመቱ ነው። በአጭሩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድኑ በተቃራኒ ቡድን press ሲደረግ በቀላሉ እጅ ይሰጣል፣ ኳስ ይነጠቃል።
- በድኑ በቦታ zonal defense ቢከላከልም ሰው በሰው የመያዝ አቅሙ man marking ደካማ ስለሆነ በተለይ በክንፍ ለሚጫውቱ የግብፅ አጥቂዎች ነፃ እንቅስቃሴ ፈቅዷል
- መከላከል ላይ ብቻ የተጠመደ ይመስላል የማጥቃት ፍላጎት initiative የለውም
-በራሱ ሜዳ እየተከላከለ ኳስ ሲነጥቅ እና ሲያገኝ ከነበረበት የመከላቀል ቅርፅ መውጣት transition from defense to attack በቶሎ አይችልም፣ እዛው ሜዳው ላይ አጭር ቅብብል እየተቀባበለ ለጥቃት ራሱን ያጋልጣል።
- ሲያጠቃ በቁጥር አናሳ ነው። ቦታ አስፍቶ የተቃራኒን የሜዳ ክልል ጠልቆ እየገባ pe*******on and mobility ማጥቃት ላይ ደካማ ነው።
- በማጥቃት እንቅስቃሴ ውስጥ ተጫዋቾች ራሳቸውን ነፃ ማድረግ እና የማጥቅያ ነፃ ሜዳ እየመረጡ የመሮጥ ችሎታቸው ደካማ ነው።
-በስነልቦና ረገድ ቡድኑ የተወስነ መሻሻል አሳይቷል። በተለይ ግብ ጠባቂው ጥሩ የመረጋጋት ባህሪ አሳይቷል። ነገር ግን አሁንም በድኑ በተቃራኒ ቡድን ሲጠቃ የድንጋጤ መከላከል ስለሚያደርግ ፣ ተከላካዬች ትእግስት አጥተው፣ በተለይ በራሳቸው የግብ ክልል አላስፈላጊ ፋውል ይሰራሉ ፣ኳስ በእጅ ይነካሉ፣ የፍፁም ቅጣት እድሎችን ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣሉ።
ቡድኑ የመሃል ሜዳ እና የፊት መስመር አሰላለፍ እና አጫዋወቱ እጅግ ደካማ ነው። ምንም የፈጠራ ችሎታ እና ብልሃት አይታይበትም። በአጭሩ የቡድኑ የማጥቃት አካሄድ በቀላሉ ተገማች ወይንም predictable ነው፣
- ቡድኑ ጨራሽ አጥቂ ይዞ መግባት አለበት፣ ፊት መስመር ላይ ኳስ የመጨረስ ስለት የሌለው ዱልዱም ቡድን ውጤታማ ሊሆን አይችልም።
* የፅሁፉ ሃሳብ ባለቤት አባቡ ሲሆን፤ አስተያየቱን እኛም
Walyas fan club ተጋርቱነዋል
Ababu Teklemariam Tiruneh
ፎቶ ከሦስት አመት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በማላዊ ብላንታዬር ላይ ግብፅን በሙሉ የጫወታ ብልጫ ሁለት ለባዶ ባሸነፉበት ጫወታ Walyas fan club
05/09/2025
መልካም እድል ድል ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ
14/03/2025
እንኳን ደስ አለን
አወከር ነስር ለእረጅም ጌዜ አጋጥማት ከነበረው ጉዳት አገግሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ዋልያዎቹን ተቀላቀለ
አወከር ነስር ከቤሔራዊ ቡድናችን ከዋልያዎቹ ጋር በሚኖርህ ቆይታ መልካም ያማረ ጥሩ የሆነ የስኬትን ጊዜ እንዲሆንልህ እንመኛለ !!!!!
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዋልያዎቹ ከወዲው መልካም እድልን ድልን ስኬት እንመኛለን !!!!!!!
02/08/2024
ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ አግኝታለች!
| የፓሪሱ ኦሎምፒክስ 10,000 ሜትር ፍፃሜ በወንዶች ተካሂዷል።
እንኳን ደስ አለን፣ ደስስስስ አላችሁ❗️በ10ሺ ሜትር ወንዶች ኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያ በበርሁ አረጋዊ አገኘች
06/06/2024
የዓለም ዋንጫ ማጣርያ 3ኛ የምድብ ጨዋታ ውጤት ሙሉ 90 ደቂቃ ተጠናቀቀ ዋልያዎቹ ከሜዳቸው ውጪ ነጥብ ተጋርተዋል በጨዋታው ዋልያዎቹ ባሳዩት ብቃት ተደስተናል !!!
🇬🇼 ጊኒ ቢሳው 0-0 ኢትዮጵያ 🇪🇹
06/06/2024
የጨዋታ ቀን !
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሦስተኛ የምድብ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 1፡00 ጊኒ ቢሳውን ይገጥማል።
- ሴፕቴምበር 24 ስታዲየም (ጊኒ ቢሳው) ላይ የሚደረገው ጨዋታን FIFA+ በቀጥታ ስርጭት ያስተላለፋል።
መልካም እድል ለዋልያዎቹ ድል ለኢትዮጵያ !
03/03/2024
ከፎቶ መሀደራችን ሮናልዲንሆ ከWalyas fan club የተበረከተለትን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ማልያ ይዞ ለማስታወሻ የተነሳው ፎቶ Walyas fan club ይለያል ለትውስታ አጋራናቹ
09/02/2024
Congratulations Mr.President ።🙏🙏🙏🙏
ኢትዮጵያ በካፍ ተወካይ አገኘች !
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ባደረገው ስብሰባ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራን የካፍ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ (executive committee) አባል አድርጎ መርጧል።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ኢሳያስ ጅራ የካፍ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው በመመረጣቸው የተሰማውን ደስታ እየገለፀ ስኬታማ የሥራ ጊዜን ይመኛል።
08/09/2023
🇪🇬 ግብፅ VS ኢትዮጵያ 🇪🇹
ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ዛሬ፡ከግብፅ ብሔራዊ ቡደን ጋር በካይሮ የመከላከያ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያከናውናሉ
ድል ለዋልያዎቹ !!!!!!