ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa

ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa

Share

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!

Photos from ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa's post 05/06/2026

የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምርያ ‎ከኢ/ር ወደ ዋ/ኢ/ር ማዕረግ ዕድገት ያገኙ ከፍተኛ መኮንኖችን አቀባበል አደረገ።

‎ሶዶ፣ ግንቦት 28/2018 ዓ.ም

ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምርያ ከኢ/ር ወደ ዋና ኢንስፔክተርነት ማዕረግ ሽግግር ላደረጉ መኮንኖች የ3ቱ ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዦችና አመራሮች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል አደረገ።

‎በመርሃ ግብር ላይ የተገኙት የከተማ ፖሊስ መምርያ አዛዥ
ኮ/ር ሀብታሙ አሰፋ እንደገለጹት ከኢ/ር ወደ ዋና ኢንስፔክተር ማዕረግ ዕድገት ላገኙ አባላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፋል።

አዛዡ አያይዘውም የፖሊስ ተቋሙ ህዝብና መንግስት የተጣለበትን አደራ በመወጣት የከተማውን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ደረጃ ማድረሱን ገልፀዋል።

ሰላም ለሁሉ መሠረት መሆኑን የጠቆሙት የፀጥታ መዋቅር የተደራጀና የተጠናከረ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

አመራሮች የሙያ ስነምግባራቸውን በመላበስ ሀገራዊ ኃላፊነት በተገቢው እንዲወጡም አመላክተዋል።
በአገልግሎታቸው የተሻሉና መስፈርቱን ያሟሉ 2 የፖሊስ አመራር ከኢ/ር ወደ
ዋ/ኢንስፔክተርነት ማደጋቸውን ገልጸዋል።

የሚጠብቁን ግዳጆችን በብቃት ለመወጣት የሙያ ስነምግባር በመላበስ በቁርጠኝነት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመጨረሻም የማዕረግ ዕድገት ያገኙ መኮንኖች፣ የተቋሙ አመራርና አባላት በጋራ የሻይ ቡና ፕሮግራም በማድረግ ተጠናቅቋል።
በጀግንነት መጠበቅ በሰባዓዊነት መጋልገል///

02/06/2026

7ተኛዉ አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በከተማችን ባሉ 3ቱም ክ/ከተማ አስተዳደር ያለ ምንም የጸጥታ ችግር በሠላም ተጠናቀቀ

ወላይታ ሶዶ ግንቦት 25/2018 ዓ/ም(ወሶከፖ)

በወላይታ ሶዶ ከተማ 7ተኛዉ አገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ችግር በሠላም መጠናቀቁን የላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ ገልጸዋል።

ምርጫዉ በከተማ አስተዳደር በ2 ምርጫ ክልልና በ166 ምርጫ ጣቢያ የነበረው ወደ ዞኑ ማዕከል ሙሉ በሙሉ ገብቷል።

ህዝቡ በሠላም የፈለገዉን ፓርቲ የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በመጠቀም ከጧቱ 12.00 እስከ ሌሊቱ 6.00 ሰዓት በሠላማዊ መንገድ ድምጹን ሲሰጥ ማምሸቱን የተናገሩት አዛዡ ህዝቡ በምርጫ ጣቢያ ላሳዩት ትዕግስት አመስግነዋል።

የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ፍጹም ሠላማዊ፣ነፃና በህዝብ ዘንድ ቁቡልነት ያለዉ እንዲሆን ፖሊስ የምርጫ ሥነ-ምግባር ህግን ባከበረ ሁኔታ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ ተገቢዉን ጥበቃ ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩት አዛዡ መላዉ የከታማ ህዝብ ከፖሊስ ጎን በመሆን ላደረገዉ ድጋፍ አመስግነዋል።

ፖሊስ የፀጥታ አካላትን በማስተባበር ቀንና ሌሊት የመራጩን ህዝብ እና የምርጫ ቁሳቁስ ደህንነት ለመጠበቅ ያሳየዉ ቁርጠኝነት የሚደነቅ እንደሆነ የተናገሩት አዛዡ ለሥራዉ ስኬት ከፖሊስ ጎን በመሆን ድጋፍ ያደረጉ አካላትን ሁሉ በከተማው ፖሊስ መምሪያና በራሱ ስም አመስግኗል።

በመጨረሻም በድምፅ አሰጣጥ ሂደት ያሳዩትን ትዕግስትና ጨዋነት ዉጤቱ ተቆጥሮ በይፋ እስከሚገለጽ ድረስ በተለመደዉ ጨዋነት በትዕግስት እንድጠባበቁ ጥሪ አቅርበዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብአዊነት ማገልገል!!

02/06/2026

7ተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል

ወላይታ ሶዶ፦ግንቦት 25/2018 ዓ.ም 7ተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም የምስጋና መልዕክት አጋርተዋል ።

7ተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ በወላይታ ሶዶ ከተማ ድምጽ በተሰጠባቸው ምርጫ ጣቢያ 166ቱም በሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ እንድሁም በህዝባችን ዘንድ ታአማንት በሞላበት መልክ በመጠናቀቁ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ በራሴና በከተማ አስተዳደር ስም እየገለጽኩ ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ሰላማዊና የአብሮነት ዋጋ ለከፈላችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናየን አቅርባለሁ ብለዋል ።

የምርጫ ድምጽ ውጤትን በተመለከተ በምርጫ ቦርድ በኩል ይፋ እስከሚደረግ በትዕግሥት መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዜጓቿ የተባበረ ክንድ እና ሀገር ወዳድነት ስሜት 7ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ በከተማችን ውስጥ ያለ አንዳች የፀጥታ ችግር እና ስጋት በሰላም ማጠናቀቅ መቻላችን የተጀመረው የለውጥ ጉዞ ምን ያህል ረጅም ርቀት መጓዝ እንደሚቻል አመላካች ነው ብለዋል።

በምርጫው ሂደት ተዋናይ የነበራችሁ የከተማችን ወጣቶች
፣ እህቶች ፣ወንድሞች፣እናቶች፣አባቶች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ፣ ማህበራት፣ምሁራን፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሎጂስቲክና ትራንስፖርት አስተባባሪዎች፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ፣የፀጥታ አካላት፣ የከተማው አመራሮች በምርጫው ስነ-ስርዓት ውጤታማነት ለነበራችሁ አስተዋፅኦ በራሴና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላቅ ያለ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል።

የከተማ ነዋሪዎች ብርድና ፀሐይ ሳይበግራቸው ከጧቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ እኩለ ለልት ድረስ በነቂስ ወጥቶ ለፈለጉት ፓርቲ ድምፅ በአግባቡ በመስጠት ሰለአሳያችሁት ትዕግሥትና ቆራጥነት በራሴና በከተማ አስተዳደር ስም ምስጋናዬ እጅግ የላቀ ነው ብለዋል።

ሰላም ወዳድ፣ ልማት ፈላጊና የሀገር ፍቅር የገባዉ መላዉ የከተማችን ህዝቦች፣ አባላትና ደጋፊዎች ምርጫው ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲየዊ እና በህዝብ ዘንዶ ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ምቹ ሁኔታ የፈጠሩትን ሁሉ ምስጋና ይገባል ብለዋል።

በአገራችን የዴሞክራሲ ስርዓት ለመገንባት ብሎም ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ 7ኛዉ አገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ ተጀምሮ በፍፁም ሰላሚዊነት እንዲጠናቀቅ የድርሻቸዉን የተወጡትን የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪዎች፣ አመራሮች፣ የመንግስት ሠራተኞች፣ የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በልባችን የታተመችዋን ይህቺን ታላቅ ሀገር አባቶቻችን ባወረሱን የጀግንነት ታሪክ መሰረት ጠብቀን ለመጪው ትውልድ እናስረክባለን።በዚህም ክብርና ኩራት ይሰማናል ብለዋል ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ!

ወ/ሮ እታገኝ ኃይለማርያም
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ
ግንቦት 25/2018 ዓ.ም

31/05/2026

''7ተኛዉ ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል'' - የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮ/ር ሀብታሙ አሰፋ።

ወላይታ ሶዶ ግንቦት 23/2018 ዓ.ም (ወሶከ)
ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በከተማ ፖሊስ መምሪያ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ገልጿል የከተማ ፖሊስ አዛዥ።

ምርጫዉ ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፖሊስ ከቅድመ ምርጫ ጀምሮ እሰከ ድህረ ምርጫ ድረስ በከተማው ሥር ባሉት 3 ክ/ከተማ አስተዳደር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በከተማችን ባሉት በ2 ምርጫ ክልልና በ166 ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ሂደት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ የፀጥታ መዋቅር መላው ህዝብን ፣ ተፎካካሪ ፖርቲን ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎችን ፣ የምርጫ ቁሳቁስ ፣ የምርጫ ጣቢያ ፣ የዕጩ ተወዳዳሪዎችን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ መጠበቅ እንዲሁም መራጩ ህዝብ ወጥተው መርጦ በሠላም እንድገባ የማድረግ ሥራ በጥብቅ ድስፕሊን መሠራት እንዳለበት አንስተዋል ።

7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሠላም እንዲጠናቀቅ በከተማ ደረጃ ኮማንድ ፖስት ተቋቋመው ሥራ መጀመሩን ገልጿል ።

በእያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያ የምርጫ ቁሳቁስ የማድረስ ሥራ በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን ያነሱት አዛዥ በእስካሁኑ ሂደት ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር አለመኖሩን ተናግረዋል።

ፖሊስ የምርጫ ሂደቱን የሚያደናቅፉ ሠላማዊ ሆኖ እንዳይጠናቀቅ ለማወክ የሚፈልጉ ጸረ ሠላም ኃይሎች ካጋጠሙ በመከታተል አስፈላጊዉን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
ፖሊስ የምርጫ አስፈፃሚዎችን፣ መራጮች እና የምርጫ ቁሳቁስ ደህንነት በመጠበቅ በከተማ የሚገኙ ከ166 በላይ ምርጫ ጣቢያዎች ሠላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቅ ኮማንድ ፖስት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል ።

ኮማንድ ፖስቱ ምርጫው ተጠናቆ ውጤት ይፋ እስኪሚደረግ ድረስ ሥራውን በተቀናጀ መልኩ እንደሚያከናውን ጠቁመዋል።

መላው ሠላም ወዳድ የከተማችን ህዝብም በሙሉ በፀጥታ መዋቅር ጎን በመቆም ትብብርና እገዛ እንዲያደርጉ ጥርን አስተላልፏል ።

ዘገባው የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ነው።
በጀግንነት መጠበቅ በሰባዓዊነት ማገልገል////

30/05/2026

''ምርጫው በሠላም እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል'' - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው።

ወላይታ ሶዶ ግንቦት 22/2018 ዓ.ም (ደኢፖኮ) ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው ገለጹ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው፥ ፖሊስ ከቅድመ ምርጫ ወቅት ጀምሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ክልሉ ለማደግ የሚተጉ ሕዝቦች ያሉበት ሰላማዊ ክልል መሆኑን አንስተው፥ ሂደቱ ፍጹም ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር እየተንቀሳቀሱ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎች የመንግሥት ሥልጣንን ለመያዝ በሚያደርጉት ሠላማዊ ትግል ከቅስቀሳ ወቅት ጀምሮ የሕዝቡን መብት ባከበረ መልኩ እንዲንቀሳቀሱ ሲደረግ መቆየቱን አንስተዋል።

ለምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ቁሳቁስ የማድረስ ሥራ እየተከናወነ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ በእስካሁኑ ሂደት ምንም ዓይነት ችግር አለማጋጠሙን ገልፀዋል።

ፓሊስ ምርጫውን ሠላማዊ ሆኖ እንዳይጠናቀቅ የሚንቀሳቀሱ ጸረ ሠላም ኃይሎችን በመከታተል እርምጃ መውሰድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን ገልፀው፤ ከአድማ ብተና ሠራዊት ጀምሮ በየደረጃው ያሉ አባላት ዝግጁ መሆናቸውን አመላክተዋል።

ከዚህም ባለፈ የፌደራል መንግሥት የሚያስተዳድራቸው ክልሉን አቋርጠው የሚያልፉ መንገዶችን በመጠበቅ ሠላማዊ ሆነው እንዲዘልቁ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ፖሊስ የምርጫ አስፈፃሚዎችን፣ መራጮች እና የምርጫ ቁሳቁስ ደህንነት በመጠበቅ በክልሉ የሚገኙ ከሦስት ሺህ በላይ ምርጫ ጣቢያዎች ሠላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቅ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ግብረ-ኃይሉ ምርጫው ተጠናቆ ውጤት ይፋ እስኪደረግ ሥራውን በተቀናጀ መልኩ እንደሚያከናውን ጠቁመዋል።

ዘገባው የደቡብ ሬድዮና ቴሌቭዥን ነው።

Photos from ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa's post 28/05/2026

የወላይታ ሶዶ ከተማ ፀጥታ ምክር ቤት በወቅታዊ ከተማዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ የምክክር መድረክ አካሄደ።

በወላይታ ሶዶ ግንቦት 20/09/2018/ ዓ/ም
በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተማማኝ ሰላም እና ፀጥታ የሰፈነው የፀጥታው ምክር ቤት ፣ በፖሊስ እና ህብረተሰቡ አንድነት መሆኑን ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማሪያም ገለፁ።

ክብርት ከንቲባዋ ባደረጉት ውይይት ፖሊስ እና የፀጥታ ሀይሎች በቅንጅት ፣ በቁርጠኝነት እና ከህብረተሰቡ ጋር በመስራት ያስመዘገቡትን ስኬት አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

ለፖሊስ ሰራዊቱ እና አጠቃላይ የፀጥታ መዋቅር ያላቸውን ልዩ አክብሮት የገለፁት ክብርት ከንቲባዋ ወ/ሮ እታገኝ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

ከንቲባው አክለውም የምርጫው ሂደት በሰላምና በሕግ የተደገፈ ሁኔታ እንዲፈፀም የፖሊስ አባላት ያላቸው ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል።

የፖሊስ አባላት በምርጫ ሂደት ውስጥ ፖለቲካዊ ወገንተኝነት ሳያሳዩ በሙያዊ ሥነ-ምግባር መሰረት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ በትኩረት እንዲሰሩም መክረዋል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ የሚከናወኑ መንግስታዊ እና ህዝባዊ ሁነቶች በድምቀት እና በሰላም እንዲፈፀሙ የፀጥታ መዋቅሩ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ከንቲባዋ አስረድተዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ በበኩላቸው በየወቅቱ ገንቢ የውይይት መድረኮችን በማመቻቸት ቅንጅታዊ አሰራርን መዘርጋት እንደተቻለ ገልፀዋል።

ወቅቱ የሚጠይቀውን ንቃት እና ብቃት በመላበስ ህብረተሰቡን በጀግንነት መጠበቅ እና በሰብአዊነት ማገልገል እንደሚገባ አዛዡ ኮማንደር ሀብታሙ አስገንዝበዋል።

የፖሊስ አመራር እና አባላት ከመላው ህብረተሰቡ ጋር ጥብቅ ትስስር መፍጠር እንደሚገባም የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ መክረዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ስላም እና ፀጥታ አስተዳደር መምሪያ ሀላፊ አቶ ካሳሁን በሊላ በየደረጃው ከሚገኙ የፀጥታ መዋቅር ጋር በመናበብ በመሰራቱ ተፈላጊውን ውጤት እና ሰላምን ማረጋገጥ እንደተቻለ ገልፀዋል።

አቶ ካሳሁን የፀጥታ ጉዳይ ቀኑን እና አመቱን ሙሉ ያለማቋረጥ የሚሰራ መሆኑን ተንትነዋል።

በወቅታዊ የሰላም እና ፀጥታ ስራዎች ላይ አትኩሮት በመስጠት የተደረገው ውይይት የነዳጅ ፣ የህብረተሰብ ተሳትፎ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ አፅንኦት ተሰጥቶበታል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው የፊት አመራሮች እና ነዋሪዎች የሚያደርጉት ያልተቆጠበ ድጋፍ በቀጣይም ለውጤታማነት እንደሚያበቃቸው ተናግረዋል።

በጀግንነት መጠበቅ በሰባዓዋነት ማገልገል////

የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምርያ

Photos from ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa's post 19/05/2026

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በወቅታዊ ትራፊክ ሥራ ዙርያ ውይይት አካህዷል

(የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፤ ግንቦት 10/2018ዓ.ም)

የዎላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ የትራፊክ ስራ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት ማካሄዱን የመምሪያው አዛዥ ኮ/ር ሀብታሙ አሰፋ አስታውቀዋል።በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የ3ቱ ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዦች፣ የትራፊክ ማስተባበርያ ኃላፍዎች፣ ማ/አ/ወ/መ/ማስ/ርያ ኃላፊዎች፣ ቡድን መሪዎችና የመምርያ ማኔጅመንት ተገኙቷሉ። በመድረኩ ላይ በዋናነት የተነሳው የነዳጅ እጥረትን ምክንያት በማድረግ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ያለገባብ የታርፍ ጭማረ በምያደርጉ አሽ/ሪዎች ላይ አስተማርና ተገቢ እርምጃ እድወሰድ የመምርያው አዛዥ ለትራፍክ ተቆጣጣርዎች ትዕዛዝ አስተላልፏል።በሌላ በኩል ነዳጅ ማደያ አከባቢ ያለውን ህገወጥነትና ከፕሮግራም ውጭና ከሰልፍ ውጭ በምመጡ ተሽከርካሪዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንድወስዱ ለ3ቱም ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዦ ኮ/ር ሀብታሙ አሰፋ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

በተጨማር በአንዳንድ ክ/ከተማዎች ከአደጋ መከላከል ጋር ተያይዞ ክፍተት መኖራቸውን ያነሱት አዛዡ ተቋሙ በሚቀጥሉት ጊዜያት ክፍተቶቹን ሸፍነው እንድሰሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

አደጋዎችን ከመቀነስ ረገድ በየትምህርት ቤቶች እየተሰጡ ያሉት የግንዛቤ ስራዎች በየመንገዱ ዳር መሰጠት እንደሚገቡ አሳስበዋል።የ3ቱም ክ/ከተማ ፖሊስ አዛዦች በቅ ቁጥጥር ፣ ክትትልና ድጋፍ እንደምያደርጉ በማለት ሐሳብና አስታያየት ሰጥቷሉ።

በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!

Photos from ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa's post 15/05/2026

የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ ክንውን ዙሪያ ምክክር መድረክ አካሄደ።

በዚህ መድረክ ላይ የወላይታ ሶዶ ከተማ የመንግስት ረዳት ተጠሪ የሆኑት አቶ መስፍን መድህን እንደተናገሩት፣ በከተማው ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ ለማስፈን የፖሊስ ተቋም፣ የመንግስት መዋቅሮች እና ህብረተሰቡ በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል።

የፖሊስ ተቋም ከህብረተሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ እየተሰራ ያለው ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በተለይም የገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤቱ ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን በመሰብሰብ ለፖሊስ አገልግሎት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

በመድረኩ ላይ የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ እንደተናገሩት፣ የፖሊስ አገልግሎትን ከቀጠና እስከ መመሪያ በማጠናከር ለህብረተሰቡ ተደራሽ እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ህብረተሰቡም ከፖሊስ ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር በከተማው ዘላቂ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረግ እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ካሳሁን በሊላ በበኩላቸው እንደገለፁት፣ በከተማው የሰላምና ፀጥታ ሥራዎች የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

የፖሊስ እና የህብረተሰብ ቅንጅታዊ ሥራ በከተማው የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑንም አስረድተዋል።

ዘገባው የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስሕዝብ ጉንኝነት ነው።

Photos from ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa's post 15/05/2026

የተለያዩ ህገ ወጥ ኮንትሮባንዶች መያዛቸውን የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
ሶዶ ከተማ ግንቦት 07/2018 ዓ/ም
ህገ ወጥ ኮንትሮባንድ የሀገር እድገትን ወደ ኋላ የሚያስቀር፣የሀገርን ኢኮኖሚን የምጎዳና የሚያቀጭጭ መሆኑ ይታወቃል።
የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ሀብታሙ አሰፋ እንደገለጹት ህገ ወጥ ኮንትሮባንዱ ሊያዝ የቻለው ከአ/ምንጭ መስመር ወደ ሶዶ ስገባ የሠለዳ ቁጥር 2/አአB26847 የሆነ የቤት መክና ከህብረተሰቡ ለፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሠረት በማደረግ ፍተሻ ስደረግ በቁጥር 8 እስር ቦንዳ ልያዝ የቻለ መሆኑን ገልጸዋል።
ኮንትሮባንድ ከመሃል ክ/ከተማ ዋዱ ቀበለ ከ1 ተጠርጣር ከነመክና የተያዘ መሆኑንም የገለጹት ኃላፊው እነዚህም እቃዎች ሙሉ በሙሉ የተለያዩ አልባሳት መሆኑንም ገልጿል።አዛዡ ጥቆማ ያደረሰውን የሕብረተሰብ ክፍል አምስገነው አሁንም ድጋፉ እንድቀጥልና ኮንቶሮባንድ ንግድ ሕጋዊ ነገዴን አቅም የምያሳጣ መሆኑንም ገልጿል።
ህገ ወጥ ኮንትሮባንድን በጋራ እንከላከል!!

#የሶዶ ከተማ ፖሊስ መምሪያ

Photos from ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ /Wolaytta sooddo ambbaa xaace kaaletaa's post 13/05/2026

ዜና ችሎት

ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቴሌኮሚኒኬሽን አውታር ላይ የስርቆት ወንጀል የፈጸሙ 3 ግለሰቦች እያንዳዳቸው በ5 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እሥራት እንድቀጡ ተወሰነ።

05/09/2018 ዓ.ም: ወላይታ ሶዶ:

በቴሌኮሚኒኬሽን አውታር ላይ የስርቆት ወንጀል የፈጸሙ 3 ግለሰቦች እያንዳዳቸው በ5 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እሥራት እንድቀጡ የተወሰነባቸው መሆኑን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፍትህ መምሪያ አስታወቀ።

ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች 1ኛ ተመስገን ኢያሱ 2ኛ መንግሥቱ ማርኬ እና 3ኛ አማኑኤል ቡሾ የተባሉ ስሆን በቀን 14/04/2018 ዓ.ም ዕለተ ማክሰኞ ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት ገደማ በወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ህብረት ቀበሌ ልደታ ማሪያም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ንብረትነቱ የኢትዮ ቴሌኮም የሆነና በመሬት ውስጥ ተዘርግቶ የነበረ ኮፔር ኬብል (ባለ 600) ዋጋው 755,683.34 የወሰዱ ስሆን ሌላ በብረት ክዳን የተሸፈነ ባለ 600 መስመር በፔሮ ብረት ፈልቅቀው በማውጣት በመጋዝ ቆርጠው በማውጣት የ3ኛ ተከሳሽ በግል ንብረቱ በሆነውና ኮድ 1-24256 በሆነ ባለ ሶስት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪ ጭኖ እየጠበቀ ሌሎች ስያዙ ሮጦ ካመለጠበት በፖሊስ ክትትል የተያዘ መሆኑን የወላይታ ሶዶ ከተማ ዐቃቤ ህግ መዝገብ ያስረዳል።

ጉዳዩን ስያከራክር የቆየው የሶዶ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማጣራት ተከሳሾች የተከሰሰበትን የወንጀል ድርጊት ፈጽሟል ስል የጥፋተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተከትሎ ተከሳሽን ያስተምራል ሌሎችም ከመሰል የወንጀል ዲርጊት እንድቆጠቡ የሚያደርግ ነው ስል ተከሳሽ በ5 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እሥራት እንድቀጣ ወስኗል።

የከተማው ፍትህ መምሪያ ህዝባዊ አገልግሎት የሚሰጡ መሠረተ ልማቶች በውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ወጪ የሚዘረጉ በመሆናቸው ህብረተሰቡ በጋራ ጥበቃ እንድያደርግ ጉዳት ስደርስባቸውም ለፍትህ የማቅረብ ሂደትን እንድደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa