ነፃነት ለሀበሻ ሴቶች

ነፃነት ለሀበሻ ሴቶች

Share

Advertize the Business and awareness for ETHIOPIAN!!!

25/08/2017

She is a daydreamer & a night thinker. She is a doer. She sees an opportunity in every problem she faces. Her curious mind is stretched by all the experiences life throws her way & what she makes out of them. She is sunshine mixed with rain, creating a beautiful rainbow. There is no lie in what she does.

05/07/2017

እድሉን ለሌላ
ስብኃት ገ/እግዚአብሄር
************************
የሰለጠኑ ሰዎች ልክ የመሆንን እድልን ለሌሎች በመስጠት ያምናሉ፡፡ በተቻለ መጠን ያ ሌላው ሰው ልክ ሊሆን ይችላል ይላሉ፡፡ እስቲ ለዚህ አንዳንድ ምሳሌዎች እንስጣችሁ፤
አንድ፡
ጓደኛህ የሆነው አቶ እንትና ስምህን እያጠፋህ መሆኑን አንድ ሰው ሲያወራልህ፡ ለራስህ አይቻልም ባይባልም ጓደኛዬ እንደዚህ የሚያደርግ አይመስለኝም፤ በማለት ትጠራጠራለህ፤ ነገሩም በዚህ ያቆማል፡፡
ሁለት፡
አንድ ጓደኛዬ ደግሞ በውን ያጋጠመውን ልንገራችሁ፣ የ8ኛ ክፍል የሆነች የ14 ዓመት ልጁ ከትምህርት ቤቷ እንደሚፈልጉት ትነግረዋለች፡፡ ወደ ትምህርት ቤቷ እየሄዱ እያለ፤ ለምን እንደፈለጉኝ ንገሪኝ? ልጅ ስለሆንሽ ያጠፋሽው ጥፋትም ካለ ምንም አደል ይላታል::
ልጆች ካንዷ ልጅ ላይ 10 ብር ሰረቁና እኔ ላይ አላከኩብኝ:: እውነቱን ንገሪኝ? ብሩን የወሰድሽው አንቺ ነሽ? አደለሁም፡፡ አምንሻለሁ! አላት አባቷ ሆኖም ገንዘቡን ሰርቃ ሊሆን ይችላል፡፡ ዳይሬክተሩ ቢሮ ገብተው እንደተቀመጡ፡ ገንዘቡን የሰረቀችው ልጅዎ ነች! ሲል ዳይሬክተሩ ተናገረ፡፡ ብያኔውን እቀበላለሁ 10 ብሩንም ለመክፈል ዝግጁ ነኝ፡፡ ነገር ግን ልጄን በደንብ የማውቃት መሆኑን ልገልፅልዎት እፈልጋለሁ፡፡ በምንም አይነት አትሰርቅም አለ፡፡ በዚሁ አቆሙና ልጅቷ ወደ ክፍሏ ገባች፡፡ በዚህ ድርጊትም አባትየው ልጁን እውነቷን ሊሆን ይችላል በማለቱ ጠቅማቷል፡፡
እስቲ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥቂት እናስብበት፡ ልጅቷ 10 ብር ሰርቃለች እንበል ከዛ በኋላ ግን ከሰው የተለየች ፍጡር ካልሆነች በስተቀር ሁለተኛ አትሰርቅም፡፡ ምክንያቱም አባቷ እምነቱን ጥሎባታል፡፡ እንዲሁም ሁሉን ማድረግ በሚችሉ ዳይሬክተር ፊት የጣለባትን እምነት እንዴት አድርጋ ታጎድላለች? ልክ የመሆንን እድል ለሌላው መስጠት በአብዛኛው ብዙ ጥቅም አለው፡፡
******************** **************************** ******************
ሌላ፡
እውነቱን ይሆናል ከሚለው አስተሳሰብ ጋር ትንሽ እነጓዝ፡
ሴትዮዋ እባሏ ኮት ላይ የከንፈር ቀለም ታያለች፤ እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ በአብዛኛው ለባልና ሚስት ግጭት ምክንያት ይሆናል፡ ይሄ የከንፈር ቀለም የኔ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ! ትለዋለች በቁጣ ጣቷን ወደ ቀለሙ ቀስራ፡፡ በእፍረት ያቀረቅራል፤ ወዳጅ የለኝም ብለህ በል ካድ ካድ በል እንጂ ካድ…! የለኝምና!... በመጥፎ ድርጊትህ ላይ ስድብ አታክልበት! ሌላው ቢቀር እውነቱን አምነህ ተቀበል!... አብደሻል!
ስልጡኗ እመቤት የከንፈር ቀለሙን መጀመሪያ እንዳየች ልትቀና ትችላለች፡፡ ግን ቆየት ብላ ስታስብ መጠራጠር ትጀምራለች፡፡ ኮቱን የከንፈር ቀለም ስለነካው የግድ ሌላ ወዳጅ ይዟል ማለት አደለማ፡፡ ቀለሙ በሆነ አጋጣሚ ሊነካው ይችላል፡፡ የባሌን ጠባይ ደግሞ በደንብ አውቀዋለሁ፡፡ በኔ ላይ ወዳጅ አይዝም፣ ቢያደርገው እንኳን ይጠነቀቃል፣ የወዳጁን የከንፈር ቀለም ተለቅልቆ ወደቤቱ አይመጣም፡፡ እውነቱን ሊሆን ይችላል ብላ ትተወዋለች፡፡ ነገሩ በዚህ ያልቃል ትዳሩም ይተርፋል፡፡
********************************* ************************ ****
ሌላ፡
በሰለጠኑት ሃገሮች መንግስት ለዜጋው እውነቱን ይሆናል የሚል እዳ ይሰጠዋል፡፡ በህግ ፊት የተወነጀለ ሰው በማስረጃ እስካልተረጋገጠበት ድረስ ከወንጀሉ ነፃ ነው፡፡ በህግ ፊት አንድ ሰው አለ ሃጥያቱ ከሚቀጣ ማስረጃ በመጣታቱ ምክንያ ዘጠኝ ወንጀለኞች ነፃ ቢለቀቁ ይመርጣል፡፡
*************************** **************** ******************
ሌላ፡
በእለት ተእለት ኑሯችን ሌላው ሰው እውነቱን ይሆናል ብሎ እድል መስጠት ጭንቀታችንንና ብስጭታችንን ያቀልልናል፡፡ ለአንድ ሰው አንድ መቶ ብር ታበድረውና እመልስልሃለሁ ባለው ቀን ላይመልስልህ ይችላል፤ገንዘቡ መቼም ቢሆን ላይመለስልህ ይችል ይሆናል፡፡ ቀዝቀዝ ብለህ ስታስበው ግን ሰውዬው ብሩን ያልመለሰው የተበደረውን የማይመልስ ልማደኛ ባለጌ ሆኖ ሳይሆን የጠበቀውን ገንዘብ ባለማግኘቱ ሊሆን ይችላል ትልና ልክ የመሆንን እድል ትሰጠዋለህ፡፡
የቀጠርከው ሰው በሰዓቱ ባለመምጣቱ መቀየም የለብህም፤ አንተ በሱ ቦታ ብትሆን ኖሮ በሰአቱ ላትደርስ ትችል ነበረና፡፡ ህይወት ያወጣንላትን ፕሮግራም ተከትላ አደለም የምትጓዘው፤ ሌላ ቀን ተገናኝታችሁ የቀረበትን ምክንያት ሲነግርህም ያልሆነ የማይረባ ምክንያት እየሰጠኝ ነው ብለህ ማሰብ የለብህም፤ የሚልህን ሁሉ ለማመን ሞክር፤ እውነቱን እየነገረህም ሊሆን ይችላል፤ ባይሆንስ ምን ጉዳት ደረሰብህ? ተወው ልክ የመሆንን እድል ስጠው፡፡

05/07/2017

በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ።
:
" በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል።
:
ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!"
አንድ ነገር ልንገራችሁ!
:
በህይወትሁ ማንንም አትውቀሱ
ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃችሀል
መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችሀል
ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችሀል
ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችሀል።
(ጋሽ ስብሃት ገብረእግዚአብሄር)

18/12/2015

GIVE A WOMAN A POWER TOOL AND SHE CAN CHANGE THE WORLD!!!

09/09/2015

I’m stronger because I had to be.
I’m smarter because of my mistakes.
I’m happier because I have known sadness and
I’m wiser because I’ve learned from my past.

18/08/2015

A Negative Mind wills Never Give You a Positive Life!
//Real Talk//

Photos 13/09/2013
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

Addis Ababa