22/12/2023
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይቅርታ ጠይቋል!
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በመሰረዙና ይቅርታ በመጠየቁ ቀጣይ ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመረጠው ህዝብ በታማኝነት እና በብቃት ለማገልገል ካለው ጽኑ ፍላጎት በመነሳት በመንግስት መስሪያ ቤቶች የሚሰጡ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻልና የተገልጋዩን ህብረተሰብ እንግልት ለመቀነስ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኑ ይታወቃል::
የከተማ አስተዳደሩ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተና ለአመራሮች ፣ ለባለሙያዎች እና ለሰራተኞች ፈተና እንዲሰጡ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ኃላፊነት መስጠቱ ይታወሳል::
ሆኖም ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው ፈተና በቴክኒክ ችግር ምክንያት በመሰረዙና ይቅርታ በመጠየቁ ቀጣይ ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል::

12/12/2023