29/12/2025
አዲስ አበባ ህብረተሰብ ተሳትፎ ልዩ ወረዳ - ብልፅግና
የሀሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልፅግና!
29/12/2025
28/12/2025
Human centeredness : the true foundation of our prosperity!
Student Nutrition: A transformative journey shaping a successful generation, rewriting the nation’s future, and laying the groundwork for quality education.
#እማኝ #የተማሪዎችምገባ
The World Deplomatic Hub!
Addis Ababa: The City with Bold Growth!
11/02/2025
ቃልን በተግባር የመተርጎም ባህላችንን በማዳበር የፓርቲያችንን አቅጣጫዎች ተፈፃሚ እናደርጋለን !
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት የልዕልና የብልፅግና ህብረት ፤ እና የምክር ቤት የብልፅግና ፓርቲ ህብረት አባላት በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችንና ውሳኔዎችን የጋራ በማድረግ ለተፈፃሚነታቸው እንደሚተጉ አረጋግጠዋል።
በመጀመርያው ጉባኤ የተቀመጡ እና በተግባር ተፈፃሚነታቸው የተረጋገጡ አቅጣጫዎች እንደ ሀገር ለተያዘው ስኬታማ የብልፅግና ጉዞ መሠረት የጣሉ እና አቅም የሆኑ እንደነበሩ ያነሱት የአዲስ አበባ ም/ቤት የብልፅግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ ማሾ ኦላና ለጠንካራ ፓርቲ ግንባታው እንደ አባል በየተቋማቱ ለተሞክሮ የሚሆኑ ተግባራትን በማበራከት ግንባር ቀደምነትን በተግባር በማረጋገጥ ከቃል እስከ ባህል በሚል በተካሄደው ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አስፍቶ መተግበር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት የልዕልና የብልፅግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ ዳዊት ምንዳዬ በበኩላቸው በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የፓርቲያችን አቅጣጫዎች ከጉባዔ እስከ ጉባዔ የርብርብ ማዕከል በመሆናቸው በአመራሩ እና በአባላት ዘንድ መስረፅና መዋሀድ ይገባቸዋል ብለዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት የልዕልና የብልፅግና ህብረት ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጀማል መሀመድ በሁለተኛው የብልፅግና ፓርቲ ጉባዔ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ለአባላት ያቀረቡ ሲሆን ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት የተጀማመሩ አበረታች ተግባራትን አጠናክሮ ማስቀጠል አንዱ የትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ መረባረብ እንደሚገባ አስረድተዋል።
የከተማችን እና የሀገራችን ፈጣን እድገት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውጤታማነትን ባህል ማድረግ ይገባል ያሉት አቶ ጀማል አመራሩ እና አባላት እንዲሁም ሁሉም ዜጋ እንቅስቃሴዎቻቸው ሁሉ ለሰላም ግንባታ አወንታዊ ሚና የሚጫዎቱ መሆናቸውን እርግጠኛ መሆን እንደሚገባቸውም ጠቅሰዋል።
የመጀመሪያውን ጉባዔ አፈፃፀሞች ከመገምገም ባሻገር የፓርቲያችንን ቀጣይ አቅጣጫዎች እንደ ብልፅግና ቤተሰብ ጭምር የጋራ መደረጉ ተቀናጅቶና ተናብቦ አልቆ ለመፈፀም አጋዥ መሆኑ በውይይቱ ላይ ተንፀባርቋል።
የብልፅግና ቤተሰብ እና የብልፅግና ህብረት የሚል አዲስ ስያሜ ያገኙት የፓርቲው መዋቅሮችም ለህብረ ብሔራዊ አብሮነትና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታው ትልቅ አቅም እንዳላቸው በመረዳት ለጠንካራ ተቋም ግንባታው የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡም የውይይቱ ተሳታፊዎች አረጋግጠዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት
03/02/2025
ቀን 26/05/2017 ዓ.ም
የእምርታ ህዋስ የስድስት ወር ሪፖርት ቀረበ
1.የእምርታ ህዋስ የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በአቶ ምንተስኖት ተስፋየ ለአባላቱ አቀርቧል።
2.ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን በመታገል የአገልግሎት አሰጣጣችንን የማሻሻል እመርታ በሚል ርዕስ ወ/ሮ አበበች በስር እና ወይንሸት ካሳዬ በጋራ የቀረበ ሲሆን በቀረቡት በሁለትም ሰነዶች ውይይት ውይይት ተደርጓል።
በዚህ መሰረት የህዋሳችን የእምርታ የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም በጥሩ ደረጃ ላይ መሆኑ በአስተያየት ተመላክቷል።በቀሪ ወራት ቢጨመሩ የሚል ሀሳቦችም ቀርበው የተግባባን ሲሆን የአባላት እና የአመራር ተሳትፎን በተመለከተ በከፍተኛ መሻሻል ላይ መሆኑ ተጠቅሷል።
በተመሳሳይ ከመሰረታዊ ድርጅት በተሰጠን እርዕስ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን በሚመለከት ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል ሁሉም አባልና አመራር ከኔ ምን ይጠበቃል የሚለውን ውስዶ ከፍተኛ ተግል ለማድረግ ቁርጠኝነት አሳይተዋል።
ለተሻለ ፖርቲ ግንባታ እምርታ ግንባር ቀደም ሁና ሚናዋን ትወጣለ!!!!!!
እናመሰግናለን!!!
02/02/2025
እንኳን ደስ ያላችሁ!!
መልካም የስራ ዘመን ይሁንላችሁ።
27/01/2025
እየሰራን ያለነው ስራ ገና ከጅምሩ በአለም ተወዳዳሪ እያደረገን ነው።
ፈጣሪ የተመሰገነ ይሁን
Hojiin hojjachaa jirru jalqabumaa kaasee addunyaa irratti dorgomaa nu taasisaa jira.
Waaqni kan galateeffame haata'u
ያየነውን ለማሳየት እንተጋለን!!
14/01/2025
" ከጉባኤ እስከ ጉባኤ በሚቀመጡ አቅጣጫዎች ታሪክ የማይሽረው ፣ ለትውልድ የሚሸጋገር አሻራችንን ለማሳረፍ እንዘጋጅ ! " አቶ ሞገስ ባልቻ
በብብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ ቤት የህብረተሰብ ተሳትፎ ልዩ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ምክትል ኃላፊ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ ፣በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብርሃም ታደሰ ፣ የልዩ ወረዳው ሰብሳቢ አቶ የኋላሸት በቀለ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም አባላት በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ከህዋስ ጀምሮ ያሉ ውይይቶች፣ ኮንፈረንሶች እና መደበኛ ጉባኤዎች በፓርቲያችን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እንደሚካሄዱ አውስተዋል።
ብልፅግና ፓርቲ የሀገራችንን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ስብራቶች ለመጠገን እና የማህበራዊ እሴቶችን ለማጎልበት አሻጋሪ ፕሮግራሞችን ቀርፆ በመተግበር በየዘርፉ ተጨባጭ ድሎችን ማስመዝገቡን አቶ ሞገስ አብራርተዋል።
በከተማችንም የህዝባችንን ህብረ ብሔራዊ አብሮነት በማጠናከር ፣ በጠንካራ የስራ ባህል ፈጣን ልማት በማስመዝገብ እና በሌሎችም እመርታዊ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆኑን ያስረዱት ኃላፊው ከጉባኤ እስከ ጉባኤ በሚቀመጡ አቅጣጫዎች ታሪክ የማይሽረው ፣ ለትውልድ የሚሸጋገር አሻራችንን ለማሳረፍ እንዘጋጅ የሚል መልክታቸውንም አስተላልፈዋል።
የህብረተሰብ ተሳትፎ ልዩ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ የኋላሸት በቀለ በበኩላቸው ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የተመሰረተው ብልፅግና ፓርቲ አካታች የሆነ ስርዓት በመዘርጋት የሀገራችንን ታሪካዊ ስብራቶች እየጠገነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
በከተማችን እየተመዘገቡ የሚገኙ ስኬቶችም የፓርቲያችን የጉባኤ አቅጣጫ በአግባቡ መተርጎማቸውን አመላካች ናቸው ያሉት አቶ የኋላሸት የቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስም ጥንካሬዎችን ለማላቅ ፣ ጉድለቶችን ደግሞ ፈጥኖ ለማረም ተግባቦት የሚያዝበት መሆኑን አስገንዝበዋል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ /ቤት የልዩ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዳርዳር ብርሀኑ ከልዩ ወረዳው ኮንፈረንስ ቀደም ብለው የተደረጉ የመሰረታዊ ድርጅት ኮንፈረንሶችን አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ከአባላት በተጨማሪ ከፍተኛ አመራሮችም በተገኙበት ፣ የውስጠ ድርጅት ዴሞክራሲን በሚያጠናክር መልኩ ፣ የጋራ ተግባቦት በሚፈጥር አግባብ በድምቀት መካሄዳቸውን ገልፀዋል።
አባላት ከቃል እስከ ባህል በሚል ርዕስ በቀረበው ሀሳብ ላይ በሳል ውይይት ማድረጋቸው የተጠቆመ ሲሆን የከተማችን ፈጣን እድገት በአባላት ላይ ከፍ ያለ ተነሳሽነት መፍጠሩንም አቶ ዳርዳር ባቀረቡት ሪፖርት ተመላክቷል።
በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ፣ በኢንስፔክሽን እና ስነ ምግባር ሪፖርት ላይ የተደረጉ ውይይቶችም ገንቢ ሀሳቦች የተነሱባቸው መሆኑም ተወስቷል።
የመተዳደሪያ ደንቡ በአግባቡ መተግበሩን ፣ የፓርቲ አስተሳሰብ ጥራት መኖሩን እንዲሁም የአባላትን መብቶች እና የፓርቲውን ገንዘብ በተመለከተ በልዩ ወረዳው ኢንስፔክሽን እና ስነ ምግባር ኮሚሽን የቀረበው ሪፖርትም በኮንፈረንሱ ላይ ቀርቧል።
በልዩ ወረዳው ኮንፈረንስ በከተማ ደረጃ ለሚካሄደው የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ቅድመ ጉባኤ ኮንፈረንስ የሚሳተፉ አመራሮችና አባላትም ነፃና ዴሞክራሲያዊ በሆነ ቀጥተኛ ምርጫ ተመርጠዋል።
በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የተጀመረው የልዩ ወረዳው ኮንፈረንስ በውብ ህብር ዝማሬዎች ፣ በብሔር ብሔረሰቦች ባህላዊ ውዝዋዜዎች እና በመሳሰሉት ተጨማሪ ድምቀት አግኝቷል።
ምንጭ:- በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ /ቤት
Click here to claim your Sponsored Listing.
