Lideta sub-city Prosperity party Branch Office

Lideta sub-city Prosperity party Branch Office

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lideta sub-city Prosperity party Branch Office, Political Party, Addis Ababa.

Photos from Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ's post 12/04/2026
12/04/2026

እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ !

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል በገዛ ፈቃዱ የሰውን ስጋ ለብሶ ከሀጢአት በስተቀር መልካሙን ሁሉ አከናውኗል።

እርስ በእርስ መተሳሰብን ፣ ትህትናን ፣ ሰላምን ፣ ከራስ ባለፈ ለሰዎች መኖርን ፣ መዋደድን ፣ ፍቅርን በአስተምሮው ብቻም ሳይሆን ኑሮ አሳይቷል።

የቱንም ያህል ችግር እና መከራ ቢመጣ ለዓላማ መፅናትን እስከ መስቀል በደረሰ ፍቅር አርአያ ሆኗል።

ትንሳኤ / ፋሲካ ከስቅለቱ በኋላ የሚከበር የደስታና የተስፋ በዓል ነው።

ከጨለማ በኋላ ብርሃን ፣ ከመውደቅ በኋላ መነሳት ፣ ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ ያበሰረበትን የትንሳኤውን በዓል ስናከብር ለተቸገሩ ወገኖቻችን አለኝታንታችንን በማሳየት የነገን ብሩህ ተስፋ በመፈንጠቅ ነው።

የከተማ አስተዳደናችን አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ በማድረግ ለነዋሪዎቿም ለጎብኝዎቿም ምቹ ያደረጋት የነዋሪዎችን ህይወት በዘላቂነት ለማሻሻል ከሚያደርገው ርብርብ ባሻገር ፣ የህዝባችንን የመረዳዳት ነባር እሴት ተቋማዊ ለማድረግ በሚደረገው ብርቱ ጥረት ነው።

በተለይም ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላትን ምክንያት በማድረግ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን እና ባለሀብቶችን በማስተባበር የሚከናወኑ የማዕድ ማጋራት ተግባራት እህትማማችነትን እና ወንድማማችነትን እያጠናከሩ ይገኛሉ።

የከተማችን ለውጥ የብዙዎችን የጉስቁልና እና የስጋት ህይወት በማስወገድ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ አስችሏል፤ አሁንም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ወገኖቻችንም የመለወጥ ተስፋን ፈንጥቋል።

እንደ ፓርቲም ሆነ እንደ መንግስት ሰው ተኮር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በማረጋገጥ የትንሳኤ በዓልን በተለመደው የመረዳዳት እሴት ማክበር እንደሚገባን መልዕክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን።

በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ልደታ ቅ/ፅ/ቤት

11/04/2026
10/04/2026

“እንደ አዲስ ልዩ ፕሮግራም “

ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር

ነገ ምሽት 3 ሰዓት ይጠብቁን!
የከንቲባ ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት


Photos from Lideta sub-city Prosperity party Branch Office's post 10/04/2026

!!

የምርጫ ምልክታችን "የስንዴ ነዶ" ነው!
"የስንዴ ነዶ"፦
• የመደመር፣
• የምርታማነት፣
• ከተረጂነት የመላቀቅ፣
• የተምሳሌትነት፣
• የልዕልና፣
• የሉዓላዊነት፣
• የበረከትና የብልፅግና ምልክት ነው።
ብልፅግናን ይምረጡ!

መንገዳችን መደመር!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ!
መዳረሻችን ሁለተናዊ ብልፅግና ነው!!




#እንሳታዉስዎ

Photos from Lideta sub-city Prosperity party Branch Office's post 10/04/2026

በልደታ ከፍለ ከተማ ለትንሣዔ በዓል የሚዉሉ ምርቶች በስፋት ቀርበዋል::
#ኑይሸምቱ
#እንሳታዉስዎ


#አድድሳባባ

Photos from Abiy Ahmed Ali's post 09/04/2026
Photos from Lideta sub-city Prosperity party Branch Office's post 09/04/2026

በአባሎቻችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ኢትዮጵያን ተምሳሌታዊ ሀገር እናደርጋለን!!!!

*****ክብርት ወ/ሮ ልዕልት ግደይ *******



በልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት በሁሉም ወረዳዎች በብልፅግና ሕብረት ደረጃ ሲካሄድ የቆየው የ2018 በጀት ዓመት የሶስተኛው ሩብ ዓመት ኮንፈረንስ በክፍለ ከተማ ደረጃ በደመቀ ሁኔታ ማጠቃለያ ኮንፈረንስ ተካሄደ።

ወ/ሮ ልዕልት ግደይ የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በመልእክታቸዉ በየደረጃው ሲካሄድ የነበረዉ ይህ ኮንፈረንስ የኢትዮጵያን ተምሳሌት በጋራ እንደምናረጋግጥ ማሳያ ነው ብለዉ የዚህ የሶስተኛው ሩብ አመት ኮንፈረንስ ማጠቃለያ ስናካሂድ ሪፖርት ገምግሞ አቅጣጫ ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን የብልፅግና ትልሞች፣ ህልሞችን እና ርዕይዉን እውን የምናደርግበት፣ ሃገራዊ ተልዕኮን በብቃት የምንወጣበት፣በሂደቱም በስኬቱም ዉጤታማ ምርጫ የምናስኬድበት ነው ብለዋል ::

ወ/ሮ ልዕልት አክለዉም በሰባተኛው ጠቅላላ ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫዉ ስኬታማ እንዲሆን የክፍለ ከተማችን የፓርቲያችን አመራሮች፣ አባላት የፓርቲውን መንታ ግቦች ስኬታማ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቃል በማለት በአባላችን ሁለንተናዊ ትጋት እና ቁርጠኝነት ስኬታማ: ፍትሃዊ እና ታማኝነት ያለው ምርጫ እናካሂዳለን ብለዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘመኑ ደሳለኝ ይህ ኮንፈረንስ በአይነቱ ለየት የሚያደረገዉ ኢትዮጵያ ለሰባተኛ ጊዜ ሀገራዊና ከተማ አቀፍ ምርጫ ለማካሄድ በተዘጋጀችበት ወቅት በመሆኑ ምርጫውን ስኬታማና በፓርቲያችን አሸናፊነት እንዲጠናቀቅ ለማድረግ መላው የክፍለ ከተማችን አመራራና አባላችን ራሱን ለተሻለ ተልዕኮ ዝግጁ በማድረግ ለጀመርነው የብልፅግና ጉዞ በሁለንተናዊ ተሳታፊነት ግንባር ቀደም በመሆን አርአያነት ያለው ስራ ሊሰራ ይገባልብለዋል::

በቀጣይ በበጀት አመቱ ምርጫን ጨምሮ የብልፅግና ተልእኮዎች በትጋትና በፍጹም ውግንና በመተግበር የጠንካራ ፓርቲን ለጠንካራ ተቋም ግንባታን እውን እናደርጋለን ለዚህም የእናንተ ሁለንተናዊ እና ንቁ ተሳትፎ ጉልህ ሚና አለው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትልና የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ የ3ተኛ ሩብ አመቱን ሪፖርት አቅርበው፣ ባለፉት አመታት በህብረቱ ጠንካራ ተሳትፎ ስኬታማ የፖለቲካ፣አደረጃጀት ፣ የፓርቲ ተልእኮ፣የሚዲያ ስራዎች ተሰርቷል ብለዋል ።

በቀጣይም የክፍለ ከተማችን የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት ጠንካራ የፖለቲካ ስራ በመስራት በሁሉም ዘርፍ ለጠንካራ ተቋም ግንባታ የራሳቸውን አበርክቶ ሊያደርጉ ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በማጠቃለያ ኮንፈረንስ ላይ የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት የሶስተኛውን ሩብ ዓመት ኮንፈረንስ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የኢንስፔክሽን ስነምግባር ኮሚሽን የ2018 በጀት ዓመት የሶስተኛው ሩብ ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዶባቸዉ አፅድቋል ::

በስተመጨረሻም ባለ 10 ነጥብ አቋም መግለጫ በማዉጣት እና በማፅደቅ ኮንፈረሱ ተጠናቋል።





#አድድሳባባ

Photos from Lideta sub-city Prosperity party Branch Office's post 09/04/2026



በልደታ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በሚል መሪቃል የ2018 በጀት አመት የ3ኛ ሩብ አመት የአባላት ኮንፈረንስ የማጠቃለያ መድረክ በክ/ከተማ ደረጃ እየተካሄደ ይገኛል።





Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Culinary Team

Attire

Website

Address

Addis Ababa