በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር  የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት, Government Official, Addis Ababa.

ራዕይ (Vision)

በ2022 ዓ.ም

አዲስ አበባ ከተማ የደንብ መተለለፍ የቀነሰባት፣ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንዲሁም ለአፍሪካ ከተሞች ተምሳሌት ሆና ማየት፡፡

ተልዕኮ (Mission)

በህብረተሰቡ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ የደንብ መተላለፎችንና ተያያዥ ሕገ-ወጥ ተግባራትን በመከታተልና በመቆጣጠር አዲስ አበባ ከተማን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ማራኪና ሰላማዊ እንድትሆን ማድረግ፡፡

Photos from በየካ ክፍለ ከተማ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት's post 06/06/2026
03/06/2026
Photos from Kirkos sub city code enforcement's post 27/05/2026
Photos from በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር  የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት's post 26/05/2026

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ዘወትር ሰኞ ማለዳ የሚያካሂደው የወርቃማ ሰኞ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግር መርሃ ግብር አስቀጥሏል።
17/09/2018 ዓ.ም
*አዲስ አበባ *
በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ዘወትር ሰኞ ማለዳ ከስራ ገበታ በፊት የሚያካሂደው የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም አካሄደ ።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ካሴ እንዳሉት ሳምንቱን በጥሩ የስራ መንፈስ ዉጤታማ ስራ ለማከናወንና በየሳምንቱ ከሰራተኞቻችን ጋር እየተማማርን እና እየተመካከርን ሳምንቱ ሙሉ ወርቃማ እንዲሆንልን መልካም ምኞት በመግለፅ እርስ በእርሳችን የምንመካከርበት፣ ልምድ የምንለዋወጥበት አገልግሎት አሰጣጣችንን የተሳለጠ ለማድረግ የምንወያበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል ።

መረጃው በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ነው።

ለበለጠ መረጃ https://linktr.ee/yekasubcitycodeenforcementoffi ይጠቀሙ።

Photos from A.A City Administration Code Enforcement Authority's post 23/05/2026
Photos from በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር  የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት's post 19/05/2026

የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት የ"ወርቃማው ሰኞ" የሕይወት ልምድ ልውውጥ መድረክ አካሄደ፤

ግንቦት 10/2018 ዓ.ም

​በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀው የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ፤ የጽሕፈት ቤታችን የግብረ ኃይል ቡድን ሽፍት መሪ የሆኑት ወ/ሮ ፍሬህይወት የራሳቸውን የሕይወት ታሪክ እና ያካበቱትን ጥልቅ ልምድ ለሠራተኞች አቅርበዋል።

​በዚህ አነቃቂ መድረክ ላይ ወ/ሮ ፍሬህይወት በሕይወት ጉዟቸው ያሳለፉትን ውጣ ውረድ፣ የተማሩባቸውን ትምህርቶች እና ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች እንዴት እንዳለፉ በሰፊው አካፍለዋል።

​ይህ ዓይነቱ ግለሰባዊ የሕይወት ልምድ ልውውጥ፤ ሠራተኞች ከሥራ ባልደረባቸው የሕይወት ተሞክሮ እና ጥንካሬ በመማር ለቀጣይ የሥራ እና የሕይወት ጉዟቸው ትልቅ ስንቅ እንዲያገኙ የሚያስችል ውጤታማ መድረክ ሆኗል።

መረጃው፦ በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ነው::

​ተጨማሪ መረጃዎችን እና የዕለት ተዕለት ተግባራቶቻችንን በፍጥነት ለማግኘት ቀጣዩን ሊንክ በመጫን ይከታተሉን፦

🌐 https://linktr.ee/yekasubcitycodeenforcementoffi

Photos from በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር  የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት's post 13/05/2026

የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት የ"ወርቃማው ሰኞ" የሕይወት ልምድ ልውውጥ መድረክ አካሄደ

ግንቦት 05/2018 ዓ.ም

​በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት "የሰው ኃይል ሥልጠና እና ልማት" በሚል መሪ ቃል በየሳምንቱ የሚያካሂደውን የ"ወርቃማው ሰኞ" መርሃ-ግብር ዛሬም በጽሕፈት ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ አከናውኗል።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ካሴ እንደገለጹት፤ የሰው ኃይል ልማት ለተቋማዊ ስኬትና ለሰው ልጅ ደህንነት ግንባር ቀደሙን ስፍራ የሚይዝ ተግባር መሆኑን ገልጸው፣ ሠራተኞች አቅማቸውን በሥልጠና ማሳደግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

​የዕለቱን የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡትና የሕይወት ልምዳቸውን ያጋሩት የደንብ ማስከበር ጽሕፈት ቤት የሥራዎች አስተባባሪ አቶ ከፈለኝ በልሁ፤ ሥልጠና ለሥራ ውጤታማነት ያለውን ፋይዳ በስፋት አብራርተዋል። አቶ ከፈለኝ አክለውም የሥልጠና እና የዕውቀት ክፍተት በሥራ ሂደት ላይ የሚያስከትላቸውን አሉታዊ ተጽዕኖዎች በመዘርዘር፣ ለችግሮቹ መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ ነጥቦችን ለውይይት አቅርበዋል።

​በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊዎች የቀረበው ሰነድ ለዕለት ተዕለት ተግባራቸው ጠቃሚ መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም መሰል የልምድ ልውውጦች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

መረጃው፦ በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ነው።

​ለበለጠ መረጃ ገጻችንን ይከታተሉ፦

🌐 https://linktr.ee/yekasubcitycodeenforcementoffi

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

https://t.me/YekaCEObot, https://www.aacea.gov.et/, http://yekasubcity

Address

Addis Ababa