09/01/2025
አንጋፋው የኢኮኖሚክስ ባለሙያ ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ አረፉ::
በምርጫ 2013 ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ለሀገራችን የፖለቲካ ስብራት መቃናት የራሳቸውን አስተዋፅኦ ያደረጉና ለብዙ ምሁራንም ወደ ፖለቲካው መድረክ እንዲመጡ አርአያ የሆኑ አንጋፋ ሰውም ነበሩ።
በፕሮፌሰሩ ሕልፈት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው፣ ዘመዶቻቸው እና ጓዶቻቸው ሁሉ መጽናናትን እንመኛለን
07/01/2025
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!
የምስረታ ሂደቱን በማጠናቀቅ ላይ የሚገኘው እና በቅርቡም ለሚደረገው ዝግጅት ላይ የሚገኘው
ለአባላትና ደጋፊዎቻችን እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የሰላም ፣የደስታ እና የአብሮነት እንዲሆንላችሁ እየተመኘን በዓሉን ስናከብር በተለመደው ኢትዮጵያዊ እሴቶቻችን በጋራ እና በአብሮነት የተቸገሩትንም በመርዳት መሆን እንዳለበት ለማስታወስ እንወዳለን!!
መልካም በዓል!!
06/11/2024
የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ ፓርቲን መቀላቀል እና አባል መሆን የምትፈልጉ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን Link በመጠቀም ፎርም መሙላት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።👇👇
የአባልነት ፎርም
"የንጋት ኮኮብ ለኢትዮጵያ" በሚል ስያሜ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት ከምርጫ ቦርድ የጊዜያዊ ፍቃድ በማግኘት በሀገር አቀፍ ደረጃ ዜግነትን መሠረት ያደረገ ፓርቲ ለመመስረት በሂደት ...
23/10/2024
የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ ቅድመ ምሥረታ ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳያካሂድ መከልከሉን በማስመልከት የተሰጠ መግለጫ።
የኢትዮጵያ ሰላማዊ ትግል በአገዛዙ መጠን ሰፊ አፈና ከጊዜ ወደ ጊዜ ወደቁልቁለት እየተንደረደረ ቢገኝም ለሀገር አንድነት፣ ሕዝባችን የተነፈገውን መሠረታዊ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መብቶች ለማስከበር፣ ለብዙ ዘመናት ብዙ ዋጋ የተከፈለለትን ዴሞክራሲን ለማግኘት ከሕዝብ ጋር በተባበረ ክንድ የጋራ ትግል ለማድረግ "የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ" በሚል ስያሜ ከምርጫ ቦርድ ያገኘውን ቅድም እውቅና በማስመልከት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት እና ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎቻችን በይፋ ለማሳወቅ ለመንግሥትና ለግል ሚዲያዎች ይፋዊ ጥሪ በማድረግ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል መግለጫ ለመስጠት በተዘጋጀንበት ወቅት ያለበቂ ምክንያት በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳይሰጥ ክልክላ ተደርጓል።
የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ ከሥርዓቱ ቀደምት ባህሪ በመነሳት እንዲህ ዓይነት ተግዳሮቶች እንደሚገጥመው ቢያውቅም አሁን ያለው መገፋት ከሕዝብ ጎን እንዲቆም ትግሉን በተጠናከረ መልኩ እንዲያካሂድ የሚያነሳሳው በመሆኑ ከምርጫ ቦርድ እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የተከለከለውን መግለጫ ለመስጠት ጥረት ያደርጋል።
በዚሁ አጋጣሚ ጋዜጣዊ መግለጫው እንዳይደረግ ላደረጋችሁ አካላት ትግላችን ለሁላችንም የምትመች አገር እንድትኖረን በማሰብ መሆኑን በመረዳት ከመሰል ድርጊታችሁ እንድትታቀቡ አበክረን እንጠይቃለን።
አደራጅ ኮሚቴው በቀጣይ በተለያዩ ከተሞች ተንቀሳቅሶ ስለ ኢትዮጵያ ንጋት የሚሰራውን ፓርቲ የማደራጀት ስራ እንደሚቀጥል በመዋቅሩ ውስጥ ላሉ ሰላማዊ ታጋዮች ያሳውቃል።
ይነጋል!
ጥቅምት 13; 2017 ዓ.ም
አዲስአበባ
የንጋት ኮከብ ለኢትዮጵያ የአደራጅ ኮሚቴ ሕዝብ ግንኙነት
ለለጠ መረጃ
Telegram👇
https://t.me/Morningstar4Eth
Facebook👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61564830160380
Tiktok👇
tiktok.com/