17/10/2025
አደረጃጀቶቻን የተልዕኮ ስኬት ማረጋገጫ ዋልታ ናቸው!
በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ወጣቶች ክንፍ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የስራ አፈፃፀም የክንፉ የዘርፍ አመራሮች ፣የህብረትና የቤተሰብ አመራሮች እንዲሁም እንዲሁም አባላት በተገኙበት ገመገመ።
ፓርቲያችን ብልፅግና መመሪያና አሰራርን የዘረጋቸው ተቋማት በማጠናከር፣ የተልዕኮ ስኬታማነት በማረጋገጥ ሁሉም የፓርቲ መዋቅር የለውጡና የተልዕኮ ባለቤት በማድረግ በጥራት ባጠረ ጊዜ ፍትሀዊነት በማረጋገጥ ያስቀመጣቸው ግቦች ያለመሸራረፍ በውጤት እየፈፀመ እንደሚገኝ በመረሀግብሩ ላይ ተገኝተው በመክፈቻ ንግግራቸው የገለፁት በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ምክትልና ፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደቻሳ ጆቴ ለዚህ ትልቁ ሚስጥር የተልዕኮውን ባለቤት መዋቅሩና ህብረተሰቡ በማሳተፍና ባለቤት አድርጎ መፈፀም በመቻሉ ነው ብሏል።
በመጀመሪያ ሩብ አመት እንደ ወጣት ክንፍ በርካታ መደበኛ የፓርቲ ተግባራቶች በተደራጀ መልኩ መፈፀሙን የገለፁት በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ ወጣት ወጣት ቤተሌሔም ትዳሩ በዝግጅት ምዕራፍ የነበሩ ጥንካሪዎችን በዝግጅት ምዕራፍ ወቅት አልቀን በመፈፀም ጠንካራ ተቋም የመፍጠር ስራ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ አስገንዝቧል።
ተልዕኮ በስኬት ለመፈፀም ተግባርን በውጤት ለማሳካት ግብ ተኮር ስራ በመስራት ተጠናክሮ የቀጠለው የሀገራችን ማንሰራራት ጉዞ ባጠረ ጊዜ ከግብ ለመፈፀም የሚያስችል የሁሉአቀፍ ተነሳሽነትና ዝግጁነት ሊኖር እንደሚገባ በብልፅግና ፓርቲ አራዳ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክተር ወ/ሪት ነጃት ሙስጠፋ ገልጿል።
በመጨረሻም በተነሱት ሀሳም አስተያየቶችና ጥያቄዎች ላይ የጋራ መግባባት በመፍጠር ተጠናቋል።
14/10/2025
በስራ እድል ፈጠራ ለወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ "ስራን በትጋት ውጤት በብቃት አንድ ክህሎት ለአንድ ወጣት"በሚል መሪ ቃል በስራ እድል ከወጣት ክንፍ ከበታች አመራሮችና ከህብረትና ቤተሰብ ፣ከወጣት አደረጃጀት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።
የክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ አቶ ጎሳ ታመነ ባስተላለፉት መልዕክት የስራ አጥነት ችግርን ለመቀነስ በቀጣይ 4 ወራት በንቅናቄ በልዩ ትኩረት እየተሳራ እንደሆነ ገልፀዋል።የስራ ዕድል ፈጠራ ስራን በትጋት ውጤት በብቃት አንድ ክህሎት ለአንድ ወጣት ዙሪያ ለስራ ፈላጊ ወጣቶች ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ በቀጣይ አራት ወራት በርካታ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
ወጣት ጎሳ አክለውም በሀገራችን በስራ ባህል ዙሪያ ያሉ ማነቆዎችን ከወጣቱ መበጣጠስ ሀገር ያሏትን ልዩ ልዩ ፀጋዎችና አቅም በመጠቀም በሃላፊነትና በተነሳሽነት ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ፣የዜጎችንና የሀገርን እምቅ ማሳደግ ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል።
የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መንግስት በሚያመቻቸው የስራ እድል አማራጮችን ሳያማርጡ ተጠቃሚ ለመሆን ወጣቶች በአካባቢያቸው በሚገኝ ፀጋ ስራ መፍጠር እንዲችሉ የሚያግዝ እና ስራ ፈጣሪ ዜጋ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
ጥቅምት 04/2018
14/10/2025
የ2 ወር የልዩ የስራ ዕድል ፈጠራ አፈፃፀም ተገመገመ
ጥቅምት 03/2018 ዓ,ም ቦሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ ጽ/ቤት
የ2 ወር የልዩ የስራ ዕድል ፈጠራ የእቅድ አፈፃፀም ከወረዳ ወጣቶችና ሰፖርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ ከወረዳ ወጣት ክንፍና ከወጣት ማህበር አመራሮች ጋር የወጣቱን የግንዛቤ አመለካከት ስርፀት ያለበትን በጋራ የተገመገመ ሲሆን።
በስተመጨረሻም የወጣቱን የስራ ዕድል እንዲፈጠርለት በአትኩረት እንደምንሰራና የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መረባረብ አለብን የሚል መግባባት ተችሏል።
12/10/2025
በስራ እድል ፈጠራ ለወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍና የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወጣትና ስፖርት ፅ/ቤት እንዲሁም የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አዲስ አበባ ወጣት ማህበር በጋራ በመሆን "ስራን በትጋት ውጤት በብቃት አንድ ክህሎት ለአንድ ወጣት"በሚል መሪ ቃል በስራ እድል ለወጣቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።
ለመድረክ ውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ ከቀረበ በኋላ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወጣትና ስፖርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ ጠንክር ባስተላለፉት መልክት የስራ አጥነት ችግርን ለመቀነስ በቀጣይ 4 ወራት በንቅናቄ በልዩ ትኩረት እየተሳራ እንደሆነ ገልፀዋል።
አክለውም የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መንግስት በሚያመቻቸው የስራ እድል አማራጮችን ሳያማርጡ ተጠቃሚ ለመሆን ወጣቶች በአካባቢያቸው በሚገኝ ፀጋ ስራ መፍጠር እንዲችሉ የሚያግዝ እና ስራ ፈጣሪ ዜጋ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ በበኩላቸው የመድረኩ አላማ የስራ ዕድል ፈጠራ ስራን በትጋት ውጤት በብቃት አንድ ክህሎት ለአንድ ወጣት ዙሪያ ለስራ ፈላጊ ወጣቶች ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ በቀጣይ አራት ወራት በርካታ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
በሀገራችን በስራ ባህል ዙሪያ ያሉ ማነቆዎችን ከወጣቱ መበጣጠስ ሀገር ያሏትን ልዩ ልዩ ፀጋዎችና አቅም በመጠቀም በሃላፊነትና በተነሳሽነት ተጠቅሞ ምርትና ምርታማነት ማሳደግ ፣የዜጎችንና የሀገርን እምቅ ማሳደግ ይኖርብናል ሲሉ ገልፀዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አዲስ አበባ ወጣት ማህበር ሰብሳቢ እንዳሉትም የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰፊ ንቅናቄ እየተደረገ መሆኑን የገለፁ ሲሆን ወጣቱ በመረጠው የስራ ዘርፍ በቀጣይ መንግስት በሚያዘጋጀው ስልጠና በመሳተፍ እራሱን የሙያ ባለቤት ማድረግ እንዳለበት መልክት አስተላልፈዋል።
10/10/2025
በሁለት ወራት ውስጥ ከ59ሺህ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል። አቶ በላይ ደጀን
መስከረም 30 ቀን 2018ዓ.ም ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ከክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊዎች፣ ከአዲስ አበባ ወጣት ማህበር እና ከአዲስ አበባ ወጣት ክንፍ አመራሮች ጋር የቀጣይ ሁለት ወራት ልዩ የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የንቅናቄ እቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን በቀጣይ ሁለት ወራት ለ59,500 ወጣቶች በስራ እድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በብሎክ፣ በክፍለ ከተማ እና በከተማ ደረጃ ስልጠና ይሰጣል ብለዋል።
የወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የቢሮው ብሎም የከተማ አስተዳደሩ ቁጥር አንድ አጀንዳ መሆኑን የተናገሩት አቶ በላይ በሁለት ወራት ውስጥ ግንዛቤ ከሚፈጠርላቸው ወጣቶች ውስጥ ከ20 ሺህ በላይ ወጣቶች ቆሚ የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የቀጣይ ሁለት ወራት ልዩ የወጣቶች የስራ ፈጠራ የንቅናቄ እቅድን አቶ መክብብ ወ/ሀና የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በየአከባቢው ያሉትን ስራ አጥ ወጣቶችን ከመመዝገብ ጀምሮ ግንዛቤ መፍጠር፣ ማሰልጠን እና ስራ እድል እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የንቅናቄ እቅዱን ለማሳካት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ከአዲስ አበባ ወጣት ክንፍ እና ከአዲስ አበባ ወጣት ማህበር ጋር በመቀናጀት እንደሚሰሩ በመድረኩ ተመላክቷል።
በ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት የስራ እድል ከተፈጠረላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል 83 ፐርሰቱ ወጣቶች መሆናቸውን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሪፖርት ያመላክታል።
08/10/2025
አመራሩ አባሉ ፈጠራን እና ፍጥነትን በመጨመር የፓርቲ እና የተቋም ተልዕኮን በውጤታማነት ማሳጀብ ይገባል።
የቦሌ ክ/ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣት ክንፍ ከስራ አስፈፃሚ እና ከአስተባባሪ ጋር የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ
መስከረም 28/ 2018
በተካሄደው የግምገማ መድረክ የክ/ከተማው የወጣት ክንፍ ኃላፊ ሄለን ለገሰ
በሩብ ዓመቱ በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ህዝባዊ እና ኃይማኖታዊ የአደባባይ በአላት በልዩ ልዩ ንቅናቄዎች የተተገበሩ ተግባራት በተቋማችን በማዋቅራችን አባላት መሰራት መቻላቸው
በውስጠ ፓርቲ የዝግጅት ምእራፍ የአመራሮቻችን አባላችን አቅም ላማሳደግ የተሰራው ስራ ተቋሙን በሰው ኃይል በፋይናንስ ለማጠናከር በእቅድ ተይዞ እየተመራበት ያለው አግባብ
የአባላችንን አቅም ከማሳደግ አሰራር እና መመሪያዎችን ከማስጠበቅ አኳያ የቤተሰብውይይት ፣የህብረት ኮንፈረንስ ወቅቱን ጠብቀው እንዲደረጉ የማድረግ ግንባር ቀደም አባላትን በማብዛት ሞዴል ህብረት እና ቤተሰብን የማጠናከር ስራዎች
የወጣቶቻችንን አመለካከት በመቅረፅ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ የተሰሩ ስራዎች እንደ ክ/ከተማችን በሩብ ዓመቱ ያመጣናቸው ተጨባጭ ለውጦች መሆናቸውን የገለፀች ሲሆን
በቀጣይም በዕቅድ መሰረት ሊሰሩ የሚገቡ እና ክ/ከተማ እና ተቋምን የተሞክሮ ባለቤት አድማስን ከማስፋት አኳያ ትኩረት አድርጎ በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫን በማስቀመጥ መጠናቀቅ ተችሏል።
👉ጠንካራ አመራር ጠንካራ ተቋም ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግስት ግንባታ ስራችን
👉 ለፓርቲ ለተቋም አቅም የሚሆኑ ሙሁራን አባላትን ማፍራት
👉 ፓርቲን በፋይናንስ ማገዝ መደገፍ
👉ብሄራዊ ገዢ ትርክት ግንባታ ለህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ማዋል
👉ጠንካራ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ለገዢ ትርክት ግንባታ ስርፀት
👉የወረዳችን የክ/ከተማችን ሠላም ማረጋገጥ የሰላም እሴት ግንባታ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት
👉የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥን ማስፈን
👉የወጣቱን ኢኮኖማያዊ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ
👉ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በመታገል ነጻ ማድረግ
👉 መጪው ሀገራዊ ምርጫ ዲሞክራሲ የሰፈነበት ለማድረግ በትኩረት መስራት ምርጫው በፓርቲያችን የበላይነት እንዲጠናቀቅ መስራት
👉የአመራር ፣ የስራ አስፈፃሚ የአባላት አቅም በመገንባት የመፈጸም እና የማስፈጸም አቅምን ማጎልበት
👉ማህበራዊ አገልግሎት(ሰዉ ተኮር) ስራዎች ማጠናከር
👉አዳዲስ ኢኒሼቲቮችን በመስራት እና በመተግበር የተሞክሮ ማእከልነትን ማስፋት ማጠናከር
👉የአረንጓዴ አሻራ መንከባከብ ፣ የከተማ ግብርና የሌማት ትሩፍት ፣ የጽዳት እና ውበት ስራዎች ማጠናከር
👉የተቋማ ግንባታ ስራዎች ይበልጥ ማጠናከር
👉የውስጠ ፓርቲ ስራዎች በእውነት ፣ በእውቀት እና በጥራት መስራት
👉አቅምን አሟጦ ለፓርቲ እና ለተቋም ማዋል
👉ኃላፊነትን በተጠያቂነት መንፈስ መጠቀም መወጣት
👉ራስን በክህሎት በእውቀት መገንባት ማሳደግ
👉አርአያነት የተላበሰ ብቁ መሪ መሆን እና ሌሎች ተከታዮችን ማፍራት የሚሉት ላይ የጋራ መግባባት ተጥሯል
06/10/2025
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸምና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ላይ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ላበረከቱ አካላት እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
04/10/2025
: Olka’insa Biyyaaf!
: For National Leap Up!
እንኳን ለ2018 የኢሬቻ ክብረ በዓል አደረሳችሁ/አደረሰን!!
03/10/2025
እንኳን ለ2018 ዓ/ም የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!!
ሀገራችን ኢትዮጵያ የረዥም ታሪክ ባለቤት፣የስልጣኔ መገኛ፣መልክዓ-ምድሯ አመቺ፣ ተስማሚ የአየርንብረት ያላት፣ቀለመ ብዙ ባህል፣ ብዝሀ ቋንቋ እና ሀይማኖት ያላቸው ህዝቦች ተከባብረው ተቻችለው እና በብዘሀነት ውስጥ ጠንካራ አንድነትን የተጎናጸፉ የጀግና ህዝቦች ሀገር ናት።
በሀገራችን ከሚገኙ ከብዘሀ ባህላዊ እሴቶች አንዱ የሆነው ኢሬቻ የኦሮሞ ሕዝብ የገዳ ስርዓት አንዱ አካል የሆነ ህዝባዊ በዓል ነው። ክረምቱ አልፎ ብራ ሲሆን ተፈጥሮን የፈጠረ ፈጣሪ የሚመሰገንበት የምስጋና በዓል ነው። የኦሮሞ ሕዝብ ጥልና ክርክርን በይቅርታ ተሻግሮ፣ በንጽሕና ፈጣሪውን ምህረት የሚጠይቅበት መጪውን ጊዜ የሰላምና ፍቅር እንዲያደርግለት ፈጣሪውን የሚለምንበት በዓል ነው።
ይኸ ታላቅ የአደባባይ በዓል አከባበር ከባህላዊ መገለጫው በተጨማሪ የቱሪስት መስህብ በመሆኑ ለሀገራችን ትልቅ ኢኮኖሚያዊ ቱሩፋትን በማስገኘት ላይ ይገኛል
በመሆኑም በዓሉ እሴቱን እና ትውፊቱን ጠብቆ በሰላም እንዲከበር የከተማችን ወጣቶች እንግዶችን በመቀበል፤የትብብርና የአብሮነትን ባህልን በማጎልበት፤ደማቅ ማህበራዊ ትስስርን በመተግበር የተለመደው ሚናችንን እንድንወጣ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ በድጋሚ እንኳን አደረሳቹ አደረሰን!!
መለሰ አባተ
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ፕሬዚዳንት
30/09/2025
የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም የዕውቅና መርሐ ግብር እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት አካሄደ፡፡
በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የቦሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ መሥፍን ኃይሌ ባደረጉት ንግግር ወጣቶች ሀገራዊ ለውጡ ዕውን እንዲሆን በግንባር ቀደምትነት የጎላ ሚና መጫወታቸውን አውስተው፣ የወጣቶች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲያድግ ከለውጥ ማግሥት ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡ የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ያከናወናቸው ስኬታማ ተግባራት በአርአያነት የሚጠቀሱ መሆናቸውን ያመለከቱት አፈ ጉባኤው፣ ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና በማቅረብ ይህ የተሳካ እንቅስቃሴ በ2018 በጀት ዓመትም በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥል ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ አስተባባሪ ወጣት ሄለን ለገሠ በበኩሏ የክፍለ ከተማው ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በ2017 በጀት ዓመት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማጠናከር ወጣቶች ለሁለንተናዊ ብልጽግና መረጋገጥ ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ባከናወነው እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በቀዳሚነት ተሸላሚ መሆኑን ገልጻ፣ ይህ ስኬት የተገኘው መላው የክንፉ አባላት በቅንጅት ያደረጉት ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው አመልክታለች፡፡ በ2018 ከሚጠበቁ ታላላቅ ተልዕኮዎች አንጻር የክንፉ አባላት ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስተባባሪዋ ገልጻ፣ በመሆኑም የክንፉን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ለማሳካት የላቀ ተሳትፎ ከአባላቱ እንደሚጠበቅ አስገንዝባለች፡፡
በመድረኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለተመዘገበው ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
መስከረም 20/2018
26/09/2025
በዩኔስኮ በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል ደማቅ አከባበር!!
26/09/2025
ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን !!!
የመስቀል በዓል በታላቅ ኃይማኖታዊ ስርዓት ከሚከበሩ በዓላት አንዱና በዓለም አቀፉ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም /UNESCO/ በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ ልዩ በዓል ነው።
በዓሉ የሀገራችን ህዝቦች አንድነት የሚጎላበት ፣የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን እየተመኘው በድጋሚ መልካም የመስቀል በዓል እንዲሆን እመኛለሁ።