15/04/2025
ግራ የገባ ነገር እኮ ነው
በዚ ድመት የሚወድ ወንድ ወንድ አደለም ትሉናላቹ እዚ ደሞ ሌላ ከየቱ እንሁን
it gives idea on people daily life
15/04/2025
ግራ የገባ ነገር እኮ ነው
በዚ ድመት የሚወድ ወንድ ወንድ አደለም ትሉናላቹ እዚ ደሞ ሌላ ከየቱ እንሁን
09/04/2025
በ 2017 ዓ.ም አንብቤያቸው በጣም የወደድኳቸው መጽሀፎች። መጽሀፎቹን የማግኘት እድል ካገኛቹ አንብቧቸው ታተርፉበታላቹ
ምኒሊክን የገደልኩት እኔ ነኝ
"አዳምጥ ፈረንጅ" በማለት ቀጠሉ "ሁሉም የአቢሲኒያው ኃይለኛው ራስ መሆኔን ያውቃሉ። ሆኖም ግን ሰዎች ከሚገምቱት በላይ ኃይለኛና ብዙ ማድረግ እንደምችል ግን ፍፁም አያውቁም።
"ሁሉም ምኒሊክን ያከብራሉ። በኢትዮጵያም ታሪክ ውስጥ ትልቁ ሰው አድርገው ያዩታል። የማይሸነፍ ሰው አድርገውም ቆጥረውታል።"
ንግግራቸውን ገታ ለማድረግ መዳፋቸውን ጭብጥ አደረጉት። በሃይልም አንቀሳቀሱት።
"እናም እሺ ምንሊክን የምበልጠው ትልቁ ሰው እኔ ነኝ። እኔ ነኝ የኢትዮጵያውያንን ጀግና የገደልኩት።"
"እርሶ ነዎት የገደሏቸው?.....እንዴት?"
"በመርዝ ነው የገደልኳቸው።"
ራስ ሙሉጌታ በነገሩ መደነቅና መገረም ያስደሰታቸው ይመስል ጨካኝና ኃይለኛ በሆነ አስተያየት በአይናቸው ቃኙኝ።
"አዲስ አበባ ላይ አንድ ግሪካዊ ዶክተር ነው መርዙን የሰጠኝ። ያለ ህመም ሞት የሚታይ ፍንጭ የሌለው። ገዳይ ወይም ዱካው ያልተገኘ ሞት። ሁሉም ነገር በሚስጥር። በአንዲት የቡና ሲኒ ምንሊክ ሞትን ፉት አሏት። ማንም በፍፁም የጠረጠረ የለም። ከኢትዮጵያ ችሎት ውስጥ ማቀነባበሩን ከረዱኝ ሶስት ታላላቅ ሰዎች በስተቀር።"
"ሶስት የወንጀሉ ተባባሪዎች?"
"አይደለም ጠንቋዮች" "አስፈላጊ ነበር...." ቃላቶቹ ከአፋቸው ሳይወጡ ቀሩ። ዳግም ደከሙ። እጃቸው ሙሉ በሙሉ ዛላ። እንደገናም የእኚህ ሽማግሌ ጦረኛ ገላ መሬት ላይ አረፈ።
የኢትዮጵያ ጦር ሚኒስትር የነበሩት ራስ ሙሉጌታ ከኮለኔል አለኸንድሮ ዴል ባዬ ጋር በመጨረሻዋ ሰአት ያደረጉት ቃለ ምልልስ ከቀይ አንበሳ መጽሀፍ የተወሰደ
ፍቅር ማለት
በኔ እምነት ፍቅር "ተራራ የሚያክለውን መሰናክል የሚያሻግር ጉልበት: የውቅያኖስ ስፋት ያህል የተዘረጋውን ልዩነት የሚያጠብ ምትሀት: ታላቅ የተባለውን ችግር የጉድፍ ያህል የሚያስንቅ ትዕቢት: የማይቻለውን ሁሉ የሚያስችል የነፍስ ሀይል ነው።"
ልረሳሽ ብጠጣ🍺 አይኔ እየሰከረ👀
ጭራሽ ሁለት አርጎሽ ያሳየኝ ጀመረ😳
ቦ ጊዜ ለኩሉ (ለሁሉ ጊዜ አለው)
“ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።”
“ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፤”
“ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመሥራትም ጊዜ አለው፤”
“ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው፤”
“ድንጋይን ለመጣል ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፤”
“ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ለመጣልም ጊዜ አለው፤”
“ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤”
“ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው።”
¹¹ ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው።
መክብብ ፫÷፲፩
ዲ/ን ኤርምያስ
*
የሚበድላት ሰው
ይሰብካታል ቆሞ ፤
አንቅሮ የሚተፋት ፡ ያነሳታል ስሞ።
አጥንቷን ሚሰብራት ፡ እስክትቆም ይጓጓል፤
ሲያሰተምራት ውሎ ፡ ሲመኛት ያነጋል!።
የትኛውን ትመን?
መሸሸጊያ ያለችው
ውስጡ ይኮሰኩሳል፥
ስትወድቅ የደገፋት ፡ ከጣላት ይብሳል።
በፈሪ ይፈነጫል ፡ የታደለው አቅም፥
ያከበረችው ሰው ፡ ክብሩን አይጠብቅም።
ለርሷ ታሪክ ሲሆን ፡ ምሁር ያበዛል ዝም፤
ሽበት ያለው እንኳን ፡ በደል አያወግዝም!
ሁሉም ተደራጅቷል
ህሊናውን አቷል
ስሜት አይገባውም፥
ሰቆቃ አይገባውም ፡ የሴት"ወየው ወየው"፤
የናቀውን እምባ ፡ በልጁ እስካላየው!።
by
21/03/2025
እግር የሚችለውን እየለካ ይራመዳል። እጅም የሚችለውን መጥኖ ይይዛል። ዓይንም በአቅሙ ልክ ይመለከታል።
ምላስ ግን ከአቅሟ በላይ ታወራለች። ሰው ታጋድላለች፣ ትዳር ትበትናለች፣ ሀገር ታምሳለች፣ ጦርነት ትለኩሳለች።
ጠቢብ በልኩ የሚያወራ ነው።!
"............. ያ ሰሜን ኢትዮጵያ የጥንታዊ ስልጣኔ መነሻ የውጭ ወራሪዎች በየጊዜው አንገታቸውን ብቅ እያረጉ ሲሰልሉት እያወደሙም ቢሆን ሲወድሙበት የኖረ የዘመናት የጦር አውድማ; ያ ሰሜን ኢትዮጵያ የውጭ ወራሪዎች በፈጠሩት መዘዝ ወንድም ከወንድሙ እየተጋጨ ሲተራረድ አንተም ተው አንተም ተው የሚል ጠፍቶ የእርስ በእርስ መጫረሻ የሆነ የደም መሬት; ያ ሰሜን ኢትዮጵያ ወንድ ልጇን ያላስገበራት ኢትዮጵያዊት እናት የለችምና የወላድ እርግማን የደረሰበት ይመስል ቦንብና መትረየስ እየለበለበው የደጋ በረሀ ሊሆን የተቃረበ ምድር; ያ ሰሜን ኢትዮጵያ ደም እንደ ውሀ እየወረደበት አጥንት እየተከሰከሰበት የሰው ልጅ አስክሬን በአውሬ እየተጎተተበት የዋይታ እና ኡኡታ ጩሀት እያደነቆረው ራሱም ሲያለቅስ የሚኖር ያልታደለ ቦታ; ያ ሰሜን ኢትዮጵያ የወደፊት እጣው እንኳን ገና በውል ያልታወቀ የሀገር ክፋይ!"
በትምህርት ተስፋ ብቆርጥ እንኳን ለሱ ስትል ጎበዝ ተማሪ ትሆናለህ
ተባረክ አቦ