House of Peoples Representatives of FDRE

House of Peoples Representatives of FDRE

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from House of Peoples Representatives of FDRE, Government Organization, House of peoples' representatives of FDRE, Addis Ababa.

03/06/2026

የም/ቤቱ 23ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል
------------------
(ዜና ፓርላማ) ግንቦት 26፣2018 ዓ.ም፤ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 23ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ግንቦት 27 ቀን፣ 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

ም/ቤቱ በነገ ስብሰባው በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ልማት ባንክ ፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በዓለምዓቀፍ የልማት ማህበር መካከል የተደረጉ የብድር ስምምነቶች ለማፅደቅ የወጡ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥትና እና በሴራሊዮን ሪፐብሊክ መንግሥታት፤ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በአንጎላ ሪፐብሊክ መንግሥታት፤ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በባንግላዲሽ ሕዝባዊ ረፐብሊክ መንግሥታት፤ እንዲሁም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በኢስዋቲኒ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት
መካከል የተፈረመውን የሁለትዮሽ የአየር አገልግሎት ስምምነት ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና ውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን የሚያፀድቅ ይሆናል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል የጋራ የባዮሎጂ ምርምር ማዕከል ለማቋቋም የተፈረመውን ስምምነት ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና ውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተያያዘም በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግሥት እና በቬትናም ሶሻሊስት ሪፐብሊክ መንግሥት መካከል የዲፕሎማቲክ ወይም ኦፊሻል የአገልግሎት ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተፈረመ ስምምነት ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና ውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የፌዴራል ታክስ አስተዳደር ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን፣ የግብርና ቢዝነስ ኩባንያ ረቂቅ አዋጅን፣ የምግብ ስርዓትና ስርዓተ ምግብ ረቂቅ አዋጅን ፣ የኢትዮጵያ የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅን እና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች ይመራል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

Photos from House of Peoples Representatives of FDRE's post 01/06/2026

የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ የተከበሩ ምህረት ሻንቆ (ዶ/ር) ድምፅ ሰጡ
-------------------
(ዜና ፓርላማ) ግንቦት 24 ቀን፣ 2018 ዓ.ም፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ የተከበሩ ምህረት ሻንቆ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

Photos from House of Peoples Representatives of FDRE's post 01/06/2026

ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ መቂ ከተማ በመገኘት ድምጽ ሰጡ
-----------------
(ዜና ፓርላማ) ግንቦት 24 ቀን፣ 2018 ዓ.ም፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ በመቂ ከተማ ቀበሌ 03 የምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

Photos from House of Peoples Representatives of FDRE's post 01/06/2026

የተከበሩ አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ድምፅ ሰጡ
----------------------
(ዜና ፓርላማ) ግንቦት 24 ቀን፣ 2018 ዓ.ም፤ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ከተማ በመገኘት የምርጫ ድምፅ ሰጥተዋል፡፡

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚወዳደሩበት ምርጫ ክልል፣ በአርባ ምንጭ ከተማ በጫሞ ካምፓስ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጽ የሰጡት የተከበሩ አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በርካታ መራጭ ተመዝግቦ በነቂስ በመውጣት እየመረጠ መሆኑ ከበፊቱ ምርጫ ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

ይህም በሀገራችን የዲሞክራሲያዊ ልምምድ እያደገ እንደመጣ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ 42 ፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት፤ የምርጫ ክርክሮችን በምርጫ ቦርድ መሪነት የተካሄደበት፣ የተሻሉ አሰራሮች በምርጫ ቦርድ የተካተቱበት በመሆኑ የዘንድሮውን ምርጫ ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

በሀገራችን ህገ መንግስት መሰረት ስልጣን የሚያዘው በምርጫ ብቻ በመሆኑ ምርጫው በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባ ገልፀው ይህን ለማደናቀፍ መሞከር ኢ-ህገመንግስታዊ እና ሀገር እንዳትሻገር የማድረግ እኩይ ተግባር መሆኑን ተናግረዋል።

የተከበሩ አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አክለውም ሀገር ወደፊት እንድትቀጥል በሚደረገው ሂደት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል በነቂስ ወጥቶ ሀገርን የሚያሻግር መንግስት የሚያፀና፣ የኢትዮጵያን ልማት እና ዕድገት የሚያረጋግጥ የፖለቲካ ፓርቲን በመምረጥ የታሪክ አካል መሆን እንደሚጠበቅባቸውም ነው ያስገነዘቡት።

መረጃው ከክልሉ ማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

26/05/2026

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሣችሁ ሲል የመልካም ምኞት መልዕክት ያስተላልፋል!
-------------
ታላቁ የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ-ስርዓት የሚከበር፣ ሕዝበ ሙስሊሙ ለፈጣሪያቸው ያላቸውን ፍቅር በታዛዥነት እስከ መስዋዕትነት ያሳዩበት ቅዱስ በዓል ነው፡፡

የአረፋ በዓል የአብሮነት፣ የሰላምና የጽናት በዓል በመሆኑ የሀገራችን ሙስሊም ማህበረሰብ ሁልጊዜም ቢሆን ከሌሎች ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመሆን ለሀገር ሠላም፣ ልማትና የጋራ ዕድገት እንዲመጣ በጋራ የሚጸልይበትም በዓል ነው፡፡

በመሆኑም የሀገራችን ሕዝበ ሙስሊም በበዓሉ ዕለት ከሚያደርገው የምስጋናና የጋራ ጸሎት ባሻገር እንደ ሀገር ያሉንን የመረዳዳት፣ የመተባበር እና የመተሳሰብ ዕሴቶች በማጠናከርና ፈጣሪ የሚያዘውን ተግባራት በመፈጸም ካለን ላይ በማካፈል፣ የተቸገሩ ወገኖችን መርዳት፤ ወላጅ አልባ ሕጻናትን መንከባከብ፤ አቅመ ደካሞችን መደገፍና የታመሙ ወገኖችን መጠየቅ ይገባል፡፡

የአረፋ በዓል የታማኝነት፣ የፍቅርና የታዛዥነት በዓል ነው። የሀገራችን ሙስሊም ማህበረሰብ በታሪኩ ዘመናት ሁሉ እነዚህን ዕሴቶች በመያዝ ለሀገራዊ አንድነት፣ ሠላምና ለልማት የበኩሉን አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል።

በመሆኑም በዓሉ ሲከበር ሀይማኖታዊ አስተምህሮው እና ዕሴቱን በመጠበቅ በሀገራችን የተጀመረውን ለውጥ ማስቀጠል እና ውጤቶችን ማስመዝገብ ይገባል፡፡

በአሁኑ ወቅት መንግሥት የሀገራችንን ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና ለማረጋገጥና የሕዝባችንን የልማት ተጠቃሚነት ለማስፋት በርካታ ሀገራዊ ተልዕኮዎችንና ሜጋ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል።

እነዚህን የመንግሥት ተልዕኮዎች ማሳካትና ሀገርን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሚቻለው ደግሞ እንደ አረፋ ያሉ የበዓሉ እሴቶችን ወደ ሀገራዊ የሥራ ባህሎች በመቀየር በታማኝነትና በፍትሐዊነት ስንሠራ ነው።

በተለይም በሀገራችን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ልዩነቶቻችንን በውይይት ለመፍታት የሚያስችል በመሆኑ ዓላማው ከግብ እንዲደርስ እርስ በርስ ይቅር በመባባልና በመደማመጥ ዘላቂ ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር ይገባል፡፡

የእምነቱ ተከታዮችም ለዚህ ሀገራዊ ምክክር ስኬታማነትና ለዘላቂ ሠላም ግንባታ እንደሁልጊዜው የበኩላችሁን አዎንታዊ ሚና እንድትጫወቱ ምክር ቤቱ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

ኢትዮጵያ በቀጣይ ቀናት የምታካሂደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሕዝባችንን የዕድገትና የልማት ጥያቄዎች ለመመለስና ጠንካራ ተቋማትን ለመገንባት መሠረት የሚጥል ነው፡፡ በዚህ ጠቅላላ ምርጫ የዴሞክራሲ ስርዓታችንን የምናጠናክርበትና የሕዝባችንን የወደፊት እጣ ፈንታ በነጻነት የምንወስንበት ታሪካዊ መድረክ በመሆኑ ማህበረሰቡ በሠላማዊና በሰለጠነ መንገድ በምርጫው ሂደት ላይ በንቃት በመሳተፍ የዴሞክራሲ ዕሴቶች እንዲጎለብቱ የበኩሉን አሻራ ሊያኖር ይገባል።

እንዲሁም ምርጫው ሠላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የእምነቱ አስተምህሮ የሚጠይቀውን የኃላፊነት ስሜት በታማኝነትና ለሀገር ደህንነት በጽናት መቆምን በተግባር ማሳየት ይገባል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የአረፋ በዓል በእውነተኛ መስዋዕትነት፣ ታዛዥነትና ታማኝነት ላይ ተመሥርቶ የሚከበር ታላቅ በዓል በመሆኑ መላው የሀገራችን ሙስሊም ማህበረሰብ ይህንን ታላቅ በዓል ሲያከብር የተለመደውን የደግነትና የወንድማማችነት ዕሴት በማንገብ ለተቸገሩት ማዕድ በማጋራት፣ ለአገራዊ ምክክሩ ስኬት በጋራ በመቆም፣ ለምርጫው ሠላማዊነት ኃላፊነታችንን በመወጣት በአጠቃላይ መላው የሙስሊሙ ማህበረሰብ ከመንግሥት ጎን በመቆም ሠላምን በመጠበቅ እና በልማት ሥራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ ሀገራዊ ተልዕኮአችን እንዲሳካ የበኩሉን እንዲወጣ ምክር ቤቱ ጥሪውን ያስተላልፋል።

በድጋሚ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሣችሁ!

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት!

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በፌስቡክ http://www.facebook.com/hoprparliament
በዩቲዩብ
https://www.youtube.com/
በቴሌግራም
https://t.me/ParlamaNews
በትዊተር
http://twitter.com/fdrehopr
በዌብሳይት
www.hopr.gov.et ይከታተሉ።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Website

Address

House Of Peoples' Representatives Of FDRE
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00