29/05/2025
የአዲስ አበባ ሆቴሎች ዳግም የኮከብ ደረጃ ምዘና ውጤት ይፋ ኾነ
| በቱሪዝም ሚኒስቴር ሲካሄድ የነበረው የ2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ሆቴሎች የዳግም የኮከብ ደረጃ ምዘና ውጤት ይፋ አድርጓል፡፡
በምዘናው የ40 ሆቴሎች ውጤት ይፋ ያደረግ ሲሆን ከባለ 5 ኮከብ ደረጃ እስከ ባለ አንድ ኮከብ ደረጃ ያገኙ ሆቴሎች ደረጃው ተሰጥቷቸዋል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የቱሪስት አገልግሎቶች ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ታሪኩ ደምሴ በንግግራቸው የቱሪዝም ሚንስቴር የቱሪስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ደረጃ የመወሰን እና ተፈፃሚነታቸውን የመከታተል ስልጣን እንዳለው ጠቅሰው ምዘና ከተደረገላቸው ከ40 ሆቴሎች ውጤት ውስጥ 34 ሆቴሎች በዳግም ደረጃ ምዘና የተደረገላቸው ሲሆን 6 ሆቴሎች አዲስ የተመዘኑ ሆቴሎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡
አክለውም በመዲናችን የነበሩ የባለ 5 ኮከብ ሆቴሎች በተጨማሪ 3 ሆቴሎች የባላ 5 ኮከብ ደረጃ አግኝተዋል ያሉ ሲሆን አዲስ ከተመዘኑ ሆቴሎች መካከል 2 ተጨማሪ ባለ 4 ኮከብ ሆቴሎች ተቀላቅለዋል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል በዳግም ደረጃ ምዘናው ከነበራቸው ከኮከብ ደረጃቸው የወረዱ ሆቴሎች ቢኖሩም የተወሰኑ ሆቴሎች ደግሞ ከነበራቸው ደረጃ ከፋ ያሉም ይገኙበታል ሲሉ አክለዋል፡፡
የምዘናው ላይ የሚንስቴር መ/ቤቱና ከክልሎች የተወጣጡ የባለሙያ ቡድኖችን በማደራጀት እንዲሁም በሁሉም ዘንድ ታአማኒነት እንዲኖረው በታዛቢነት 6 የሙያና የሆቴል ዘርፍ ማህበራት በሂደቱ እንዲሳተፉ ተደርጓል ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ባለ 5 ኮከብ ደረጃ ያገኙ ሆቴሎች
***
1. ሀያት ሬጄንሲ ሆቴል
2. ስካይ ላይት ሆቴል
3. ሸራተን አዲስ ሆቴል
4. ኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል
5. ካፒታል ሆቴል
6. ራዲሰን ብሉ ሆቴል
7. ማሪዮት ኤክስኪዩቲቭ ሆቴል
8. ጎልደን ቱሊፕ ሆቴል
9. ሂልተን አዲስ ሆቴል
10. ኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል
11. ኔክሰስ ኢን ሆቴል
27/05/2025
ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ
ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ፓርኮች መካከል የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ቀዳሚ ነዉ፡፡ ፓርኩ በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በስተ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 120 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ ረጅሙን ራስ ደጀን ተራራን ጭምር አቅፎ ይዟል፡፡
የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኙ ዋልያ፣ ቀይ ቀበሮ፣ ጭላዳ ዝንጀሮ፣ የምኒልክ ድኩላ ወዘተ... የመሳስሉ ብርቅዬ እንስሳቶችን መገኛ ነው። ከ2 መቶ የአእዋፍ ዝርያዎች የመጠለያ ጎጇቸው ነው። ከእዚህ የአእዋፍ ዝርያዎች መካከል አምስቱ በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ ናቸው።
በሌላ በኩል ከ1ሺህ 200 በላይ የተለያዩ የዕፅዋት ዝርያዎች በፓርኩ ዉስጥ ይገኛሉ፡፡ አስደናቂውን ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) እ.ኤ.አ. በ1978 ዓ.ም በዓለም በቅርስነት መዝግቦታል፡፡
የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ሀገራችን ከቱሪዝም ዘርፉ ለምታገኘዉ ገቢ ድርሻ እጅግ የጎላ ነዉ፡፡ አስደማሚውን የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ይጎብኙ!
Amhara
27/04/2025
16ኛው የቦሌ ክፍለ ከተማ የኪነ ጥበብ ሳምንት ውድድር ተካሄደ፡፡
**************************
“የወል ትርክታችን ለነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ ውድድር ከአሥራ አንዱም ወረዳዎች የተውጣጡ ተወዳዳሪዎች በባሕላዊና ዘመናዊ ውዝዋዜ፣ በተውኔት፣ በሥዕል፣ በድምጽ፣ በመነባንብ፣ በአጭር ፊልም እና በሰርከስ ምድቦች በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና በአማተር ክበባት ውድድር ያደረጉ ሲሆን፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ባሕል ኪነጥበብ እና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ራቢያ ያሲን በውድድሩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር መንግሥት ኪነጥበብ በሀገር ግንባታ ያለውን ጉልህ ሚና በመገንዘብ ለዘርፉ ማደግ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝና የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደርም የኪነጥበብ ዘርፉ የሚጠበቅበትን ሚና በአግባቡ እንዲጫወት በላቀ ትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ የኪነጥበብ ውድድሩ ከውድድር ባሻገር በክፍለ ከተማው የሚገኙ አማተር የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ታዳጊዎች አቅማቸውን ወደ አደባባይ እንዲያወጡ ዕድል የሚሰጥ እንደሆነ ያመለከቱት ኃላፊዋ፣ በክፍለ ከተማ ደረጃ በሚደረገው ውድድር በየዘርፉ አሸናፊ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በሚካሄደው ከተማ አቀፍ የኪነጥበብ ሳምንት ውድድር ቦሌን ወክለው የሚሳተፉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ሚያዚያ 19/2017
***************************
18/03/2025
🇪🇹
የቦሌ ክፍለ ከተማ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የ6 ወር የሥራ አፈጻጸም ምዘና በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙት አሥራ አንድ ክፍለ ከተሞች የ3ኛ ደረጃን አገኘ።
ጽ/ቤቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዘርፉ ባከናወነው የላቀ አፈጻጸም የ3ኛ ደረጃ በማግኘቱ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ሰርተፊኬት የተበረከተለት ሲሆን፣ በጽ/ቤቱ ሥር ከሚገኙ ቡድኖች የሆቴሎች አገልግሎት አሰጣጥ ቡድን 1ኛ ፣ የቤተ-መፃህፍት ቡድን 2ኛ ፣ የኪነ-ጥበብ መድረኮች ቡድን 3ኛ ከሁሉም የክፍለ ከተማ አቻ ቡድኖች መካከል በአፈጻጸማቸው በመውጣት የላቀ ውጤት አስመዝግበዋል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ራቢያ ያሲን በበጀት አመቱ በ6ወር ውስጥ ለተመዘገበው የአፈፃፀም ውጤት የክፍለ ከተማው ኮር አመራር፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አጠቃላይ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ላደረጉት አስተዋጽኦ በጽ/ቤቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል።