02/06/2026
ከባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የተላለፈ የምስጋና መልዕክት፣
ግንቦት 25/2018 ዓ.ም
ውድ የባስኬቶ ዞን ህዝቦች፣ የብልፅግና ፓርቲ አባላት እና ደጋፊዎች፤
በ7ኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ሂደት ወቅት በከፍተኛ ንቃት፣ ኃላፍነት በተሞላ መንገድ ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁት አስተዋጾ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በህደቱ በንቃት በመሳተፍ እንዲሁም በድምጽ መስጫ ዕለት ከማለዳ እስከ ምሽት በትዕግስት በመጠበቅ ድምጻችሁን በመስጠት ኃላፊነታችሁን የተወጣችሁት ለሀገራችን የዴሞክራሲ ጉዞ ጉልህ አስተዋጽኦ ያለው በመሆኑ ላደረጋችሁት ሁሉ ከልብ እያመሰገንን
ፓርቲያችን ብልጽግና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህልና በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ፓርቲዎች ተፎካክረው ህዝብ በህጋዊ መንገድ በሚሰጣቸው ድምጽ ብቻ ስልጣን እንድያይዙ ማድረግ አንዱ የዴሞክራሲ ባህል መሆኑን የሚያምን በመሆኑ በምርጫው ከዝግጅት ጊዜ ጀምሮ በዞናችን በምርጫው ላይ ከተወዳደሩ ፓርቲዎች ጋር የጋራ ጉዳዮች ላይ አብሮ ስሰራ ቆይቷል።
በመሆኑም በዞናችን ምርጫው በሠላም እንድጠናቀቅ ላደረጋችሁት አስተዋጾ እያመሰገንን ምርጫው ሠላማዊ ሆኖ መጠናቀቁ የህዝባችን የዴሞክራሲ ባህል እያደገ መምጣቱን፣ ለሰላም፣ ለልማት እና ለእድገት ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው።
በመሆኑም ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠል መስራት እንዳለብን እየገለጽን እስከ አሁን የምርጫው ህደት ያለምን ኮሽታ በሠለማዊ መንገድ እንድጠናቀቅ ላደረጋችሁ የጸጥታ አካላትና መላው ህዝባችን ምስጋና እያቀርብን ቀጣይ በምርጫ ቦርድ በኩል የምገለጸውን ውጤት በመከታተል የኢትዮጵያን ማሸነፍ እናረጋግጣለን ።
የባስኬቶ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት
ግንቦት፣25/2018ዓ.ም
ላስካ
01/06/2026
በኦብጫ ማንዲታ ቀበሌ ሁለት የታዛቢዎች ባጅ ይዞ የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሎ 3500 ብር ተቀጣ
ላስካ፦ግንቦት 24/2018 ዓ.ም
በባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ በኦብጫ ማንዲታ ቀበሌ በሚገኘው ኦብጫ ጫማና ምርጫ ጣቢያ ሁለት የታዛቢዎች ባጅ በመያዝ ሕገ-ወጥ የምርጫ ማጭበርበር ወንጀል የፈጸመው ግለሰብ በገንዘብ ተቀጣ።
ተከሳሹ አቶ ወንድሙ ምታቸው የተባለው ግለሰብ በምርጫ ጣቢያው መገኘት ከሚገባው ሕጋዊ አሠራር ውጪ ሁለት የታዛቢዎች ባጅ በአንድ ላይ ይዞ ለማጭበርበር ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ሥር ውሏል።
የግለሰቡን ሕገ-ወጥ ድርጊት የተመለከተው ለዚሁ ተግባር የተቋቋመው ጊዜያዊ ችሎት ፍርድ ቤት የቀረቡትን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ ግለሰቡን ጥፋተኛ ነው ብሎታል።
በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ አቶ ወንድሙ ምታቸው ላይ የ3 ሺህ 500 (ሦስት ሺህ አምስት መቶ) ብር የገንዘብ መቀጮ ውሳኔ አስተላልፎበታል።
ይህ እርምጃ የምርጫውን ፍፁም ሰላማዊነት፣ ታማኝነትና የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተዘረጋው የቁጥጥር ሥርዓት በተሟላ ሁኔታ እየሠራ መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ነው የተጠቆመው።
ግንቦት 24/2018 ዓ.ም
ላስካ
01/06/2026
እስካሁን ባለው የምርጫ ሂደት ያልተገባ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አልታየም - ኢሰመኮ
ግንቦት 24/2018 ዓ.ም
እስካሁን ባለው የምርጫ ሂደት ያልተገባ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አልተመለከትሁም አለ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ)።
በኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የተመራ የኮሚሽኑ ቡድን በአርባምንጭና በጅማ ምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደትን ተመልክቷል፡፡
በዚህ ወቅት ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ እንዳሉት÷ ለአካል ጉዳተኞች ጭምር የተመቻቹ የምርጫ ጣቢያዎች ተመልክተዋል።
የምርጫ መስፈርቶችን ያሟላ የምርጫ ሂደትን መታዘባቸውንም ተናግረዋል።
የምርጫ ሂደቱ ፍጹም ሰላማዊና መስተጓጉል ያልታዩበት መሆኑን ጠቅሰው፥ ቡድኑ እስካሁን ባለው የምርጫ ሂደት ያልተገባ የሰብዓዊ መብት አያያዝ አለመመልከቱን ገልጸዋል።
የምርጫ ታዛቢዎች እና መራጩ ዜጋ በሰዓቱ በምርጫ ጣቢያው በመገኘት ምርጫውን ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ኮሚሽኑ በ175 የምርጫ ክልሎችና ከ2 ሺህ 700 በላይ በሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች የመታዘብ ሥራውን እያከናወነ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
በምርጫ ሂደቱ ያለውን የሰብዓዊ መብት ሁኔታ በመከታተልና በድህረ ምርጫ የሚኖረውንም ሂደት በአግባቡ በመምራት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
በምርጫ ሂደቱ ቅሬታዎችን ለማስተናገድ በተዘጋጀው የቅሬታ መከታተያ ስርዓትም የምርጫውን ሂደት እየተከታተለ እንደሆነ አስረድተዋል።
ምርጫው ሕብረተሰቡ ለቀጣይ አምስት አመታት የሚመራውን አካል በድምጹ የሚያረጋግጥበት በመሆኑ እንደሀገር ለመምረጥ የተመዘገበው ከ54 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ይበጀኛል የሚለውን ፓርቲ በመምረጥ ሕገመንግስታዊ መብቱን እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል።
01/06/2026
በባስኬቶ ዞን ባስኬቶ ልዩ ምርጫ ክልል መራጩ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ የወደደውን ፓርቲ እየመረጠ ነው
ተዘዋውረን ምልከታ ባደረግንባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በተረጋጋ ሁኔታ መራጩ ህዝብ በቀጣይ ያስተዳድረኛል ይወክለኛል ላለው ፓርቲ ድምጹን በመስጠት ላይ ነው።
በባስኬቶ ልዩ ምርጫ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ዶክተር ኤልያስ አሰፋ በባስኬቶ ልዩ ምርጫ ክልል ቦላ ባስኬቶ አርብ ገበያ ምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጽ ሰጥተዋል።
ያነጋገርናቸው መራጮች ምርጫው ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲያው መሆኑን ገልጸው ይወክለኛል ያስተዳድረኛል ያሉትን ፓርቲ መምረጣቸውን ገልጸዋል።
ዘገባው #ደሬቴድ
01/06/2026
መራጮች ስለ ምርጫው ፍትሐዊነትና ግልጽነት ያላቸውን እምነት ገለጹ
ግንቦት 24/2018 ዓ/ም
በባስኬቶ ዞን በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ካለፉት የምርጫ ታሪኮች በተለየ መልኩ ፍትሐዊ፣ ግልጽና ነጻ በሆነ መንገድ እየተከናወነ እንደሚገኝ ያላቸውን እምነትና አስተያየት ገለጹ።
በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች በመዘዋወር ያነጋገርናቸው መራጮች ያለምንም ውጫዊ ጫና ወይም ክትትል፣ ድምፅ መስጫ ክፍሉ ውስጥ በነፃነት በመግባት የሚፈልጉትን ፓርቲ ምልክት በምስጢር መምረጥ መቻላቸው ለሂደቱ ፍትሐዊነት ትልቅ ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል።
በምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ የገዥው ፓርቲም ሆነ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ታዛቢዎች እኩል ተገኝተው ሂደቱን በቅርብ መከታተላቸው፣ በድምፅ አሰጣጡ ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ የአሰራር ግድፈቶችን ያስቀረና እምነት የጣሉበት መሆኑን መራጮች አረጋግጠዋል።
የዕድሜ ባለጸጎችና አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ ማግኘት በጣቢያዎች ውስጥ ለነፍሰ ጡር እናቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለሽማግሌዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ ያለምንም እንግልት ድምፅ እንዲሰጡ መደረጉ የሂደቱን ሰብአዊና ፍትሐዊ አቀራረብ እንደሚያሳይ ተጠቅሷል።
ካለፉት የምርጫ ልምዶቻችን ጋር ስናነጻጽረው የዘንድሮው ምርጫ የሕዝብ ድምፅ የሚከበርበት መሆኑን ከመነሻው ማየት ችለናል ሲሉ መራጮች ገልጸዋል።
መራጮች ምርጫው ሙሉ በሙሉ በራሳችን ህሊናና ፍላጎት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ፍትሐዊነቱ የታመነ ነው ብለዋል።
የተለያዩ ፓርቲዎች ታዛቢዎች እዚያው ቁጭ ብለው ሲያዩ ስንመለከት ሂደቱ ግልጽ እንደሆነ እንረዳለን ያሉት መራጮች የእኛ ድምፅ በትክክል ተቆጥሮ የሕዝብ ውሳኔ ይፋ እንደሚሆን ሙሉ ተስፋ አለን ሲሉም ስሜታቸውን አጋርተዋል።
ግንቦት 24/2018 ዓ/ም
ላስካ
01/06/2026
ደቡብ ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው
እርሶስ መርጠዋል?
01/06/2026
የምርጫ ማጭበርበር ወንጀል ፈጽሞ የተገኘው ግለሰብ በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ
ላስካ፦ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም
በባስኬቶ ዞን በላስካ ዙሪያ ወረዳ በሣሣ ማኬሳ ቀበሌ በሚገኘው ድንጋላ ገበሬዎች ማሰልጠኛ ምርጫ ጣቢያ በዛሬው ዕለት የምርጫ ማጭበርበር ወንጀል ፈጽሞ የተገኘው ግለሰብ በገንዘብ መቀጮ ተቀጥቷል።
ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ረፋድ በግምት 5:30 ሰዓት ላይ የሌላ ሰውን የምርጫ ካርድ በመያዝ ለማጭበርበር የሞከረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተይዞ የገንዘብ መቀጮ ተወስኖበታል።
ተከሳሽ ኤርሚያስ መትሶ የተባለው ግለሰብ የኢዜማ (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ) ፓርቲ አባልና ለትብብር አንድነት ታዛቢ በመሆን ባጅ ለብሶ በምርጫ ጣቢያው ተገኝቶ ነበር።
ተከሳሹ የራሱ ያልሆነውን እንዲሁም ሕጋዊ መኖሪያ ቦታው ምርጫ ከሚደረግበት ክልል ውጪ የሆነውን የአቶ ብላቴ ሳንገኘው የተባሉ ግለሰብን የድምፅ መስጫ ካርድ በመያዝ ሕገ-ወጥ በሆነ መንገድ ለማጭበርበር ሲሞክር በወቅቱ በነበረው ጥብቅ ቁጥጥር እጅ ከፍንጅ ሊያዝ ችሏል።
የወረዳው ዓቃቤ ሕግ የወንጀል ድርጊቱን አስመልክቶ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 471 (ሐ)ን በመጥቀስ ተከሳሹን በሰነድና በሰው ማስረጃዎች በማስደገፍ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የመንደታ ጊዜያዊ ችሎት ፍርድ ቤት ክስ መስርቶበታል።
የዓቃቤ ሕግን የሰውና የሰነድና የሰው ማስረጃዎች በሚገባ መርምሮ በመቀበል የተከሳሽንም የመከላከያ ማስረጃዎችና ሐሳብ በዝርዝር ካደመጠ በኋላ ተከሳሽ ኤርሚያስ መትሶ ዓቃቤ ሕግ በጠቀሰው የወንጀል ድንጋጌ ቁጥር 471(ሐ) ሥር ጥፋተኛ መሆኑን አረጋግጧል።
በዚህም መሠረት ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ አቶ ኤርሚያስ መትሶ በ4 ሺህ 500 (አራት ሺህ አምስት መቶ) ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።
የተወሰደው ፈጣንና ሕጋዊ እርምጃ የምርጫውን ፍፁም ታማኝነት፣ ሰላማዊነትና የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተዘረጋው ሥርዓት በሚገባ እየሠራ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል።
ግንቦት 24/2018 ዓ.ም
ላስካ
01/06/2026
ዶ/ር ኤልያስ አሰፋ በምርጫ ክልላቸው ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።
ግንቦት 24/2018 ዓ/ም
ብልጽግና ፓርቲን በመወከል የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዕጩ ተወካይ ዶ/ር ኤልያስ አሰፋ ባስኬቶ ልዩ ምርጫ ክልል ዓርብ ገበያ መንደር ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፅ ሰጥተዋል።
ግንቦት 24/2018 ዓ/ም
ላስካ
27/05/2026
የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ በመገኘት የአንግላ "Comprehensive Health Center” መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አደረጉ።
ግንቦት 19/2018 ዓ.ም
የፌደራል፣ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ በመገኘት የአንግላ Comprehensive Health Center” መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
የአንግላ "Comprehensive Health Center” ከዛው ቀን ጀምሮ ከአንግላ ቁ1-ቁ5 ለአምስት ቀበሌዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጻል።
በጤና ማዕከሉ ምረቃ ፕሮግራም ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባስኬቶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዕጩ ዶ/ር ሳሙኤል ደሳለኝ መንግስት የመከላከልና አክሞ የማዳን ጤና ፖሊስን መሠረት በማድረግ ባለፉት ጥቅት የለወጥ አመታት ተጨባጭ ለውጦችን አስመዝግቧል ብለዋል።
ብልጽግናን ለማረጋገጥ ጤናማ ዜጋ መፍጠር ተቀዳሚው አጀንዳ ነው ያሉት አስተዳዳሪው የማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅ በርካታ ተግባራት መፈጸማቸውን ገልጸዋል።
ተቋሙ የታለመለትን አገልግሎት መስጠት እንዲችል መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ያሉት ዕጩ ዶ/ር ሳሙኤል ደሳለኝ ህብረተሰቡ የተቋሙን ጉድለቶች በየጊዜው እየገመገመ እንዲሞላ አሳሰበዋል።
የባስኬቶ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሬህይወት ቃናኦ በዞኑ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት በርካ ተግባራት እየተፈጸመ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የላስካ ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተመስገን አዘነ በብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት የዜጎችን ጤና ለመጠበቅ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል።
የላስካ ዙሪያ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ታጎ የጤና ማዕከሉ ከዛሬ ጀምሮ ከአንግላ ቁ1-ቁ5 አምስቱን ቀበሌዎች ተደራሽ ያደረገ አገልግሎት እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
የአንግላ ክላስተር ነዋሪዎች በበኩላቸው የጤና ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ በርቀት ምክንያት የሚደርሳቸውን የገንዘብና የጤና ጉዳት የሚቀንስላቸው በመሆኑ አመስግነዋል።
በምረቃው በሚንስትር ማዕረግ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና ውሳኔ አፈጻጸም ቋሚ ኮሚቴ ፀሐፊ ክብርት ፍሬሕይወት ዱባሌን ጨምሮ የክልልና የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
ግንቦት 19/2018 ዓ.ም
ላስካ
27/05/2026
ብልጽግናን ይምረጡ
የምርጫ ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው