04/06/2026
የአራተኛ ሩብ ዓመት የወረዳዎች ድጋፍና ክትትል ግብረመልስ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
===============================
25/9/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ
የአቃቂ ቃሊቲ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በስሩ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የአራተኛ ሩብ ዓመት ድጋፍና ክትትል ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በተገኙ ውጤቶችና መስተካከል ባለባቸው ግብረመልሶች ዙሪያ ከወረዳዎች የዘርፉ ብድን መሪዎችና አስተባባሪዎች ጋር የጋራ መድረክ አካሂዷል። በውይይት መድረኩ የተለዩ ክፍተቶችና በጥንካሬ የሚወሰዱ ግኝቶች ተጠምረው የቀረቡ ሲሆን በመድረኩ አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል። በውይይት መድረኩ የተገኙት የጽ/ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳ ይህ ኦዲት መሰል ድጋፍና ክትትል ሁሉም ወረዳ ያለበትን ቁመና በግልፅ ያመላከተ መሆኑን ገልፀው የዓመቱ መጨረሻ ላይ የምንገኝ እንደመሆናችን በክፍተት የታዩ ስራዎች በከፍተኛ ተኩረት በቀናት ውስጥ ተጠናቀው መቀረብ ያለባቸው መሆኑን በአጽንኦት አንስተዋል። በመጨረሻም የዚህ ዓመት አፈጻጸማችን እንደ ከዚህ ቀደሙ ቀዳሚ በመሆን በውጤት እንደሚደመደመ መግባባት ላይ ተደርሷል።
20/05/2026
የስራና ክህሎት ጽ/ቤት በ9 ወራት ውስጥ የወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ከ37 ሺ በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የስራ ዕድሎችን መፍጠሩን ገለፀ።
ግንቦት 12/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ክህሎት መር የሆነና ውጤት ተኮር የሥልጠና ሥርዓትን በመዘርጋት ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል የማፍራት ተልዕኮውን በስኬት እየተወጣ ይገኛል።
ጽ/ቤቱ በተለይም የወጣቶችንና የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥን ዋነኛ ግቡ ያደረገው ይህ ተቋም አምራች ዜጎችን ወደ ሥራ በማስገባት ለሀገር ዕድገት የድርሻውን እያበረከተ ነው።
በ2017 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች አንደኛ በመውጣት ተሸላሚ የነበረው ጽ/ቤቱ በ2018 በጀት ዓመትም ይህንኑ የላቀ ድል ለማስቀጠል የሚያስችሉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። የሥራ ዕድል ፈጠራው ከዕለት ጉርስ ባለፈ ቋሚ የሥራ አጥነትን ችግር ለመቅረፍ ያለመ ሲሆን ፣ ክፍለ ከተማው ያሉትን ጸጋዎች በመለየት ለዜጎች ዘላቂና ጊዜያዊ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ውጤታማ የሥራ ስምሪት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በበጀት ዓመቱ በ9 ወራት ውስጥ ለማህበረሰብ በግንዛቤ ፈጠራ ረገድ ሰፊ ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን፣ ለ91 ሺህ 772 ነዋሪዎች እንዲሁም በሥራ ባህልና ምርታማነት ዙሪያ ለ71 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተደርጓል። በተጨማሪም ለ45 ሺህ ሥራ ፈላጊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በመስጠትና ለ37 ሺህ ሰልጣኞች የክህሎት ሥልጠና በማመቻቸት ለሥራ ዝግጁ እንዲሆኑ ተደርጓል። ይህም ጽሕፈት ቤቱ ከዕቅዱ በላይ አፈጻጸም እንዲያስመዘግብ አስችሎታል።
የሥራ ዕድል ፈጠራንና የኢንተርፕራይዝ አደረጃጀትን በተመለከተ፣ ለ36 ሺህ 995 ዜጎች ሥራ ለመፍጠር ታቅዶ ለ37 ሺህ 090 ሥራ ፈላጊዎች ዕድሉ የተመቻቸ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ 32 በመቶው በመደበኛ ዘርፍ የተፈጠሩ ናቸው። በተመሳሳይ 1 ሺህ 594 ኢንተርፕራይዞችን በማደራጀትና 43 ሺህ 721 የሥራ ዕድል መፍጠሪያ ጸጋዎችን በማጥናት ለሥራ ፈላጊዎች አዳዲስ አማራጮችን ማሳየት ተችሏል። ይህም ዜጎች የሥራ ፈጣሪነት መንፈስን እንዲያዳብሩ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል።
ኢንተርፕራይዞችን ከማጠናከር አንጻር ለ510 ኢንተርፕራይዞች የ204 ሚሊዮን ብር የብድር አቅርቦት የተመቻቸ ሲሆን፣ 150 የሚሆኑት ደግሞ የመሣሪያ ሊዝ ድጋፍ አግኝተዋል። የቁጠባ ባህልን በማሳደግ በኩልም 1 ሺህ 475 ኢንተርፕራይዞች ከ327 ሚሊዮን ብር በላይ በፍቃደኝነት መቆጠብ የቻሉ ሲሆን፣ 544 ኢንተርፕራይዞች ከጀማሪ ወደ አንስተኛ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ተደርጓል። ይህ ስኬታማ ጉዞ 58 ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን በማፍራት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተሞክሮ ተመዝግቧል።
13/05/2026
ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ መሠረታዊ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ተጀመረ !
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ግንቦት 5/2018 ዓ.ም
ለተከታታይ 12 ቀናት የሚቆይ የብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ መሠረታዊ የሕይወት ክህሎት ስልጠና ዛሬ በአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተጀመረ።
ስልጠናው ወጣቶች በሥራ ቦታ የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ለመቋቋም፣ የግንኙነት፣ የቡድን ሥራ፣ የችግር አፈታት እና የውሳኔ አሰጣጥ ክህሎቶችን ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሬጅስትራል ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ጥላሁን ገልፀዋል ።
ፈቃድ ያላቸው በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ስርአጥ ስደተኞች ስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ና ባሉ ድርጅቶች በሚመርጡት ዘርፍ የስራ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ አላማ ያደረገ ስልጠና መሆኑን የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፕሮጀክት አስተባባሪ ኑርሰማ ረሽድ ገልፀዋል ።
ስልጠናው ከሙያ ብቃት ጎን ለጎን የሰዎች ግንኙነት እና የራስን ሕይወት የማቀናጀት አቅምን በማጎልበት ወጣቶችን ለሥራ ገበያ የተሻለ ዝግጅት ለማድረግ ዓላማ ያደረገ እንደሆነ የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን ወ/ሮ ፋንታዬ ባብሎ ገልፀዋል ። አያይዘውም አስተሳሰብ ቀይረን እውቀት ለመጨመር ያለመ ስልጠና ስለሆነ ስልጠናው በተገቢው መልኩ እንዲካሔድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል ።
13/05/2026
የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የሪፎርም ኮሚቴ አባላት የስራ አፈፃፀም ውይይት አካሄዱ።
አቃቂ ቃሊቲ 5/09/2018 ዓ.ም
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የሪፎርም ኮሚቴ አባላት የስራ አፈፃፀም ውይይት በዛሬው ዕለት አካሂደዋል። የጽ/ቤቱ የአባይት ተግባራት አፈፃፀም የሚመሩ የተለያዩ ኮሚቴዎች እስካሁን ያለቸው አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበና ቀሪ ስራዎች የተለዩበት ውይይት የተካሄደ ሲሆን ውይቱን የጽ/ቤቱ ም/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳና የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ አስተባባሪ አቶ አታኸልቲ ፀጋዬ መርተውታል። የጽ/ቤቱ የሪፎርም ስራዎች በተሻለ አፈፃፀም ላይ የሚገኙ መሆኑ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል። በመጨረሻም የጽ/ቤቱ ም/ጽ ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳ የዓመት ተግባራችንን በዚህ ወር መጨረስ እንደሚገባ አንስተው ያላለቁና መስራት ያለባቸው ተጨማሪ ስራዎች በፍጥነትና በጥራት ሊጠናቀቁ እንደሚገባ በማሳሰብና አቃጣጫዎችን በመስጠት የውይይት መድረኩ ተጠናቋል።
08/05/2026
የአንጎላ ልኡካን ቡድን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የስራ ጉብኝት አደረገ
ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ጽ/ቤት በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት እና ስራ ፕሮጀክት (UPSNP) ዙሪያ ከአንጎላ ሀገር ለመጡ ልኡካን ቡድን አባላት ልምድና ተሞክሮ አካፈለ።
በአለም ባንክ እና በኢትዮጵያ መንግስት የፋይናንስ ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው ይህ ፕሮጀክት፣ በክፍለ ከተማው በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ፕሮጀክቱ በዋናነት የአረንጓዴ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ፣ የከተማ ጽዳትና ውበት፣የከተማ ግብርና ስራዎችን ያቀፈ ነው።
እነዚህ ተግባራት መንግስት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻልና የስራ እድል ለመፍጠር የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳዩ መሆናቸው በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።
የአንጎላ ልኡካን ቡድን በተለይ በክፍለ ከተማው ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘውን "የብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም" ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የፌዴራል፣ የከተማ እና የክፍለ ከተማ የስራ ኃላፊዎችና አስተባባሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ ልኡካኑ በአምራች ድርጅቶች ውስጥ ያለውን የስራ እንቅስቃሴ በአካል ተመልክተዋል።
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተከናወነ ያለው የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ውጤታማ በመሆኑ እናኢትዮጵያ ከተረጂነት ወደ ምርታማነትእያደረገች ያለችዉን ጉዞ አድንቀዉ የአንጎላ መንግስት ይህንን ተሞክሮ በመውሰድ በሀገሩ ተግባራዊ ለማድረግ መሆኑ ተጠቁሟል።
24/04/2026
የሁለተኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የተፅዕኖ ግምገማ ሂደቱ ያለበት ሁኔታ ተገመገመ።
16/08/2018 ዓ.ም
=================================
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የሁለተኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የተፅዕኖ ግምገማ ሂደቱ ያለበት ሁኔታ ከወረዳዎች ጋር ዛሬ በጽ/ቤቱ ገመገመ። የጽ/ቤቱ ም/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳና የስራ ስምሪት ቡድን መሪ ወ/ሮ ሀመልማል በተገኙበት የሁለተኛ ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ተግባራዊ በተደረገባቸው በረዳዎች ወረዳ 1,3,4,8 impact evaluation assesment ሰራ በተያዘለት ፕሮግራም ለመጨረስ ከ4ቱ ወረዳ ከመጡ አስተባባሪ ቡድን መሪ እና ፎካሎች ጋር ሂደቱን በጥልቀት ገምግመዋል። በድረኩም የታዩ ጠንካራ አፈፃፀሞች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የተነሳ ሲሆን በክፍተት የታዩ የተግባር አፈፃፀሞች ፈጥነው መስተካከል እንደሚገባቸው በጽ/ቤት ም/ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ ዘነበ ወዬሳ ተጠቁሟል። በቀጣይም የስራ ሂደቱ በየጊዜው መረጃ እየተወሰደ እንደሚገመገምና በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ተግባሩ መጠናቀቅ እንደሚገባው ተነስቷል።
21/04/2026
የክፍለከተማው ስራና ክህሎት ጽ/ቤት የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ዘርፍ ቀሪ ዕቅዶች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።
13/08/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ
====================================
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የስራና ክህሎት ጽ/ቤት የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ዘርፍ በዛሬው ዕለት በዘርፉ ቀሪ ዕቅዶች ዙሪያ ከክፍለከተማውና ከወረዳዎች ከተገኙ ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል። ለውይይቱ መነሻ ያቀረቡት የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አኸልቲ ፀጋዬ ሲሆኑ በዘርፉ የሚገኙ ሶስቱን ቡድኖች ማለትም ኢንተርፕራይዝ ድጋፍ፣ገበያ ልማትና የደረጃ እድገትናተሞክሮ ቀመራ ቡድኖች የዘጠኛ ወር አፈፃፀማቸውንና ከአመት ዕቅድ አንፃር የሚቀሩ አፈፃፀሞችን ለይተው አቅርበዋል። ከክፍለከተማና ከወረዳ የተገኙ የስራው ባለቤት የሆኑ ቡድን መሪዎች በቀሪ ዕቅዶች ዙሪያ በቀረበው ሰነድ ላይ የውይይት ሃሰቦችን አንስተው ቀሪ ተግባሮች በምን መልኩ መጠናቀቅ እንደሚገባቸውና እንደተግዳሮት የሚያሰጓቸውን ሃሳቦች አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የጽ/ቤቱ ም/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘነበ ወዬሳ የተነሱ ሃሳቦች ዙሪያ ምላሾችን የሰጡ ሲሆን ቀሪ ዕቅዶችን ቀድሞ በዚህ ወር ማጠናቀቅ ስለሚገባ በነዚህ ተግባራት ዙሪያ የስራ አቅጣጫ የሰጡ ሲሆን በቀጣይም ተግባሩ የደረሰበትን ለመገምገምና ሂደቱን በየጊዜው በጥብቅ መከታተል እንደሚገባ አንስተው የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል።
17/04/2026
በቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን በተጨማሪ ፋይናንስ 3 የምልመላ ሂደት የምልከታ ግብረ-መለስ ሰጠ።
9/08/2018 ዓ.ም አቃቂ ቃሊቲ
==================================
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የፌደራል ሱፐርቪዥን ቡድን በተጨማሪ ፋይናንስ 3 የምልመላ ሂደት፣ የአካባቢ ልማት ትግበራ ቅድመ ዝግጅት ስራዎች እና የኑሮ ማሻሻያ ተግባራትን በክፍለ ከተማውና በ2 ወረዳዎች ባደረገው ምልከታ የተገኘውን ግብረመልስ የ13ቱም ወረዳ ቡድን መሪዎች በተገኙበት የጋራ በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ተችሏል።
11/04/2026
እንኳን ለጌታችን ለመድህኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ‼