Mesganu Arga Moach

Mesganu Arga Moach

Share

Mesganu Arga Moach, Ambassador True believer in possibility !!!!

26/05/2026

መልካም የአረፋ በአል

ለመላው የእሰልምና እምነት ተከታይ ወንድሞች እህቶች ቤተሰቦች ወዳጀችበሙሉ እንኳን ለኢድ አልድሃ የአረፋ በአል በሰላም በጤንነት አደረሳችሁ!!
በአሉ የደስታ እነዲሆን እመኛለሁ !!

Photos from Mesganu Arga Moach's post 20/05/2026

Wonderful season for Arsenal and Arsenals fan
Big congratulations!!

Photos from Mesganu Arga Moach's post 14/05/2026

ቀኑ ለጋዝ አንቸ ለገረምቦ እና ለአጫወደ ማህበረሰብ ልዩ የደስታ ቀን ነበር: ስላደረጋችሁልን መልካም አቀባበል በእጅጉ አመሰግናለሁ::

እናቶች ከየቤታችሁ ቡና ተሸክማችሁ ወተትና እርጎ ይዛችሁ በመምጣት ላሳያችሁን ፍቅር አመሰግናለሁ::

ለናንተ መስራት መድከም ያስደስታል!
ቃል የገባሁትና ቃል ከገባሁት በተጨማሪ ይዤ በመምጣቴ በእጅጉ ደስ ብሎኛል:: የአባቶች የእናቶቻችን ምርቃት ዋጋ አለውና ተሳክቷል::
ውሃው ነክቼም በዓይኔ በማየቴ እድለኛ ነኝ::

ለእናቶቻችን ምን ያህል ደስታ እንደሚሰጥ አውቃለሁ::ንፁህ ውሃ ለማግኝት ስትጏዙት የነበረውን ርቀት ያውም የወንዝ ውሃ ለማግኝት ምን ያህል ስትንከራተቱ እንደነበር በመረዳት ችግሩ አሁን ስለተቀረፈ ደስ ብሎኛል::

የጀመርነው የልማት ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

ምን ጊዜም የእናቶቻችን ምርቃት አይለየን 🤲

Photos from Mesganu Arga Moach's post 12/05/2026

ዛሬ ለጋዝ አንቸ እናቶች ህፃናት እና ማህበረሰብ ልዩ የደስታ ቀን ነው!!

እንኳን ደስ ያላችሁ !!!
የትምህርት ቤት ግንባታው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በይፋ አስጀምረናል!! "የምስጋና የበጎ አድራጎት ድርጅት " ጥረቱ ትሳክቶ ይኸው ዛሬ የትምህርት ቤቱ ግንባታና የውሃው ፕሮጀክት ለማስጀመር በቅተናል:: ቃል ከገባነው የውሃ ፕሮጀክት በተጨማሪ የትምህርት ቤት ግንባታም ማሳካት በመቻላችን በእጅጉ ደስ ብሎኛል:: ህዝብ ተጠቃሚ ሲሆን ከማየት በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ::

ማህበረስባችን ለዘመናት ሲያነሳው የነበረው የትምህርት ቤትና የውሃ ጥያቄ መመለስ በመቻላችን ደስታዬ ታላቅ ነው: የትምህርት ቤት ግንባታ ደረጃውን የጠበቀ አስፍላጊው ግባአት የመማሪያ ክፍሎች: ላይበራሪ :የአስተዳደር ብሎክ : የሶላር መብራትና ሌሎች የውስጥ ቁሳቁሶች የሚሟሉለት ይሆናል::

የጣሊያን መንግስትና የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ሙሉ ወጪውን በመሸፈን ላሳዩት ድጋፍ በቃላት የማይገለፅ ምስጋና አቀርባለሁ::

የረዳን እግዚአብሄር ምስጋና ይግባው::
ለምርቃቱ ያብቃን !!

Photos from Mesganu Arga Moach's post 03/05/2026

በጣም በጣም ደስ ብሎኛል!!

የተጀመረው የጋዛንቸ የንፁህ መጠጥ ውሃ በጥናቱ መስረት 180 ሜ ጥልቀት አስተማማኝ ውሃ ተገኝ ቷል:: በእጅጉ ደስ ብሎኛል!!ሌሎች ስራዎች በተያዘላቸው እቅድ መሰረት ይቀጥላሉ:
በስራው ላይ እየደከማችሁ ላላችሁ የአከባቢው ነዋሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ:::

Photos from Mesganu Arga Moach's post 30/04/2026

ዛሬ በሞህር አክሊል ሐዋሪያት ከተማ ተገኝቼ በቅርቡ ያስመረቅነው ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ስራ የሚጀምርበትና ተማሪዎች መቀበል ስለሚጀምርበት ሁኔታ ከትምህርትባለሙያዎች ከየትምህርት ቤቱ ከተውጣጡ ርዕሰ መምህራን ጋር እጅግ መልካምና ገንቢ ውይይት አድርገናል:: የወርዳው አመራር ላሳያችሁት ቁርጠኝነት በሳል አመራር አመስግናለሁ::
የካቶሊክ ቤተክርስትያን የእምድብር አገረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ፍቅሬ ቃል በገቡት መሰረት ለአዳሪ ትምህርት ቤቱ የሚያገለግሉ የማጣቀሻ መፅሃፍትና ኮምፒውተሮች አስረክበዋል: እጅግ አድርጌ አመስግናለሁ::
የምስጋና የበጎ አድራጎት ድርጅት ትምህርት ቤቱ የማደራጀት ስራ ይቀጥላል::

Photos from Mesganu Arga Moach's post 23/04/2026

ቁፋሮው ተጀምሯል!!

የጋዛንቸ አንደኛና መካከልኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና የአከባቢው ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ እንዲያገኝ የገባነው ቃል እውን ለማድረግ ይኸው ቁፋሮ ተጀምሯል :በቅርቡም ይጠናቀቃል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ :ትብብር እያደረጋችሁ ያላችሁ የዞንና የወረዳ አስተዳደሮች አመሰግናለሁ:: የአከባቢው ማህበርሰብ እንኳን ደስ ያላችሁ!! እኔ በእጅጉ ደስ ብሎኛል ለመመረቅም ያብቃን !!
ትብብር ላደረጋችሁልኝ አጋሮቼን ላቅ ያለ የአክብሮት ምስጋናዬን አቀርባለሁኝ::

የኩነበርንም በቅርቡ እንጀምራለን
ፈጣሪ ይርዳን!!

Photos from Mesganu Arga Moach's post 23/04/2026
Photos from በጉራጌ ዞን የእኖር ወረዳ የመንግስት ኮሚዩንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት's post 14/04/2026

የንፁሀ መጠጥ ውሃ ማህበረሰቡ እንዲያገኝ በገባነው ቃል መሰረት ተጀምሯል። የትምህርት ቤቱ ግንባታ ጎን ለጎን የሚከናወን ይሆናል ።
የረዳችሁን አካላት የጣሊያን አለም አቀፍ ትብብርን ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሀ።

11/04/2026

መልካም የጌታችን የኢየሱሰ ክርስቶስ የትንሳኤ በአል እንዲሆን እመኛለሁ!!

መልካም ፋሲካ !!

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa