ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis

ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis, Political organisation, Addis Ababa.

Photos from ቦሌ 02 ኮሚዩኒኬሽን/Bole 02 Communication's post 05/12/2025
Photos from ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis 's post 02/08/2025

🏆
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በራስ አቅም የተገነባው ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳ ተመረቀ።

በወረዳው ገርጂ 40/60 ኮንዶሚኒየም አካባቢ የተገነባውን ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳ መርቀው የከፈቱት የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር እሸቱ ለማ ባደረጉት ንግግር በክፍለ ከተማው የሚገኙ ወረዳዎች "አንድ ወረዳ፣ አንድ ፕሮጀክት" በሚል መርህ ኅብረተሰቡንና አጋር አካላትን በማስተባበር የልማት ሥራዎችንና ፕሮጀክቶችን በማካሄድ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። "ወረዳዎቻችን የሕዝብን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማሳደግ ከአንድ በላይ ፕሮጀክቶችን አቅደው በመገንባት ላይ ናቸው" ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የወረዳ 14 አስተዳደር ከነዋሪው ኅብረተሰብ ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የእግር ኳስ ሜዳ ወጣቶችና ታዳጊዎች በስፖርት ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ እና ምቹ የመኖሪያ አካባቢ ለመፍጠር ጉልህ ሚና እንደሚጫወት በመግለጽ መላው የወረዳው ነዋሪዎችና አስተዳደሩ ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜና በጥራት እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ርብርብ በክፍለ ከተማው አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የወረዳ 14 አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሱራፌል ባያብል በበኩላቸው በወረዳው በራስ አቅም ለመገንባት ከታቀዱ ሰባት ፕሮጀክቶች መካከል የእግር ኳስ ሜዳ አንዱ መሆኑን ገልጸው፣ ፕሮጀክቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የወረዳው ነዋሪዎችና አጋር አካላት በባለቤትነት መንፈስ በመሥራት ፕሮጀክት በታቀደው መሠረት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውን አመልክተዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ወቅት በቦሌ ክፍለ ከተማ እና በወረዳ 14 አስተዳደር አመራሮች መካከል በተደረገው የእግር ኳስ ጨዋታ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ቡድን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ሐምሌ 26/2017

Photos from ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis 's post 21/07/2025

እንኳን ደስ አላችሁ
ሰበር የድል ዜና

እንኳን ደስ አለን፣እንኳን ደስ አላችሁ!!

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም ካሉት 11ዱም ወረዳዎ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የዘመናዊ ተሸከርካሪ መኪና ተሸላሚ ሆኗል፡፡

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሱራፌል ባያብል እንዲሁም የወረዳ 14 የብልፅግ ፓርቲ
ኃላፊ አቶ ዋገኔ ተሻገር እንደሉት ታላቁ የኢላላ ቃልኪዳን ስኬት እንዲረጋገጥ አሻራቸውን በማሳረፍ ርብርብ ላደረጉ አመራሮች፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የሰላም ሠራዊት አባላትና የጸጥታ አካላት፣ በጎ አክቲቪስት እንዲሁም ባለሀብቶችና ለመላው የወረዳው ነዋሪዎች የወረዳ 14 አስተዳደር ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል ብለዋል ፡፡

በድጋሜ "እንኳን ደስ አላችሁ፣ እንኳን ደስ አለን":!!!!!
የኢላላ ፊርማችን ተረጋግጧል፡፡

ሀምሌ 14 /2017 ዓ ም
#ቦሌ ወረዳ 14 ኮሙኒኬሽን

Photos from ማንሰራራት's post 18/07/2025
18/07/2025

#ኢላላ

ኢላላ ሁለት ግቦች አሉ እነሱም
1) ጠንካራ ውህደት ያለው ዘመኑን የዋጀ ተወዳዳሪና ውሳኔ ሰጭ አመራር መፍጠር መቻል እና
2) ሁሉም የተቋም ኃላፊና ባለሞያ 7/24 የሥራ ባህልን በመላበስ የተቋሙን ዕቅድ አልቆ በመስራት ከ200% እስከ 500% በማሳካትና የሕዝብን እርካታ በማሳደግ ወረዳውን የተሞክሮ ማዕከል ማድረግ ነው። ሁለቱም ተሳክተዋል ቃል በተግባር‼️

ELLALIANS

Photos from ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis 's post 17/07/2025
Photos from ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis 's post 17/07/2025


ቦሌ ወረዳ 14 አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ በቦሌ ክ/ከተማ ከሚገኙ 11ዱም ወረዳዎች በፓርቲ ስራ በ2017 አመታዊ የስራ አፈፃፀም 2ኛ ወጣ ።

2ኛ እንኳን ደስ አላችሁ
ቃል ኪዳን
የኢላላ ቃል የታመነ በውጤት የፀና በቴክኖሎጂ ፈጠራ በትግበራና በተራማጀነቱ የተሞክሮ ማዕከልነቱን በየ ቀኑ በስኬት እያጀበ ከአዲስ አበባ እስከ ባሮ_ጋምቤላ ከቦሌ ወረዳ 14 እስከ አዲስ አባበ ከተማ አስተዳደ የተሞክሮ ማዕከል የሆነው ቦሌ ወረዳ 14 አስተዳደር ዛሬም 2ኛ ደረጀ ይዞ የዓመቱን በጀት ዓመቱን በድል አጠናቋል ።

ቃል ኪዳን ስምምነትና የቃልን በተግባርና በወጤት የማፅናትና ላሰብነው ህልም መሳካት ለሁሉም የስኬት መንገድ አመላካች ቀስት ነው።
14_ኢላላ የተግባር_የይቻላል_ማሳያ_ወረዳ_14
ሀምሌ 10/2017 ዓ ም
#ቦሌ ወረዳ 14 ኮሙኒኬሽን

Photos from ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis 's post 15/07/2025

" የሰባተኛ ዙር አረንጓዴ አሻራ የኦዲት ሥራ
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር የአሯንጓዴ አሻራ ኦዲት ኮሚቴ በክፍለ ከተማ ተዋቅሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ችግኝ ቆጠራ ለማድረግ የሱፐርቪዥኑ ኮሚቴ በወረዳው ተገኝተው ስራ ጀምረዋል።

የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወገኔ ተሻገር በተቀመጠው አቅጣጫ ሱፐርቪዥን ኮሚቴውን አስተባብራዋል ።
ወረዳ 14 ፓርቲ ሚዲያ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🙏🙏
8/11/2017

Photos from ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis 's post 15/07/2025

የወል ቤቶች ፣ ለወል እውነት ፣ ለትውልድ መሰረት !!

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊና ሌሎችንም ጉዳዮች የምንጋራበት የወል ቤት ፣ የወል እውነት እና ለመጪው ትውልድ መሰረቶች ናቸው።

የወረዳው አስተዳደር በበጀት አመቱ የተሰሩ ፕሮጀክቶችን ምረቃ አስመልክቶ ከምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ ተጠሪዎች ጋር ዛሬ ውይይት አድርጓል።

በቦሌ ክ/ከተማ የወረዳ 14 አስተዳደር የኢላላ ቃልኪዳን ውጤት የሆኑ 7ቱ ፕሮጀክቶች በመጪው ቅዳሜ ጀምሮ የመመረቅና ለአገልግሎት ክፍት የማድረግ ስራ እንደሚጀመርና በሁሉም ብሎኮች ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ ውይይት እንደሚደረግም ተገልጿል።

የወረዳው ምክርቤት ቋሚ ኮሚቴ ተጠሪዎች በአስተዳደሩ በበጀት አመቱ የተሰራው ስራ ተዓምራዊ ነው ብለዋል።ወረዳው ለበርካታ አመታት በህዝብ ሲነሱ የነበሩ ችግሮችን የመለሰበትና ለመጪው ትውልድ መሰረት የጣሉ ፕሮጀክቶችን ያጠናቀቀበት መሆኑን በአድናቆት ተናግረዋል።

የወረዳው ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ተጠሪዎች ይህ አመራር ወርቃማው ነው ፤ ለሀገር እና ለትውልድ መሰረት የሚሆኑ ስራዎችን በአጭር ጊዜ የሰራና በቀጣይም ለማስቀጠል አቅም ፣ እውቀትና ክህሎቱ ያለው ነው ሲሉ የወረዳው ህዝብ ዘንድሮ እድለኛም ነው በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል።

በመጨረሻም የ7ቱ ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም አስመልክቶ የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሱራፌል ባያብል "የወል ቤቶች ፣ ለወል እውነት ፣ ለትውልድ መሰረት" በሚል ሰነድ ዙሪያ በሁሉም ቀጠናዎች እና ብሎኮች ከህዝብ ጋር ተከታታይ ውይይት እንዲደረግ አሳስበዋል።

Photos from Bole Woreda 14 Communication's post 15/07/2025
Photos from ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis 's post 04/07/2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሱፐርቪዥን ቡድን በቦሌ ክፍለ ከተማ በተመረጡ ወረዳዎች የሚያደርገውን ምልከታ ዛሬም ቀጥሏል፡፡

ቡድኑ በወረዳ 14 አስተዳደር በመገኘት የአስተዳደሩን የበጀት ዓመቱ የፓርቲና የመንግሥት ተግባራት በሰነድ እና በአካል ምልከታ የሱፐርቪዥን ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

ሰኔ 27/2017

Photos from ቦሌ ወረዳ 14 ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ/Bole Wored 14 political trend analysis 's post 01/07/2025

በወረዳው የተለመደውን የሰንደቅ አላማ መስቀል ሰነ ስራዓት ተካሄዳዋል ።በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14
የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው በማለት የወረዳ 14 አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሱራፌል ባያብል ለአመራሮችና ሰራተኞች ሰነ ስራዓቱ ሁሌሜ ሰረተኛው ስራ ከመግበቱ በፊት በመውጫ ሰዓትም ሰነ ሰራዓቱ አክብሮ ወደ ስራ መግበት እንደለበቸው አሰስቦዋል።
ሰኔ 24/2017
#ቦሌ ወረዳ 14 ኮሙኒኬሽን

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa