31/05/2026
ኢትዮጵያ ትመርጣለች::
ምርጫው ፍጽም ሰላማዊ፣ዲሞክራሲያዊ እና ቅቡልነት ያለው ምርጫ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ ነው።
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን, Government Organization, Tewodros Square, Churchill Avenue, Addis Ababa.
To become competent and effective institution that has been able to create a vibrant civil society sector and a civilized culture that ensures the full benefit of the society by 2030.
31/05/2026
ኢትዮጵያ ትመርጣለች::
ምርጫው ፍጽም ሰላማዊ፣ዲሞክራሲያዊ እና ቅቡልነት ያለው ምርጫ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ ነው።
26/05/2026
የኢፌዲሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዬች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም የጤናና የተቸገሩትን የምንረዳበት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቱን ይገልጻል ።
መልካም በዓል!
25/05/2026
ባለስልጣኑ በአገልግሎት አሰጣጥ እና የስሜት ልህቀት ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ፡፡
*****************************************************************
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በስሩ ለሚገኙ ባለሙያዎች ጥራት ባለው አገልግሎት አሰጣጥ፣ በተገልጋዮች አቀባበል፣ በአካታችነትና የስሜት ልህቀት ላይ ያተኮረ ስልጠና አጋር ከሆኑ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ያካሄደ ሲሆን ስልጠናው የተቋሙን ሰራተኞችና ባለሙያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ አቅም ከማሳደግ ባለፈ ተገልጋዮች ወደተቋሙ ሲመጡ ጥራትንና ቅልጥፍናን ያማከለ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የሚያስችል ነው፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ያሳካቸውን የለውጥ ትሩፋቶች ለማስቀጠል የባለስልጣኑ ባለሙያዎችና ሰራተኞች ትልቅ ድርሻ ያላቸው በመሆኑ መሰል ስልጠናዎችን በመስጠት የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ወጥነት ባለው መልኩ ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል፡፡
23/05/2026
ከ50 ሚሊዮን በላይ ድምጾች…ምርጫ 2018…የሚዲያና ሲቪክ ማኅበራት ሚና Ethiopian Election 2026 | Media | Civic society | #ዳጉ ከ50 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተመዘገቡበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ መስጫ ቀን ቀናት ብቻ ቀር...
22/05/2026
20/05/2026
በሲቪል ማህበራት ዘርፍ በተከናወኑ የሪፎርም ተግባራት ሲቪክ ምህዳሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰፍቷል፡፡
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ግንባታ፣ በልማት፣ በዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ እና በዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ረገድ የማይተካ ሚና የሚጫወቱ ዋነኛ ተዋናዮች ናቸው። በተለይም የሕግ ማዕቀፍ ሪፎርሙን ተከትሎ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው እየጎላ የመጣ ሲሆን፣ ከመንግስትና ልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ለሀገር ሁለንተናዊ እድገትና ለፖሊሲ ግብዓት በማመንጨት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።
ይህንን ሚና በመገንዘብም ከለውጡ በፊት አሳሪ የነበሩ ህጎችና ተቋማዊ አሰራሮች ላይ የሪፎርም እርምጃዎችን በመዉሰድ የሚጨበጥ ለዉጥ ከተመዘገበባቸዉ ዘርፎች መካከል አንዱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች(ሲማድ) ነዉ፡፡
መንግሥት የኢትዮጵያን ዘላቂ ሰላምና ብልጽግና ለማሳካት የሁሉም ዜጎች አስተዋጽዖ አስፈላጊ መሆኑን በጽኑ በማመን ሰዎች በተለያዩ ፍላጎቶቻቸውና ዝንባሌያቸው ተደራጅተው ለመሥራት ሳንካ የሆኑባቸውን እንቅፋቶች ለማስወገድ ከወሰዳቸው ጉልህ የሪፎርም እርምጃዎች አንዱ አዲሱ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ 1113/2011 መውጣቱ ነው። አዋጁ ቀደም ብሎ የሲቪክ ምኅዳሩን ያላግባብ ያጣበቡ ድንጋጌዎችና አሠራሮችን በማረም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽና የመደራጀት ሕገ መንግሥታዊ መብቶች እንዲጠበቁ ጉልህ ሚና ተጫውቷል።
የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አስተዳደር ማሻሻያ በክልሎችም እንዲተገበር ባለፉት ዓመታት በተደረገው ክትትል 11 ክልሎች ተመሳሳይ የሪፎርም ሕጎች አውጥተው በትግበራ ላይ ይገኛሉ።
20/05/2026
20/05/2026
ለዲሞክራሲያዊ የምርጫ ስኬት የመገናኛ ብዙኃን ሚና በሚል ርዕስ የፓናል ወይይት በመደረግ ላይ ይገኛል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር የተዘጋጀው ይህ መድረክ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንስትር እናትአለም መለሰን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ ተወካዮች፣ የምርጫ ቦርድ ተወካዮች፣ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችና የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮችና መሰል ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
መድረኩ ላይ በስትራቴጂያዊ የትርክት ግንባታ እና ሀገራዊ መግባባትን ለማጠናከር እንዲሁም የሀሰተኛ መረጃን በመከላከል የመረጃ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥና መሰል አላማዎችን ያነገበ ነው።
የፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚንትር እናትአለም መለሰ በዲሞክራሲ ምርጫ ወቅት የመገናኛ ብዙኃን ሚና ጉልህ መሆኑን ጠቁመው እንደምርጫ ባሉ የዲሞክራሲ ስርአቶች ህዝብ የመወሰን አቅሙን የሚያዳብርበት እና የሚያለማምድበት በመሆኑ እንዲሁም የተዛባ መረጃን የሚያጠራበትን ሁኔታ መፍተጠር የሚዲያ ድርሻ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመድረኩ የበተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የፓናል ውይይቱ የሚቀጥል ይሆናል።