Addis MESOB - One Center Digital Government Service

Website

Addis MESOB - One Center Digital Government Service Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis MESOB - One Center Digital Government Service, Public & Government Service, Adwa Street, Arada SC, Addis Ababa.
(1)

Addis MESOB is a public office for one-stop service center designed to serve the residents of Addis Ababa with multiple public services under one roof making government services faster, more efficient, and citizen-focused.

09/10/2026

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን

06/10/2026

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

06/10/2026

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰየሙ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 7ኛው ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመንግሥት መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።

! ! !

ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግርና የአብሮነት መርሐ-ግብር በሁሉም የአዲስ መሶብ ማዕከላት ተካሄደ::Addis MESOB: መስከረም 25/2019 ዓ.ም.ዘወትር ሰኞ ማለዳ በአዲስ መሶብ አ...
05/10/2026

ሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የእውቀት ሽግግርና የአብሮነት መርሐ-ግብር በሁሉም የአዲስ መሶብ ማዕከላት ተካሄደ::

Addis MESOB: መስከረም 25/2019 ዓ.ም.

ዘወትር ሰኞ ማለዳ በአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግሥት አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሚካሄደው የሰራተኞች የእውቀት ሽግግርና የአብሮነት መርሃ-ግብር (ወርቃማው ሰኞ) በሁሉም የአዲስ መሶብ ማዕከላት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ በመስቀል ተጀምሮ በልዩ ልዩ መርሐ-ግብራት ተከናወነ።

በመርሐ-ግብሩ የየማዕከላቱ ሠራተኞች ያሏቸውን ዕውቀቶች፣ የተሻሉ ልምዶችና ተሞክሮዎች እርስ በእርስ በመጋራት አዳዲስ ቴክኖሎጂና ዘመናዊ አሠራሮች ላይ ያላቸውን ግንዛቤና ክህሎት የሚያዳብሩበት እንዲሁም የስራ ተነሳሽነትና ተቋማዊ ፍቅር የሚገነባበት ሁለንተናዊ መድረክ ነው::

አዲስ መሶብ ከሚሰጠው ፈጣን፣ ዲጂታል እና ሥነ-ምግባር የተሞላው አገልግሎት ባሻገር ለማህበራዊ ትስስር ልዩ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ፤ የተቋሙ አንጸባራቂ ስኬት መሠረት የሆኑትን ሰራተኞች አቅም የሚያጎለብተው ይህ የአብሮነትና የመማማሪያ መርሃ-ግብር በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የማዕከሉ አመራሮች አረጋግጠዋል።

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ዛሬ ይካሄዳል Addis MESOB : መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ  ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይከናወናል። በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 5...
05/10/2026

የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ዛሬ ይካሄዳል

Addis MESOB : መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም

የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይከናወናል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌደራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን ተጠሪነቱም ለሀገሪቱ ሕዝብ መሆኑ ተደንግጓል።

በተጨማሪም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀመር በተደነገገው መሠረት፣ የመንግሥት ምስረታ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ይከናወናል።

በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መንበር ያገኘው የፖለቲካ ፓርቲ የፌደራሉን ሕግ አስፈጻሚ አካል የሚያደራጅ ሲሆን፣ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ ሕግ አስፈጻሚ አካል በዕለቱ በይፋ ኃላፊነት ይረከባል።

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

የኢሬቻ በአል በሁሉም የአዲስ መሶብ ማዕከላት አመራር እና ባለሙያዎች በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡
02/10/2026

የኢሬቻ በአል በሁሉም የአዲስ መሶብ ማዕከላት አመራር እና ባለሙያዎች በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡

የኢሬቻ በአል በአዲስ መሶብ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡ Addis MESOB: መስከረም 21/2019 ዓ.ም. ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አን...
01/10/2026

የኢሬቻ በአል በአዲስ መሶብ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡

Addis MESOB: መስከረም 21/2019 ዓ.ም.

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኒስኮ ካስመዘገበቻቸው የማይዳሰሱ ቅርሶች መካከል አንዱ የሆነው የ2019 ዓ.ም ኢሬቻ በአል ‹‹ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት›› በሚል መሪ ቃል በአዲስ መሶብ በድምቀት ተከበረ፡፡

የኢሬቻ በአል በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው፣ ከገዳ ሥርዓት የሚመነጭ፣ የምስጋና፣ የሰላም፣ የእርቅና የአብሮነት መገለጫ ኢትዮጵያዊ እሴት በመሆኑ እሬቻ ሰው ከፈጣሪው፣ ሰው ከሰው፣ እንዲሁም ሰው ከተፈጥሮ ጋር ያለውን ሰላምና ፍቅር የሚያድስበት ታላቅ የአደባባይ በአል ነው፡፡

ኢሬቻ ከበአልነቱ ባሻገር ለሀገራዊ መግባባትና የህዝቦች ትስስር፣ በስፋት ሀገራችን ትኩረት ሰጥታ እየሠራችበት ለምትገኘው ከአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪዝም መዳረሻነት ግብ ያለው አስተዋጽዖ ከፍተኛ ነው፡፡

መርሃ - ግብሩ በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት በልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ሲከበር የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ደሳለኝ ተረፈ እና ሌሎች የማዕከሉ የሥራ ኃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች እንዲሁም ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

የተሰጠን ሀላፊነት  መብት ሳይሆን አደራ ነው። ያለፉትን አምስት ዓመታት “የከተማችንን መልክ እንቀይራለን፤ የሕዝባችንን ክብር እንመልሳለን፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ እናስመስላታለን” ...
01/10/2026

የተሰጠን ሀላፊነት መብት ሳይሆን አደራ ነው።

ያለፉትን አምስት ዓመታት “የከተማችንን መልክ እንቀይራለን፤ የሕዝባችንን ክብር እንመልሳለን፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አበባ እናስመስላታለን” ብለን የገባነውን ቃል ከጠበቅነው በላይ ተሳክቷል፡፡

ሆኖም የትናንቱ ስኬት የነገውን ኃላፊነት አይተካም። ትናንት የከተማችንን ገጽታ ለመቀየር ሠርተናል፤ በርካታ ቁጥር ያላቸው ስራዎችን አከናውነናል። በቀጣዩ ምዕራፍ ደግሞ የነዋሪዎቻችንን የዕለት ተዕለት ኑሮ በተጨባጭ ማሻሻል የሚችሉ ስራዎች የምናከናውንበት ይሆናል። ከእንግዲህ ልማታችንን የምንለካው በሠራነው ፕሮጀክት ብዛት እና በቁጥር በሚተነተን ሪፖርት ብቻም አይሆንም። ይልቁንም አንዲት እናት ምን ያህል የኑሮ ጫና ቀነሰላት ? አንድ ወጣት ምን አይነት ኑሮውን የሚያሻሻልበት ሥራና ዕድል አገኘ? አንድ ነጋዴ የመንግስት አገልግሎት ሳይንገላታ በክብር ማግኘት ቻለ ወይ? አንድ ቤተሰብ ምን ያህል የተሻለ መኖሪያ ቤት፣ ጥራት ያለው ት/ቤትና የጤና አገልግሎት ፣ ውሃ፣ መንገድና ትራንስፖርት አገኘ? የሥራችን የመጨረሻ ውጤት የእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ መለኪያ መሆን አለበት።

አዲስ አበባንችን ለኑሮ የምትመች፣ የነዋሪዎቿን ክብር የምትጠብቅ ከተማ ጥራት ያለው ሰፊ መሠረተ ልማት እንገነባለን። ያረጁና የተጎሳቆሉ አካባቢዎችን አድሰን፥ የንጹሕ መጠጥ ውሃ፣ የመንገድና የፍሳሽ መሠረተ ልማት፣ ትራንስፖርትና መኖሪያ ቤት ተደራሽነትን እናሻሽላለን።

ዘመናዊ የሕክምና ማዕከላትን በማስፋፋት፣ የግሉን ዘርፍ በማበረታታት፣ የጤና ቱሪዝምን በማሳደግ፣ የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን በማጠናከርና የትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትሐዊነትና ጥራትን በማሻሻል ለኑሮ ተመራጭ የሆነች ከተማን እንገነባለን፡፡

በአጠቃላይ የምንፈልጋት አዲስ አበባ ሕፃናት በደህንነትና በተስፋ ቦርቀዉ የሚያድጉባት፣ ወጣቶች ጥራት ያለው ሥራና ዕድል የሚያገኙባት፣ ሴቶች መብታቸውን በእኩልነት የሚጠቀሙባት፣ ነጋዴዎችና ኢንቨስተሮች ምቹ የስራ ሁኔታ የሚያገኙባት፣ ሁሉም ነዋሪ ከተማዋን “የእኔ” ብሎ የሚኮራባት እና የሚገነባት ከተማ እንድትሆን ማድረግ ነው ።

አዲስ አበባ የሁላችን ቤት ናት። በመንግስት ብቻ የምትገነባ አይደለችም። የሁላችን ኃላፊነት ናት። የሁላችን ተስፋም ናት። ትናንት ያየነው ለውጥ መዳረሻችን አይደለም፤ የቀጣዩ ጉዞ መነሻችን እንጂ። ከተባበርን እንችላለን፤ ከተጋን እናደርጋለን፤ አቅማችንን ካስተባበርን የበለጠ ውጤት ማምጣት እንችላለን።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በከተማችን የተመዘገቡ ስኬቶች የመላው ከተማችን ነዋሪዎች ፥ የንግድ ማህበረስብ ፥ የልማት አጋዥ የሆኑ ባለሃብቶች፥ ምሁራን የከተማ አስተዳደራችን አመራሮች፥ ሰራተኞች ፥ አጋር አካላት ፥ ሴቶች፥ ወጣቶች፥ የነቃ ተሳትፎ ድምር ውጤት በመሆኑ ከልብ እናመሰግናለን።

በቀጣይም የከተማችን ዕጣ ፈንታ በአመራሩ ትከሻ ላይ ብቻ የሚወድቅ አይደለምና የሁላችንም ኃላፊነት መሆኑን በመገንዘብ አብረን ፥ተደጋግፈን ከተመልካችነት ወደ ተሳታፊነትና ባለቤትነት በመሸጋገር፣ የጋራ ራዕይ ሰንቀን በጋራ እንድንጓዝ ጥሪዬን አቀርባለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Addis MESOB

The New Horizon of Service !

ለተጨማሪ መረጃ ወይም አስተያየት:

Contact Center: በ9838 ኦፕሬተሮቻችንን ያግኙ

Website: addis.mesobcenter.et

Telegram: https://t.me/addismesob ቤተሰብ ይሁኑን!

Address

Adwa Street, Arada SC
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 21:00
Tuesday 08:00 - 21:00
Wednesday 08:00 - 21:00
Thursday 08:00 - 21:00
Friday 08:00 - 21:00
Saturday 08:00 - 21:00
Sunday 08:00 - 21:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis MESOB - One Center Digital Government Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share