23/02/2026
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከባኩሳ ብሔራዊ ፓርክ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ፊርማ (Memorandum of Understanding) ስነ-ስርዓት አካሄደ፡፡
የካቲት 15/2018 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአዊ ብሄረሰብ አስተደዳር ከሚገኘው ባኩሳ ብሔራዊ ፓርክ ጋር በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
15/11/2025
ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ሰጪነቷን ትቀጥላለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
*******************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ መፍትሔ ሰጪነት ከአፍሪካ የመሪነት ሚናዋን መጫወት እንደምትቀጥል አስታወቁ።
ኢትዮጵያ COP 32ን ለማስተናገድ ያቀረበችውን ጥያቄ በሙሉ ድምፅ ለደገፈው ለአፍሪካ የተደራዳሪዎች ቡድን ምስጋና አቅርበዋል።
አፍሪካ በብራዚል ቤሌም ከተማ በተካሄደው የ2025ቱ የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (COP 30) ላይ በአንድ ድምፅ ተናግራለች፤ ዓለምም ሰምቷታል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
የሰው ልጅ ከሚያጋጥሙት እጅግ ከባድ ተግዳሮቶች አንዱ የሆነውን ችግር ለመፍታት የሚደረገውን የጋራ ጥረት እንድንመራ ለተሰጠን ዕድልም እናመሰግናለን ነው ያሉት።
የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም እንዲህ ያለ ወሳኝ ኃላፊነት ስለሰጠንም ክብር ይሰማናል ብለዋል በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።
ይህ እውቅና ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ባሳየችው የመሪነት ሚና እና ዋና ዋና ዓለም አቀፍ ዝግጅቶችን የማስተናገድ አቅሟ ላይ ያላችውን እምነት የሚያንፀባርቅ እንደሆነ ገልጸዋለ።
ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2027 በአዲስ አበባ የሚካሄደው COP 32 ጠንካራ እና ትርጉም ያለው ውጤት እንዲያስመዘግብ እና በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የጋራ እርምጃዎችን ለመውሰድ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በቁርጠኝነት እንደምትሠራም ቃል ገብተዋል።
አፍሪካ የመፍትሔ አህጉር መሆኗን እና በዓለም አቀፍ ጥረቶች ውስጥ ቁርጠኛ አጋር መሆኗን ለማሳየት ኢትዮጵያ የመሪነት ሚናዋን መጫወት ትቀጥላለችም ብለዋል።
13/11/2025
በፈንድቃ ከተማ ለሰሰካውቶች እና ለቀጠና ስካውት አስተባባሪዎች ስለብዝሃ-ህይወት ሀብቶች ስልጠና ተሰጧል። በመድረኩም ወንድ= 19 ሴት=17 ድምር=36 ሰልጣኞች ተሳትፈዋል።
10/11/2025
የብሔራዊ ፓርኩ የወረዳ ፓርክ መማክርት ኮሚቴ ማጠናከር የተቻለ ሲሆን በመድረኩም ወንድ=10 ሴት=1 ድምር=11 የመማክርት አባለት ተገኝተዋል። በመጨረሻም ጥብቅ ስፍራውን ከችግር ለማውጣት ሁሉም ባለድርሻ እና አጋር አካላት በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሶል።
01/11/2025
የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ትርጉምና አደረጃጀት
/ክፍል ሶስት / የመጨረሻ ክፍል...
👉በተለያዩ ርእሶች ላይ የተዘጋጁ ፊልሞችን ወይም የቪዲዮ ካሴቶችን በመዋስ ለክበቡና ለሌሎች ማህበረሰብ አባላት ማሳየት ከተለያየ አቀጣጫ ስለ አካባቢ ትምህርትና አውቀትን ለማግኘት አጋጣሚ ይፈጥራል፡፡ፊልም የማሳየቱ ሂደት ከተጠናቀቀ በሃላ በፊልም ዋና ዋና ጪብጦች ላይ መወያየት ግንዛቤ የበለጠ ሊያዳብር ይችላል፡፡
👉 ኢግዚቢሽን በማዘጋጀት የተለያዩ መረጃዎችንና ትምህርታዊ መግለጫዎችን ለህብረተሰቡ ለማስተላለፍ፡፡
👉 የአካባቢ አያያዝና አጠቃቀምን የሚያንፀባርቁ ፎቶግራፎች፣ ሞዴሎች፣ ቻርቶች፣ ቁሳቁሶች፣ ናሙናዎች፣ወዘተ አደራጅቶ በኢግዚቢሽን መልክ በማዘጋጀት ግንዛቤን ማጎልበት፣
👉 የክበብ መጽሄት በማዘጋጀት የክበቡን እንቅስቃሴ፣ በአካባቢ ላይ ያተኮሩ አጫጭር ጽሁፎች፣ግጥሞችና አጫጭር ታሪኮችን እንዲካተት ማድረግ፡፡በተጨማሪ መጽሄቱ ሰዎችን ለማስተማር ሊውል ወይም ለገቢ ማሰገኛ ሊውል ይችላል፡፡
👉 የፓናለ ውይይት በማዘጋጀት በአካባቢ እንክብካቤ መርሆች፣በአካባቢ ብክለት፣በአፈር መሸርሸር፣በብዛ ሂወት መመናመን፣በደን መጨፍጨፍ፣በፈጣን የህዝብ እድገት፣በማገዶ እንጨት እጥረት፣በአየር ንብረት ለውጥ፣ወዘተ በመሳሰሉ የአካባቢ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማካሄድ፡፡
👉 በውይይቱ ላይ በርካታ ሃሳቦች፣አስተያየትና ጥያቄዎች የሚቀርቡ በመሆኑ ግንዛቤን ያሳድጋል፡፡
👉 የመግባባት ስሜት በመፍጠር የአካባቢ እንክብካቤ ተግባራትን ያጠናክራል፡፡
👉 የሃሳብ መሰጫ ሳጥን በማዘጋጀት ለተሰጡ አስተያየቶችና ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ መስጠትና ምላሺ በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በግልጽ መለጠፍ፡፡
👉 በተጨማሪ ከአባላቱ ወይም በአካባቢ ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለ ክበቡ ያላቸውን ሃሳብ የአሰራር ጉድለት ወይም አጠቃላይ አስተያየትን በዚሁ ዘዴ ማግኘት ይቻላል፡፡
👉 ከክበቡ የሚጠበቁ ውጤቶች
• በአካባቢ እንክብካቤ ክበብ አባላት አማካኝነት ህብረተሰቡ ስለ አካባቢ ጉዳዮች የተሸለ መረጃና እውቀት ያገኛል፣
• የአካባቢን ምሉዕነት የሚያስገኙ ሰብአዊ፣ህይወታዊና ፊዚካለዊ ትስስሮችና አንዱ ለሌላው መኖር አስፈላጊነትን ግንዛቤ የስገኛል፣
• የክበቡ አባላትና ሌላው የህብረተሰብ ክፍል ተፈጥሮአዊ አካባቢን እንዲያደንቅ ስለመስህብነታቸው ግንዛቤ እንዲይዝ ያስችላል፣
• ሰው ህይወቱ በተፈጥሮ ሃብት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተረድቶ የተፈጥሮ ሃብትን በተገቢው ሁኔታ መንከባከብና መጠቀም የጀምራል፣
• የተፈጥሮ ሃብትን በተገቢው መንገድ ከመጠቀም አንጻር አማራጪ ምንጮችን ለመፈለግ፣ለማግኘትና ለመጠቀም የሚያሰችል ችሎታ ያስገኛል፣
• አካባቢን ለመንከባከብ፣ለመጠበቅና ለማልማት እነዲሁም በተገቢው ሁኔታ ለመጠቀም በሚደረገው ጥረት ውስጥ በፈቃደኝነትና በዜግነት ስሜት እንዲሳተፉ ያሰችላል፣
• ጤናማ አካባቢና ለአካባቢ እንክብካቤ ዝንባሌ ያለው ህብረተሰብ ይፈጥራል፣
• አካባቢን የሚበክሉ አካላት ጉዳት እንዳያደረሱ ለሚመለከተው አካል መረጃ ደርሶ ችግሩ የሚቀረፍበት ስርአት በቀላሉ ይፈጠራል፡፡
👉 የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ተደረሽነት የማስፋትና የማጠናከሪያ ዘዴዎች፤
በማስታወቂያ ሰሌዳ መጠቀም
ማስታዎቂያ ሰሌዳ የአካባቢ መልዕክት የያዙስእሎች፣ቻርቶች፣ፖስተሮች፣ ፎቶ ግራፎች፣በራሪ ወረቀቶች፣ጽሁፎች፣ ወዘተ የመሳሰሉ የአካባቢ መረጃዎቸን ለክበብ አባላትና ለህብረተሰቡ ለማሳተፍ የሚያገለግል መሳሪያ ነው፡፡
በመስክ ጉብኝት ወቅት የተደረጉ እንቅስቃሴዎች፣የጉብኝቱን ፍሬ ሃሳብ የሚገልጹ ፎቶግራፎች፣የተጠናቀቁና በመተግበር ላይ ያሉ የክበቡ ፕሮጀክቶች፣ የክበቡ አመታዊ ጉባኤ ስብሰባዎ
30/10/2025
የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ትርጉምና አደረጃጀት
/ክፍል ሁለት / የቀጠለ..........
👉 የክበብ_ጉባኤ_ምስረታ
የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ አባል ለመሆን የሚሹ ፈቃደኞች መገኘታቸው ከተረጋገጠ ቀጣዩ ስራ የክበቡን መስራች ስለ ጉባኤ ማካሄድ ነው፡፡
መስራች ጉባኤውን ለማካሄድ ስብሰባው የሚካሄድበትን ቀን፣ ሰአትና ቦታ መስራች ጉባኤው የሚነጋገርባቸውን አጀንዳወች የሚገልጽ ማስታወቂያ በተለያዩ ስፍራወች መለጠፍ አንዱ አማራጭ ነው፡፡
ሌላው መንገድ አባል ለመሆን ፈቃደኝነታቸውን በገለጹ ሁሉ የጥሪ ደብዳቤ እንዲደርሳቸው ማድረግ ነው፡፡
ሌላ የተሸለና አመቺ የጥሪ ማስተላለፊያ መንገድ እንደአመቺነቱ መጠቀም ይቻላል፡፡
ክበቡን ለማቋቋም ሃሳብ ያመነጨው/ጩ ግለሰብ ወይም ስብስብ ስለ ክበቡ አስፈላጊነት፣የክበብ አላማ፣በክበብ ውስጥ መሳተፍ ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም፣ጉባኤው የሚነጋገርባቸውን ዝርዝር አጀንዳወች እና በመስራች ጉባኤው ላይ ክበቡን ሊያጠናክር የሚችል የኮሚቴ ምርጫ የሚካሄድ ስለመሆኑ ማብራሪያ መስጠት ክበቡ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለማቀናጀትና ለመምራት፡
• ሊቀመንበር ም/ሊቀ መንበር
• ፀሀፊ፣የህዝብ ግኑኝነትና እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች ሊኖሩ ይገባል፡፡
👉 በአካባቢ እንክብካቤ ክበባት የሚከናወኑ ተግባራት
የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት ከተቋቋሙበት አላማና ግብ በመነሳት በርካታ ተግባራት ሊያከናውኑ ይችላሉ፡፡
👉 ሊያከናውኑ ከሚችሉዋቸው ተግባራት መካከል ጥቂቶቹ
• የከተማና የገጠር ኑዋሪወችን የሚያሳትፍ አካባቢን የሚመለከቱ ህዝባዊ ስብሰባዎች፣ዓውደ ጥናቶች፣ወዘተ ማዘጋጀትና የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማጎልበት፡፡
ለዚህም እንዲረዳ ድራማ፣በራሪ ጽሁፎችን፣ሙዚቃ፣ፊልም፣ ስዕል፣ወዘተ በመሳሪያነት መጠቀም ይቻላል፡፡
• ወቅታዊነት ያለቸውን አካባቢያዊ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ ማስተላለፍ እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢዎች ጠቃሚ መረጃዎችን ማሰባሰብና ልዩ ልዩ ዘዴወችን ተጠቅሞ ማሰራጨት፣
• በአካባቢ እነክብካቤና በንጽህና አጠባበቅ ተግባራት ላይ መሳተፍ
• በአካባቢ ነክ ጉዳዮች ላይ ተቆርቋሪነታቸውን ማሳየት ቤተሰባቸውንና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ከጎናቸው ማሰለፍ፣
• አካባቢና ልማትን የተመለከቱ ለምርምር ስራ የሚረዱ መረጃዎችን በማሰባስ ለተመራማሪዎችና ለተቋማት ድጋፍ መስጠት፣
• ለአካባቢ ጥበቃ በሚበጁ ልማዳዊ እውቀትና ክህሎት ላይ ጥናት ማድረግና የልምድ ልውውጥ ማካሄድ ፣
• በአካባቢያቸው ፣በክልል፣በብሄራዊና በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ መሰል ድርጅቶች ጋር በመረጃ መረብ መተሳሰር፣
• ለአካባቢ ትምህርትና እንክብካቤ ጠቃሚነት ባላቸው አካባቢያዊ ፣ብሄራዊና ዓለም አቀፋዊ በዓላት ላይ (ለምሳሌ የአለም አካባቢ ቀን፣የደን ቀን እና የበረሃማነት ቀን) በመሳተፍ ግንባር ቀደም ሚና መጫወት፣
• የተፈጥሮ ሃብቶችን በዝርዝር ማጥናት ፣/ለምሳሌ የአየር ንብረት፣የውሃ ሃብት፣እፅዋት፣የአካባቢ ንፅህናና ጤና፣የቆሻሻ አያያዝ ፣በሚህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ምክንያት፣በአካባቢ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ነገሮች፣ክበቡ በተቋቋመበት አካባቢ የሚታዩ የአካባቢ ችግሮች የመሳሰሉትን በሙሉ ወይም በከፊል ሊያካትት ይችላል፡፡
• ክበባቱ ተደራጅተው እንደሚገኙበት አካባቢ ለምሳሌ፣ ት/ቤቶች፣ከፍተኛ የት/ተቋማት፣ድርጅቶች፣ የመኖሪያ አካባቢ፣አነስተኛ መሬት ለማግኜት ጥረት በማድረግ የዛፍ ችግኝ ማፍላት፡፡የዘር አመራረጥ፣የመደብ አዘገጃጀት፣የችግኝ አፈላልና እንክብካቤ፣ችግኞችን የማዛወር፣ወዘተ ዘዴዎችን ለክበብ አባላት በተግባር በማሳየት ማስተማርና ማሳወቅ፡፡
• በገጠር አካባቢ ወይም በከተሞች ዙሪያ የሚቋቋሙ ክበባት የማገዶ ዛፍ መትከያ ቦታ የማግኘት እድል ስለሚኖር የማገዶ እጥረትን ለማቀለል የሚያስችል ስራ መስራት፡
• ጉብኝት በማድረግ ተፈጥሮአዊ አካባቢያችንን በመመልከት ውበትን የማድነቅ አጋጣሚ የሚፈጥር ሲሆን እውነተኛ ክሰተቶችንና ሁነታዎችን መመልከት፡፡ጉብኝቱ የአፈርና የውሃ ጥበቃ የሚካሄድባቸውን ፕሮጀክቶችን፣የተራቆቱ አካባቢዎችን፣ ኢንዱስትሪዎችን አመራረት ሂደትና የቆሻሻ አወጋገድ ስርአትን፣የውሃ ማጣሪያዎችን፣ በሰዎች ጥረት እዲያገግሙ የተደረጉ አካባቢዎችን ፣ወዘተ ሊካተት ይችላል፡፡
• ከሌሎች አቻ ክበባት ጋር ህብረት በመፍጠርና በመቀናጀት የልምድና የመረጃ ለውውጥ ማዳበር፡፡ (ለምሳሌ ከስነህዝብ ክበባት አባላት ጋር በፈጣን የህዘብ ቁጥር አድገትና በአካባቢ መካከል ስለአለው ትስስር ትምህርታዊ ክርክር ወይም የፓናል ውይይት ማካሄድ ይቻላል፡፡)
ክፍል 3 ይቀጥላል...
የአብክመ የአካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 2018 ዓ.ም ባህርዳር
30/10/2025
የትምህርት ቤቶች የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት አባላት ለአካባቢ ጥበቃ ተግባራት አይተኬ ሚና አላቸው።
👉 የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት ትርጉምና አደረጃጀት፦
ክፍል አንድ
የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ማለት ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ያላቸውን ዕውቀት፣ፍለጎትንና ትኩረት ለማጋራትና በጋራ ለመስራት በማሰብ የሚመሰርቱት የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ስብስብ ነው፡፡
ለምሳሌ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚቋቋም ክበብ ባብዛኛው ተማሪዎች፣መምህራንና የአሰተዳደር ሰራተኞች የሚያሳትፍ ነው፡፡በተመሳሳይ በስራ ቦታ የሚቋቋም ክበብ (በግልም ሆነ በመንግስት መስሪያ ቤት) በተቋሙ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችን የሚያሳትፍ ሆኖ የሚቋቋም ነው፡፡
• የአካባቢ እንክብካቤ ማህበር ማለት፡- በአንድ ቀበሌ ወይም ከተማ አካባቢ የሚኖር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአካባቢያቸው ችግሮችና እንክብካቤ ዙሪያ በጋራ በመስራት አካባቢን ለመጠበቅና ለማልማት ለመጠቀም ተመሳሳይ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች በአንድ ላይ ተደራጅተው አካባቢን እያለሙ የራሳቸውን ገቢ ለመሳደግ የሚuuም ተuም ነው፡፡
👉 የበጎ ፈቃደኝነት ማህበር ማለት፦
በአንድ በተወሰነ ቀበሌ ወይም ከተማ ክልል ውስጥ የሚኖሩ ማህበረሰቦች በበጎ ፈቃደኝነት ተመሳሳይ ፍላጎትና ዓላማ ያላቸው በአንድ ላይ በመደራጀት የራሳቸው ውስጠ ደንብ በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ አስጸድቀው በአስተዳደርና ጸጥታ ጉዳይ መ/ቤት ማህበሩ ተቀባይነት አግኝቶ ህጋዊ ሰርትፍኬት የተሰጣቸው አካባቢን ለመጠበቅና ለማልማት(ለመንከባከብ) የተደራጁ ትርፍ አልባ የሆኑ የበጎ ፈቃደኝነት ማህበር ይባላሉ፡፡
ተባባሪ አባል፤- ከክበቡ ክልል ውጪ የሆነ ሰው የማህበሩን ወይም የክበብ ዓላማ አምኖበትና ተቀብሎት አባል ለመሆን ጥያቄ ሲያቀርብ በተባባሪ አባልነት ደረጃ ይመዘገባል፤
በአካባቢ እንክብካቤ ክበብ መሳተፍ በሁሉም አባላት ዘንድ ስለ አካባቢ ግንዛቤ፣ዕውቀት ፣ክህሎት፣ዝንባሌና ተሳትፎ እንዲኖር ጥሩ አጋጣሚ የፈጥራል፡፡
ይህ ደግሞ የአካባቢ ግንዛቤን ከማሳደግ ባሻገር ውሎ አድሮ የአስተሳሰብና የአሰራር ለውጥ ያስከትላል፡፡
ከላይ እንደተጠቀሰው የአካባቢ ክበባት አካባቢን ለመንከባከብ ፍላጎት ባላቸው በማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ወይም ቡድን ሊቋቋሙ ይችላሉ፡፡ ከፍተኛ የትምህርትተቋማት፣(ኮሌጆች፣ ዩኒቨርስቲዎች)፣የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት፣ኩባንያዎች፣መኖሪያ አካባቢዎች፣ ፋብሪካዎች፣ የገጠርና የከተማ አስተዳደሮች/ቀበሌዎች/፣እድሮች፣መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድረጅቶች፣የሃይማኖት ተቋማት፣ ወዘተ የአካባቢ እንክብካቤ ክበባትና ማህበራት ሊቋቋሙና የግንዛቤ ስራና ተሳትፎ ሊከናወንባቸው የሚችሉ ተቋማት ናቸው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች ህብረተሰቡ በተለያዩ አደረጃጀቶች በተለይም በልማት ቡድን በመደራጀት በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራወችን በመፈጸም ላይ የሚገኝ በመሆኑ የተለየ አደረጃጀት መፍጠር ሳያስፈልግ ወደ ተግባር መግባት ይቻላል፡፡
👉የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ሚና፦
የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት የሚያከናውኑት ተግባር በተጨማሪ በጎ ተጽኖዎችን መፍጠር የሚችሉ ናቸው፡፡
ከሚፈጠሩት በጎ ተጽኖዎች መካከል
በሚያካሂዱት የአካባቢ ጥበቃና አያያዝ ትምህርት እንዲሁም በሚፈጽሙት ተግባር የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና የአካባቢ እንክብካቤ ተሳትፎ ማጠናከር እንዲሁም በአካባቢ የደንና አየር ንብረት ለውጥ ሚኒስቴር የወጡትንና ወደፊት የሚወጡትን ሕጎች፣ፖሊሲዎችና ደንቦች በተመለከተ በህብረተሰቡ ዘንድ ግንዛቤ እንዲጎለብት ያግዛሉ፣ በህብረተሰቡ ዘንድ የመስራት ዝንባሌን ያዳብራሉ፣
የጾታና ሌሎች ልዩነቶች እንደይኖር በማድረግ በጋራ የመስራት መንፈስን ያጠነክራሉ፣ በአካባቢ ልማት ላይ የመሳተፍ የመንከባከብና በአግባቡ የመጠቀም አቅምን ያጎለብታል፣
በአካባቢ ላይ የምርምርና የፈጠራ ስራዎችን በመስራት የአካባቢ መንከባከቢያ ቴክኖሎጅን የመጠቀም አቅምን የዳብራሉ፣ ከተለያዩ ፕሮጀክቶች ጋር ትስስር በመፈጠር አካባቢን ለመንከባከብ የሚያስችሉ ተግባራትን እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል፣ የመኖሪያና የስራ አካባቢ ጽዱና ለኑሮ ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ ያስችላቸዋል፣ የሃገሪቱን የተፈጥሮ ሃብት ለማስተዋወቅ፣ ለመጠበቅ እና የሃገርን እወቅና ሌሎች የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ለመሳተፍ የሚያበቁ መሆናቸው ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
👉 የአካባቢ እንክብካቤ ክበብ ጠቀሜታ፦
በተገቢ ሁኔታ የተደራጁ የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት በርካታ ጠቀሜታ አላቸው፡፡ከጥቅሞች መካከል ጎላ ያሉት መጥቀስ ይቻላል፡፡
• በመደበኛና መደበኛ ባልሆኑ ትምህርት ሊቀርቡ የማይችሉ አካባቢያዊ ጉዳዮችን ለተማሪዎችና ለመላው ህብረተሰብ በስፋት ለማሳወቅ ይረዳሉ፡፡
ለምሳሌ አካባቢና ጤናን፣አካባቢንና ድህንነትን፣አካባቢንና የህዝብ ቁጥር እድገትን፣የማገዶ እጥረትን፣የደን መመናመንን፣የአፈር መከላትን፣የብዛህይወት መጥፋትን፣ የአካባቢ ብክለትን፣የአየር ንብረት ለውጥን የመሳሰሉት ጉዳዮችን በማንሳትና በመወያየት፣ግንዛቤን ለማጎልበትና መፍትሄ ለመፈለግ የሚያስችሉ ናቸው፡፡
👉 የአካባቢ ክበባቱና ማህበራት፦
በሚደራጁበት አካባቢ(ለምሳሌ በት/ቤቶች፣በከፍተኛ የትምርት ተቋማት፣ በመኖሪያ ቤቶች፣በሌሎች ድርጅቶችና በገጠር አካባቢ) በሚታዩ ቀዳሚ የአካባቢ ችግሮች ላይ በማተኮር ተግባራዊ እርምጃ ለመውሰድ ያስችላሉ፡፡
• ህብረተሰቡ በአካባቢ እንክብካቤ ተግባራት ውስጥ የለውን ተሳትፎ ለማጎልበትና ለማበረታታት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራሉ፡፡
በአካባቢ እንክብካቤ ክበብ በመሳተፍ የሚገኙ ጥቅሞችና መልካም አጋጣሚወች መካከል ከስራ ባልደረቦችና ከጎረቤት ጋር በመነጋገር ለጋራ ችግሮች መፍትሄ ማምጣት፣
አቅምን የሚያጎለብቱ አውደ ጥናቶች፣አጫጭር ስልጠናወችና ኮንፍረንሶች ላይ መሳተፍ፣
ከአካባቢ አኳያ ጠቀሜታ ያላቸውን ቦታወች በመጎብኘት ተፈጥሮን ማድነቅና መንፈስን ማደስ፣ ስለአካባቢ የሚገልጹ የተለያዩዐመረጃወችን(ከመጽሄቶች፣ከስላይድ ፊልሞች፣ከቪድዮ ፊልሞች፣ከኢንተርኔት፣ወዘተ)የመግኘት እድል፣ ለክበቡ እንቅስቃሴ የሚገለጹ ዜናዎችንና ዘገባዎችን ማንበብና ግንዛቤ ማጎልበት፣ በአካባቢ እንክብካቤ ተግባራትና በግንዛቤ ስራዎች ላይ መሳተፍ፣ አካባቢን ለማሻሻል በሚደረግ እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት መሳተፍ፣ በክበቡ ውስጥ ላደረጉት የለቀ አስተዋጽኦ ማበረታቺያ ማግኜት በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
በአካባቢ እንክብካቤ ክበብና ማህበር በመሳተፍ የሚገኙ ጥቅሞችና መልካም አጋጣሚወች መካከል ከስራ ባልደረቦችና ከጎረቤት ጋር በመነጋገር ለጋራ ችግሮች መፍትሄ ማምጣት፣
አቅምን የሚያጎለብቱ አውደ ጥናቶች፣አጫጭር ስልጠናወችና ኮንፍረንሶች ላይ መሳተፍ፣
ከአካባቢ አኳያ ጠቀሜታ ያላቸውን ቦታወች በመጎብኘት ተፈጥሮን ማድነቅና መንፈስን ማደስ፣
ስለአካባቢ የሚገልጹ የተለያዩ መረጃወችን (ከመጽሄቶች፣ከስላይድ ፊልሞች፣ከቪድዮ ፊልሞች፣ከኢንተርኔት፣ወዘተ)የመግኘት እድል፣
ለክበቡ እንቅስቃሴ የሚገለጹ ዜናዎችንና ዘገባዎችን ማንበብና ግንዛቤ ማጎልበት፣
በአካባቢ እንክብካቤ ተግባራትና በግንዛቤ ስራዎች ላይ መሳተፍ፣
አካባቢን ለማሻሻል በሚደረግ እንቅስቃሴ ውስጥ በንቃት መሳተፍ፣
በክበቡ ውስጥ ላደረጉት የለቀ አስተዋጽኦ ማበረታቺያ ማግኜት በዋነኛነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
👉 የአካባቢ እንክብካቤ ክበብና ማህበር አመሰራረት
የአካባቢ ክበብን ለማቋቋምና ለማደራጀት ተነሳሽነት ያለው ግለሰብ በቅድሚያ ፍለጎት ያላቸውን በመለየት ስለ ጉዳዩ በሰፋት ማወያየት የመጀመሪያው ስራው ሊሆን ይገባል፡፡
ከዚህ በመቀጠል ከውይይት የተገኙ ጠቃሚ ሃሳቦችን በመያዝ ሙያዊ፣ቁሳዊና ሞራላዊ ድጋፍ ሊሰጡ ከሚችሉ ግለሰቦች፣ ተቋማት፣መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ከግሉ ዘርፍ ጋር ግኑኝነት መፍጠር ያሰፈለጋል፡፡
የአካባቢ እንክብካቤ ክበባት ሲደራጁ ራዕይና አላማ ሊኖራቸው የገባል፡፡ክበቡን ወይም ማህበሩን ለማደራጀት ተነሳሺነት ያለው ግለሰብ፣ድርጅት፣ተቋም ወይም ቡድን የክበቡን ራዕይና አላማ መነሻ ሃሳብ ማመላከት ይጠበቅበታል፡፡
ሲደራጅ የተቀረጸ ራዕይና አላማ ክበቡ ከተጠናከረ በኋላ ሊሻሻል የሚችል ነው፡፡ የአካባቢ እንክብካቤ ክበባትን ራዕይና አላማን ለማዘጋጀት ከዚህ በታች የቀረበውን ምሳሌ መሰረት ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡
👉 ራዕይ
ህብረተሰቡን ያሰተፈ ዘለቂ የተፈጥሮ ሃብት አያያዝና አጠቃቀምን በማስፈን ከብክለት የፀዳ ተቋምና የመኖሪያ አካባቢ ተፈጥሮ ማየት፡፡
👉 ዓላማ
የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማዳበር ዘላቂነት ያለው የአካባቢ እነክብካቤና አያያዝ በማራመድ ለሰውና ለሌሎች የተፈጥሮ ሃብቶች ህልውና ጤናማ ሁኔታ እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡
====== ክፍል 2 ይቀጥላል=======
የአብክመ የአካባቢ እና ደን ጥበቃ ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ጥቅምት /2018 ዓ.ም ባህርዳር
26/10/2025
#አቶ ጋሻው እሸቱ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር የህዝብ ግንኙነት ረዳት አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።
➧መልካም የስራ ዘመን ይሁንልዎ!🙏
12/10/2025
በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ደርሶበት ከነበረው ቃፍታ ብሔራዊ ፓርክ ወደ ኤርትራ የተሰደዱ 50 ዝሆኖች መመለሳቸው ተገለጸ
ጥቅምት 1/2018 (አሐዱ ሬዲዮ) የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረውና ከኤርትራ ጋር የሚዋሰነው ቃፍታ ብሔራዊ ፓርክ አሁናዊ ሁኔታው በመሻሻሉ፤ ተሰደው የነበሩ 50 ያክል ዝሆኖች ወደ ፓርኩ ተመልሰዋል ሲል የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን ለአሐዱ ገልጿል፡፡
"ብሔራዊ ፓርኩ ከሰሜኑ ጦርነት በፊት እንደ ሞዴል የሚወሰድ ነበር" ያሉት የባሰልጣን መስሪያ ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን መኮንን፤ በ2017 በአማራ ክልል መንግሥት እና በወረዳው በተደረገ ሕግ የማስከበር ሥራ አዎንታዊ ለውጦች ታይተዋል ብለዋል፡፡
በዚህም ከዚህ በፊት ወደ ኤርትራ ተሰደው የነበሩ 50 ዝሆኖች የተመለሱ ሲሆን፤ በውስጡ ያሉ ሌሎች እንስሳትም የመረጋጋት እና ቁጥራቸው የመጨመር ሁኔታ ተስተውሏል ሲሉ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡
የሰሜኑን ጦርንት ተከትሎ በፓርኩ ውስጥ ሕገ-ወጥ እርሻ፣ የደን ጭፍጨፋ፣ ሕገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ቁፋሮ፣ እጣን ማውጣት እንዲሁም የመንግሥት አካላት ጭምር የተከዜ ወንዝን በመጠቀም ፓርኩ ውስጥ በመስኖ እርሻ ሲያለሙ እንደነበርም አያይዘው ተናግረዋል፡፡
ሆኖም ከወረዳ እስከ ክልል ድረስ በተሰራው ሕግ የመስከበርና የግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ለውጥ መጥቷል ብለዋል፡፡
ከሕገ-ወጥ የወርቅ ማዕድን ማውጣት እና ከዕጣን ማውጣት ጋር የተያያዙ ሕገ-ወጥ ተግባራት አሁንም ሙሉ ለሙሉ አልተፈቱም፤ በቀጣይም ተጨማሪ ሥራ ይጠይቃል የተባለ ሲሆን አሁን ያለበት ሁኔታ ግን እየተሻሻለ ነው ተብሏል፡፡
በእመቤት ሲሳይ