27/05/2026
የፓሊስና ርምጃው ጋዜጣችንን ሙሉ ዘገባ በሚከተለው የቴሌግራም ገፅ ማግኘት ትችላላችሁ 👉🏿
ፖሊስና ርምጃው ጋዜጣ በየ15 ቀኑ እየታተመ የሚወጣ ጥቅምት 23 ቀን 1953 ዓ.ም ተመሰረተ
በጋዜጣው ላይ የሚታተሙ ማናቸውንም ፁሁፎች ማግኘት የሚችሉበት
27/05/2026
የፓሊስና ርምጃው ጋዜጣችንን ሙሉ ዘገባ በሚከተለው የቴሌግራም ገፅ ማግኘት ትችላላችሁ 👉🏿
ፖሊስና ርምጃው ጋዜጣ በየ15 ቀኑ እየታተመ የሚወጣ ጥቅምት 23 ቀን 1953 ዓ.ም ተመሰረተ
24/05/2026
ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም የምትወጣው ጋዜጣችን የተለያዩ ተቋማዊና ወንጀል ነክ ዜናዎችን፣ ታሪኮችን እንዲሁም የተለያዩ ፁሁፎችን ይዛለች ያንብቧት ይከታተሏት!
01/05/2026
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቁጥጥር ስር አዋለ
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ የኮንትሮባንድ ፖሊስ መምሪያ ከጉምሩክ ኮሚሽን ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ባከናወነው ተከታታይ ኦፕሬሽን ከሚያዚያ 01 እስከ ሚያዚያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ሃያ ቀናት ውስጥ ከባድ የኢኮኖሚ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉና ከብር መቶ ሚሊዮን በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል።
በኮንትሮባንድ ፖሊስ መምሪያ የሬጅመንት 4 አዛዥ ምክትል ኮማንደር ጀማል ደቀቦ እንደገለጹት የሬጅመንቱ ሠራዊት የሀገርን ሉዓላዊነትና ኢኮኖሚ ከኮንትሮባንድ ስጋት ለመጠበቅ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሁሉ ከጉምሩክ ባለሙያዎች ጋር በመናበብ ተልዕኮውን በስኬት እየተወጣ ይገኛል። አዛዡ አክለውም ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ መሠረት በበረራና በኬላ ፍተሻዎች በተደረገ ጠንካራ ክትትል ከተያዙት ዕቃዎች መካከል የተለያዩ መድኃኒቶች፣ ሲጋራና ሺሻዎች እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች እንደሚገኙበት ገልጸዋል።
እነዚህ ህገ-ወጥ ዕቃዎች በተለያዩ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ሙከራ ሲደረግ በአዋሽ እና በመተሃራ ኬላዎች ላይ በተደረገ ጥብቅ ክትትል በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን የተያዙት ዕቃዎችም በአዋሽ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ገቢ ተደርገዋል። ምክትል ኮማንደር ጀማል ደቀቦ የኮንትሮባንድ ዝውውር በሀገር ላይ የሚያስከትለውን ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳቶች በመረዳት ሠራዊቱ ከሌሎች የፀጥታ አካላትና ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ቅንጅት አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በመጨረሻም ህብረተሰቡ ማንኛውንም የወንጀል ድርጊት ሲመለከት በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፣ በዘጠኝ ዘጠኝ አንድ ነፃ የስልክ መስመር፣ በሰው አልባ የፖሊስ አገልግሎት ማዕከል (SPS) ወይም በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በማሳወቅ የተለመደ ትብብሩን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ:- ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ሚዲያ
29/04/2026
“ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተገናኘ ዋና ወንጀል ፈፃሚ (Mastermind) የሆኑ አደገኛ ግለሰቦችን በሕግ ፊት ማቆም ማለት ህዝባችንን ማክበር ነው።” የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ ከሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ጋር በተገናኘ ዋና ወንጀል ፈፃሚ (Mastermind) የሆኑ አደገኛ ግለሰቦችን በሕግ ፊት ማቆም ማለት ህዝባችንን ማክበር ነው ያሉት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በተገመገመበት ወቅት ነው።
የተከበሩ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አያይዘውም ማኅበረሰቡን በወንጀል መከላከል ሥራ ላይ የማሳተፉ ሂደት ባደገ ቴክኖሎጂ ጭምር ታግዞ ይበልጥ እያደገ መምጣቱ የፖሊስ ተቋምን ሕዝቡ እንደ ራሱ ቤት እንዲቆጥረውና በተቋሙ ላይ ያለው እምነት እንዲጎለብት የሚያደርግ በመሆኑ፣ የተጀመረው አበረታች ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳስበዋል።
የፖሊስ ተቋም ግንባታ ኢትዮጵያዊ ቀለም እንዲኖረው የተከናወኑ ተግባራት የሚያስመሰግኑ መሆናቸውን የገለጹት የተከበሩ ሰብሳቢ ኢትዮጵያን የሚመስል ተቋም ከመገንባት አኳያ የተጀመረው ስራ በተቋሙ ውስጥ በሚገባ እየተገለጠ እንደሚገኝና በተለይም የብሔር ብሔረሰቦች ተሳትፎን ከማረጋገጥ አንጻር የተሰራው ሥራ እጅግ አስተማሪና አርአያነት ያለው መሆኑን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ሪፖርቱን አቅርበው በተነሱት ጥያቄዎች ላይ በሰጡት ማብራሪያ ተቋሙ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይን ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፤ በተለይም የአሻራ አገልግሎትን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማዘመን የተጀመረው ሥራ በ2019 ዓ.ም መጀመሪያ ላይ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ሥራ እንደሚገባ አስታውቀዋል። ቴክኖሎጂው ዜጎች ካሉበት ሆነው አገልግሎቱን በቀላሉ እንዲያገኙ የሚያስችል ከመሆኑም ባለፈ፣ የወንጀል ጉዳዮችን በቀላሉ ለመከታተል (Trace) ለማድረግ እና ሰዎች ከወንጀል ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
በሎጂስቲክስና በመሠረተ ልማት ረገድም ተቋሙ ቀደም ሲል የነበረበትን አሮጌ ትጥቅና የአሠራር ዘይቤ በመቀየር ዘመኑን የዋጁ ፓትሮል ተሽከርካሪዎችንና ድሮኖችን በስፋት ጥቅም ላይ ማዋሉን ክቡር ኮሚሽነር ጀነራሉ አንስተው በቀጣይ ለፖሊስ አገልግሎት የሚውሉ ሄሊኮፕተሮችን መጠቀም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል። ይህም ተቋሙ ሀገርን የሚመጥንና በቀጠናው እንደ ሞዴል የሚወሰድ ፕሮፌሽናል የፖሊስ ተቋም ለመገንባት የያዘውን ግብ የሚያሳካ መሆኑን በአጽንኦት ተናግረዋል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ኢሳ ቦሩ በሰጡት አስተያየት የፖሊስ ቀዳሚ ተግባር ወንጀል ከመፈጸሙ በፊት አስቀድሞ መከላከል መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህ ረገድ ማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎትና የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ ውጤት እያመጡ መሆኑን ገልጸዋል።
በተለይም በሰው አልባ ስማርት ፖሊስ ጣቢያ (Smart Police station) እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች የፖሊስን ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑንና ይህም ተቋሙ በኢትዮጵያ ታሪክ ዘመኑን የዋጀ የፖሊስ ተቋም ለመገንባት ለጀመረው ጉዞ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።
የወንጀል ምርመራ ተግባራትም በተመሳሳይ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ እየተከናወኑ እንደሚገኙ የገለጹት የተከበሩ ምክትል ሰብሳቢው የምርመራ ሥራዎች የተጠርጣሪዎችን ሰብዓዊ መብት በጠበቀ መልኩ እንዲከናወኑ መደረጉንና ቀደም ሲል በምርመራ ወቅት የነበሩ ችግሮች በአሁኑ ወቅት መቀረፋቸውን አንስተው ይህም በሕግ የበላይነትና በፍትሕ አሰጣጥ ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣቱን ገልፀዋል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት በቀረበው የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ላነሷቸው በርካታ ጥያቄዎች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ስትራቴጂክ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
https://web.facebook.com/EthiopianFederalPolice1/
29/04/2026
የሀገር ሰላም እና ደኅንነትን በተሻለ ሁኔታ ማረጋገጥ ተችሏል - ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል
******************
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ባከናወናቸው መጠነ ሰፊ የሕግ ማስከበር እና የሪፎርም ሥራዎች፣ የሀገራችንን ሰላም እና ደኅንነት ይበልጥ አስተማማኝ ደረጃ ላይ ማድረሱን አስታወቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የኮሚሽኑን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በዛሬው ዕለት ገምግሟል።
ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ዝርዝር ሪፖርት፣ ተቋሙ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሕዝብ አመኔታ ግንባታ ረገድ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች ይፋ አድርገዋል።
ባለፉት 9 ወራት ከ629 ሺህ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች እና ባለድርሻ አካላት ጋር የሰላም ውይይት ተካሂዷል።
በ2017 በጀት ዓመት 504 የነበረው በሕገ-ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተያዘ የጦር መሣሪያ ብዛት፣ በዘንድሮው ጠንካራ ቁጥጥር ወደ 241 ዝቅ እንዲል ተደርጓል።
ከ2 ሺህ በላይ ዜጎችን ከሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎች መታደግ የተቻለ ሲሆን፣ 751 አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ለሕግ ቀርበዋል።
የተለያዩ መንግሥታዊ እና ሕዝባዊ በዓላት ምንም ዓይነት የፀጥታ ስጋት ሳይገጥማቸው በሰላም እንዲጠናቀቁ ተደርጓል።
ተቋሙ የሕዝብ አለኝታ ለመሆን የጀመረው ጉዞ በቴክኖሎጂ የታገዘ መሆኑ ተገልጿል። በወንጀል ምርመራ ጥበብ እና በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የታየው ከፍተኛ መሻሻል፣ ፖሊስ በሕዝብ ዘንድ የላቀ ተአማኒነት እንዲያገኝ አስችሎታል።
በኢትዮጵያ ታሪክ ዘመኑን የዋጀ እና የኢትዮጵያን ቀለም የሚመስል አሳታፊ የፖሊስ ተቋም መገንባት መቻሉ የሚበረታታ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ እፀገነት መንግሥቱ ገልጸዋል።
የሕግ እና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮሚሽኑን ሪፖርት በመገምገም፣ በሂደቱ የታዩ ጥንካሬዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስቧል።
በተለይም የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ እና የዜጎችን ደኅንነት አስተማማኝ በሆነ ሁኔታ ለመጠበቅ የጀመራቸውን የሪፎርም ሥራዎች አጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ሰጥቷል።
ምንጭ፡-EBC
24/04/2026
ለፀረ- ሰላም ቡድኖች ሊደርስ የነበረ የክላሽንኮቭ ጥይት በቁጥጥር ሥር ዋለ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፦ ለፀረ-ሰላም ቡድኖች ሊደርስ የነበረ 1 ሺህ 272 የክላሽንኮቭ ጥይት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ፖሊስ አስታውቋል።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር ሊውል የቻለው በዲላ ከተማ ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ሕገ- ወጥ ጥይት በማከማቸት ለፀረ ሰላም ቡድኖች ለማስተላለፍ ሲሞክር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖለስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ባካሄደው ኦፕሬሽን ነው።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ከአጋር የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ከጽንፈኛና ሽብር ቡድኖች ተልዕኮ በመቀበል የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ላይ ጠንካራ ክትትል በማድረግና በቁጥጥር ሥር በማዋል ውጤታማ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ኅብረተሰቡ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ሲመለከት በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፤ በ991 ነፃ የስልክ መስመር እና የሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያን (SPS) በመጠቀም ወይም በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ቀርቦ ጥቆማ በመስጠት የዘወትር ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።
ቀጥለው ያሉትን ሊንኮች በመጫን ወቅታዊ መረጃዎችን ይከታተሉ፦
የአማርኛ ቋንቋ ገፅ
https://web.facebook.com/EthiopianFederalPolice1/
24/04/2026
የኢትየጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሚያዝያ 8 እስከ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ጠንካራ ኦፕሬሽን 890.2 ሚሊዮን ብር የዋጋ ግምት ያላቸው የገቢና የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዙን አስታወቀ
********************************************************
ዕቃዎቹ ሊያዙ የቻሉት አጋር የፀጥታ አካላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በጥቆማ እና በፓትሮል ክትትል በወንጀሉ ከተጠረጠሩ 43 ኮንትሮባንዲስቶች እና ከሰባት ተሽከርካሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በቁጥጥር ሥር ከዋሉ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግብርና ምርቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ጥፍጥፍ ወርቅ፣ የተለያዩ ማዕድናት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት እና የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡
በተመሳሳይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት 450 ሚሊዮን፣ ፣ በአዋሽ 126 ሚሊዮን እና ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት 108 ሚሊዮን ብር የዋጋ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል።
ኅብረተሰቡ የኮንትሮባንድ ዝውውር በሀገራችን ላይ የሚያስከትለውን ዘርፈ-ብዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳቶች በመገንዘብ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ሲመለከት በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፤ በ991 ነፃ የስልክ መስመር እና የሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያን (SPS) በመጠቀም ወይም በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ቀርቦ ጥቆማ በመስጠት የዘወትር ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።
Ethiopian Federal Police
24/04/2026
ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም የወጣችው ጋዜጣችን የተለያዩ ተቋማዊና ወንጀል ነክ ዜናዎችን፣ ታሪኮችን እንዲሁም የተለያዩ ፁሁፎችን ይዛለች ያንብቧት ይከታተሏት!ሙሉ የጋዜጣውን ዘገባ ቴሌግራም ሊንካችንን በመጫን ማግኘት ይችላሉ
08/04/2026
ሚያዚያ 01 ቀን 2018 ዓ.ም የምትወጣው ጋዜጣችን የተለያዩ ተቋማዊና ወንጀል ነክ ዜናዎችን፣ ታሪኮችን እንዲሁም የተለያዩ ፁሁፎችን ይዛለች ያንብቧት ይከታተሏት!
06/04/2026
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይፈለግ የነበረ አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም)ን ከነግብረ-አበሮቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
ከ3 ሺህ በላይ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ በማዘዋወር፣ ከ100 በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገ እና ከ50 በላይ ሴቶች እንዲደፈሩ ያደረገው ይትባረክ ዳዊት (ክብሮም)ን ከ9 ግብረ-አበሮቹ ጋር በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ አጠናቆ ለዓቃቢ ህግ መላኩን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ይህንን ውስብስብና ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ምርመራ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከል ከሚሰራ The Regional Operational Centre in support of the Khartoum process (ROCK) ከተባለ ድርጅት ጋር ባደረገው የመረጃ ልውውጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ ይፈለግ የነበረው አደገኛ ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ ይትባረክ ዳዊት አለሙን በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ላይ ፖሊስ በቅንጅት በቁጥጥር ሥር አውሏል።
ተጠርጣሪው በፓስፖርት ስሙ ይትባረክ ዳዊት አለሙ፣ ቤተሰቦቹ በልጅነቱ ያወጡለት ስም ጳውሎስ ዳዊት ወልዳይ፤ ወንጀል መስራት ሲጀምር የሚታወቅባቸው ስሞች አድሀኖም፣ ሱዳን ሀገር የሚታወቅበት ስም አህመድ፤ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ የሚጠቀምበት ስም ሙኒር ሲሆን ክብሮም ደግሞ በስዊድን እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚጠቀምባቸው ሀሰተኛ ስሞች መሆናቸውን ፖሊስ በምርመራው አረጋግጧል፡፡
ፖሊስ እነዚህን ስሞች ለምርመራው አጋዥ አድርጎ ያደገ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተጠናከረ ምርመራና ክትትል በማድረግ ከ70 በላይ በሀገር ውስጥና በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ዋና ዋና የሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችን ከለየ በኋላ ዋናውን ተጠርጣሪ ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ህገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ተከታትሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራውን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡
ፖሊስ የተያዙትንም ሆነ ያልተያዙትን ተጠርጣሪዎች በወንጀሉ ያፈሩትን ሀብት በጥናት በመለየት ሌሎች ሀብቶቻቸውንና በባንክ የሚገኝ ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ በፍርድ ቤት እንዲታገድ ማድረጉን ገልጿል፡፡
ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪ ቡድኑ ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ በርካታ ወጣቶችን ከኢትዮጵያ፣ ከሱዳን፣ ከኤርትራ፣ ከጅቡቲ፣ ከኬንያ እና ከሶማሊያ በመመልመል ወደ ሊቢያ በመውሰድ ሊቢያ ውስጥ ባዘጋጁት መጋዝን እንዲታገቱ በማድረግ የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ ከቤተሰቦቻቸው በማስላክ፤ ገንዘብ ያልከፈሉትን በቀን አንድ ጊዜ ብቻ በትንሹ ምግብ እንዲመገቡ በማድረግ፣ በጎማ፣ በዱላ እና በኤሌክትሪክ ገመድ በሰንሰለት እጅ እና እግራቸውን አስረው በመግረፍና በማስገረፍ፣ የውሃ ማሸጊያ ፕላስቲክ አቃጥለው ሰውነታቸው ላይ በማንጠባጠብ ከፍተኛ ስቃይ በማድረስ፣ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመፈፀም በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው እንዲያልፍ፣ የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው፣ ሴቶች እንዲደፈሩ እና ከፍተኛ አካላዊና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት እንዲደርስባቸው ማድረጋቸውን ፖሊስ በምርመራ ማረጋገጥ ችሏል፡፡
ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ሊቢያ ውስጥ ተጎጅዎችን አግተው የሚያሰቃዩባቸው አምስት ማከማቻ መጋዘን እንዳላቸው እና በዚህ አደገኛ ወንጀል ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ በህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ሲንቀሳቀስ እንደነበረ ፖሊስ በሰበሰበው ማስረጃ ማረጋገጥ የቻለ ሲሆን ከ100 በላይ ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸውን በሀገር ወስጥና በውጭ ሀገር የምስክርነት ቃል የመቀበል ሥራ መሰራቱንም ጨምሮ ገልጿል፡፡
ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሊቢያ፤ ሱዳን፤ ቤልጂየም፤ እንግሊዝ፤ ካናዳ፤ ኖርዌይ፤ ኔዘርላንድ፤ ሉግዘንበርግ እና ስዊዘርላንድ ከሚገኙ አስራ ስድስት ተጎጅዎች ላይ ቃል መቀበሉንም ፖሊስ አሳውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በሀገርና በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለውን ይህንን ድንበር ተሻጋሪ ወንጀል ለመከላከል ዘመኑ ያፈራቸውን የምርመራ ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም በተሟላ ፖሊሳዊ ስብዕናና ስነ-ምግባር እየተመራ በላቀ ቁርጠኝነት ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል።
ተቋሙ ከሀገራት ጋር በፈጠረው የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነትም ዓለም አቀፍ የወንጀል ተፈላጊዎችን ጭምር በቁጥጥር ሥር አውሎ በተለያየ ጊዜ ምርመራ በማጣራት በሀገር ውስጥ በህግ እንዲጠየቁና የተወሰኑት ደግሞ ከሀገራት ጋር ባለው የወንጀለኛ ልውውጥ ስምምነት መሰረት ተላልፈው እንዲሰጡ እያደረገ ይገኛል፡፡
ይህ ውስብስብ ድንበር ተሸጋሪ የወንጀል ጉዳይ በተሳካ ሁኔታ እንዲጣራ ከፖሊስ ጋር በትብብር ለሰሩት ለፍትህ ሚኒስቴር፣ ለብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ለROCK እና በጉዳዩ ላይ መረጃ ሲሰጡ ለነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ላቅ ያለ ምስጋና እያቀረበ ኅብረተሰቡ ማንኛውንም የወንጀል ድርጊት ሲመለከት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፤ በ991 ነፃ የስልክ መስመር እና ሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያ (SPS) በመጠቀም ወይም በአቅራቢያው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት ቀርቦ ጥቆማ በመስጠት የዘወትር ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል፡፡
https://web.facebook.com/EthiopianFederalPolice1/