14/03/2026
የተሰባጠረ የአመጋገብ ስርዓት ጤናማና አምራች ዜጋን ለማፍራት!
(አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4 ቀን 2018 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር)
ግብርና ሚኒስቴር ከአለም ምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ጋር በመተባበር ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ ባለሙዎች እና ለግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ የህብረት ስራ ማህበር ባለሙያዎች የኢትዮጵያ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለአራት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡
ስልጠናው በንድፈ-ሃሳብና በተግባር የታገዘ ሲሆን የኢትዮጵያ ምግብን መሰረት ያደረገ የአመጋገብ መመሪያ አተገባበር፣ ስርዓተ-ምግብ ተኮር ግብርናን መሰረት ያደረገ የምግብ አዘገጃጀት እንዲሁም የምግብ ደህንነትና ጥራት አጠባበቅ ላይ ያተኮረ ነው፡፡
አንድ ሰው በቀን ውስጥ ስድስቱን የምግብ ምድቦች ማለትም ብዕርና አገዳ/መደበኛ፣ ጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ የእንስሳት ተዋፅዖ እና ቅባት/ዘይት እንዲሁም በአንድ ገበታ ደግሞ አራት የምግብ ምድቦችን አካቶ መመገብ እንዳለበት በስልጠናው ተገልጿል፡፡
የተሰባጠረ የአመጋገብ ስርዓት ጤናማ እና አምራች ዜጋን ለማፍራት ሚናው የጎላ መሆኑንም በመድረኩ ተመላክቷል፡፡
07/02/2026
ዜና
የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር ስምንተኛ(8ኛ) ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ፡፡
(አዲስ አበባ፣ ጥር 30/2018 ዓ/ም ፣ግብርና ሚኒስቴር ሸማቾች ማኅበር)
የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር በዛሬዉ ቀን በግብርና ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አደራሽ የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ፣ንዑሳን ኮሚቴ አባላት፣ተጋባዥ እንግዶች(የፌደራል ህብረት ሥራ ኮሚሽን አደራጅ ክፍል ፣ኦዲት ክፍል ባለሙያ) እና የማህበሩ አባላት በተገኙበት 8ኛ ዙር ጠቅላላ ጉበኤ ተደረገ፡፡
በጠቅላላ ጉባዔዉ በኢትዮጵ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የ2018 ዓ/ም ኦዲት ሪፖርት ከኢት/ህ/ሥ/ኮሚሽን ኦዲተር ባለሙያዎች ቀርቦ ዉይይት ከተደረገበት በኋላ በሙሉ ድምዕ የፀደቀ ሲሆን በቀጣይ በጀት ዓመት ለማህበሩ ዉጤታማነት የሚረዳ ግብዓቶች ከቤቱ እና ከ ኦዲት ሪፖርት ማግኘት ተችሏል፡፡
አዲሱ የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ሸማቾች ኃ/የተ/ህብረት ስራ ማህበር አመራሮች እና ንዑሳን ኮሚቴዎች በተለያዩ ምክንያት የለቀቁ ሲሆን የስራ አመራሩ አጠቃላይ ሪፖርት በማህበሩ ሥራ አመራር ቦርድ የ2018 እቅድ በማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ልደቱ ሞላ ፣ የቁጥጥር ኮሚቴ የ2017 ዓ.ም ሪፖርት በአቶ ተመስገን ደሳለኝ አማካኝነት እና እቅድ በወ\ሮ አዲሳለም በየነ የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ እና ዉስጣ ደንብ ለ አባላት ቀርቧል በዚህም ማሻሻያ የተደረገ ሲሆን ፡፡ በዚህ መሠረት የቀረቡ ሪፖርቶችን ቤቱ በመልካምነት በመቀበል በቀጣይ መስተካከል ያለባቸዉን ነገሮች ዝርዝር በማቅረብ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
በመጨረሻም በ2017 ዓ/ም ከ9 ሚልዮን ባለይ ትርፍ የተረፋ ሲሆን የትርፍ ክፍፍል አወሳሰን በተመለከተ ለአባላቱ ዉሳኔ እንዲያስተላልፉ ቀርቦ በአባሉ ምርጫ ወደ ዕጣ ማዞር የሚፈልግ እንዲዞረለት፣ትርፍ ክፍፍሉን መዉሰድ የሚፈልግ በለው እጣ መጠን ትርፍ ክፍፍል አስከ የካቲት 30/2018 ዓ፣ም ድረስ ብቻ እንዲቀበል የተወሰነ ሲሆን በዚህ ጊዜ ተገኝቶ ትርፉን መዉሰድ ያልቻለ አባል ያገኘዉ ትርፍ ወደ ዕጣ የሚዞር መሆኑን የሥራ አመራር ልቀመንበር እና የቁጥጥር ኮሚቴ ሰብሰቢ ለተነሱት ጥያቄዎች እና እቀድ እና ደንቦች በማጻደቅ ማብራሪያ በመስጠት ጉባዔዉ ተጠናቅቋል፡፡
ዘጋቢ፡- ልደቱ ሞላ
ፎቶ፡ ጌታቸው ምትኩ
10/01/2026
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በኅብረት ሥራ ማህበራት ማሻሻያ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ
******
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 51ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
የኅብረት ሥራ ማህበራት ማሻሻያ አዋጅም ምክር ቤቱ የተወያየበት አንዱ አጀንዳ ነበር፡፡
በስራ ላይ ያለው የኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 985/2009 ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ከተቀመጡ አቅጣጫዎች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ለማድረግ አዋጁን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ማሻሻያ አዋጁ መዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡
ምክር ቤቱም በማሻሻያ አዋጁ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
07/01/2026
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን እና መድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!! በዓሉ የደስታ እና የብልፅግና እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቴ ነው::
መልካም ገና!!!
26/09/2025
ውድ የማህበራችን አባላት እና ቤተሰቦች
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰዎ!
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!
MOA COOPERATIVE
ስለ ማህበራችን ወቅታዊ መረጃዎችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችን https://moa cooperative በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ!