ኮልፌ ወረዳ 02 ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት kolfe woreda 02 peace and security office

ኮልፌ ወረዳ 02 ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት  kolfe woreda 02 peace and security office

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኮልፌ ወረዳ 02 ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት kolfe woreda 02 peace and security office, Government Organization, Addis Ababa.

17/07/2026

ነገ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል። ሰልፉ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።
***
ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ/ም

፦ በትግራይ ክልል እየተባባሰ የመጣውን ቀውስ ለመቃወምና ለማስቆም እንዲሁም ለፌደራል መንግስትና ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ''አፈሳ ይቁም ሰላም ይስፈን'' በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፉ ይደረጋል።
ሰልፉ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በዝህም መሰረት:-
# ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ቅ/ዑራኤል አደባባይ
# በቦሌ መንገድ ወደ መስቀል አደባባ ኦሎምፒያ አደባባይ
# ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ
# ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ መስቀል ለገሀር መብራት
# ከለገሀር ቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታዲዮም ለገሀር ቴሌ ማቋረጫ
# ከአራት ኪሎ ወደ መሰቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ-መንግስት
# ከካሳንቺስ በመቅረዝ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ መቅረዝ ሆስፒታል አጠገብ
# ከአምባሳደር ቴአትር ወደ መሰቀል አደባባይ ሐራምቤ መብራት የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

ከዛሬ ሐምሌ 10 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ በመስቀል አደባባይና በዙሪያው ባሉ መንገዶች ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ተሽከርካሪ ለአጭርም ሆነ ረዥም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

መረጃው የአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ነው

15/07/2026
Photos from ኮልፌ ወረዳ 02 ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት  kolfe woreda 02 peace and security office's post 12/07/2026

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሄደ።
በመርሃ ግብሩ የወረዳው አመራሮች፣ ሠራተኞች፣የሰላም ሰራዊት የወጣቶች ክንፍ አባላትና የተለያዩ የማህበረሰብ አባላት በበጎ ፈቃድ በመሳተፍ የደም እጥረት ለሚጋለጡ እናቶች፣ ህፃናት፣ የአደጋ ተጎጂዎች እና ሌሎች ህሙማን ሕይወት ለማዳን የሚያግዝ ደም ለግሰዋል።
በዚህ አጋጣሚ ኃላፊዎች የደም ልገሳ የሰው ሕይወትን የሚታደግ ከፍተኛ ሰብዓዊ ተግባር መሆኑን በመግለጽ፣ ማህበረሰቡ በቀጣይም በመደበኛነት በደም ልገሳ መርሃ ግብሮች እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

Photos from ኮልፌ ወረዳ 02 ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት  kolfe woreda 02 peace and security office's post 12/07/2026

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቅዳሜና እሁድ የገበያ ማዕከላት የምርት አቅርቦት በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ መቀጠሉን የገቢያ ማረጋጋት ግብረሀይል ቁጥጥር እና ምልከታ አድርጓል ።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 በሚገኙ የገበያ ማዕከላትና የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት የሚቀርቡ መሰረታዊ የፍጆታ ምርቶች አቅርቦት በተሻለ ጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠናክሮ መቀጠሉን የአካባቢው ሸማቾች ገለጹ።

በአሁኑ ወቅት በገበያው ላይ የሚስተዋለውን ያልተገባ የዋጋ ንረት ለመግታትና ህብረተሰቡን ከአስፈላጊ በላይ ወጪ ለመታደግ ወረዳው እያደረገ ያለው የገበያ ማረጋጋት ስራ ውጤት እያሳየ መሆኑን የነዋሪዎች አስተያየት ያመለክታል።

በወረዳው የሚገኙ የተለያዩ የገበያ ማዕከላትን የሚገበያዩ ሸማቾች እንደገለጹት፤ ቀደም ሲል በአንዳንድ ምርቶች ላይ ይታይ የነበረው የአቅርቦት እጥረትና የዋጋ መዋዠቅ አሁን ላይ እየተቀረፈ መጥቷል። በተለይም እንደ ስኳር፣ ዱቄት፣ ጥራጥሬና የሽንኩርት ምርቶች ባሉ መሰረታዊ ሸቀጦች ላይ የሚታየው አቅርቦት ህብረተሰቡ በሰላም መገበያየት እንዲችል ማድረጉን ጠቁመዋል።

"በተለይ ምርቶቹ ጥራታቸውን የጠበቁ ከመሆናቸውም በላይ ከግል ነጋዴዎች ጋር ሲነፃፀር ማህበረሰቡን በእጅጉ የጠቀመ ተመጣጣኝ ዋጋ ነው ያላቸው።"

የወረዳው አስተዳደር በበኩሉ፤ የሸማቹን ማህበረሰብ ፍላጎት ለማሟላት ከአምራቾችና ከአቅራቢዎች ጋር በቀጥታ በመቀናጀት ምርቶችን ያለ ምንም መካከለኛ ለገበያ ማቅረብ በመቻሉ ዋጋውን ማረጋጋት መቻሉን አስታውቋል።

ክፍተቶች እንዳይፈጠሩም የክትትልና የቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በቀጣይም የምርት አቅርቦቱ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን እንደሚሰራ የአስተዳደሩ መረጃ ያመላክታል።

Photos from ኮልፌ ወረዳ 02 ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት  kolfe woreda 02 peace and security office's post 12/07/2026

ሰላምና ፀጥታ ባለፉት አምስት አመታት

በሰላምና ፀጥታ ስራችን ህዝባችንን ባለቤት አድርገን በሰራነው ስራ አንድም ኮሾታና ሳይሰማ የከተማችንን ሰላም ዘላቂ አድርገነዋል።

ባለፉት አምስት አመታት ከ200ሺ በላይ የሰላም ሰራዊትን በማደራጀት እንዲሁም ከ10ሺ በላይ የህዝብ ቅጥር ጥበቃ አሰልጥኖ በማሰማራት የማይተካ ህዝባዊ ሚናቸውን ተወጥተዋል።

በከተማችን የፀጥታ መዋቅሩ የሰላም ሰራዊትና ነዋሪው በቅንጅት በመስራታቸው መድናዋን ''የሰላም ከተማ'' በመባል ተጠቃሽ አድርጓታል።

ደንብ መተላለፎችን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን ለማጠናከር በተወሰዱ እርምጃችም በከተማዋ የሚታዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ተችሏል።

በተለይም ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ህገ ወጥ ማስታወቂያ ፣ህገ ወጥ የጎዳና ንግድ፣ ህገ ወጥ የእንስሳት ዝውውርና እርድ፣ ህገ ወጥ የመንገድ አጠቃቀምና የህገ ወጥ ግንባታ ቁጥጥር ስራዎች የህግ የበላይነትን በማስከበር የደንብ መተላለፎችን በዘላቂነት በመቀነስ የነዋሪውን ንብረትና መብት በማስከበር ላይ መሰረታዊ ለውጦች ተመዝግበዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Photos from Addis Ababa Police's post 12/07/2026
Photos from ኮልፌ ወረዳ 02 ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት  kolfe woreda 02 peace and security office's post 19/06/2026

ወረዳ 02 በወረዳችን የኑሮ ዉድነት አና ገቢያ ቁጥጥር እንዲሁም ያሉት የቅዳሜና እሁድ ገበያ አቅራቢዎች የምርት ጥራት አቅርቦት ስታንዳርድ እና የምርት ዋጋ ሁኔታ በተጨማሪ የተጠያቂነት ስረዓት እና የቀጣይ አቅጣጫ ላይ ጋር በዋና ስራ አስፈፃሚ በተመራ ግብረ ሀይል አባላት ጋር በሳል ውይይት ተደርጓል።

Photos from ኮልፌ ወረዳ 02 ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት  kolfe woreda 02 peace and security office's post 29/05/2026

በበቀን 21/09/2018 በአንድ ማዕከል የተሰጠው የሰላም ሰራዊት ስምሪት

Photos from ኮልፌ ወረዳ 02 ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት  kolfe woreda 02 peace and security office's post 21/03/2026

የወረዳ 2 ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት እና የጋራ ሙለታ ማህበር ወጣቶች ጋር በጋራ በመሆን የ1447ኛውን የኢድ አል-ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ፣ በወረዳችን በሚገኙ ለአቅመ ደካሞችና ለከፋ ማህበራዊ ችግር ተጋላጭ ለሆኑ ወገኖቻችንን እና የፀጥታ አጋዥ ለሆኑ ሰላም ሰራዊት ማእድ የማቋደስ መርሃ ግብር አድርገናል ።

Photos from Addis Ababa City Peace and Security Administration Bureau's post 20/03/2026
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa