EOTC Lawyers Executive Committe ኢኦተቤ የሕግ ባለሙያዎች ዐብይ ኮሚቴ

EOTC Lawyers Executive Committe
ኢኦተቤ የሕግ ባለሙያዎች ዐብይ ኮሚቴ

Share

በኢ/ኦ/ተ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የሕግ አገልግሎት መምሪያ የሕግ ባለሙያዎች ዐብይ ኮሚቴ መልዕክት የሚተላለፍበት ገፅ ነው

Photos from EOTC Lawyers Executive Committe
ኢኦተቤ የሕግ ባለሙያዎች ዐብይ ኮሚቴ's post 09/11/2025

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጠቅላይ ቤተ ክህነት በሕግ አገልግሎት መምሪያ የሕግ ባለሙያዎች ዐብይ ኮሚቴ መንፈሳዊ ጉባኤና ምክክር መርሐ ግብር ብፁአን አባቶች በተገኙበት አከናወነ::

የሕግ ባለሙያዎች ዐብይ ኮሚቴ ከተጣለበት ኃላፊነት ጎን ለጎን መንፈሳዊ ጉባኤ በማዘጋጀት የአባላቱን ሁለንተናዊ መንፈሳዊ ሕይወት በስብከተ ወንጌል ለማነፅ ይቻል ዘንድ በ2 ወር አንድ ጊዜ መርሐ ግብር ያዘጋጃል::

በዕለተ ቅዳሜ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ, ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የሚኒሶታና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ, ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ, ብፁዕ አቡነ ሚካኤል የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት, የመምሪያው ኃላፊ አፈ መምህር አባ ገብረሥላሴ ጌትነት እና መምህራነ ወንጌል በተገኙበት ተከናውኗል::

የዕለቱን ትምህርተ ወንጌል ዲን ያረጋል አበጋዝ ያስተማሩ ሲሆን ዘማሪት ሲስተር ፋሲካ በዝማሬ አገልግለዋል::

በዕለቱም በተደረገ ወቅታዊ ምክክር የአርሲ ሀገረ ስብከትን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ስፍራዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ , በአገልጋይ ካህናትና ምዕመናን ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በተመለከተ ምክክር የተደረገ ሲሆን እንዲህ አይነት ድርጊቶችን በተመለከተ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የሰብዓዊ መብት ማስከበር ሥራን በልዩነት የሚሠራ ግብረ ኃይል እንዲዋቀርና ለተግባራዊነቱም ከሚመለከታቸው የቤተ ክርስትያናችን እንዲሁም መንግስታዊ አካላት ጋር በቅርበት በመሥራት ለውጤት ለመትጋት ኃላፊነት ተወስዷል::

በተጨማሪም በዕለቱ የተገኙት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ "ከመቼውም ጊዜ በላይ ይህ የሕግ ባለሙያዎች ስብስብ ለቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎት አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይነትም በጋራ በመሥራት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሚተጉ" ገልፀው አባታዊ ቡራኬና ቃለ ምዕዳን ሰጥተው መርሐ ግብሩ ተጠናቋል::

07/11/2025

ነገ ቅዳሜ

30/10/2025

የማይቀርበት መንፈሳዊ ጉባዔ🙏 ከወዲሁ አጀንዳችንን እናስተካክል!!!

21/10/2025
Photos from EOTC Lawyers Executive Committe
ኢኦተቤ የሕግ ባለሙያዎች ዐብይ ኮሚቴ's post 29/09/2025

ወጣት ብሩክ ኦዳ ወይም በማኅበራዊ ሚዲያ ስሙ ባሮክ 21 እየተባለ የሚጠራው ወንድማችን በተጠረጠረበት የወንጀል ጉዳይ በወቅቱ ፈፀመ የተባለው ድርጊት ከሃይማኖቱ ክብር እና ቁጭት የተነሳ በፈፀመው ተግባር በሕግ ቁጥጥር ስር ውሎ በጊዜ ቀጠሮ ላይ የነበረ ሲሆን ተጠርጣሪውም ከተያዘበት ጊዜ ጀምሮ ለሃይማኖቱ ቀናኢ በመሆን ለፈፀመው ተግባር ላይ በመያዙ በዚህ ልዩ ምክንያት የኢኦተቤክ የሕግ ባለሙያዎች ዐብይ ኮሚቴ የተሰየሙ 6 ጠበቆችን መድቦ ጉዳዩን ሲከታተል ቆይቷል::

በዚህም መሰረት ዛሬ መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት በዋለው ችሎት በተደረገ የሕግ ክርክር ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪውን በ 30ሺ ብር ዋስ ጉዳዩን ከውጭ ሁኖ እንዲከታተል ትዕዛዝ ሰጥቷል::

በሌላ በኩል በቤተክርስቲያን አባቶች ጥቆማ አቅራቢነት የእመቤታችን ስዕለ አድህኖን የቀደደች ግለሰብም ዛሬ ፍ/ቤት የቀረበች ሲሆን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ በመከታተል የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ የሕግ ጉዳይ መረጃዎች:- ገፃችንን ይከታተሉ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address

Addis Ababa
183