አዲስ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ addis ketma culture &arts office

አዲስ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ   addis ketma culture &arts office

Share

Arts

Photos from አዲስ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ   addis ketma culture &arts office 's post 04/02/2026

አዲስ አበባ የብዙ ብሔር ብሔረሰቦች መገኛና የጥበብ ማዕከል መሆኗን የሚያሳይ ታላቅ ፌስቲቫል።

17ኛው ከተማ አቀፍ የባህል ፌስቲቫል “አዲስ አበባ የባህል እና ፈጠራ ሞዛይክ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚካሄደው ደማቅ ፌስቲቫል
ጥር 24/2018 ዓ.ም አዲስ ከተማ

Photos from አዲስ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ   addis ketma culture &arts office 's post 02/02/2026

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ ጥበብ ጽ/ቤት በክፍለ ከተማው ስር የሚኙ ቋሚ
ቅርሶችን ጉብኝት አደረገ::

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ቋሚ ቅርሶች መካከል 3 ጉብኝት ቦታዎችን ለማየት ተችሏል:: ከነሱም መካከል
*ሂንዱ መሃጃን የባንየን አስክሬን ማቃጠያ
*መርካቶ አዳራሽ ቁጥር 1 እና ቁጥር 2 ሲሆኑ በዚህ ጉበኝት ላይም አባገዳ
የምክርቤት አባላት ከመማክርት ዘርፍ
ሴት ማህበር ወጣት ሊግ እና አማተሮች ተሳትፈውበታል ::
ጥር /21/2018ዓ.ም አዲስ ከተማ

Photos from የአዲስ አበባ ባህል እና ኪነ-ጥበብ ቢሮ - Addis Ababa Culture & Arts bureau's post 15/01/2026
Photos from አዲስ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ   addis ketma culture &arts office 's post 15/01/2026

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ ጥበብ ጽ/ቤት በሌብነትና ብልሹ አሰራር እና ግልጽነትና ተጠያቂነትን ማስረጽ በሚል ለሠራተኛ ስልጠና ተሰጠ
ታህሳስ /2018ዓ.ም አዲስ ከተማ

Photos from አዲስ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ   addis ketma culture &arts office 's post 05/01/2026

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ "የጉባ ብስራቶች የወል ትርክት ትዕምርቶች" በሚል መሪ ቃል የ5ኛ ዙር የአብርሆት ስነ-ጽሑፍ ማዕድ ተካሄደ።
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት የ5ኛ ዙር የአብርሆት ስነ-ጽሑፍ ምሽት አካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ በቀለ ጉታ የሥነ-ጽሑፍ ምሽት ገዢ ትርክትን በማጽናት የነገ ሀገራችን ተስፋን የምናለመልምበት መሆኑን በመረዳት ለህዝባችን ብሎም ለዲሞክራሲያዊ ግንባታ ማበብ ወሳኝነት ያለው በመሆኑ ሁላችንም በተሰጡን ኃላፊነት ከዳር ማድረስ አለብን ብለዋል።

የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ማዕረግነሽ ደምሴ በበኩላቸው የሥነ-ጽሑፍ ምሽት የወል ትርክቶችን ለመጪው ትውልድ በኪነ-ጥበብ ዘርፎች ማስተማርና ማስረፅ ትልቅ ሥራችን አድርገን ልሰራው ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

በኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለታዳሚው ቁምነገር የሚቀስምበት የተለያዩ ትርዕቶችና ሁነቶች ባማረና በደመቀ ሁኔታ አቅርበዋል።
ታህሳስ27/2018 ዓ.ም
አዲስ ከተማ

Photos from አዲስ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ   addis ketma culture &arts office 's post 02/01/2026

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ ጽ/ቤት
የኪነ ጥበብ ኢንዱስትሪ ማበልፀግና ማስፋፋት ቡድን የአንደኛ ደረጃ የሥዕልና የሙዚቃ መምህራን የሙያ ማጎልበቻ
ስልጠና ተሰጠ::
ታህሳስ24/2018 ዓ/ም አዲስ ከተማ

Photos from አዲስ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ   addis ketma culture &arts office 's post 31/12/2025

መጭውን የገና በዓል አስመልክቶ የዕደጥበብ ውጤቶች ምርትና አገልግሎት የሚያስተዋውቅ ባዛር ተከፈተ::
የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ባህልና ኪነጥበብ ጽ/ቤት መጭውን የገና በዓል አስመልክቶ የእደጥበብ ውጤቶችን ምርትና አገልግሎት የሚያስተዋውቅ ባዛር በአስተዳደሩ ግቢ በይፋ ተከፍቷል::

የጽ/ቤቱ ሃላፊ ወ/ሮ ማዕረግነሽ ደምሴ ሐገር በቀል የሆኑ የእጅ ስራ ውጤቶችን ምርት መጠቀም ተገቢ መሆኑን ታሳቢ ያደረገ ባዛር ነው ብለዋል::

የጽ/ቤቱ የባህል እሴቶችና ዕደጥበብ ሃብቶች ቡድን መሪ አቶ አሳቤ ሙላት ባዛሩ የእደጥበብ ውጤቶችን ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ጠቅሰው ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ በመሆኑ የአስተዳደሩ ሰራተኞችና ነዋሪዎች መገበያየት ይችላሉ ብለዋል ::
ታህሳስ 22-2018ዓ.ም
የአዲስ ከተማ

Photos from አዲስ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ   addis ketma culture &arts office 's post 31/12/2025

አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ባህል ኪነ- ጥበብ ጽ/ቤት አቻ ተቋም ጋር ልምድ ልውውጥ አካሄደ ::
በልምድ ልውውጡ የክፍለ ከተማውን ባህል ኪነጥበብ ጽ/ቤት አገልግሎት አሰጣጥ፣ ዘመናዊና ባህላዊ ሙዚቃ ክፍሎች አደረጃጀት፣ የአንፊ ቲያትር ግንባታ እና አገልግሎት አሰጣጥ ፣ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ቤተ-መጻህፍትና አጠቃላይ
የጽ/ቤቱ አደረጃጀት ላይ ልምድ መለዋወጥ ችለናል
ታህሳስ 21/4/2018 አዲስ ከተማ

Photos from አዲስ ከተማ ባህልና ኪነ-ጥበብ   addis ketma culture &arts office 's post 30/12/2025

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የባህልና ኪነ - ጥበብ ጽ/ቤት የቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ቡድን ከህግ ማዕቀፍ አንጻር ስለ ቅርስ ህጉ ምን ይላል በሚል የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ ታህሳስ 20/2018 ዓ/ም አዲስ ከተማ

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Addis Ababa