Bole Woreda 03 Education office

Bole Woreda 03 Education office

Share

Education for All

Photos from Bole Woreda 03 Education office's post 04/05/2026

ዛሬ ጠዋት እራስን ማሻሻል ላይ መሰረት ያደረገ የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄዷል !!

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በዛሬው እለት የተደረገ ሲሆን በ "Manage Emotions" በሚል ርዕስ How to understand and manage yours emotions ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
መልካም የስራ ሳምንት ይሁንልን🙏

ቀን:- 26/08/2018

Addis Ababa Education Bureau

Photos from Addis Ababa Education Bureau's post 06/04/2026
06/04/2026

ዛሬ ጠዋት እራስን ማሻሻል ላይ መሰረት ያደረገ የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄዷል !!
መልካም ሳምንት ይሁንልን🙏

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በዛሬው እለት የተደረገ ሲሆን ""ውጤታማ እና ስኬታማ"" ለመሆን የሚያስፈልጉዎት ዋና ዋና ነገሮች በሚል ርዕስ ላይ ውይይት ተደርጓል።
በስራዎት ውጤታማ መሆን ይፈልጋሉ ? እንግዲያውስ እነዚህን የስነ-ልቦና መመሪያዎች አንብባችሁ ተግባራዊ አድርጓቸው፡፡

በስራችን ውጤታማ ለመሆን ከሚያስፈልጉን ነገሮች መካከል የስነልቦና ዝግጅት የመጀመሪያው የስራ መሳሪያችን ነው፡፡
ሁላችንም በተሰማራንበት የስራ መስክ ውጤታማ እንድንሆን ከሚረዱን ዋና ዋና ነገሮች መካከል ስንመለከት በጥቅቱ፡፡

1, ፍላጎት፡-
በስራችን ስኬታማ ለመሆን ከሚያስፈልጉን ነገሮች መካከል ፍላጎትየመጀመሪያው እና ዋናወ መሰረታዊ የስኬት ምስጢር ነው፡፡

2, እምነት፡-
እምነት አላማችን የሚገነባበት መሠረት ስለሆነ ሁላችንም የምንሰራውን ስራ አምነን መቀበል እና በመጨረሻም ውጤታማ እንደምንሆን ተስፋ ማድረግ አለብን፡፡

3, እራስን ማሳመን፡-
ወደ ስራ ከመግባታችን በፊትም ሆነ ስራ ላይ ከተሰማራን በኋላ በስራችን ውጤታማ ለመሆን እራሳችንን አሳምነን መስራት ሌላኛው የውጤታማነት ቁልፍ ነው፡፡ስለዚህ እራሳችንን አሳምነን በስነ-ልቦና ዝግጁ መሆን እና ወደስራ መግባት ያሰፈልጋል፡፡

4, እቅድ ማውጣት-
እቅድ ማውጣት ጊዜን በአግባቡ እንድንጠቀም ያደርገናል፡፡ከዚህ በተጨማሪ በየጊዜው የምንሰራውን ስራ ለመገምገምም እድል ይሰጠናል፡፡

5, ጽናት፡-
የምንሰራው ስራ ተሳክቶ ውጤታማ እስክንሆን ድረስ ያለመሰልቸት በፅናት መስራት ያስፈልጋል፡፡
ወርቅ በእሳት ይፈተናል እንደሚባለው ሁሉ በስራችን በርካታ ፈተናዎች እና ውጣ ውረዶች ሊደርሱብን ይችላሉ፡፡ ቢሆንም ግን በፅናት መስራት አለብን፡፡

28/07/2018

Addis Ababa Education Bureau

Photos from Bole Woreda 03 Education office's post 26/03/2026

ትምህርት የሀገር ግንባታ መሰረትና የሁሉም ስኬቶች ቁልፍ ነው ‼

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ትምህርት ፅ/ቤት ዛሬም የተገልጋዩን ክብርና ምቾት የሚጠብቅ ተቋም ለመፍጠር በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ሚና ያለውን የቢሮ ማዘመን ስራ በማከናወን በዛሬው እለት አስመርቋል ።

የወረዳው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሰላማዊት አየለ ሁሌም ትምህርትን ስናስብ በሀገር እና ተቋም ግንባታ ላይ ያለውን ሁለንተናዊ ሚና እውን በማድረግ በኩል የሚጠበቅበትን ላቅ ያለ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል ። ይህንን በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል የቢሮ ምቹነት ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ በቀጣይ ለሚመዘገቡት ስኬቶች ሁሉ አጋዥ ሀይል ይሆናል በማለት ገልፀዋል ።

የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ ፋሲል ግዛው ለተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ ምቹና ሳቢ የሆነ የስራ ቦታን ማዘጋጀት የውጤት ነፀብራቅ መሆኑን ገልፀው አሁንም በትብብር ለተሻለ ስኬት መስራት ይገባል በማለት ገልፀዋል ።

በመጨረሻም በወረዳው የትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ታምራት በቀለ ወደ ክ/ከተማ ባደረጉት እድገት መሰረት ሽኝት ተደርጎላቸዋል ።



Addis Ababa Education Bureau Zelalem Mulatu Demu Tilahun Abbaa Gammachis Tsehay Merga Sintayehu Eshetu Abera Simbirtu Barii

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address

Bole Woreda 03
Addis Ababa