Gullele Woreda 1 Communication- ወ1

Gullele Woreda 1 Communication- ወ1 Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gullele Woreda 1 Communication- ወ1, Government Organization, sheromadaa, Addis Ababa.

04/09/2026
የአከራይ ተከራይ ውል ማጠናቀቂያ ጊዜ ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ ቀረው የአከራይና ተከራይ ግንኙነትን በሕጋዊ ማዕቀፍ የማጠናከር ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል!ጉለሌ ወረዳ 1 ኮሙኒኬሽን 29/12/201...
04/09/2026

የአከራይ ተከራይ ውል ማጠናቀቂያ ጊዜ ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ ቀረው የአከራይና ተከራይ ግንኙነትን በሕጋዊ ማዕቀፍ የማጠናከር ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል!

ጉለሌ ወረዳ 1 ኮሙኒኬሽን 29/12/2018 ዓ.ም

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስተዳደር ድል በትግል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ለአራት ወረዳዎች የሚሰጠው የውል ማዋዋል አገልግሎት ከሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የተቀመጠው የአንድ ወር የጊዜ ገደብ በማለቁ ተጨማሪ 20 ቀናት እንዲራዘም ተደርጎ አሁንም አገልግሎቱ እየተሰጠ ይገኛል ሲሉ የጉለሌ ክፍለ ከተማ የቤቶች አስተዳደር ባለሙያ አስተባባሪ አቶ እዮብ አረጋ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ያነጋገርናቸው ውል ተዋዋይ አቶ ኃይለማሪያም የማነ በበኩላቸው፣ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ቀልጣፋና ፈጣን መሆኑን ገልጸዋል። ሆኖም ግልጋሎት የሚሰጥበት ቦታ በጣም ጠባብ በመሆኑ እና አራቱም ወረዳዎች በአንድ ቦታ እንዲስተናገዱ በመደረጉ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ መጨናነቅ መፈጠሩን ጠቁመዋል።

በወረዳው የሚገኙ አከራዮች እና ተከራዮች ሕጋዊ እና ግልጽነት ያለው ሥርዓት እንዲከተሉ ለማስቻል ሲሰራበት የቆየው የውል ማደስ እና ማጠናቀቂያ የጊዜ ገደብ ልክ ነገ ላይ ደርሷል።

ውሉን ለማደስ እና አዲስ ውል ለመዋዋል የተሰጠው የጊዜ ገደብ ማጠናቀቂያው ዋዜማ ላይ በመገኘቱ፣ እስካሁን ውላቸውን ያላደሱ አካላት የቀረችውን እጅግ አጭር ሰዓት በመጠቀም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

በጉዳዩ ላይ ሐሳባቸውን የሰጡ ተገልጋዮች እና የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ይህ ውነድ ከሁለቱም ወገኖች (ከአከራይም ሆነ ከተከራይ) የሚጠበቁ መብቶችና ግዴታዎች በግልጽ እንዲሰፍሩ በማድረግ ሊፈጠሩ የሚችሉ አለመግባባቶችን በቅድመ-መከላከል መልክ እንደሚፈታ ገልጸዋል።

አስተዳደሩ የሕብረተሰቡን ደህንነት፣ ሰላም እና የሰፈራ ሥርዓት አስተማማኝ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ባለድርሻ አካላት ሁሉ ያላንዳች እንግልት የውል ማጠናቀቂያ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ጥሪውን ያስተላልፋል።

ማሳሰቢያ፡- የቀረችው አንዲት ዕለት ብቻ በመሆኗ ሕጋዊ አሠራርን በመከተል ራሳችሁን ከህጋዊ ተጠያቂነት ይጠብቁ!

ለህብረተሰባችን የሚገባውን የክብር አገልግሎት እንሰጣለን!”ጉለሌ ወረዳ 1 ኮሙኒኬሽን 29/12/2018 ዓ.ምየወረዳችን ነዋሪዎች በተሰጠው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ያላቸውን እርካታ ገለጹ! ...
04/09/2026

ለህብረተሰባችን የሚገባውን የክብር አገልግሎት እንሰጣለን!”

ጉለሌ ወረዳ 1 ኮሙኒኬሽን 29/12/2018 ዓ.ም

የወረዳችን ነዋሪዎች በተሰጠው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ያላቸውን እርካታ ገለጹ! 🌟

መንግስት ለህብረተሰቡ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ዘመናዊ፣ ግልጽና ህዝብ ተኮር ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም መሰረት በወረዳው ለተገልጋዮች የላቀ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

በዛሬው ዕለት በአገልግሎት ለማግኘት ከመጡት ተገልጋዮቻችን መካከል የተወሰኑ አስተያየቶች ሰጪዎች “ቀደም ሲል አገልግሎት ለማግኘት ረጅም ሰዓታት እንመላለስ ነበር፤ አሁን ግን በባለሙያዎች አቀባበል፣ በሰዓት አከባበር እና ያለ ምንም ውጣ ውረድ በፈጣን ሁኔታ አገልግሎት ማግኘት ችለናል።

ተገልጋዮች አክለው “ሰራተኞቹ በፈገግታና በትዕግስት እያስተናገዱን ይገኛሉ፤ የቢሮ አሰራሩም ግልጽ መሆኑ አድናቆትን ይሰጣል። ይህ መልካም ጅምር ተጠናክሮ እንዲቀጥል እናበረታታለን።”

የህዝባችንን እርካታ ማረጋገጥ የዕለት ተዕለት ተግባራችንና ዋነኛ ተልእኳችን ነው። ከህብረተሰቡ የሚሰጡን ገንቢ አስተያየቶችና አበረታች ቃላት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ትልቅ ጉልበት ይሆኑናል።

✨ ህዝባችንን ማገልገል ታላቅ ክብር ነው! ✨

" መሰረታዊ የግብር እና ኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን እናረጋጋለን !! "በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መጪው የ2019 የአዲስ ዓመት  በዓል ምክንያ...
03/09/2026

" መሰረታዊ የግብር እና ኢንዱስትሪ ፍጆታ ምርቶችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ገበያን እናረጋጋለን !! "

በጉለሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር መጪው የ2019 የአዲስ ዓመት በዓል ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ምርቶች የሚያቀርቡ አንቀሳቃሾችና ኢንተርፕራይዞች ምርታቸውን የሚያስተዋውቁበት ባዛርና ኤግዚቢሽን ተከፈተ።

በክፍለ ከተማው ንግድ ጽ/ቤት ፣ ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ፣ ኢንዱስትሪ ጽ/ቤት ፣ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ፣ ህብረት ስራ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን መጪው የ2019 አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የባዛር መክፈቻ ስነ-ስርዓት ተካሄደ።

በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ ፣ የክፍለ ከተማ አመራሮች ፣ አምራቾችና ሸማቾች በተገኙበት ተከፍቷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደተናገሩት ኤግዚብሽንና ባዛሮች የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አኳያ የላቀ ሚና እንደሚጫወቱ ገልጸው አምራቾችን በማበረታታት ህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት እንዳለበት ገልጸው በኤግዚቢሽንና ባዛሩ አምራቹና ሸማቹን የሚያገናኝ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር በቀል ምርቶችን የሚያገኙበት ስለሆነ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች የአዲስ ዓመት የበዓል ዝግጀት የሚሆኑ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ በሚቀርበው ባዛሮች በመሄድ ምርቶቹን እንዲሸምቱ ጠቁመዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚና ስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ታደሰ በበኩላቸው ኤግዚቢሽን እና ባዛሩ የኑሮ ውድነትን በማረጋጋት ኢንተርፕራይዞች በተመጣጣኝ ዋጋ ምርቶቻቸውን ለገበያ በማቅረብ እና በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው በመግለጽ የአዲስ ዓመት ባዛርና ኤግዚቢሽን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን የሚያነቃቃ ፣ ነዋሪዎች በንግድ ባዛርና ኤግዚቢሽን ላይ በመገኘት ጥራት ያላቸውን ምርቶችን በተመጣኝ ዋጋ እንዲሸምት ጥሪ አቅርበዋል።

በኤግዚቢሽን ባዛሩ ላይ ኢንተርፕራይዞችና አንቀሳቃሾች የተሳተፉ ሲሆን በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ፣ በንግድ ኢንተርፕራይዝ ፣ በከተማ ግብርና ፣ በኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዞች ፣ በአገልግሎት ዘርፍ አንቀሳቃሾች የሚሳተፉ ሲሆን በርካታ ነዋሪዎች ሰዎች ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

በክፍለ ከተማው እየተካሄደ በሚገኘው ኤግዚቢሽን እና ባዛር የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን የገበያ ትስስር እንደሚፈጠርላቸው ይጠበቃል።

በኤግዚቢሽንና ባዛሩ መሠረታዊ ፍጆታ ምርቶች ፣ የከተማ ግብርና ውጤቶች ፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፣ የእንጨት ምርቶችና የቤት ዕቃዎች የባህል አልባሳት ፣ ባህላዊ መጠጦች እና የሸክላ ውጤት ምርቶች ቀርበው እየተሸጡ ይገኛል።

የፖሊስ ሴንተሪዎች መስፋፋት የወንጀል ድርጊቶችን ከመግታት እና ፀጥታ ስጋቶችን ከማቃለል አኳያ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ነዋሪዎች ገለፁ ፡፡ጉለሌ ወረዳ1  ኮሙኒኬሽን 28/12/2018 ዓ.ምበ...
03/09/2026

የፖሊስ ሴንተሪዎች መስፋፋት የወንጀል ድርጊቶችን ከመግታት እና ፀጥታ ስጋቶችን ከማቃለል አኳያ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ነዋሪዎች ገለፁ ፡፡

ጉለሌ ወረዳ1 ኮሙኒኬሽን 28/12/2018 ዓ.ም

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 አስተዳዳር በቀጠና 3 ብሎክ 29 አካባቢ ከዚህ ቀደም የነበረውን ከፍተኛ የወንጀል፣ የሌብነት እና የህገ-ወጥ እንቅስቃሴ ስጋት ለመቅረፍ የሚያስችል አዲስ የፖሊስ ሴንተር ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ።

የፖሊስ ሴንተሩ መገንባቱን ተከትሎ በአካባቢው ይፈጸሙ የነበሩ ወንጀሎች በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የፀጥታ አካላት አስታውቀዋል።

የአካባቢው ነዋሪ እና የሰላም ሰራዊት አባል የሆኑት ወ/ሮ ፀሐይ ተሾመ እንደተናገሩት፤ ቀደሞ አካባቢው አቀማመጡ ገደላማ እና ጫካማ በመሆኑ ለወንጀል መደበቂያ፣ ለሱስ ማስኬጃ እንዲሁም ለሌብነት የተጋለጠ ነበር። በተጨማሪም ለሰላም ሰራዊቱ መደበኛ የስብሰባ እና የፊርማ ማስፈረሚያ ቦታ ስላልነበረ ስራዎችን ለማከናወን ከፍተኛ ፈተና ይጋረጥ እንደነበር አብራርተዋል።

የቀጠናው ኦፊሰር ሳጅን ጀማል መሐመድ በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል አካባቢው ላይ በነበሩ የወንጀል ስጋት ቦታዎች ላይ ጥናት በማድረግ እና ህብረተሰቡን በማስተባበር የግንባታ ስራው እንደተጀመረ ገልጸዋል።

ህብረተሰቡ የነበረውን የፋይናንስ፣ የጉልበት እና የቁሳቁስ (ማቴሪያል) አቅም በማስተባበር፣ ከወረዳው እና ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር የፖሊስ ሴንተሩን ገንብቶ ማጠናቀቅ ችሏል።

አቶ ሀሰን ገብረመስቀል የተባሉት የአካባቢው ነዋሪ በሰጡት አስተያየት፤ የፖሊስ ሴንተሩ መገንባት ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር ያለውን ግንኙነት እና አብሮ የመስራት ባህል ያጠናከረ መሆኑን ገልጸዋል። የሴንተሩ መከፈት እና የሰላም ሰራዊቱ መዋቀር ከተከናወነ ወዲህ በነዋሪዎች መኖሪያ ቤት እና በአካባቢው ይፈጸሙ የነበሩ የስርቆት፣ የሞባይል ቅሚያ እና የቤት ሰበራ ወንጀሎች በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንሱ አድርጓል።

የአካባቢው ነዋሪዎች እና የፀጥታ አካላት አክለው እንደገለፁት፤ የተገኘው የሰላም እና የፀጥታ ውጤት ህብረተሰቡ "የፖሊስ ዓይን እና ጆሮ" በመሆን ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት መስራቱ የመጣ ውጤት ነው። በቀጣይም የጀመሩትን ሁለንተናዊ ድጋፍ በማጠናከር ከፀጥታ አካላት ጎን እንደሚቆሙ እና የአካባቢውን ሰላም አብረው እንደሚያስጠብቁ ተናግረዋል።

03/09/2026
በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬ...
03/09/2026

በሀገራችን የመጀመሪያውን የተለየ የቤት መግዣ ብድር መልሶ ማጠናከሪያ ኩባንያ ለማቋቋም የሚያስችለውን ታሪካዊ የትብብር ማዕቀፍ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) መካከል ስምምነት ዛሬ አከናውነናል።

‎በ100 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ካፒታል የተቋቋመው እና በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ አስተዋፅኦ የሚያደርግበት ይህ ተቋም፤ በባንክ ዘርፋችን ውስጥ የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አለመመጣጠንን የሚቀርፍ እና በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ የሚሆን የቤት መግዣ ብድር ፋይናንስን የሚያስገኝ ይሆናል።
‎
‎ይህ አጋርነት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገነቡና የኢትዮጵያውያንን ክብር የጠበቁ 1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለማቅረብ እንዲሁም በፋይናንስ ሥርዓታችን ውስጥ የግል ዘርፉን ተሳትፎ ለማስፋት ያስቀመጥነውን ግብ የሚያሳካ ወሳኝ እርምጃ ነው።
‎ኢትዮጵያ ፈጣን፣ ጠንካራ እና ሁሉንም ያካተተ ኢኮኖሚ መገንባቷን ትቀጥላለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years  ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና...
02/09/2026

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፉ Act For Early Years ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት እድገት ሻምፒዮን” ተብለው እውቅና ተሰጣቸው።

ይህ እውቅና የከንቲባ አዳነች አቤቤ አመራራቸውንና የከተማ አስተዳደሩ ለሕፃናት እድገት እያደረገ ያለውን ኢንቨስትመንት በተለይም በ"የአዲስ አበባ የወደፊት ተስፋ የቅድመ ልጅነት እድገት ተነሳሽነት" የተሰጠ እውቅና ነው።

ኢኒሼቲቩ ቀዳማይ ልጅነትን በመንግሥታት ፖሊሲዎች እና በዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት አጀንዳ ማዕከል ላይ ለማስቀመጥ በትኩረት ይሰራል።

ይህ እውቅና የተሰጠው ከቀድሞው የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም አቀፍ ትምህርት ልዩ መልዕክተኛ ጎርደን ብራውን በኩል የኢኒሼቲቭ አጋሮች በመወከል ሲሆን ፣ UNICEF እና UNESCOን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመተባበር የተሰጠ ነው።

እውቅናው አዲስ አበባን በአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት እድገት የከተማ አመራር ተምሳሌት ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረው ይታመናል።

ተቋሙ በተለያዩ የኮሙኒኬሽን አውታሮች የመረጃ ምህዳሩን በማስፋት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ የተለያዩ አካላት ሀሳባቸውን ገለጹየጉለሌክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት  በአዳ...
02/09/2026

ተቋሙ በተለያዩ የኮሙኒኬሽን አውታሮች የመረጃ ምህዳሩን በማስፋት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ እንደሚገኝ የተለያዩ አካላት ሀሳባቸውን ገለጹ

የጉለሌክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት በአዳዲስ የፈጠራ ስራዎች መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ ለተለያዩ ትልልቅ ሚዲያዎች የመረጃ ምንጭ በመሆንና የአስተዳደሩን የልማትና የፕሮጀክት ስራዎች የተሸጠበት መንገድ በማጠናከር መንግስትና ማህበረሰብን እንደ ድልድይ በመሆን ሚናውን እየተወጣ እንደሚገኝ ወጣት ሪታ ፍቃዱ ሀሳቧን ተናግራለች ።

በሌላ በኩል ከሚዲያ አካላት ጋር ተወዳዳሪ ብቻ ሳይሆን ስራዎቹን በወቅታዊና ተአማኒነት በማከናወን የነዋሪው ድምጽ መሆኑን ከፍ በማድረግ አጠናክሮ መሄድ እንዳለበት አቶ ጸሀዩ ከበደ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

በተጨማሪም በክፍለ ከተማና በወረዳ የሚታዩትን በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች የመረጃ ተደራሽነት ምህዳሩን በማስፋት ትልቅ አቅም መሆኑን አቶ ጎሹ አስተያየት ሰጥተዋል።

እንዲሁም በቴክኖሎጅ የሚሰጡ ስራዎችን በተጠናከረ መልኩ በማስቀጠል የአስተዳደር ስራዎችን የመሸጥ፣ግንዛቤ የመፍጠርና ክፍተትን የመሙላት ሚናውን እንደተወጣም ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

Address

Sheromadaa
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gullele Woreda 1 Communication- ወ1 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share