13/03/2026
Bethelem Jebel
Wish all the best for all of my followers
13/03/2026
13/03/2026
ኢራን ግጭቱን ለማቆም ሦስት ቅድመ ሁኔታዎችን አቀረበች‼
የኢራኑ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዘሽኪያን በመካከለኛው ምስራቅ እየተካሄደ ያለውን ወታደራዊ ግጭት ለማቆም ሦስት ዋና ዋና ቅድመ ሁኔታዎችን ይፋ አደረጉ።
ፕሬዝዳንቱ ከሩሲያ እና ፓኪስታን መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ቀጣይነት ያለው ሰላም ለማስፈን የሚከተሉት ነጥቦች መሟላት እንዳለባቸው አሳስበዋል፦
📌የኢራን ሉዓላዊነት እና ጥቅሞች መከበር፣
📌በግጭቱ ለደረሰው ጉዳት ተገቢው የካሳ ክፍያ መፈጸም፣
📌ወደፊት መሰል ጥቃቶች እንዳይሰነዘሩ ጠንካራ ዓለም አቀፍ ዋስትና መሰጠት።
ፕሬዝዳንቱ ለወቅታዊው ቀውስ እስራኤልንና አሜሪካን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን፣ እነዚህ ሁኔታዎች ሳይሟሉ ሰላም እንደማይወርድ ገልጸዋል።
በሌላ በኩል፣ አሜሪካና እስራኤል ላለፉት ሁለት ሳምንታት በኢራን ላይ ተከታታይ ጥቃት ቢሰነዝሩም፣ የኢራን መንግሥት የመፍረስ ስጋት እንዳልደቀነበት ሮይተርስ የአሜሪካን የምሁራን ግምገማ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ጥቃቱ የኢራንን መንግሥት ለመጣል ያለመ ቢሆንም፣ የአገሪቱ አመራር አሁንም በጠንካራ ቁመና ላይ እንደሚገኝ ተመልክቷል።
13/03/2026
✅ ሰዎች ምን እየተካሄዳ ነው?
👉በጦርነት መሐል የተደረገ ጉዞ‼
✅ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ውጥረት ወደነገሰበት መካከለኛው ምስራቅ አቀኑ‼
✅ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጅቡቲ ጉብኝታቸውን አጠናቅቀው፣ አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር ከባድ የጦርነት ውስጥ ወደገቡበት መካከለኛው ምስራቅ አምርተዋል።
✅ይህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግጭቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ቀጠናውን የጎበኙ የመጀመሪያው የዓለም መሪ አድርጓቸዋል።
09/03/2026
#ሰበር
አረብ ኢምሬትስ በይፋ ጦርነቱን ተቀላቀለች!
👉 ባለፉት ቀናት በኢራን ከፍተኛ የሚሳኤል እና ድሮን ጥቃት ሰለባ የነበረችው ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ ኢራን ላይ ጥቃት ፈጽማለች። ይህ የUAE ጥቃት ጦርነቱ ከተጀመረ የመጀመሪያው ጥቃት ተብሎ ተመዝግቧለ። የአገሪቱ መከላከያ ቢሮ ኢራን ላይ ጥቃት መፈጸሙን ይፋ አድርጓል። ይህም ጦርነቱ አድማሱን እያሰፋ ተጨማሪ ኃይላትን እየጋበዘ ለመሆኑ ማረጋገጫ ሆኗል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Website
Address
Addis Ababa
001

10/03/2026
10/03/2026