09/03/2026
አምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል የወተት ላሞች ለአርሶ አደር አስተላለፈ
*****************************
አምቦ ግ.ም.ማ፤ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም.
በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል አርሶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በውተት ምርታቸው ከፍተኛ የሆኑ የወተት ከብቶችን ለአርሶአደሩ የማስተላለፍ መርሐ ግብር የምርምር የስራ ሃለፊዎች፤ የአምቦ እና ደንዲ ወረዳ የመንግስት ስራ ሃለፊዎች፤ እና የአካባቢ ሽማግሌዎች በተገኙበት በአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል ጊንጪ ንዑስ ማዕከል አካሄደ፡፡
ዶክተር ጀማል ቶላ የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ማዕከሉ ለምርምር ተግባር ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ በእጽዋት ጥበቃ ምርምር እና በሌሎች በርካታ የምርምር ዘርፎች ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን የልህቀት ማእከልነት ደረጃ የደረሰ ሲሆን በእንሰሳት ምርምርም አመርቂ ስራ በማከናወን የሚታወቅ እና በአከባቢውም ዝናን ያተረፈ ነው ብለዋል፡፡ ዶክተር ጀማል አክለውም በዛሬው እለት የተገናኘነውም በእንሰሳት ምርምር ዘርፍ ያገኘነውን ስኬት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በወተት ምርታቸው ከፍተኛ ደረጃ ያለቸውን እንዲሁም የደም ደረጃቸው ከ50-87% የሚደርሰው 13 የተሻሻሉ የወተት ላሞችን ለ13 አርሶ አደሮች ለማስተላለፍ በመሆኑ ምርምሩ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያለውን ከፍተኛ ፋይዳ በተግባር የሚያሳይ ነው በማለት ተናግረዋል፡፡
ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ኢንስቲትዩታችን ካሉት 23 የምርምር ማዕከላት አምቦ የግብርና ምርምር ማእከል አንዱ እንደዚሁም የመንግስትን የግብርና ልማት ለማረጋገጥ ተግተው ከሚሰሩት መካከል ሲሆን በተለይ በዛሬው እለት በወተት ምርታቸው ከፍተኛ የሆኑ ላሞችን ለአርሶ አደሩ ለማስተላለፍ ሲሰራ ቆይቶ ለዚህ ስኬት መብቃቱን በተግባር ሊያሳይ መሆኑ እጅግ የሚበረታታ እና የሚያስመሰግን ስራ ስለመሆኑ እንዱ ማሳያ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዶክተር ተስፋዬ አበራ በአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል የጊንጪ ንዑስ ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር በበኩላቸው እንደ እንሰሳት ተመራማሪነቴ ዛሬ ከብዙ ድካም በኋላ በሁሉም ያላሰለሰ ትብብር እነሆ ምርታማነታቸው የተረጋገጠ የወተት ላሞች ለአርሶአደሩ ለማስተላለፍ መብቃታችን የኢንስቲትውታችን እናም ዘርፉ ስኬት ነው ሲሉ ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የጋራ ውይይት በተደረገበት ወቅት አርሶአደሮች የአምቦ ግብርና ምርምር ማዕከል ለስራችን ውጤታማነት እና ለኖሮአችን መሻሻል በሁሉም የምርምር ዘርፍ ክፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ነው በማለት ምስጋናቸውንና አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
ላሞቹን እዚህ ደረጃ ለማድረስ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዋል።
Ambo Agricultural Research Center Transfers Dairy Cows to Farmers
*****************************
Ambo ARC, March 07, 2026 G.C.
The Ambo Agricultural Research Center, under the Ethiopian Institute of Agricultural Research, conducted a program to transfer high-yielding dairy cattle to farmers, aimed at benefiting the farming community. The event took place at the Center's Ginchii Sub-Center, attended by research center officials, government executive officials from Ambo and Dandi districts, and local elders.
In his welcome address, Dr. Jemal Tola Horo, Director of the Ambo Agricultural Research Center, stated that since its establishment, the Center has achieved successful outcomes, particularly in plant protection research and various other fields, attaining the status of a center of excellence. He noted that it is also renowned in the region for its commendable work in animal research. Dr. Jemal added that today's event marks the transfer of 13 improved dairy cows, with a blood level ranging from 50-87%, to 13 farmers. This demonstrates the practical significance of ensuring farmers benefit from the success achieved in the animal research sector.
In his opening speech, Professor Nigussie Dechassa, Director General of the Ethiopian Institute of Agricultural Research (EIAR), stated that among the Institute's 23 research centers, Ambo ARC is one that diligently works to ensure the government's agricultural development goals. He emphasized that the Center's success, after sustained effort, in transferring these high-yielding dairy cows to farmers is a highly commendable achievement, practically demonstrating the realization of its research objectives.
Dr. Tesfaye Abera, Director of the Ginchii Sub-Center at Ambo Agricultural Research Center, for his part, expressed that as an animal researcher, being able to finally transfer these productive dairy cows to farmers after much hard work and unwavering collaboration from all sides is a testament to the success of the Institute and the sector.
Finally, during a joint discussion session held at the end, the beneficiary farmers expressed their gratitude and admiration, stating that the Ambo Agricultural Research Center has made a significant contribution to the effectiveness of their work and the improvement of their livelihoods across all research sectors.
More than 2 million Birr was invested to raise the cows to this standard.