Konta Zone Labor and Skills Development Department

Konta Zone Labor and Skills Development Department ክህሎትን በማሳደግ፣ የሥራ ዕድልን በመፍጠርና የሥራ ባህልን በመገንባት የኮንታ ዞን ብልጽግና እናረጋግጣለን።

ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች ምን ምን ናቸው? አዋጁ ምን ይላል? ክፍል ስድስት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዜጎች በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማረ...
18/02/2026

ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ብቁ የሚያደርጉ መስፈርቶች ምን ምን ናቸው?

አዋጁ ምን ይላል?

ክፍል ስድስት

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዜጎች በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥና መብታቸውን ለማስከበር ስልጠናንና የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓትን ዋነኛ መሣሪያው አድርጓል።

በዚህ ክፍል ላይ በአዲሱ አዋጅ የተቀመጡት አራት መሠረታዊ የብቃት መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦

📍የትምህርትና የቋንቋ ዝግጁነት

✅ማንኛውም በውጭ ሀገር ለሥራ የሚሰማራ ዜጋ፣ የሚሰማራበት የሥራ መስክ የሚጠይቀውን መሠረታዊ እውቀትና ክህሎት መያዝ ይኖርበታል።

✅ከዚህ ባለፈም የሠራተኛውን መብት ለማስከበር የመጀመሪያው እርምጃ የሥራ ውልን መረዳት በመሆኑ፤ ሠራተኛው ቢያንስ በሚረዳው ቋንቋ የሚዘጋጀውን ውል አንብቦ የመረዳት አቅም ሊኖረው እንደሚገባ አዋጁ በግልጽ ይደነግጋል።

📍የሙያ ብቃት

✅በውጭ ሀገር የሚሰማራ ማንኛውም ሠራተኛ በትምህርት፣ በሥልጠና ወይም በተግባር ያገኘውን እውቀትና ክህሎት አግባብነት ካለው የትምህርት ተቋም ወይም የምዘና ማዕከል በተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ማረጋገጥ ይኖርበታል።

📍ተመላሾች

✅በአዲሱ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አዋጅ በውጭ ሀገር ሲሠሩ ቆይተው ወደ ሀገር የተመለሱ ዜጎች በሰሩበት የሥራ መስክ ድጋሚ መሰማራት ቢፈልጉ፣ የክለሳ ሥልጠና ወስደው አግባብ ባለው የምዘና ማዕከል የተሰጠ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ከያዘ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ ለመሥራት ብቁ ይሆናል፡፡

✅ነገር ግን ከዚህ ቀደም ከሚሰሩበት የሥራ መስክ መቀየር ከፈለጉ እንደ አዲስ ሥልጠና ወስደው ብቃታቸውን በምዘና ማረጋገጥ እንዳለባቸው አዋጁ ያስገድዳል።

📍የጤና ምርመራ

✅የጤና ምርመራ የሚከናወነው በጤና ሚኒስቴር እና እንደ አስፈላጊነቱ በመዳረሻ ሀገራት በጋራ በሚመርጡና ጥራታቸው በተረጋገጠ የጤና ተቋማት ብቻ ይሆናል።

✅የጤና ምርመራው የሚከናወነውም ሠራተኛው አሠሪው የሚጠይቃቸውን ሌሎች የብቃት መስፈርቶች ማሟላቱ ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ አዋጁ ይደነግጋል።

📍ሕጋዊ የጉዞ ሰነዶች

✅ማንኛውም ስምሪት በሕጋዊ መንገድ እንዲከናወን አስፈላጊው የጉዞ ሰነዶች ማጣራት ሂደት በሚኒስቴሩ በኩል ይከናወናል።

✅ለውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ጉዞ የሚያስፈልጉ ሰነዶች እንደ ጉዳዩ አግባብነት በኤጀንሲው ወይም በሠራተኛው አማካኝነት ለሚኒስቴሩ ይቀርባሉ።

✅ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዜጎች ደህንነቱ የተጠበቀ ጉዞ እንዲያደርጉ ለማስቻል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ይሠራል።

በኤላ ሀንቻኖ ወረዳ የወጣቶች እርሻ ማዕከል የእርሻ ስራ በይፋ ተጀመረበኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ የወጣቶች እርሻ ማዕከል የእርሻ ስራ በወምባ የማላ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል።በቦታው ተገኝተው...
27/01/2026

በኤላ ሀንቻኖ ወረዳ የወጣቶች እርሻ ማዕከል የእርሻ ስራ በይፋ ተጀመረ

በኮንታ ዞን ኤላ ሀንቻኖ ወረዳ የወጣቶች እርሻ ማዕከል የእርሻ ስራ በወምባ የማላ ቀበሌ በይፋ ተጀምሯል።

በቦታው ተገኝተው የእርሻ ስራውን ያስጀመሩት የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማላ ማዴሶ እንዳሉት እንደ ወረዳ ስራ ፈላጊ ወጣቶችን የስራ ባለቤት ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ እንዳለ በማንሳት የዚህ ቀበሌ የወጣቶች እርሻ ማዕከል ጅማሮ አንዱ ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።

ከዚህ መነሻ ወጣቶች በተሰማሩበት የስራ መስክ ሁሉ ወጥ የሆነ አቋም በመያዝ ለሌሎች አካባቢዎች ተሞክሮ ሊሆኑ የሚችሉ ውጤታማ ስራዎችን ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ይህ ካልሆነና ከጊዜ ጊዜ በስራ ሂደት ለውጥ የማይታይ ከሆነ ከግለሰቦች አልፎ መንግስትንም ጭምር ኪሳራ ውስጥ የሚጥል መሆኑን አቶ ማላ አስረድተዋል።

የወረዳው ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አስናቀ አሰፋ በበኩላቸው ወጣቶችን በእርሻ ሥራ ለማሰማራት በአንድ ማዕከል ብቻ 57 ሄ/ር መሬት በኢ/ዝ ስም ተለይቶና ካርታ ተሰርቶ ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰዋል።

ይህ የተለየው መሬት ከእርሻ ስራ ባሻገር ለድለባም ሆነ ለማሞከት ምቹ መሆኑን አንስተዋል።

ከዚህም 30 ሄ/ር ለእርሻ ሥራ የተላለፈ መሆኑን ያነሱት አቶ አስናቀ በዚህም በ3 ኢ/ዝ 16 ወጣቶች የስራ ስምሪት ማገኘታቸውን ተናግረዋል።

ለእርሻ ከተለየው 30 ሄ/ር ውስጥም 10 ሄ/ሩ ተመንጥሮ በሜካናይዜሽን እርሻ መጀመሩን ጠቁመዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ወጣቶች ውሎ አድሮ ጭምር ሰርተው የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን አንዳንድ ምቹ ሁነታዎች መፈጠሩን አስታውሰው የመኖሪያ ቤት ፣የእህል መጋዝንና የመፀዳጃ ቤት ለአብነት ተጠቃሾች ናቸው ብለዋል።

በቀጣይ ጊዜም በማሞከትና በማደለብ ዘርፍም ለወጣቶች የሰራ ስምሪት ለመስጠት አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንዳለ አሳውቀዋል።

በእርሻ ስራ ከተሰማሩ ወጣቶች ውስጥም ወጣት በቀለ እና ወጣት አለማየሁ እንደ ቀበሌያችን ውጤታማ ስራ ሰርተን ለሌሎች ወጣቶች አረአያ ለመሆን ብርቱ ትግል እናደርጋለን ሲሉ ሀሳብ ሰጥተዋል።

ዘገባው፦ የኤላ ሀንቻኖ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

በጪዳ ከተማ የሥራና ክህሎት ዘርፍ አፈጻጸም ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ። ኮንታ|| (ጥር 17/2018 ዓ.ም) በጪዳ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ተግባራት ያለቡበትን ደረጃ ለመገምገም...
26/01/2026

በጪዳ ከተማ የሥራና ክህሎት ዘርፍ አፈጻጸም ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

ኮንታ|| (ጥር 17/2018 ዓ.ም) በጪዳ ከተማ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ተግባራት ያለቡበትን ደረጃ ለመገምገም የሚያስችል ውይይት የከተማው ከንቲባ በተገኙበት ተካሂዷል።

በመድረኩ የዘርፉ ጥንካሬዎችና ድክመቶች በዝርዝር የተለዩ ሲሆን፣ ተቋማዊ አሠራርን ለማሳለጥ የሚያስችሉ ጠንከር ያሉ የሥራ መመሪያዎች ተቀምጠዋል።

በውይይት ወቅት በዩኒት ስር ያሉ ባለሙያዎች የሥራ ድርሻቸውን ለቅሞ የመፈጸም ጉድለት የታየባቸው መሆኑ ተገልጾ፣ ችግሩ በአፋጣኝ እንዲታረም ጥብቅ አቅጣጫም ተቀምጧል።

በተጨማሪም በሥራ ስምሪት አሰጣጥ ላይ ይታይ የነበረው መንቀራፈፍ ተወግዶ፣ በአዲስ አደረጃጀትና ፍጥነት ወደ ተግባር እንዲገባ የዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ባሻ በላይነህ አሳስበዋል።

የዕዳ አመላለስ ሥራን በተመለከተ የከፋይ መረጃዎች በግልጽ ተለይተው እንዲያዙ የተወሰነ ሲሆን፣ ከዕዳ የተሰበሰበ ገንዘብ በኦሞ ባንክ ሳይቀመጥ በፍጥነት ስርጭት እንዲደረግ ተጠቁመዋል ።

ከዲጂታል መረጃ አያያዝ ጋር ተያይዞም በሚፈለገው ፍጥነት መንቀሳቀስ ያልተቻለው የባዮሜትሪክስ ምዝገባ አፈጻጸም ወደ ሙሉ ተግባር መግባት እንደሚጠበቅ ተመላክቷል።

የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማፋጠን የተጀመሩ ፕሮጀክቶች አፈጻጸምም በመድረኩ በዝርዝር ቀርቦ ተገምግመዋል።

በመጨረሻም የከተማው ከንቲባ ለተቋሙ ባህሪና አሠራር ልዩ ትኩረት በመስጠት ግምገማውን በብስለት በመምራታቸው ተገቢው ምስጋና አቅርቧል ስል የዘገበው የኮንታ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ነው ።

‎ከተረጂነት ወደ አምራችነት በሚል ዕሳቤ በኢን/ዝ የተደራጁ ሴቶች ስራቸውን ጀምረዋል።‎‎በጪዳ ከተማ አስተዳደር ከተረጂነት ወደ አምራችነት በሚል ዕሳቤ ደረቅ እንጀራ አቅራቢ ማህበር የተደራጁ...
14/01/2026

‎ከተረጂነት ወደ አምራችነት በሚል ዕሳቤ በኢን/ዝ የተደራጁ ሴቶች ስራቸውን ጀምረዋል።
‎
‎በጪዳ ከተማ አስተዳደር ከተረጂነት ወደ አምራችነት በሚል ዕሳቤ ደረቅ እንጀራ አቅራቢ ማህበር የተደራጁ በቁጥር ሰባት ሴቶች በዛሬው ዕለት ስራ ጀምረዋል።
‎
‎የብልጽግና ፓርቲ ግቦች መካከል አንዱ የሆነው ተረጂነትን ዜሮ የማድረግ ግብ በከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ተሰጥቶበት እየተሰራ ያለ ሲሆን እነዚህ አባላት ወደ ምርታማነት እንዲቀየሩና የሰውን ዕጅ ጠባቂ ከመሆን ራሳቸውን እንዲችሉ የከተማ አስተዳደሩ መንግስት መነሻ ካፒታል ስስት መቶ ሺህ (300,000)ብር ድጋፍ እንዳደረገላቸው ተገልጿል።
‎
‎በዚህም ወደ አምራችነትና ወደ ምርታማነት ለመሸጋገርና የስራ ባህልን ለማሻሻል የታለመ እንደሆነ ነው የተገለጸው።
‎
‎መንግስት ለነዚህ ማህበራት ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ የገበያ ትስስርም የፈጠረላቸው ሲሆን መንግስት በፈጠረውና ባመቻቸው ስራ ዕድል ደስተኞች መሆናቸውን በመግለፅ ለውጤታማነት እንሰራለን ሲሉም ገልጸዋል።
‎ዘገባው፦ የጪዳ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።
‎

በካፋ ዞን በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ የተሰሩ ስራዎች ሀገራዊ የብልጽግናን ጉዞ የሚያፋጥኑ መሆናቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች በካፋ ዞን ...
14/01/2026

በካፋ ዞን በወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ የተሰሩ ስራዎች ሀገራዊ የብልጽግናን ጉዞ የሚያፋጥኑ መሆናቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ።

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ባለሙያዎች በካፋ ዞን የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

ጉብኝቱ የተደረገው የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎች እና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የስራ እንቅስቃሴ መሆኑ ተገልጿል።

አመራሮቹ ጊምቦ ወረዳና ቦንጋ ከተማ አስተዳደር ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ወጣቶችን ተጠቃሚ ልያደርጉ የሚችሉ ተግባራትንና ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስራ እንቅስቃሴን ተመልክተዋል።

በዚህ ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ ፤ በዞኑ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ሀገራዊ የብልጽግናን ጉዞ ልያፋጥኑ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዞኑ ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እየተቻለ መሆኑን ማየት ችለናል ብለዋል።

የሌማት ትሩፋት እንሼቲቮችን ልያረጋግጡ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስቴር ደኤታው ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አብይ አንዴሞ (ዶ/ር) በበኩላቸው በዞኑ ለወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ የተሰጠው ትኩረት አበረታች ነው ብለዋል።

ወጣቶችን የቴክኒክና ሙያ ተቋማት አጫጭር ስልጠና ተጠቃሚ በማድረግ ስራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

ጉብኝቱ በዞኑ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ድጋፍና ልምድ የተገኘበት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የካፋ ዞን ስራና ክህሎት መመሪያ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ኃይሌ ናቸው።

በቀጣይ ከጎብኚዎች የተገኙ ልምዶችንና አዳዲስ ሀሳቦችን ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል ሲል ደሬቴድ ቦንጋ ቅርንጫፍ ዘግቧል።

በዞኑ ሰፊው ወጣቶችን የሚያቅፍ የገጠር የወጣቶች ሥራ  ዕድል ፈጠራ  ትኩረት  ተሰጥተው  እየተሰራ  እንደሚገኝ ተገለጸ።በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ኮንታ ዞን በተያዘው በጀት ዓ...
05/01/2026

በዞኑ ሰፊው ወጣቶችን የሚያቅፍ የገጠር የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ተሰጥተው እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለጸ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ ኮንታ ዞን በተያዘው በጀት ዓመት ሰፊ ወጣቶችን የሚያቅፍ የገጠር፣ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ ገለጸዋል።

በዞኑ፣ አመያ ዙሪያ ወረዳ፣ በጊምባ አጋሬ ቀበሌ በቡና ልማት ኢንዱስትሪ የተሰማሩ ወጣቶች በበኩላቸው በዘርፉ ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በዞኑ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራን በመሠረታዊነት በመደገፍ ዘርፉን ለማሻገር ትኩረት መሰጠቱን የገለጹት አስተዳዳሪው፥ በዚህም በዞኑ ያለውን እምቅ የግብርና አቅም በተሟላ መልኩ ጥቅም ላይ ለማዋልና በሂዴቱም ለዜጎች ሥራ ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ በዞኑ ሶስት መዋቅሮች በቁጥር ስምንት እያንዳንዳቸው 200 ወጣቶችን የሚያቅፉ የእርሻ ማዕከላት የማደራጀት ሥራ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ በማንሳት፣

የመሬት ዝግጅት፣ ቀላልና አነስተኛ የማምረቻ ማሽነሪዎች ግዢ የማሳለጥ ተግባር እየተከናወነ ነው ያሉት አቶ ተስፉ፥ ለተግባሩ የዞኑ መንግሥት ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መድቦ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል።

የቡና ልማት ኢንዱስትሪ ሰብሳቢ ወጣት አንድነት ታደለ እንደገለፀው ማኅበሩ 10 አባላትን በመያዝ በአነስተኛ ካፒታል የተቋቋመስሆን አሁን ላይ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ቋሚ ሀብት ማፍራት መቻሉን ገልጸዋል።

በዘንድሮው የምርት ዘመን 200 ኩንታል ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ሰፊ የዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን የገለጸው ወጣት አንድነት በሂዴቱም ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል።

የመንግሥት ድጋፍና ክትትል ለተሻለ ውጤት እንዳደረሳቸው የገለጸው ሌላኛው የማኅበሩ አባል፥ አለማየሁ አሰፋ አሁን ላይ በቡና ልማት ሥራ ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የቀበሌው የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀበሻው ዶላንጎ በበኩላቸው፥ ወጣቶቹ የሥራ ባህልን በማሻሻልና ውጤታማ በመኾን ለሌሎች ምሳሌ መሆናቸውን ገልጸዋል።

03/01/2026

Address

Ameya

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Konta Zone Labor and Skills Development Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share