Arbaminch city youth and sport office

Arbaminch city youth and sport office

Share

ጤና ይስጥልን! ይህ የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች ጉዳይና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽ/ቤት ይፋዊ የትስስር ገጽ ነዉ

Photos from Arbaminch city youth and sport office's post 17/07/2026

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ343 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥሉ ይገባል። አቶ አይሶፄ ሂሎታ

የአርባምንጭ ከተማ የክረምት በጎ አብይ ኮሚቴ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርትን ገመገመ፡፡

አብይ ኮሚቴው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ ከሚመለከታቸው የሴክተር ኃላፊዎች ጋር በመሆን ታቅደው የተከናወኑ ተግባራትን መነሻ በማድረግ አፈጻጸሙን ገምግመዋል፡፡

‎ የዘንድሮው የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበረሰቡን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ በሚያስችሉ 18 ዘርፎች ተግባራዊ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ የአርባምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ እና የአቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አይሶፄ ሂሎታ እንደገለጹት የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዕቅድ በማቀድ አፈጻጸሙን እየገመገሙ መምራትና ተግባሩን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዘንድሮው የክረምት መርሃ ግብሩ 62 ሺህ ወጣቶችን በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ላይ በንቃት በማሳተፍ 343 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክሮ ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

‎በበጎ ተግባር በርካታ አካላትን በማሳተፍ የእነዚህን አቅማቸውን በማቀናጀት በማህበረሰቡ ውስጥ ያለውን ችግር ለመፍታት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

አቶ አይሶጼ አክለውም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራራቸውን ማጠናከር፣ በበጎ ተግባራት የሚሳተፉ አካላትና ማህበራትን ማሳተፍ፣ የክረምት ትምህርት ተግባር ማጠናከር፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት ግንባታ ማድረግ ስራዎችንና ሌሎችን በልዩ ትኩረትና ቅንነት መፈጸም ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና የክረምት በጎ ፈቃድ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሀብታሙ አበራ እንደተናገሩት የ2018 በጀት ዓመት የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን በቅንጅት በመስራት የታለመለትን ግብ ለማሳካት ሁሉም የኮሚቴ አባላት ከዕቅድ እስከ ትግበራ ድረስ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይጠበቃል ብለዋል።

በ2017 ዓ/ም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ የተሻለ ውጤት ማስመዝገቡ የተገለጸ ሲሆን በ2018 ዓ/ም ከተጀመረ በ15 ቀናት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራት የደም ልገሳ፣ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ፣ትምህርትና ስልጠና፣የችግኝ ተከላ መርሃግብር እና ሌሎች መካሄዱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል

በመድረኩ በክረምት በጎ እየተከናወኑ ያሉ የተግባር አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ‎አፈጻጸሙን መነሻ በማድረግ ግምገማ ተደርጓል፡፡

በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ ኮሚቴው በከተማው የሚገኙ ወጣቶች፣ ባለሀብቶችና አጠቃላይ ማህበረሰቡ በበጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ በንቃትና በባለቤትነት ስሜት እንዲሳተፉ በማድረግ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገልጿል።

ኮሚቴው በተለያዩ ስራ ዘርፎች የተከናወኑ የእስካሁኑ ተግባራትን በጥልቀት ከገመገሙ በኃላ ቀጣይ ተግባራትን ስኬታማ ማድረግ የሚያስችል አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በአሰፋ ጪሻ

Photos from Arbaminch city youth and sport office's post 17/07/2026

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርኃ-ግብር ማህበራዊ አንድነትን የሚያጠናክር ነው ። ወ/ሮ ሊዲያ ከንቲባ

የወጣቶች ክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃግብር ተጀምሯል።

በአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር አባያ ክፍለ ከተማ የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የችግኝ ተከላ መርሃግብር ተካሄዷል።

‎ የደን መጨፍጨፍን ለመዋጋት፣ የተራቆቱ የመሬት ገጽታዎችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ፣ የብዝሀ ሕይወት ሀብትን ለማሻሻል እና ህብረተሰቡን በማስተባበር ዛፎችን በመትከል እና በመንከባከብ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም የአረንጓዴው አሻራ ኢኒሼቲቭ የላቀ አስተዋጾ አለው።

የከተማው ምክትል ከንቲባና ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ከንቲባ በመርኃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በጋራ የሚሳተፉበት መድረክ በመሆኑ ማህበራዊ አንድነትንና መተጋገዝን የሚያጠናክር መሆኑን ገልፀዋል።

እያንዳንዱ ዜጋ ራሱ የተከለውን ችግኝ በመንከባከብ ለአካባቢ ጥበቃ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ምክትል ከንቲባዋ አሳስበዋል።

በአርባምንጭ ከተማ የአባያ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሰፋ ኦዞ ከተሞቻችንንና መንደሮቻችንን አረንጓዴ በማድረግ ለነዋሪዎች ምቹና ሳቢ የአየር ሁኔታ መፍጠር እንዳለብን ተናግረው ።

‎በክረምት በጎ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ፣ የአረጋዊያን ቤት ጥገናና የደም ልገሳን ጨምሮ የተለያዩ ተግባራት የሚከናወኑ ሲሆን በክፍለ ከተማው የመርሃግብሩ ማስጀመሪያ የችግኝ ተከላ መካሄዱን ገልፀዋል።

‎በመርሃግብሩ የከተማው ምክትል ከንቲባና ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ከንቲባን ጨምሮ ከተማ ደጋፊ አመራር ፣ ክፍለ ከተማና ቀበሌውን አመራሮች ፣ የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተገኝተው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

Photos from Arbaminch city youth and sport office's post 16/07/2026

በአርባ ምንጭ ከተማ በክረምት በጎ ተግባር ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ከ150 በላይ ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱ ተገለፀ

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር በክረምት ወራት እየተከናወኑ የሚገኙ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች ያሉበትን ደረጃና የእስካሁን የአፈጻጸም ሂደት የቴክኒክ ኮሚቴው ገምግሟል።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአርባ ምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሀብታሙ አበራ ለክረምት ወቅት ከተለዩ የትኩረት መስኮች አብዛኞቹ በከተማ ደረጃ ወደ ተግባር ገብተው ውጤት መመዝገባቸውን ጠቁመዋል።

በተለይም የተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች በማስተባበር 50 የአቅመ ደካሞችን ቤት ለመገንባትና እድሳት ሥራ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በብሎኬትና በጡብ ለማከናወን ጠንካራ ዝግጅት እንደሚደረግ አውስተዋል።

አቶ ሀብታሙ አያይዘውም የትምህርት፣ የጤና፣ የመንገድ ደህንነት እና የመሠረተ ልማት ጥገና ሥራዎች በትኩረት መሰራት እንዳለባቸው ገልጸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይህንን ዓላማ ለማሳካት እንዲረባረቡ አሳስበዋል።

የአርባ ምንጭ ከተማ የወጣቶችና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ የሱነህ ሳሙኤል በበኩላቸው፤ በአሁኑ ወቅት የችግኝ ተከላ፣ የቤት ግንባታ፣ የደም ልገሳ እንዲሁም የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርትና ስልጠና ተግባራት በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

አክለውም ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ወደ ተግባር ያልተገቡ ጥቂት ዘርፎችን ለማከናወን እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች የተጀመሩትን ተግባራት በተቀናጀና በተሳለጠ መልኩ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት እንደሚተጉ አውስተው የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከወትሮው ይበልጥ እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

Photos from Arbaminch city youth and sport office's post 14/07/2026

ገበታ ለትውልድ አርባምንጭ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስዋፅኦ ላበረከቱ አካላት እውቅና ተሰጣቸው

አርባምንጭ፣ሀምሌ 7/2018 (አርባምንጭ ከተማ መ/ኮሚዩኒኬሽን

ገበታ ለትውልድ ፕሮጀከት እውን እንዲሆን እውቀታቸውን ፣ ጉልበታቸውን ያለስስት በመጠቀም ቀን ከሌሊት በትጋት እና በፅናት በመምራት ፕሮጀክቱ በአጭር ግዜ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱት ለማዕድን ሚንስትር እና ለገበታ ለትውልድ አርባምንጭ አስተባባሪ ኢንጀር ሀብታሙ ተገኝ የጋሞ ህዝብ የክብር እና የጀግንነት መገለጫ የሆነ ስጦታ በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ እና በጋሞ አባቶች ተሰጥቷቸዋል።

በተጨማሪ የገበታ ለትውልድ አርባምንጭ በአጭር ጊዜ ባማረ መልኩ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው መኃንዲሶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመርሃ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የገበታ ለትውልድ አርባምንጭ ዕለት በዕለት በልዩ ትኩረት በመከታተል ለዚህ ላበቁት ለአርባምንጭ ፣ ለጋሞ ዞን ህዝብ ሁሌም መልካምን ለሚመኙት ለጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር ) የከበረ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ኢንጂነር ሀብታሙ በፈተና ጠንክሮ መውጣት ምን እንደሆነ ያሳዩ፣ ፕሮጀክቱን የክልሉን ህዝብ በሚመጥን መልኩ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልፀው ኢንጂነሩ የመንገድ እና የህንፃ ብቻ ሳይሆን ሰውን የሚቀርፁ የሚያንፁ የሰው ማህንዲስ ጭምር ናቸው ብለዋል።

ይህ የሀገር ሀብት የሆነው የገበታ ለትውልድ አርባምንጭ ፕሮጀክት ባማረ ሁኔታ በአጭር ግዜ እንዲጠናቀቅ ጊዜያቸውን፣ አቅማቸውን እውቀታቸውን ሁሉ በመጠቀም በብዙ ፈተናዎች መሀል ፅንቶ በመቆም ለከፈሉት ትልቅ ዋጋ የከበረ ምስጋቸውን አቅርበዋል።

ከርዕሰ መስተዳድሩ በመቀጠል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ ጨምሮ የክልሉ ካቢኔ አባላት፣የጋም ዞን እና የአርባምንጭ ከተማ አስተዳድር ፣ የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ተረፈ፣ ኢንጂነር አንዳልካቸው እና ሌሎች መሃንዲሶች ፕሮጀክቱ በታላቅ ስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋፅኦ በራሳቸው እና በክልሉ መንግስት ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የማዕድን ሚንስትር እንዲሁም የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አስተባባሪ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በበኩላቸው አርባምንጭ ያላት የተፈጥሮ ውበት ከሁሉ አካባቢ ለየት የሚያደርጋት የበርካታ ፀጋዎች ባለቤት፣ ሰላምን የሚወድ ህዝቦች መዲና ለግንባታ፣ ለኢንቨስትመንት ምቹ ከተማ መሆኗን ገልፀው በዚህች ውብ ከተማ ይሄ ትልቅ ፕሮጀክት እውን በመሆኑ ታላቅ ደስታ ተሰምቶኛል ብለዋል።

የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ በለውጡ መሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በልዩ አመራር ጥበብ ተቀናጅተን፣ተባብረን እንዲንሰራ በቅተናል ነው ያሉት።

ገበታ ለትውልድን ጨምሮ በከተማው የሚሰሩ የኮሪደር ልማቶች በጥራትና በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠናቀቁን የተናገሩት ከንቲባው ለፕሮጀክቱ መጠናቀቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምስ አድማሱ የመንግስት ምቹ ፖሊሲና ቁርጠኛ አመራር የተነሳ ጸጋዎችንን ማየትና መግለጥ የጀመርንበት ፣የህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ተጀምረው እየተጠናቀቁ ያሉ ሌሎች ደግሞ የተመረቁበት ቁጥራቸው በርካታ ነው ብለዋል።

ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል ዋነኛ የሆነውና ተጠናቆ ተመርቆ መነጋገሪያ የሆነው የኢትዮጵያን ትኩረት የሳበው የገበታ ትውልድ አካል የሆነው የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ነው ብለዋል።

Photos from Arbaminch city youth and sport office's post 10/07/2026

የክልሉ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቴክኒክ ኮሚቴ የእስካሁን ተግባራት አፈፃፀምን በበይነ መረብ ገምግሟል

ሐምሌ 03/2018 ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቴክኒክ ኮሚቴ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠቃለያና የተግባር ምዕራፍ የእስካሁን አፈፃፀምን በበይነ መረብ ገምግሟል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ 2018 የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ ክልል አቀፍ ንቅናቄ በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ተካሂዶ ወደ ስራ መገባቱ ይታወቃል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና የቴክኒክ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ አቶ ንጋቱ ዳንሳ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሀገር ደረጃ ባህል እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ቃል የ 2018 የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ክልል አቀፍ ማስጀመሪያ በከፍተኛ ድምቀት ተካሂዶ ወደ ስራ መገባቱን አስታዉሰዋል።

ባለፉት ስምንት አመታት በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በተሰራው ስራ በርካታ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ ዉጤታማ ስራዎች መሠራታቸዉን አቶ ንጋቱ ጠቁመዋል።

በክልሉ ሰኔ 22 የተጀመረውን የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እስከ መስከረም/2019 የመጨረሻ ሳምንት ድረስ በከፍተኛ ትኩረት ማከናወን እንደሚገባም አሳስበዋል።

በትምህርት፣ ጤና፣ የቤት ግንባታ፣ ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ አገልግሎትና ሌሎች ተግባራትን የፓርቲ ዲስፕሊን ባከበረና የተቀመጡ አቅጣጫዎችን ባስጠበቀ መልኩ መተግበር ይገባል ብለዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና የቴክኒክ ኮሚቴው ም/ሰብሳቢ አቶ ሳጌ ሻምባ በተያዘው ዓመት በቂ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰዋል።

በሂደቱ የሚስተዋሉ ችግሮችን በተደራጀና በተናበበ መንገድ በመፍታት በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተቀመጡ ዕቅዶችን ጥራትና ተደራሽነት ጠብቆ ማሳካት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ኮሚሽን ኮሚሽነርና የቴክኒክ ኮሚቴዉ ፀሐፊ ማርቆስ ማቴዎስ ክልላዊ የማብሰሪያ መርሃ-ግብሩን ተከትሎ ወደ ተግባር ምዕራፍ መገባቱን አመልክተዋል።

እስካሁን በተሰሩ ስራዎች 255 ዩኒት የደም ልገሳን ጨምሮ በችግኝ ተከላ፣ የቤት ግንባታ፣ የከተማ ዉበትና ፅዳት እንዲሁም በሌሎች 18 የበጎ ፈቃድ ዘርፎች በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ገልፀዋል።

በየዓመቱ በክረምት ወራት የሚከናወነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፤ ወጣቶችንና ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመቅረፍ ላይ እንደሚገኝ በዉይይቱ ተነስቷል።

በመዋቅሮች መካከል የሚስተዋለውን የአፈፃፀም ልዩነት በፍጥነት በማስተካከል በቀጣይ ጊዜያት ተግባሩን ዉጤታማ አድርጎ መምራት እንደሚገባ አፅኖት ተሰጥቷል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ 3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተሳታፊ የሚያደርጉ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተመላክቷል።

በዉይይቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት እና የዞኖችና ሪጂዮ ፖሊሲ ከተሞች የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።

Photos from Arbaminch City Health Department የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ's post 10/07/2026
Photos from Arba Minch Blood and Tissue Bank Service የአርባ ምንጭ ደም እና ሕብረ-ህዋስ ባንክ አገልግሎት's post 09/07/2026
Photos from Arbaminch city youth and sport office's post 09/07/2026

በአርባ ምንጭ ከተማ የክረምት በጎ ተግባራት አፈጻጸም በቴክኒክ ኮሚቴ ተገመገመ

አርባምንጭ፦ ሐምሌ 2/2018 ዓ/ም (አርባምንጭ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን)

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር በክረምት ወራት ለማከናወን ያቀዳቸውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎች ያሉበትን ወቅታዊ ደረጃና የአፈጻጸም ሂደት የቴክኒክ ኮሚቴው በዝርዝር ገምግሟል።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአርባ ምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አበራ ለክረምት ወቅት የተለዩ 18 ዋና ዋና ተግባራትን በከተማ ደረጃ ውጤታማ በሆነ መንገድ ማከናወን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይም የተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች በተቀመጠው ዕቅድ መሠረት የአቅመ ደካሞችን የቤት ግንባታና እድሳት ሥራ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በብሎኬትና በጡብ ማከናወን እንዳለባቸው ገልጸዋል።

አቶ ሀብታሙ አያይዘውም የትምህርት፣ የጤና፣ የመንገድ ደህንነት እና የሰላም ዕሴት ግንባታ ሥራዎች ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ገልጸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ቀድመው አቅደው ወደ ተግባር መግባታቸውን አውስተዋል።

የአርባ ምንጭ ከተማ የወጣቶችና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ የሱነህ ሳሙኤል በበኩላቸው፤ በአሁኑ ወቅት የችግኝ ተከላ፣ የቤት ግንባታ፣ የደም ልገሳ እንዲሁም የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርትና ስልጠና ተግባራት በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አብራርተዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች የተቀመጡትን ዕቅዶች በተቀናጀና በተሳለጠ መልኩ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት እንደሚተጉ አውስተው የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አስታውቀዋል።

08/07/2026

🩸 በዚህ ክረምት የህይወት ስጦታ ይስጡ!
ደም በመለገስ የሰዎችን ህይወት ያድኑ! 🩸
ደም መስጠት የሚያስገኘው ጥቅም እጅግ የላቀ ነው። የደም ልገሳ፦
> በሰውነት ውስጥ አዲስ ደም እንዲፈጠር ይረዳል
>የልብ ህመም ስጋትን ይቀንሳል
>ሌሎች ብዙ የጤና ጥቅሞችን ያስገኛል
ከዚህ በተጨማሪም ደም በመለገስዎ የሌሎችን ህይወት ያድናሉ። አንድ ነጠላ የደም ልገሳ ብቻ እስከ ሶስት ሰዎች ህይወት ማትረፍ ይችላል።ከእንግዲህ አያመንቱ! ወደ ደም ባንክ በመሄድ ደም ይለግሱ። በፈቃደኝነት ደም መለገስ የሰብአዊነትና የጀግንነት ተግባር ነው።

08/07/2026

የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መስፍን መንዛ(ዶ/ር) ዓመታዊ የግብር መክፈያ ወቅትን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት፡-
***

ከፍተኛ የልማት እንቅስቃሴ ላይ የምትገኘው ከተማችን ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ፍትሀዊ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝባችንን የልማት ጥያቄዎች በራስ አቅም በብቃት ለመመለስ፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ብሎም ለክልልና ለሀገር ዘላቂ ልማትና ሁለንተናዊ ብልጽግና ስኬታማ ለማድረግ በገቢ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት አድርጋ እየሰራች ትገኛለች።

የከተማው አስተዳደርም ለከተማችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት መሠረት የሆኑ የልማት እንቅስቃሴ ለማጠናክር፣ የበለፀገ ማህበረሰብ ለመፍጠርና የህዝቡን የልማት ጥያቄዎችን እየመለሰ በሚገኝበት በዚህ ወቅት ታማኝ የሆኑ ግብር ከፋዮቻችን አመታዊ ግብር ክፍያቸውን የሚከፍሉበት ሐምሌ 1 ቀን የግብር ንቅናቄ በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

እንደሚታወቀው ግብርን በወቅቱ በታማኝነት መክፈል የዜግነት ግዴታ ብቻ ሳይሆን ሀገርን የመውደድና የማልማት ብሎም የተሻለ ሀገር በመገንባት ለትውልድ የማሻገር ኃላፊነት የተሞላው አኩሪ የዜግነት ተግባር ነው።

ግብርን በወቅቱ መክፈል አንድም ግብር ከፋዩን ከአላስፈላጊ የወለድና የቅጣት ክፍያ ይታደጋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት በየአከባቢው ለሚሰጣቸው መንግስታዊ አገልግሎቶችና የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ወጪ የሚሆን የፋይናንስ አቅም ይፈጥራል፡፡

በከተማችን የምትገኙ ግብር ከፋዮቻችን የገቢ ግብር አዋጅን ተከትሎ የ2018 ግብር ክፍያን በተሰጠው የመክፈያ ቀናት ውስጥ የግብር ክፍያን በመፈፀም የከተማችን ልማትና እድገት ለማፋጠንና ለነገ የተሻለ ሀገርን በመፍጠር የብልጽግና ተምሳሌት እንድትሆን የድርሻችሁን እንድትወጡ ስል የከበረ ጥርዬን አቅርባለው።

ግብር ከእኔ ለእኔ ከእኛው ለእኛው ነውና ሀገሩን የሚወድ ሁሉ የግብር ግዴታውን መወጣትና የግብር ህጉን ማክበርና በማስከበር ሀገራዊ ኃላፊነታችንን በጋራ እንወጣ!

መስፍን መንዛ (ዶ/ር)
የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ

ሐምሌ 1፣2018 ዓ፣ም
አርባምንጭ || ኢትዮጵያ

Want your business to be the top-listed Government Service in Arba Minch'?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Website

Address

Arbaminch
Arba Minch'
21