13/04/2026
መንገዳችን መደመር፣ ምርጫችን የስንዴ ነዶ፣ መዳረሻችን ሁለንተናዊ ብልጽግና!
የምንከተለው መንገድ፣ የምንመርጠው ምልክት እና የምንመኘው ግብ በአንድነት ተሳስረው የኢትዮጵያን አዲስ ምዕራፍ ይተልማሉ። ይህ ጉዞ የትናንቱን መልካም እሴት ጠብቆ፣ የዛሬውን አቅም አቀናጅቶ ለነገው ትውልድ የምትመች ሀገር የመገንባት ጉዞ ነው።
መደመር እንዲሁ ቁጥርን ማብዛት ሳይሆን ባለን ላይ መጨመር፣ የጎደለውን መሙላት እና የተበተነውን አቅም ማቀናጀት ነው። ያለፉ ስህተቶችን እያረምን፣ መልካም ስራዎችን ደግሞ በማስቀጠል ሀገራዊ አንድነትን እናጠናክራለን። የሁሉንም ኢትዮጵያውያን እውቀት፣ ጉልበትና ሀብት በማቀናጀት የጋራ ቤታችንን እንገነባለን።
የስንዴ ነዶ እንዲሁ ምልክት ብቻ ሳይሆን የሉዓላዊነታችን እና የጥንካሬያችን መገለጫ ነው። በላባችንና በወዛችን ለምለሙን መሬታችንን አልምተን፣ እጃችንን ከልመና አውጥተን የምግብ ሉዓላዊነታችንን እናረጋግጣለን። ነዶው የትጋትና የድካም ውጤት ነው። በአንድነት ተሰባስቦ የታሰረ ነዶ ደግሞ የማይበገር አንድነታችንን ያሳያል። ከቤት ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ የሚተርፍ ምርት በማምረት የኢኮኖሚ ጥንካሬያችንን እናበስራለን።
ብልጽግና ለጥቂቶች ሳይሆን ለሁሉም፤ በአንድ ዘርፍ ሳይሆን በሁሉም ዘርፍ የሚረጋገጥ የነፃነትና የክብር ኑሮ ነው።ዘመናዊ መሠረተ ልማት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የተደላደለ የኢኮኖሚ ሕይወት። ሰላም፣ ፍትህ፣ አብሮነትና የማንነት ኩራት የታከለበት ማህበረሰብ መፍጠር። ዛሬ የምንተክለው የብልጽግና ዘር ለልጆቻችን የምትመችና የተከበረች ኢትዮጵያን ያስረክባል።
11/04/2026
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አይሶጼ ሂሎታ ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
የኃላፊው ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ነው፤
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው/ ፋሲካ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!
መላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው /ፋሲካ/ በዓል በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን! እያልኩ መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ።
የትንሳኤ/ ፋሲካ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶችና ትውፊቶች ታጅቦ በታላቅ ድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ ነው።
ባለፉት ሁለት የፆም ወራት፣ የእምነቱ ተከታዮች የተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነስርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ አሳልፈዋል፤ በፆም፣ በፀሎት፣ በንሰሃ፣ በአጠቃላይ በፈሪሃ እግዚአብሔር መንፈስና በመታዘዝ ታላቅ ኅይማኖታዊ ድባብ ውስጥ ሆነዉ ቆይተዋል።
የፆሙ ማሳረጊያ የሆነዉ የትንሳኤ በዓል የአዲስ ሕይወት ማብሰሪያ፣ የመነቃቃትና የማንሰራራት መንፈስን መጎናጸፊያ ታላቅ በዓል ነዉ። በዓሉ የጨለማውን ድባብ ተሻግሮ ወደ ብርሃንና ብርታት መንፈስ መሸጋገሪያ፣ የአሸናፊነትና የፅናት ምልክት ተደርጎም ይወሰዳል።
ብርታትንና ትጋትን የመጎናፀፍ ኃይል የሚንፀባረቅበትም ነዉ።
ስለሆነም በዓሉን ስናከብር የተስፋ፣ የይቻላልና ጀምሮ የመጨረስን መንፈስ ከፍ በማድረግ በፆሙ ወራት ሲዘወተሩ የቆዩ መልካም እሴቶችና ትውፊቶች ተጠናክረው ይቀጥሉ ዘንድ የበኩላችሁን እንድትወጡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ።
የኃይማኖት ተቋማት፣ የኃይማኖት አባቶች እና ምዕመናን በሀገራችን ዘላቂ ሠላም እዉን እንዲሆን በፀሎትና በምክር የበኩላቸዉን እያበረከቱ ይገኛሉ፤ መልካም ዜጋ በማነጽ ሂደትም የኃይማኖት ተቋማትና የኃይማኖት አባቶች ከፍተኛ ሚና አላቸው።
በመሆኑም ይህንን ጥረት በማጠናከር በሰላሟ የምትታወቀው፣ በአብሮነትና በመቻቻል እሴቶች የዳበረች ከተማችን በሀገር ደረጃ ያላት ተመራጭነትና ልማቷ ከወትሮው በላቀ ከፍ እንዲል የድርሻችሁን ታበረክቱ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት በዓል እንዲሆን ከልብ እመኛለሁ።
መልካም በዓል!
አይሶጼ ሂሎታ
የአርባምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ
ሚያዚያ 3/2018 ዓ.ም
አርባምንጭ||ኢትዮጵያ
11/04/2026
ብልፅግና መምረጥ ለሁለንተናዊ እድገትና ለጋራ ተጠቃሚነት!
በሀገራችን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጉዞ ውስጥ ሴቶች የጀርባ አጥንት፣ ወጣቶች ደግሞ ሞተሮች ናቸው። ብልፅግና ፓርቲን መምረጥ የሴቶች ተሳትፎ የወጣቶች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።
ሴቶችና ከፖለቲካ ስልጣን ባለፈ በየደረጃው በሚገኙ የፖሊሲ አውጪነት ስፍራዎች ላይ እኩል ተሳትፎ እንዲኖራቸውና የሀገሪቱን እጣ ፈንታ እንዲወስኑ የተጀመሮው ጅማሮን ማስቀጠል የኢኮኖሚ ነፃነትና ማህበራዊ ጥበቃን በመገንባት ሴቶች በየትኛውም ቦታ በነፃነትና በክብር እንዲንቀሳቀሱ ማረጋገጥ ነው።
ወጣቱ ትውልድ የሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆን የዛሬው ሰራተኛና መሪ ነው። የዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ ጥራት ያለው የስራ ዕድልና የሰላም ባለቤትነት ማረጋገጥ፤ ወጣቱ የጦርነት መሳሪያ ሳይሆን የሰላምና የልማት አምባሳደር የሚሆንባት በሐሳብ የበላይነት የምታምን ኢትዮጵያን መገንባት ማለት ነው።
ብልፅግናን መምረጥ ማለት ያረጀውን የፖለቲካ ትርክት ሰብሮ፣ ሁሉንም ዜጋ እኩል የሚያይ አዲስ ምዕራፍ መጀመር ችግሮችን በመነጋገር በመወያየት የኢትዮጵያን ከፍታ ማረጋገጥ ነው።
ድምጽዎን ለብልፅግና በመስጠት እኩልነትን ያረጋግጡ የፈጠራ አቅምን ያሳድጉ ለልጆቻችን የምትመች ኢትዮጵያን አብረን እንገንባ።
ብልፅግና ለሁለንተናዊ እድገትና ለጋራ ተጠቃሚነት!
10/04/2026
ብልጽግና ፓርቲ በአንድ ዘርፍ ሳይሆን በሁሉም ዘርፍ የሚረጋገጥ የነፃነትና የክብር ኑሮ ነው። ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የተደላደለ የኢኮኖሚ ሕይወት፣ ሰላም፣ ፍትህ፣ አብሮነትና ማንነት ኩራት የታከለበት ማህበረሰብ የሚፈጥር ነው።
ዛሬ የምንተክለው የብልጽግና ዘር ለልጆቻችን የምትመችና የተከበረች ኢትዮጵያን ያስረክባል።
ብልጽግናን ይምረጡ!
አቶ ፀጋዬ ጌታቸው
የአርባምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ
10/04/2026
አርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ 1 ሺህ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ማዕድ አጋራ
አርባምንጭ፡ሚያዝያ 02/2018 ዓ/ም (አርባምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያ)
የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ በከተማው ከሁሉም ቀበሌ ለተወጣጡ 1 ሺህ ለሚሆኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ለእያንዳንዳቸው 25 ኪሎ ዱቄት 3 ሊትር ዘይት ድጋፍ አድርጓል።
የአርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባ መስፍን መንዛ (ዶ/ር) የከተማዋ ነዋሪዎች የትንሳኤ በዓልን ሲያከብሩ ካላቸው በማካፈል፣ አቅም የሌላቸውን በማገዝ ፣ ፍቅራችንን እየገለጽን የምናሳልፍበት በዓል መሆን አለበት ብለዋል፡፡ ያለንን ተካፍሎ መብላትና አቅመ ደካሞችን ማገዝ ባህላችን ነው ያሉት ከንቲባው በበዓላት ወቅት ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በመተጋገዝ፣ ያለው ለሌው በማካፈል አብሮ ሊያሳልፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከፊታችን የሚከበረው የትንሳኤ በዓልን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙና ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው ወገኖች በደስታ እንዲያሳልፉ የተለያዩ ድርጅቶችና ተቋማት ድጋፍ በማደረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አካላትን በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።
የአርባምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አይሶጼ ሂሎታ ማዕድ ማጋራት መተሳሰብን፣አንድነትንና መደጋገፍን የሚያጠናክር ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል። በከተማው በርካታ አቅመ ደካማና አረጋዊያን እንደሚገኙ ጠቅሰው ህብረተሰቡ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ አካላትን በመረዳት በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ አብነት ተስፋዬ በበኩላቸው፣ ከተማ አስተዳደሩ በየበዓላቱ መሰል ድጋፍ እያደረገ መቆየቱን አመላክተዋል ።
ድጋፍ የተደረገላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ለተደረገላቸው ድጋፍ ከተማ አስተዳደሩን አመስግነው ቋሚ ገቢ አስከሚያገኙ ድረስ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የአርባምንጭ ከተማ ከንቲባ መስፍን መንዛ (ዶ/ር)፣የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አይሶጸ ሂሎታን ጨምሮ አስተባባሪ አካላት፣የከተማው አመራሮች እና ሌሎች ተገኝተዋል።
10/04/2026
የአርባ ምንጭ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አይሶጼ ሂሎታ ለስቅለት እና ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችንና ለመድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት እና የትንሳኤ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ።
የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለትና ትንሣኤ በዓል በየዓመቱ በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በደማቅ ሐይማኖታዊ ስነስርዓት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ ነው።
እየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ህይወቱን የሰጠው ለሰው ልጅ ፍፁም ፍቅር ሲል በመሆኑ እኛም የክርስቶስን አርዓያ በመከተል በሁሉም መስክ በፍቅር፣ በመተሳሰብ መኖር እና መስጠትን የህይወታችን አካል በማድረግ ተደጋግፈን መቆማችንን በተግባር እናሳይ።
እኛም የሰው ልጆች ከክርስቶስ ሕይወት የምንማርበት ነገር ቢኖር ፍቅርን፣ ይቅርታንና ምህረትን፣ ትዕግስትን፣ የጠራ ዓላማና ራዕይ ካለን የሚያጋጥሙንን ጊዜያዊ መከራዎችንና ፈተናዎችን በድል መወጣት የምንችልበት የመንፈስ ጽናትንና ጉልበትን ነው።
የትንሳኤ በዓል ዋዜማ ላይ ህማማቱን እያሰብን ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት የተከፈለውን ዋጋ እያሰብን በዓሉን እንድናከብር እያሳስብኩ በባህላችንና በእምነታችን መሠረት ካለን አካፍለን ከተቸገሩ ወገኖቻችን ጋር ተደጋግፈን በጋራ እንድናሳልፍ አደራ ማለት እወዳለሁ።
እንደወትሮው ሁሉ ሠላማችንን ነቅተን በመጠበቅና አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙም ለፀጥታ ኃይሎች ፈጥነን በማሳወቅ ለአከባቢያችን ብሎም ለክልላችን ሰላም ዘብ እንድንሆን በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
በመጨረሻም በዓሉ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የመቻቻል፣ የአብሮነትና ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነት ይበልጥ የሚናጠናክርበት እንዲሁም ለከተማችን ብሎም ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ለመስራት የምንነሳበት እንዲሆን እመኛለሁ።
መልካም የስቅለትና የትንሳኤ በዓል ይሁንላችሁ!
አቶ አይሶጼ ሂሎታ
የአርባምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ
ሚያዚያ 2/2018 ዓ.ም
አርባምንጭ||ኢትዮጵያ
10/04/2026
የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር መስፍን መንዛ ለስቅለት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አርባምንጭ ፣ ሚያዚያ 02/2018 ዓ.ም(አርባ ምንጭ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያ)
ከንቲባ መስፍን መንዛ(ዶ/ር) ባስተላለፉት የ2018 የስቅለት በዓል መልዕክት ሕዝበ ክርስቲያኑ ይህንን ታላቅ መንፈሳዊ ፀጋ ያለውን በዓል ሲያከብር በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም በፍቅርና በአብሮነት መንፈስ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦
የተወደዳችሁ የከተማችን ነዋሪዎች፣ እንግዶች እና መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችንና መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት በሠላምና በጤና አደረሳችሁ! አደረሰን!።
በክርስትና እምነት አስተምህሮ ጌታችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ፍቅር ሲል በመስቀል ላይ የከፈለው ዋጋ ያሳየውን ፍጹም ፍቅርና የይቅርታና የማዳኑን ሚስጥር በማስታወስ የሚከበረው " በዓለ ስቅለት " በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ሥርዓቶች በመላው ዓለም ይከበራል።
ከ2 ሺህ 18 የምህረት ዓመታት በፊት በእስራኤል የሔሮድስ ንግስና ዘመን ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጲላጦስ ዐደባባይ ተገርፎ፣ከሊቶስጥራ እስከ ቀራኒዮ ድረስ መስቀል አሸክመው እየተገፈተረ በምድር ላይም እየተጣለ ተወስዶ በቀራኒዮ አደባባይ በመስቀል ላይ ሲሰቀል ምንም ሐጢያትና በደል ሳይኖርበት ስለሰው ልጅ ፍፁም ፍቅር ብቻ ህይወቱን አሳልፎ የሰጠባትን "ዕለተ-አርብ" የስቅለት ቀን ቤተክርስቲያን በፆም፤በፀሎት፣ በስግድትና በአርምሞ ትቀደሳለች።
ሕዝበ ክርስቲያን የሆንን እኛ የክርስቶስን አርዓያ በመከተል መስጠትን የህይወታችን አካል አድርገን በፍቅር እንድንኖር ያሳዬን የፅድቅ መምህራችን እርሱ ነውና ምሳሌነቱን በሕይወት ዘመናችን ሙሉ እንተግብረው።
በመሆኑም ይህን ታላቅ ሐይማኖታዊ በዓል ስናከብር በአብሮነት መንፈስ ያለንን ማህበራዊ አንድነታችንን በማጠናከር፣ በተለመደው የመተጋገዝና የመረዳዳት እንዲሁም በመጋራት እንዲሆን ጥሪዬን በአክብሮት አቀርባለሁ ።
በከተማችን የሚገኙ የእድሜ ባለፀጋ ከሆኑ አረጋውያን፣ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ከተጎዱና ከተፈናቀሉ ወገኖቻችንን ጎን ሆንና በመተጋገዝ በዓሉን በፍቅር ልናከብር ይገባል።
ከሕዝባችን ጋር የጀመርናቸው በርካታ የልማት ሥራዎችና የመልካም አስተዳደር እና የፍትሕ ጥያቄዎችን በጋራ ለመፍታት በትጋት የምንሰራበት ወቅትም በመሆኑ ሕዝበ ክርስቲያኑ የሚጠበቅበትን ድርሻ እንዲወጣም እጠይቃለሁ ።
በዓሉን በሰከነ ሁኔታ እንድናከብር ጥሪ እያቀረብኩ ድንገተኛ አደጋና አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲገጥማችሁ ለሚመለከተው አካልና ለጸጥታ አካላት በጥቆማ በማሳወቅ የተለመደ ትብብራችሁን እንድታደረጉ ስልም መልዕክቴን እገልፃለው።
በድጋሚ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የስቅለት በዓል እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ ።
ፈጣሪ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ይባርክ !
መስፍን መንዛ (ዶ/ር)
የአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ
ሚያዚያ 2/2018 ዓ.ም
አርባምንጭ || ኢትዮጵያ