Ataye City Government Communication office

Ataye City Government Communication office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ataye City Government Communication office, Government Organization, Ataya, Shewa, Ataya.

የሙዝ ክላስተር በደዋ ጨፋ ወረዳ ገርቢ ቀበሌ በሁለቱ የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኛ።አጣዬ፦ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም (አጣዬ ከተማ ኮሙኒኬሽን
26/10/2026

የሙዝ ክላስተር በደዋ ጨፋ ወረዳ ገርቢ ቀበሌ በሁለቱ የዞን ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኛ።

አጣዬ፦ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም (አጣዬ ከተማ ኮሙኒኬሽን

የሰሜን ሸዋ ዞን የከተማ ክላስተር  ተቋማት የወረዳ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላቶች  በተገኙበት 1ኛ ሩብ አመት ስራዎች በቨርቸዋል ሚቲንግ  ተገመገመ።የሩብ አመቱን ሪፓርት ያቀረበት  የከተ...
26/10/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን የከተማ ክላስተር ተቋማት የወረዳ አመራሮችና የማኔጅመንት አባላቶች በተገኙበት 1ኛ ሩብ አመት ስራዎች በቨርቸዋል ሚቲንግ ተገመገመ።

የሩብ አመቱን ሪፓርት ያቀረበት የከተማ ክላስተር መምሪያ ሀላፊዎች ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት፣ ንግድና ገበያ ልማት ፣ ስራና ክህሎት፣ ከተማና መሰረተ ልማት እና ባህል ስፖርት መምሪያ ሀላፊዎች ሲሆኑ በሩብ አመቱ የተከናወኑ ስራዎችን በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ውይይቱን የመሩት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ እና የከተማ ክላስተር አስተባሪ የሆኑት ወይዘሮ ሰአዳ ኢብራሂም ሲሆኑ በማጠቃለያቸው በክላስተሩ ተቋም በሩብ አመት የተጀመሩ ጅምር ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው በማመላከት በቀጣይ በክላስተሩ ትኩረት ተደርገው የሚከናወኑ ተግባራቶችን ቆጥረው አንስተዋል።

በመጨረሻም በከተማ ክላስተር ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች በሩብ አመቱ በሰሩት ስራ የተመዘኑ ሲሆን በዚህ መሰረትም
ከገጠር ወረዳ፦
1ኛ.ባሶና ወራና
2ኛ.እንሳሮ ወረዳ
3ኛ.ሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ከ1እስከ 3 የወጡ ሲሆን
ከከተማ አስተዳሮች፦
1ኛ.ሸዋርቢት ከተማ አስተዳደር
2ኛ. አረርቲ ከተማ አስተዳደር
3ኛ.ደብረሲና ከተማ አስተዳደር ደረጃ ይዘዋል::

መድረኩም የቀጣይ ነጥቦችና አቅጣጫዎች ተመላክቶበት ተጠናቋል።

የሰሜን ሸዋ ዞን አመራሮች በደዋ ጨፋ ወረዳ የሙዝ ክላስተር ልማትን ጎበኙ**በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሽ አለማየሁ የተመራ  ቡድን፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ...
26/10/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን አመራሮች በደዋ ጨፋ ወረዳ የሙዝ ክላስተር ልማትን ጎበኙ
**
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሽ አለማየሁ የተመራ ቡድን፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደዋ ጨፋ ወረዳ በገርቢ ቀበሌ የሚገኘውን የሙዝ ክላስተር ልማት ጎብኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ አባፍሮ፣ እንዳሉት በአካባቢው የተገኘው ሰላምና የሕዝቦች አብሮነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው፣ ለሰላም መረጋገጥ የጸጥታ አካላት፣ የሃይማኖትና የባህል አባቶች እንዲሁም መላው ማኅበረሰብ ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

አክለውም አንጾኪያ እና አካባቢው ትልቅ የልማት አቅም እንዳለው የተገለፁ ሲሆን፣ ክልሉና ዞኑ በጀመሩት አዲስ የዕይታ ጉዞ እና የ25 ዓመት የልማት እቅድ መሰረት ሰላምን በማስፈን የተሻለ ውጤት ለማምጣት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

​በመጨረሻም አቶ አህመድ አሊ ይህ አካባቢ ትልቅ እምቅ አቅም ያለው በመሆኑ፣ በጋራ በመቆም ሰላማችንን ጠብቀን ወደ የተሻለ ልማት መሸጋገር እንችላለን ብለዋል

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሽ አለማየሁ በበኩላቸው፣ ሰላምን ለማስፈን ባለፉት አራት ዓመታት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ጠቁመው፣ ሰላም ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የተገኘውን ሰላም ወደ ዘመናዊ ግብርናና ዘላቂ ልማት በመቀየር የማኅበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ መካሽ አካባቢው ሙዝ፣ ፓፓያ፣ ማንጎና ሌሎች ፍራፍሬዎችን በስፋት ለማምረት ምቹ የተፈጥሮ ሀብትና የውሃ አቅም እንዳለው በመጥቀስ፣ የክላስተር ልማትን በማስፋፋት የአርሶ አደሩን ገቢ ማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ከድህነት የሚያላቅቁ የልማት ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በጉብኝቱ ላይ ከአንጾኪያ ገምዛ፣ ከኤፍራታና ግድም፣ ከቀወት፣ ከጣርማ በርና ከሸዋ ሮቢት ከተማ የመጡ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም ተገኝተዋል።

ሰላም ለልማት፤ አብሮነት ለጋራ ብልጽግና!

#ሰላም #ልማት #የሙዝክላስተር #ደዋጨፋ #የሕዝቦችአብሮነት

የገጠር ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ! የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠር ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ተቋማት የ2019 በጀ...
26/10/2026

የገጠር ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተጀመረ!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠር ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ተቋማት የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም የጋራ ግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት ባሕር ዳር ከተማ መካሄድ ጀምሯል። በምክትል ርዕሠ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ ክቡር ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በተገኙበት በዚህ የምክክር መድረክ፤ የዘርፉ ተቋማት የማኔጅመንት አባላትና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

መድረኩ ተቋማቱ በሩብ ዓመቱ ያቀዷቸውን ተግባራትና ያመጧቸውን ውጤቶች ከተቀመጡ ግቦች አንጻር ለመገምገም፣ የታዩ ክፍተቶችን ለመለየት እና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።

የመድረኩን መከፈት ያበሰሩት የዘርፉ አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር) ባስተላለፉት መልእክት፤ የገጠር ኢኮኖሚ ልማት ዘርፍ ለክልሉ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እድገት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል። በመሆኑም የተቋማት የሥራ አፈጻጸም በዘልማዳዊ አቀራረብ ሳይሆን በተጨባጭ መረጃ፣ በውጤትና በተጠያቂነት መመርመር እንዳለበት አስገንዝበዋል።

አያይዘውም የግምገማው ዋና ዓላማ የተከናወኑ ተግባራትን በሪፖርት ማቅረብ ብቻ ሳይሆን አፈጻጸሙን ከዕቅድ ጋር በማነጻጸር ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና አፈጻጸምን የሚያደናቅፉ ማነቆዎችን መለየት በመሆኑ፣ ተቋማት በቅንጅት የመሥራትና ሀብትን በአግባቡ የመጠቀም ግዴታ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በመድረኩ በሚቆየው ጊዜ ውስጥ በምግብ ዋስትና፣ በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት፣ በእንስሳት ሀብት፣ በመሬት አስተዳደር፣ በማዕድን ልማትና በኅብረት ሥራ ማኅበራት ዘርፎች የቀረቡ የሩብ ዓመት ሪፖርቶች ተገምግመው የቀጣይ አቅጣጫ ይቀመጥባቸዋል።

በተለይም የሰብል ምርታማነት፣ የቴክኖሎጂ አቅርቦት፣ የማዕድን አስተዳደርና የአደጋ ስጋት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥራዎች በትኩረት ከሚገመገሙት መካከል ይገኙበታል። ይህም ተቋማት በተናጠል ያከናወኗቸውን ተግባራት ከማቅረብ ባለፈ፣ የጋራ ግቦችን ለማሳካት ያላቸውን የቅንጅት አሠራር ለማጠናከርና የሀብት አጠቃቀምን ለመመርመር ያስችላል።

በማጠቃለያውም የግምገማው ትኩረት የተገኙ ውጤቶችን በማጉላት ብቻ ሳይወሰን፣ የታዩ ችግሮችን በመፍትሔ በመመለስ፣ የተቋማትን ተጠያቂነት ለማጠናከርና ለገጠር ማኅበረሰብ የሚደርሱ የልማት ጥቅሞችን ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችሉ የተግባር እርምጃዎችን በመለየት ላይ ያተኩራል። በመሆኑም ይህ የጋራ ግምገማ መድረክ የውጤት መለኪያ፣ የክፍተት መለያና ለቀጣይ ስኬት ጠንካራ መሠረት እንደሚሆን ተገልጿል

አቶ ታደሰ አስፋውና ቤተሰቦቻቸው ለአጣዬ አረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ማዕከል የምግብና የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረጉአጣዬ፦ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም (አጣዬ ከተማ ኮሙኒኬሽን)በአጣዬ ከተማ...
25/10/2026

አቶ ታደሰ አስፋውና ቤተሰቦቻቸው ለአጣዬ አረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ማዕከል የምግብና የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረጉ

አጣዬ፦ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም (አጣዬ ከተማ ኮሙኒኬሽን)

በአጣዬ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ ታደሰ አስፋው እና ቤተሰቦቻቸው በአጣዬ አረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ማዕከል ለሚገኙ አረጋውያን የምግብ፣ የገንዘብና የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረጉ።

በድጋፍ መርሐ ግብሩ ላይ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጌጤናሽ ማሞ፣ አቶ ታደሰ አስፋውና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ለአረጋውያኑ የማዕድ ማጋራትና የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።

አቶ ታደሰ አስፋው በትናንትናው ዕለት ለአረጋውያኑ ማዕድ ያጋሩ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ 20 ሺህ ብር በጥሬ ገንዘብ፣ 13 ሜትር የሽንት መከላከያ ሌዘር፣ በአቶ ደረጀ ዘውዱ አስተባባሪነት የተገኘ 43 ኢንች ቴሌቪዥን፣ የሀይላድ የመጠጥ ውሃ እና አንድ መሶብ እንጀራ ድጋፍ አበርክተዋል።

የአጣዬ አረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ማዕከል መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጡሩሰው መኮንን፣ ለማዕከሉና በውስጡ ለሚገኙ አረጋውያን ለተደረገው ድጋፍና ስጦታ ምስጋና አቅርበዋል።

በተመሳሳይ፣ የከተማው ሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጌጤናሽ ማሞ፣ አረጋውያንን መደገፍ ታላቅ በጎ ተግባር መሆኑን ገልጸው፣ ድጋፉን ላደረጉት አቶ ታደሰ አስፋውና ቤተሰቦቻቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ኃላፊዎ እንደተናገሩት አረጋውያንን በመደገፍ ከሰማይ በረከትና ከምድር ምስጋና እንደሚገኝ በመግለጽ፣ ሌሎችም በጎ ፈቃደኞች ይህንን ተግባር እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም አረጋውያኑ ለድጋፍ አድራጊዎቹ በረከትና መልካም ምኞታቸውን ካቀረቡ በኋላ የድጋፍ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

የአጣዬ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም  ግምገማና  የእውቅ እና ና ምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ።አጣዬ፦ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም (አጣዬ ...
25/10/2026

የአጣዬ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የእውቅ እና ና ምስጋና ፕሮግራም ተካሄደ።

አጣዬ፦ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም (አጣዬ ከተማ ኮሙኒኬሽን)

በአጣዬ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የአጣዬ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።
በግምገማው የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ አቶ መስፍን አስፋው፣ የተቋሙ ባለሙያዎች፣ የተጋበዙ እንግዶችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

በዚሁ ወቅት የሆስፒታሉ የሩብ ዓመቱ የሥራ ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን፣ የጤና አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ የታካሚዎችን ቁጥር ማሳደግ፣ የተኝቶ ሕክምና ቆይታን መቀነስ፣ የሕፃናትን ጤና በተሻለ ሁኔታ መከታተልና የእናቶች ጤና አገልግሎትን ማሳደግ ከተከናወኑ ሥራዎች መካከል ተጠቅሰዋል። በተጨማሪም ውስብስብ የነበረውን የቀዶ ጥገና ክፍል ጥገና ማጠናቀቅ ከትኩረት የተሰጣቸው ሥራዎች መካከል ተካቷል።

የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጁ በሪፖርቱ ላይ በተነሱ ጉድለቶችና በቀጣይ ሊሠሩ በሚገቡ ሥራዎች ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ፣ የመድኃኒት እጥረትን መቀነስ፣ የሰው ኃይል እጥረትን ማሟላት፣ የመሠረተ ልማት ጥገናን ማሻሻል፣ ድጂታላይዝ ማድረግ Full EMR) የሀብት አሰባሰብ ማጠናከር ልዩ ትኩረት የሚሹ ሲሆን የንብረት አያያዝን ማጠናከርና የሕክምና አገልግሎት ጥራትን ማሳደግ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን ገልጸዋል።

እነዚህን ጉድለቶች ለማረምና የተቋሙን አፈጻጸም ለማሻሻል እንደሚሠራም አመልክተዋል።

በመጨረሻም በ2018 ዓ.ም ጥሩ አፈጻጸም ላሳዩና በጡረታ ለተሰናበቱ የተቋሙ ሠራተኞች የዕውቅና ሰርተፍኬትና ሽልማት በመስጠት የግምገማ መርሐ ግብሩ ተጠናቋል።

ተ

በአጣዬ ከተማ በ3R ፕሮጀክት አማካይነት የሚገናባው ኮምፖነንት 2 እየተገነቡ ያሉ ማዕከላት በክልል ሀላፊዎች ተጎበኙ።አጣዬ፦ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም (አጣዬ ከተማ ኮሙኒኬሽን)በአጣዬ ከተማ ...
25/10/2026

በአጣዬ ከተማ በ3R ፕሮጀክት አማካይነት የሚገናባው ኮምፖነንት 2 እየተገነቡ ያሉ ማዕከላት በክልል ሀላፊዎች ተጎበኙ።

አጣዬ፦ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም (አጣዬ ከተማ ኮሙኒኬሽን)

በአጣዬ ከተማ አስተዳደር እና በኤፍራታና ግድም ወረዳ በኮምፖነንት 2 (Component 2) ፕሮጀክት እየተገነቡ ያሉ ማዕከላት በአማራ ክልል ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የ3R ፕሮጀክት አስተባባሪዎችና በከተማውና በወረዳው አመራሮች ተጎበኙ።

በጉብኝቱ የአማራ ክልል ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የ3R ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መሐመድ ኡመር፣ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጌጤናሽ ማሞ፣ የአጣዬ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ በላቸው ትዜ እንዲሁም የከተማውና የወረዳው አመራሮች በተገኙበት ሀጉብኝቷል።

የክልሉ የ3R ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ መሐመድ ኡመር እንደገለጹት፣ ጉብኝቱ በኮምፖነንት 2 ፕሮጀክት ሥር በጾታዊ ጥቃት ለተጎዱ ሴቶች አገልግሎት የሚሰጡ ማዕከላት የግንባታ ሂደትን ለመከታተል የማያስችን መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም ጉብኝት በከሚሴ፣ በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ፣ በአጣዬ ከተማና በኤፍራታና ግድም ወረዳ እየተገነቡ ያሉ እና የሚገኙ ፕሮጀክቶችን መጎብኛታቸውን ገልፀውልናል።በቀጣይም በመገባት ላይ ያሉ ተገንብተው እንደሚጠናቀቁ ተናግረዋል።

የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ወጣቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ጌጤናሽ ማሞ በበኩላቸው፣ በዚህ የበጀት ዓመት በኮምፖነንት 2 ፕሮጀክት ሥር አራት አዳዲስ ማዕከላት እየተገነቡ ሲሆን፣ ሦስት ማዕከላት ደግሞ በጥገና ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ግንባታና የጥገና ሥራዎቹ በቅርቡ ተጠናቀው ማዕከላቱ ለተጠቃሚዎች አገልግሎት እንዲሰጡ የማድረግ ዕቅድ መኖሩንም አመልክተዋል።

ፕሮጀክቱ በጾታዊ ጥቃት ለተጎዱ ሴቶች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማጠናከርና ተጎጂዎች ተገቢውን ድጋፍ እንዲያገኙ ለማስቻል ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿ ጉብኝቱ ተጠናቋል።

ከቤተሰብ እና ከምቾት ርቃችሁ የሀገርን ዳር ድንበር ለምታስከብሩ ጀግኖቻችን ሁሉ ክብር እና ምስጋና ይገባችኋል!
25/10/2026

ከቤተሰብ እና ከምቾት ርቃችሁ የሀገርን ዳር ድንበር ለምታስከብሩ ጀግኖቻችን ሁሉ ክብር እና ምስጋና ይገባችኋል!

በአጣዬ ከተማ 119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን "የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።አጣዬ፦ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም (አጣዬ ከተማ ኮሙኒኬሽን)በአጣዬ ...
25/10/2026

በአጣዬ ከተማ 119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን "የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

አጣዬ፦ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም (አጣዬ ከተማ ኮሙኒኬሽን)

በአጣዬ ከተማ 119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን "የድል ሠራዊት" በሚል መሪ ቃል የከተማው ፣የወረዳው ፣ የሰራዊቱ አመራር በተገኙበት በዛሬው እለት በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

የ119ኛው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የድል በዓል ሲከበር የተገኙት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የ107ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አበባው ሞላ የኤፍራታና ግድም ወረዳ ተቀዳሚ አሰተዳዳሪ አቶ አበራ መኮንን እና የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር እንድሪስ ፣ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰዓዳ ይማም እና ምክትል ከንቲባ አቶ በላቻው ትዜ፣ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ወንድሙ ካሳ፣የመከላከያ አመራር እና የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ የ107ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር ሰራዊት ተገኝተዋል።

በእለቱም በፓናል ውይይት እና በተለያዩ ፕሮግራም ሲከበር ቆይቶ ተጠናቋል።

119 ዓመታትን በኩራት፤ በጀግንነት፤ ለተፈራች ሀገር ጋሻ በመሆን - የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት #ትልቅህዝብ  #ታላቅ ርዕይ #አዲስሚዲያኔትዎርክ  #የትዉልድድምጽ #አዲስአበባ #ኢትዮጵያትክ...
25/10/2026

119 ዓመታትን በኩራት፤ በጀግንነት፤ ለተፈራች ሀገር ጋሻ በመሆን - የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት

#ትልቅህዝብ
#ታላቅ ርዕይ
#አዲስሚዲያኔትዎርክ
#የትዉልድድምጽ
#አዲስአበባ
#ኢትዮጵያ
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

Address

Ataya, Shewa
Ataya
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ataye City Government Communication office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share