Sidama prison communication

Call Contact the organization

Sidama prison communication government communication

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በንሳ ዳዬ ማረሚያ ተቋም የግብርና ልማት ሥራ ትኩረት ሰጥት እየሠራ መሆኑን ገለፀ ።‎መስከረም 17/2019 ዓ.ም‎         ሀዋሳ‎‎...
27/09/2026

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በንሳ ዳዬ ማረሚያ ተቋም የግብርና ልማት ሥራ ትኩረት ሰጥት እየሠራ መሆኑን ገለፀ ።

‎መስከረም 17/2019 ዓ.ም
‎ ሀዋሳ
‎
‎ ******
‎
‎የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በንሳ ዳዬ ማረሚያ ተቋም የግብርና ልማት ሥራ ትኩረት ሰጥት እየሠራ መሆኑን የተቋሙ ኃላፊ ም/ኢ/ር ብርሃኑ ፉታና ገለፀ::
‎
‎በንሳ ዳዬ፣ የማረሚያ ተቋማት የግብርና ልማት ሥራዎችን በማጠናከር የታራሚዎችን የሥራ ክህሎት ለማሳደግና የተቋማትን የልማት አቅምን ለማጎልበት እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ።
‎
‎
‎በተቋሙ የእርሻ፣ የአትክልት፣ የፍራፍሬ እና የቡና ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ታራሚዎች በተግባር የሙያ ክህሎት እንዲያገኙ ዕድል እየተፈጠረላቸው ነው።
‎
‎የግብርና ሥራው ታራሚዎች ከተቋሙ ከወጡ በኋላ ራሳቸውን በሥራ እንዲደግፉ ከማስቻል ባለፈ፣ የሥራ ልምድና ኃላፊነት ስሜት እንዲያዳብሩ አስተዋፅኦ እንዳለው ተገልጿል::
‎የ
‎ግብርና ልማቱ በቀጣይ የተለያዩ የምርት ዘርፎችን በማካተት እንዲጠናከር በመሥራት ላይ መሆኑም ተጠቁሟል።
‎
‎ሀዋሳ:- መስከረም 17/2019 ዓ.ም.
‎
‎
‎
‎ ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን **
‎ ሀዋሳ
‎ለበለጠመረጃ-
‎Telegram_https://t.me/Hawayige
‎Facebook-https://www.facebook.com/profile.php?id=100075985375250

የሲብክመ ፍትህ ቢሮ አመራር በሀዋሳ ማረሚያ ተቋም ጉብኝት አደረጉ። ‎‎ሀዋሳ:- መስከረም 12/2019 ዓ.ም.‎‎የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ክቡር ማቶ ማሩ እና የቢሮ ...
22/09/2026

የሲብክመ ፍትህ ቢሮ አመራር በሀዋሳ ማረሚያ ተቋም ጉብኝት አደረጉ።
‎
‎ሀዋሳ:- መስከረም 12/2019 ዓ.ም.
‎
‎የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ክቡር ማቶ ማሩ እና የቢሮ አመራር በማረሚያ ተቋሙ ጉብኝት አድርገዋል።
‎
‎በጉብኝቱ ወቅት የተቋሙን አጠቃላይ የሥራ ሁኔታ፣ የእስረኞች አገልግሎትና የተቋሙን መሠረተ ልማት ሁኔታ በተመለከተ ምልከታ ተደርጓል። በወቅቱም በተቋሙ የሚገኙ አንዳንድ በወቅቱ ዝናብ ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት ተደርጓል።
‎
‎ክቡር ማቶ ማሩ በጉብኝቱ ወቅት የተነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ ችግሮች ከተፈጠሩ በኋላ ጊዜያዊ መፍትሄ ለመስጠት የተደረገውን ርብርብ አድንቀው ምስጋና አቅርበዋል።
‎
‎በተለይም የተቋሙ መሠረተ ልማት በአስቸኳይ እንዲሻሻል፣ የተነሱ ጉዳዮችም በተያዘው አሠራር እንዲፈጸሙ አሳስበዋል። ከሚመለከታቸው አካላትም ተገቢውን ድጋፍ ለማስገኘት ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዋል።
‎
‎
‎
‎
‎
‎
‎መስከረም 8/2019 ዓ.ም
‎
‎ ሀዋሳ
‎** ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን ****
‎ ሀዋሳ
‎ለበለጠመረጃ-
‎Telegram_https://t.me/Hawayige
‎
‎Facebook-https://www.facebook.com/profile.php?id=100075985375250
‎
‎

19/09/2026

🇨🇳 ቻይና በትላልቅ የእርሻ ማሳዎች ላይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሚሠሩ አረም አጥፊ ማሽኖችን ሥራ ላይ አዋለች።

እያንዳንዱ ማሽን ካሜራ ፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ሌዘር የተገጠመለት ሲሆን፣ ካሜራው እፅዋቱን ሲቃኝ አርቴፊሻል ኢንተለጀንሱ ዋናውን ሰብል ከአረም በመለየት ሰብሉ እንዳይጎዳ ይጠብቃል።

ይህ ማሽን አሁን ላይ ወደ አውስትራሊያ ተልኮ ጥቅም ላይ የዋለ ሲሆን በዚያ የሚገኙ ትላልቅ እርሻዎች ምንም ዓይነት የኬሚካል ተባይ ማጥፊያ ሳይጠቀሙ አረምን በብቃት ለመቆጣጠር አስችሏቸዋል ሲል ዥንዋ ዘግቧል።

መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ/ም

የመረጃ ምንጭ

በኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስትር ለሲዳማ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አመራሮች እና ባለሙያዎች በተሻሻለው  የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ምንነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ።መስከ...
19/09/2026

በኢፌዴሪ ፍትህ ሚኒስትር ለሲዳማ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አመራሮች እና ባለሙያዎች በተሻሻለው የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ ምንነት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል ።

መስከረም 9/2019 ዓ.ም
‎ ሀዋሳ
‎
‎ ***
‎ ‎ ‎ ‎ነባሩ ሕግ በ1954 ዓ.ም የወጣና በወቅቱ የነበረውን አሃዳዊ የመንግሥት መዋቅር መሠረት ያደረገ በመሆኑ አሁን ላይ ያለውን የፌደራል ስርዓት አወቃቀር ወደ መሬት ለማውረድ አስቸጋሪ ሆኖ መቆየት፣ ‎የሕገ-መንግሥታዊ መብቶች መስተጓጎልና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ጉድለት፣ ‎በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ እየተከናወኑ ያሉ የፍትሕ ሥርዓት ማሻሻያዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ አለመገኘት፣ ‎የመንግሥትና የሕዝብ ጥቅምና ፍላጎቶች በበቂ ሁኔታ የሚረጋገጡበት ዘመናዊ ሥርዓት አለመኖር፣ ‎ ከወንጀል ፍትሕ የሚገኙ ውጤቶች የሕብረተሰቡን ደኅንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማረጋገጥ አቅም ማነሳቸውየኮምፒውተር፣ የኢንተርኔትና የኤሌክትሮኒክስ መረጃዎች የሚበረበሩበት፣ የሚያዙበትና በፍርድ ቤት የማስረጃነት ደረጃቸው የሚወሰንበት ሥርዓት አለመኖር፣ ‎ለምርመራ ማጠናቀቂያ፣ ክስ ለመመሥረትና ፍርድ ለመስጠት ግልጽና አሳሪ የጊዜ ገደቦች አለመቀመጣቸውና ፍትሕ እንዲዘገይ ማደረጉ፣ ‎መርማሪ ፖሊስና ዐቃቤ ሕግ በቅደም-ተከተል መሥራታቸው መዝገቦች በተደጋጋሚ እንዲመላለሱ፣ የምስክሮች መጉላላት እንዲፈጠርና ማስረጃ እንዲጠፋ ምክንያት ማድረጉ፣ ‎በወንጀል ጉዳዮች የሚደረጉ አለም አቀፍ ትብብሮችን በተመለከተ ወጥና የተሟላ የሕግ ማዕቀፍ ያልነበረ መሆኑ፣ ‎ከባሕላዊና ዘመናዊ አማራጭ የክርክር መፍቻ ዘዴዎች ጋር በተያያዘ ሥርዓት ያልተበጀለት መሆኑ፣ ‎በ1996/97 ዓ.ም ከወጣው የወንጀል ሕግ ጋር አብሮ ባለመዘመኑና የተወሳሰቡ ወንጀሎችን በማስረጃ በማረጋገጥ እውነቱን አንጥሮ ለማውጣት የነበረው ሚና ከሚጠበቀው በታች በመሆኑ የመፈጸሚያ መሣሪያነቱ ተዳክሞ በመቆየቱ ።
‎
‎
‎ ከላይ የተዘረዘሩትን ተግዳሮቶች እልባት ከመስጠት ባለፈ የሕግ አውጭው፡- ‎ከዓለም አቀፍ እሴቶች፣ መርሆዎችና ስምምነቶች ጋር የተጣጣመ ዘመናዊ የወንጀል ፍትህ ሂደት ‎የተጎጂዎችና የተጠርጣሪዎች መብት የሚያስከብርና የሕግ የበላይነትን የሚያሰፍን ወጥና የተሟላ ሕግ፤ ‎ዓለምአቀፍ መብቶችን ለመጠቀምና ግዴታን ለመወጣት የሚያስችል ሕግ፤ ‎ለጠቅላላው ጥቅም የሚሰራ የሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ድንጋጌዎችን ያካተተ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ እንደሆነ ያምናል። ‎በዚህም መሰረት የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ እንዲወጣ ሆኗል። ‎
‎
‎የማረሚያ ቤት ተቋም- ሰብዓዊ አያያዝና ማሕበራዊ ተሃድሶ (አንቀጽ 22) ‎
‎
‎በቁጥጥር ሥር ያሉ ሰዎችን ማቆየት፣ ማረም እና የፍርድ ቤት ትእዛዞችን መፈጸም፦ በጥበቃ ሥር ያሉ ተከሳሾችን በማረፊያ ቤት ያቆያል፣ ፍርደኞችን ያርማል፣ እንዲሁም ፍርድ ቤት በፈለጋቸው ጊዜ ያለምንም መዘግየት ለችሎት የመገኘት መብታቸውን ያረጋግጣል። ‎የታራሚዎች ምደባና ሰብዓዊ ክብካቤ፦ በማረሚያ ቤት ያሉ ሰዎችን በጅምላ ማጎር የተከለከለ ነው። ታራሚዎችና ተከሳሾች በዕድሜ፣ በጾታ፣ በወንጀል ዓይነት እና በጤና ሁኔታቸው ተለይተው ሰብዓዊ ክብራቸው በሚጠብቅ መልኩ መያዝ አለባቸው። ‎የግንኙነትና የቅሬታ ሥርዓት፦ ታራሚዎች ከጠበቃቸው፣ ከሐኪማቸው፣ ከሃይማኖት መሪያቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር በግል የመገናኘት መብት አላቸው። እንዲሁም ለሚደርስባቸው ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ የተፋጠነ ምላሽ የሚሰጥ የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት ይዘረጋል። ‎ማኅበራዊ መልሶ መቀላቀል (Reintegration)፦ ታራሚዎች ከእስር

17/09/2026
ለ2019 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ::‎‎   *******‎‎‎የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን  ኮሚሽነር ኮንታሞ ቡርቃ እንኳለ2019 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል ...
10/09/2026

ለ2019 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ::
‎
‎ *******
‎
‎
‎የሲዳማ ክልል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኮንታሞ ቡርቃ እንኳለ2019 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
‎
‎በመልዕክታቸውም የማረሚያ ኮሚሽን አባሎችና ሠራተኞች እንዲሁም ማረሚያ ተቋማት የሚገኙ አባሎችና ሠራተኞች እና የህግ ታራሚዎች እንኳን ለ2019 በሠላም አደረሳችሁ ካሉ በኃላ ይህ አዲሱ አመት ባለፈው ዓመት የነበሩትን መልካም አፈጻጸም በማጠናከር በአዲስ ሀሳብ እና በመፍጠር አቅም የማረሚያ ተቋምን የክሎት ስልጠና እና የፈጠራ ማዕከል የማድረግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥልበት እና የህግ ታራሚዎች በዕርምት ወቅት በሚሠሩት መልካም ሥራዎች ህብረተሰብን በማገልገል የበደሉትን ማህበረሰብ የሚክሱበት ዘመን እንዲሆን ምኞታቸዉን በመግለፅ ለሁሉም ይህ አዲስ አሜት:
‎የስኬት
‎የደስታ
‎የእድገት
‎የብልግና
‎የሠላም
‎ያሰቡትፈችሁትን መልካም ነገር ሁሉ የሚታሳኩበት ይሁንላችሁ ብሏል።
‎
‎
‎
‎
‎ጳጉሜ 4/2018 ዓ.ም
‎
‎ ሀዋሳ
‎
‎** ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሙኒኬሽን **
‎ ሀዋሳ
‎ለበለጠመረጃ-
‎Telegram_https://t.me/Hawayige
‎
‎
‎Facebook-https://www.facebook.com/profile.php?id=100075985375250
‎

Address

Sidama
Awassa

Telephone

+251949259686

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Sidama prison communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Sidama prison communication:

Shortcuts

Share