23/08/2026
#ማስታወቂያ
የካፍ «ዲ» አሰልጣኝነት ስልጠና ለመውሰድ ለተመዘገባችሁ በሙሉ
የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በጥምረት ያዘጋጀው የካፍ «ዲ» አሰልጣኝነት ስልጠና የሚጀምርበት ቀን ስለታወቀ ለዚህ የስልጠና መድረክ ምዝገባችሁን ላጠናቀቃችሁ ሰልጣኞች በሙሉ ስልጠናው ከነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የሚሰጥ በመሆኑ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጋችሁ በወቅቱ እንድትገኙ እናሳውቃለን።