Ebinat_Town_Civil_Service

Website Contact the organization

Ebinat_Town_Civil_Service To give free and fair services

07/09/2026
23/08/2026
17/07/2026
12/06/2026

ስለኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) ምን ያህል ያውቃሉ?

ኢትዮ ኮደርስ (Ethio Coders) በኢትዮጵያ የወደፊት የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ እጅግ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ፕሮግራም ነው። ይህ ፕሮጀክት በዋናነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን በቴክኖሎጂ ለማብቃትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ ነው።

​ኢትዮ ኮደርስ ፤

​1. የዲጂታል ክህሎት ክፍተትን መሙላት

​በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የሥራ ገበያ ወደ ዲጂታል እየተቀየረ ነው። ፕሮግራሙ ወጣቶች የኮዲንግ (Coding)፣ የዳታ ሳይንስ (Data Science) እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እውቀት እንዲኖራቸው በማድረግ የክህሎት ክፍተቱን ይሞላል።

​2. የሥራ ዕድል ፈጠራ

​የሪሞት (Remote) ሥፍራዎች፡ ወጣቶች ባሉበት ሆነው ለዓለም አቀፍ ኩባንያዎች በኢንተርኔት አማካኝነት እንዲሰሩና የውጭ ምንዛሬ እንዲያስገኙ ይረዳል። የግል ሥራ (Freelancing)፦ በራሳቸው ተነሳሽነት የሶፍትዌር ውጤቶችን በማልማት ገቢ እንዲፈጥሩ ያግዛል።

​3. ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ያለው ሚና

​የኢትዮጵያ መንግስት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። የኢትዮ ኮደርስ ፕሮግራም ለዚህ ስትራቴጂ ስኬት እንደ ሞተር ሆኖ ያገለግላል፤ ምክንያቱም የዲጂታል ስርዓቱን የሚገነቡት እነዚህ የሰለጠኑ ዜጎች ስለሆኑ ነው።

​4. የቴክኖሎጂ ፈጠራና ስራ ፈጣሪነት (Entrepreneurship)

​ወጣቶች ኮዲንግ ሲማሩ ችግር ፈቺ የሆኑ የሞባይል መተግበሪያዎችን እና የዌብሳይት አገልግሎቶችን መፍጠር ይችላሉ። ይህም በሀገር ውስጥ ያሉ ችግሮችን (ለምሳሌ በግብርና፣ በጤና እና በትምህርት ዘርፍ) በቴክኖሎጂ ለመፍታት ያስችላል።

​5. ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት

​ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከአፍሪካ አልፎ በዓለም ደረጃ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንድትሆንና የሰለጠነ የሰው ኃይል ኤክስፖርት እንድታደርግ (ወይም በሀገር ውስጥ ሆና አገልግሎት እንድትሰጥ) መሰረት ይጥላል።

​ኢትዮ ኮደርስ ወጣቱ ትውልድ ከሸማችነት ወደ ቴክኖሎጂ ፈጣሪነት የሚሸጋገርበት፣ ሀገሪቱ ደግሞ በዲጂታል ዘመን ያላትን ድርሻ የምታረጋግጥበት ፕሮግራም ነው።

12/06/2026

የኢትዮጵያ የመንግስት ሠራተኞች የጡረታ መመሪያ!!!

ማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ በተቀጠረው በ60 ቀናት ውስጥ ለጡረታ በማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መመዝገብ አለበት፡፡

2ኛ የጡረታ አበል ለቀጣይ ተቀማጭ የሚሆነው ገንዘብ ከሠራተኛ 7% ሲሆን ከመንግስት ደግሞ 11% በድምሩ 18% ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ግን ከሠራተኛ 7% እና ከመንግስት 25% በድምሩ 32% ነው፡፡

3ኛ ጡረታ የሚያስወጡ ምክንያቶች:-
፩=በእድሜ ምክንያት 60 ዓመት ሲሞላው
፪=በራሱ ፈቃድ
፫=በጤና ጉድለት
፬=በስራ ለይ በደረሰ አካል ጉዳት
፭=በሞት ናቸው፡፡

4ኛ የጡረታ አበል በውክልና የሚከፈለው:-
፩= በእርጅና
፪=በህመም
፫= ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ
፬= በትምህርት ወዳ ሌላ ቦታ በመሄድ
፭=በእስራት ምክንያት ናቸው፡፡

5ኛ የጡሮታ አበል በይርጋ የሚዘጋው:-
፩=የጡረታ አበል ጥያቄ ሳይቀርብ ወይም የተወሰነለትን ጡረታ ሳይወስድ ከ3 ዓመት በላይ ከቆየ አይከፈለውም፡፡ በቀጣይ ከአመለከተበት ቀን ጀምሮ ይከፈለዋል፡፡
፪=የዳራጎት ጡረታ ሳይጠየቅ ቀርቶ ወይም የተጠየቀውን 3ዓመት ድረስ ሳይወስድ ከቆየ በይርጋ ይዘጋል (አይከፈልም)::

6ኛ በእድሜ 60 ዓመት ሲሞላው ለሠራተኛው የሚሰጥ የጡረታ አበል ስሌት:-
= ከተቀጠረበት ቀን ጀምሮ እስከ 10 ዓመት ድረስ ያለው አገልግሎት በ30% ሲባዛ ከ10 ዓመት በላይ ያለው እያንደንዱ አገልግሎት ግን 1.25 ይባዛል፡:ለምሳሌ 28 አመት አገልግሎት ያለው ስሌት 10ዓመት×30% + 18ዓመት ×1.25= 30+22.5= 52.5% ነው፡፡ በዚህም መሠረት ለጡረታ የሚያዘው ደመወዝ የመጨረሻው የ36ወራት (3ዓመት) ብቻ ስለሆነ በ3ዓመቱ ሲከፈል የነበረው ደመወዝ 5,000 ቢሆን ጡረታው 52.5% ×5,000ብር = 2,625 ብር ጡረታ ያገኛል ማለት ነው፡፡

7ኛ በጀማሪ ቅጥር ወቅት ቀንና ወር ሳይሞላ ዓ,ም ብቻ በህይወት ታሪክ ተሞልቶ ከተገኘ የጡረታ ቀንና ወር የሚያዘው በኢ/ያ አቆጣጠር ከሆነ ነሐሴ 30 ተብሎ ሲያዝ እ.ኤ.አ ከሆነ ታህሳስ 31 ቀን ተብሎ ይታሰባል፡፡

8ኛ በረሱ ፍላጎት ጡረታ የመውጣት መብት እድሜው 55 ዓመት ሲሆንና 25 ዓመት አገልግሎት ሲኖረው ሆኖ ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊት ግን ከሚወጡበት ዓመት 5ዓመት ቀድሞ መውጣት ይችላሉ ፡፡

9ኛ የሟች ጡረታ የሚወርሱ ልጆች ከ18ዓመት በታች ወይም አካል ጉዳተኛ ልጅ ከሆነ 21ዓመት በታችና የሟች እናትና አባት ናቸው፡፡

10ኛ ለጡረታ አበል ለማስፈፀም የሚያስፈልጉ ማስረጀዎች:-
፩=በህይወት ታሪክ የተሞላው መረጃ (ጡ1እና 2)
፪=የሙከራና የቋሚ ቅጥር ደብደቤ
፫= የጡረታ መለያ ቁጥር
፬= የ36 ወራት የደመወዝ መረጃ
፭= የዝውውር፣ የደረጃ ዕድገትና የደመወዝ ለውጥ የተደረገበት ደብደቤ
፮= የጋብቻ እና የልጆች ማስረጃ
፯= የባለጡረታ ወይም የወራሽ ፎቶ ግራፍ
ናቸው፡፡
follow share
life leaner እነደለጠፈው

12/06/2026

Address

Ebinat Tawn
Bahir Dar
679476

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ebinat_Town_Civil_Service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ebinat_Town_Civil_Service:

Shortcuts

Share